cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
37 114
المشتركون
+2624 ساعات
+1817 أيام
+62230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ዲኑል ኢሥላም በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ አምላካች አሏህ በተለያየ ዘመነ መግቦት"dispensation" መልእክተኛ ልኳል፥ ያ የሚላከው ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ አማኞች ሊታዘዙት እንጂ አልተላከም፦ 4፥64 ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ "ኢዝን" بِإِذْن ማለት "ፈቃድ" ማለት ሲሆን አንድ አማኝ የተላከው መልእክተኛ መታዘዝ የአሏህ ፈቃድ ነው፥ በዚህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ሉጥ፣ ሹዕይብ፣ ዒሣ ወዘተ "ታዘዙኝ" በማለት ይናገራሉ፦ 26፥108 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ 26፥126 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ 26፥144 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ 26፥163 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ 26፥169 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ 3፥50 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዘዙኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑኒ" أَطِيعُونِ ነው፥ አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ እንዳለብን ሲናገር "መልእክተኛውን ታዘዙ" በማለት ነው፦ 24፥56 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልእክተኛውን ታዘዙ! ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑ" أَطِيعُوا እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰዎች ለአሏህ "ታዘዙ" የተባሉበት ትእዛዝ ግን ለእርሱ ብቻ አምልኮታዊ መታዘዝ ነው፦ 22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ! ለአሏህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ "አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" ካለ በኃላ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ" በማለት ያስቀምጣል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን ለእርሱ በብቸኝነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፦ 39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ!፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት እራሱ "መታዘዝ" ማለት ነው፦ 3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ለአሏህ ብቻ በውጥን የሚደረግ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፥ "ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው። "ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ" "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ነው። አንድ ማንነት ለአሏህ ብቻ በአምልኮ ሲታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይባላል፦ 3፥84 «እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ 2፥136 «እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ 29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው፥ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት በነጠላ "ታዛዥ" ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥሩ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው። ታዲያ ቀደምት ነቢያት ሙሥሊሞች አይደሉም? ዲናቸውስ "ፈጣሪ አንድ አምላክ ነው" ተብሎ እርሱ ብቻ በአምልኮ መታዘዝ አይደለምን? ወደ እኛም የተወረደው እና ወደ የመጽሐፉ ሰዎች የተወረደው ግልጠተ መለኮት ጭብጡ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፦ 21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ አሏህ ከጥንት ጀምሮ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሎ ለሚልከው ነቢይ የሚገልጠው ይህ ግልጠት ነው፥ "የምናወርድ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑሒ" نُوحِي ሲሆን የሚወርድለት "ወሕይ" وَحْي ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፦ 3፥64 በል፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ ይህቺ የጋራ ትክክለኛ ቃል አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው፦ 3፥64 እርሷም፦ "አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው"። أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ "ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር "አርባብ" أَرْبَابً ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። አሏህን በአምልኮቱ እና በጌትነቱ መታዘዝ ኢሥላም ሲሆን ይህንን ሐቅ ካስተባበሉ ሑጃህ እንዲቆምባቸው እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፦ 3፥64 ምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ" በሏቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! ሙሥሊም አድርጎ ወደ እርሱ ይውሰደን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
إظهار الكل...
...
إظهار الكل...
10ኛ ዙር የነሕው ደርሥ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 10ኛ ዙር የነሕው ደርሥ! አን-ነሕው" اَلنَّحْو ማለት "ሰዋስው"grammar" ማለት ሲሆን የቁርኣንን እና የጥንቱን የአነጋገር ዘይቤ በዐማርኛ እና በእንግሊዝኛ በተደገፈ መልኩ መማር የምትፈልጉ ሁሉ ቦታው ክፍት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሦስት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ-አሳብ በኢሥም ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 11 ናቸው፥ እነርሱም፦ 1. ኢሥሙል ማዕሪፍ፣ 2. ኢሥሙል ዐለም፣ 3. ኢሥሙል ጂንሥ፣ 4. ኢሥሙል ዐደድ፣ 5. ኢሥሙ አድ-ደሚር፣ 6. ኢሥሙል ኢሻራህ፣ 7. ኢሥሙል መውሱል፣ 8. ኢሥሙል ኢሥቲፍሃም፣ 9. ኢሥሙል ሚልክ፣ 10. ኢሥሙል ወስፍ፣ 11. ኢሥሙ አዝ-ዘርፍ ናቸው። ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በፊዕል ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 7 ናቸው፥ እነርሱም፦ 1. ሸኽስ፣ 2. ዐደድ፣ 3. ጂንሥ፣ 4. ተወቱር፣ 5. ሲጋህ፣ 6. ሓላህ፣ 7. ጁምላህ ናቸው። ፨ የሦስተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በሐርፍ ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 7 ናቸው፥ እነርሱም፦ 1. ሐርፉል ጀር፣ 2. ሐርፉል አጥፍ፣ 3. ሐርፉ አት-ተፍሲል፣ 4. ሐርፉል መስደሪይ፣ 5. ሐርፉ አን-ነፍይ፣ 6. ሐርፉል ሐስድ 7. ሐርፉ አሽ-ሸርጥ ናቸው። ደርሡ በሳምንት አንዴ የሚለቀቅ ሲሆን በሁለት ሳምንት አንዴ የሁለቱ ሳምንት ጥያቄ ፈተና ይኖራል። ፈተናው ከ 10 የሚወሰድ ሲሆን ከ 6-10 ማምጣት ይጠበቅባችኃል። ከ 6 በታች ሦስት ጊዜ ካመጣችሁ በሰርተፍኬት አናስመርቅም። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ! እኅት ጀሙቲ፦ http://t.me/JemutiMenhajself34 ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
إظهار الكل...
አሥ ሠለፉ አስ ሷሊሑን የሚያከብሩት እነዚህን ሁለቱን በዓላት ብቻ ነበር። እነዚህ ሦስት ትውልድ፦ ፨፦ የመጀመሪያው ትውልድ “ሰሓቢይ” صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው፣ ፨፦ ሁለተኛው ትውልድ “ታቢዒይ” تَابِعِيّ ሲባሉ ለጥቆ ያሉ ናቸው፣ ፨፦ ሦስተኛው ትውልድ “ታቢዑ አት-ታቢዒን” تَابِع التَابِعِين ሲባሉ ሠልሶ ያሉ ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ “አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን” ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም “መልካሞቹ ቀደምት” ይባላሉ፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72 ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን በመንሀጃቸው ውስጥ ስለ መውሊድ  አላስተማሩም፥ መውሊድን አልተገበሩትም። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት “ፍኖት” “ፋና” “መንገድ” ማለት ነው። በታሪክ እንደሚታወቀው ለመጀመርያ ጊዜ "የነቢያችን”ﷺ”  የልደት ቀን" ተብሎ መከበር የተጀመረው ግብፅ ውስጥ በፋጢሚዩን በአራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ነው፥ የጀመሩትም ክርስቲያኖች ከሚያከብሩት "ልደት" ኮርጀው ነው። ክርስቲያኖች ደግሞ የሚያክብሩት ከመጽሓፋቸው ተፈቅዶላቸው ወይም ታዘው ሳይሆን ከፓጋን ኮርጀው ነው። ስለ ገና ይህንን ጽሑፍ ይመልከቱ፦ https://t.me/Wahidcom/3665 ስለዚህ ሦስተኛ በዓል መውሊድ መጤ እና ቢድዓ ነው፥ “ቢድዓህ” بِدْعَة የሚለው ቃል “በደዐ” بَدَّعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው፥ “ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው። ያለ ኢትባዕ የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም አዲስ አምልኮ ቢድዓህ ነው፦ ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23 ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ኹጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አሏህ የመራውን ማንም አያጠመውም፥ አሏህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአሏህ መጽሐፍ ነው፥ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ዘንዳ ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው በዐሊሞች በያን ከተደረገበት “ሙብተዲዕ” مُبْتَدِئ ይባላል። ቢድዓህ ደግሞ ምንጩ ዝንባሌን መከተል ነው፥ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦ 79፥40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፥ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى 79፥41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ አላህ ዝንባሌ ከመከተል ይጠብቀን! ከቢድዓህ እርቀን በኢትባዕ ብቻ እርሱ የምናመልክ ያርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
إظهار الكل...
መውሊድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ “መውሊድ” مَوْلِد‎ የሚለው ቃል "ወለደ" وَلَدَ ማለትም "ወለደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልደት” ማለት ነው፥ "የልደት ቀን፣ ቦታ እና በዓል እራሱ "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይሉታል። በተለይ ነቢያችን”ﷺ” ተወለዱት ተብሎ የሚከበርበት ቀን "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይባላል፥ ይህንን የመውሊድ እሳቤ ለማወቅ ከዝንባሌ ነጻ ሆነን ስለ ሸሪዓችን ጠንቅቀህ ማወቅ ይጠበቅብናል። መፍረድ ያለብንም ከአሏህ በወረደው ሸሪዓህ ብቻ ነው፦ 5፥48 በመካከላቸውም አሏህ ባወረደው ሕግ ፍረድ። فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦ “ፈርድ” فَرْد‎ “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ “መክሩህ” مَكْرُوه‎ እና “ሐራም” حَرَام ናቸው። አምላካችን አሏህ ሐላል ያላደረገውን ነገር ሐላል ማድረግ ዝንባሌን መከተል ነው፦ 5፥48 እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን፡፡ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة ሲሆን “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት እራሱ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን ዒባዳህ አሏህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው። “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን የተወረደውን “መከተል” ማለት ነው፥ ያለ ኢትባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢትባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦ 6፥106 ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ 7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ “ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” ማለት ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው፥ ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ዒድ ብቻ ያከብራል። “ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦ ጃሚዒይ አት ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121 ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
إظهار الكل...
ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ዘንዳ ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው በዐሊሞች በያን ከተደረገበት “ሙብተዲዕ” مُبْتَدِئ ይባላል። ቢድዓህ ደግሞ ምንጩ ዝንባሌን መከተል ነው፥ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦ 79፥40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፥ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى 79፥41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ አላህ ዝንባሌ ከመከተል ይጠብቀን! ከቢድዓህ እርቀን በኢትባዕ ብቻ እርሱ የምናመልክ ያርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
إظهار الكل...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

መውሊድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ “መውሊድ” مَوْلِد‎ የሚለው ቃል "ወለደ" وَلَدَ ማለትም "ወለደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልደት” ማለት ነው፥ "የልደት ቀን፣ ቦታ እና በዓል እራሱ "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይሉታል። በተለይ ነቢያችን”ﷺ” ተወለዱት ተብሎ የሚከበርበት ቀን "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይባላል፥ ይህንን የመውሊድ እሳቤ ለማወቅ ከዝንባሌ ነጻ ሆነን ስለ ሸሪዓችን ጠንቅቀህ ማወቅ ይጠበቅብናል። መፍረድ ያለብንም ከአሏህ በወረደው ሸሪዓህ ብቻ ነው፦ 5፥48 በመካከላቸውም አሏህ ባወረደው ሕግ ፍረድ። فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦ “ፈርድ” فَرْد‎ “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ “መክሩህ” مَكْرُوه‎ እና “ሐራም” حَرَام ናቸው። አምላካችን አሏህ ሐላል ያላደረገውን ነገር ሐላል ማድረግ ዝንባሌን መከተል ነው፦ 5፥48 እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን፡፡ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة ሲሆን “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት እራሱ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን ዒባዳህ አሏህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው። “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን የተወረደውን “መከተል” ማለት ነው፥ ያለ ኢትባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢትባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦ 6፥106 ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ 7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ “ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” ማለት ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው፥ ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ዒድ ብቻ ያከብራል። “ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦ ጃሚዒይ አት ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121 ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏ አሥ ሠለፉ አስ ሷሊሑን የሚያከብሩት እነዚህን ሁለቱን በዓላት ብቻ ነበር። እነዚህ ሦስት ትውልድ፦ ፨፦ የመጀመሪያው ትውልድ “ሰሓቢይ” صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው፣ ፨፦ ሁለተኛው ትውልድ “ታቢዒይ” تَابِعِيّ ሲባሉ ለጥቆ ያሉ ናቸው፣ ፨፦ ሦስተኛው ትውልድ “ታቢዑ አት-ታቢዒን” تَابِع التَابِعِين ሲባሉ ሠልሶ ያሉ ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ “አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን” ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም “መልካሞቹ ቀደምት” ይባላሉ፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72 ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን በመንሀጃቸው ውስጥ ስለ መውሊድ አላስተማሩም፥ መውሊድን አልተገበሩትም። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት “ፍኖት” “ፋና” “መንገድ” ማለት ነው። በታሪክ እንደሚታወቀው ለመጀመርያ ጊዜ "የነቢያችን”ﷺ” የልደት ቀን" ተብሎ መከበር የተጀመረው ግብፅ ውስጥ በፋጢሚዩን በአራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ነው፥ የጀመሩትም ክርስቲያኖች ከሚያከብሩት "ልደት" ኮርጀው ነው። ክርስቲያኖች ደግሞ የሚያክብሩት ከመጽሓፋቸው ተፈቅዶላቸው ወይም ታዘው ሳይሆን ከፓጋን ኮርጀው ነው። ስለ ገና ይህንን ጽሑፍ ይመልከቱ፦ https://t.me/Wahidcom/3665 ስለዚህ ሦስተኛ በዓል መውሊድ መጤ እና ቢድዓ ነው፥ “ቢድዓህ” بِدْعَة የሚለው ቃል “በደዐ” بَدَّعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው፥ “ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው። ያለ ኢትባዕ የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም አዲስ አምልኮ ቢድዓህ ነው፦ ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23 ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ኹጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አሏህ የመራውን ማንም አያጠመውም፥ አሏህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአሏህ መጽሐፍ ነው፥ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ
إظهار الكل...
ተጸጸተ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦ 65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ አሏህ አንድ ነገር ከመከሰቱ፣ ከመሆኑ፣ ከመደረጉ፣ ከመከናወኑ በፊት ያለውን ሩቅ ነገር እና አንድ ነገር ከተከሰተ፣ ከሆነ፣ ከተደረገ፣ ከተከናወነ በኃላ ያለውን ግልጹን ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፦ 64፥18 ሩቁን ነገር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ "አማሬ ኲሉ" ማለት "ሁሉን ዐዋቂ" ማለት ነው፥ መለኮት "ሁሉን ዐዋቂ" ነው። በባይብል አንዱ አምላክ "ሁሉን ዐዋቂ" ነው፦ 1 ዮሐንስ 3፥20 አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና "ሁሉንም ያውቃል"። ὅτι μείζων ἐστὶν ὁ Θεὸς τῆς καρδίας ἡμῶν καὶ γινώσκει πάντα. ቅሉ ግን አንድ ማንነት በሠራው ሥራ ከተጸጸተ ያንን ሥራ ከመሥራቱ በፊት ስለማያውቅ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። ለምሳሌ፦ ሰው በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፦ ዘጸአት 13፥17 አምላክ፦ "ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው እና ወደ ግብፅ እንዳይመለስ" ብሎአልና። אָמַ֣ר אֱלֹהִ֗ים פֶּֽן־יִנָּחֵ֥ם הָעָ֛ם בִּרְאֹתָ֥ם מִלְחָמָ֖ה וְשָׁ֥בוּ מִצְרָֽיְמָה׃ እዚህ አንቀጽ ላይ "እንዳይጸጽተው" ለሚለው የገባው ግሥ " ፐን ዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው። የእስራኤል ሕዝብን የፈርዖንን ሠራዊት ሰልፍ ባየ ጊዜ ከግብፅ መውጣቱ ጸጽቶት ወደ ግብፅ መመለስ ከከጀለ በመውጣቱ ይጸጸት ነበር፥ የእስራኤል ሕዝብን ሰው ስለሆነ የወደፊቱን ሰማያውቅ በሠራው ሥራ ሊጸጸት ስለሚችል ፈጣሪ እንዳይጸጸቱ መክሯቸዋል። ሰው የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስላልሆነ በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፥ የሰው ተቃራኒ አምላክ ደግሞ የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስለሆነ በሚሠራው ሥራ አይጸጸትም፦ ዘኍልቍ 23፥19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ አምላክ ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። לֹ֣א אִ֥ישׁ אֵל֙ וִֽיכַזֵּ֔ב וּבֶן־אָדָ֖ם וְיִתְנֶחָ֑ם 1 ሳሙኤል 15፥29 የእስራኤል ኃይል አይዋሽም አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና። וְגַם֙ נֵ֣צַח יִשְׂרָאֵ֔ל לֹ֥א יְשַׁקֵּ֖ר וְלֹ֣א יִנָּחֵ֑ם כִּ֣י לֹ֥א אָדָ֛ם ה֖וּא לְהִנָּחֵֽם׃ ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መጸጸት" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ከዚያ በተቃራኒው ያህዌህ በሠራው ሥራ እንደተጸጸተ ባይብሉ ይናገራል፦ ዘፍጥረት 6፥6 ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም እጅግ አዘነ። וַיִּנָּ֣חֶם יְהוָ֔ה כִּֽי־עָשָׂ֥ה אֶת־הָֽאָדָ֖ם בָּאָ֑רֶץ וַיִּתְעַצֵּ֖ב אֶל־לִבֹּֽו׃ እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጸጸተ" ለሚለው የገባው ግሥ "ይዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው፥ ያህዌህ የተጸጸተ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ነው። የሠሩትን ወንጀል ዓይቶ "ከመነሻው ሰው መፍጠር አልነበረብኝም" ብሎ በሠራው ሥራ ተጸጸተ፥ መጸጸት ለሁሉን ዐዋቂ አምላክ የተገባ ባሕርይ አይደለም። በእርግጥ "ናኻም" נָחַם የሚለው ቃል "ተጸጸተ" ብቻ ሳይሆን "አዘነ" "ራራ" "አጽናና" "ረዳ" "ተቆጣ" የሚል ፍቺ ይኖረዋል፥ ይህንን ይዘን፦ ፨"ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አዘነ" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ራራ" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አጽናና" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ረዳ" ፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ተቆጣ" ትርጉም ይሰጣልን? እራሱ በሠራው ሥራ ማዘን፣ መራራት፣ መጽናናት፣ መርዳት፣ መቆጣት ትርጉም አይሰጥም፥ ነገር ግን እራሱ በሠራው ሥራ ተጸጽቷል። ይህ የፈጣሪ ባሕርይ በፍጹም አይደለም፥ "አምላክ ይጸጸት ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም" "እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም" ከሚሉት አናቅጽ ጋር ከመጋጨት አልፎ በመላተም ይፋጫል። የሚያሳዝነው "ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ" ብሎ የሚነግረው ያህዌህ ወይም ሙሴ ሳይሆን ማንነቱ በውል የማይታወቅ ሰው ነው፥ ይህ ውሉ የማይታወቅ ሰው ንግግር ይዘን እንደ አምላክ ቃል መሞገት አግባብ አይደም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
إظهار الكل...
አረጋግጡ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ ለፍቶ አዳሪ እና ሠርቶ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ነጥቆ አዳሪ እና አውርቶ አዳሪ የሆኑት የሚድያ ጡረተኞች ወሬን ሳያረጋግጡ ሾላ በድፍኑ ሊቦተረፉ ማየት የተለመደ ጉዳይ እየሆነ መጥቶአል፥ አበው "እፍ ብለህ ታነዳለህ እፍ ብለህ ታጠፋለህ" በሚል አገርኛ ብሒላቸው ሚድያን ለአሉታዊ ነገር የሚጠቀሙ ተንኮለኛ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ለአውንታዊ የሚጠቀሙ ቅን ሰዎች አሉ። የሚድያ ጡረተኞች የሚያመጡትን ወሬ ባተሎ እና ተላላ ሆኖ ከማራገብ ይልቅ ማረጋገጡ አምላካዊ ትእዛዝ ነው፦ 49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ "ነበእ" نَبَأ ማለት "መረጃ"information" ሲሆን የሚመጣልንን መረጃ ከማረጋገጥ ይልቅ ቸኩለን ያለ ዕውቀት እና ያለ ማስረጃ መናገር ትርፉ ሰውን መጉዳት እና የሕሊና ጸጸት ነው። እውነተኛ ሰው በማስረጃ ያረጋግጣል፦ 2፥111 «እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ "ቡርሃን" بُرْهَان ማለት "ማስረጃ"evidence" ማለት ሲሆን አንድን ነገር ለማረጋገጥ ማስረጃ ጉልህ እማኝ እና ዋቢ ነው። እውነተኛ ሰው በተጨማሪ በዕውቀት ያረጋግጣል፦ 6፥143 «እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ» በላቸው፡፡ نَبِّئُونِي بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229 አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው”። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ ያለ ዕውቀት አንድን ነገር በነሲብ፣ በጭፍን እና በደንዳናነት መከተል አይፈቀድም። ያለዚያ የፍርዱ ቀን ጭፍኑ ሰው ከጆሮ፣ ከዓይን እና ከልብ ተጠያቂ ነው፦ 17፥36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል! መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ቅጥፈታዊ መረጃ እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ የሚጠፋው እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ሲያረጋግጥ ነው። ስለዚህ አንድ ነገር ከሚድያ ጡረተኞች ስንሰማ በመሸኮል አጀንዳ አርገን ከማራገብ ይልቅ ተረጋግተን በማስረጃ እና በዕውቀት መፈተሽ አለብን! መረጋጋት ከአሏህ ነው፥ ችኮላ ከሸይጧን ነው፦ ጃምዒይ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27 ሐዲስ 118 ጀዳህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መረጋጋት ከአሏህ ነው፥ ችኮላ ከሸይጧን ነው"። عَنْ جَدِّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الأَنَاةُ مِنَ اللَّهِ وَالْعَجَلَةُ مِنَ الشَّيْطَانِ ‏"‏ ኢማም አሥ ሡዩጢይ ሠነዱን ሐሠን ብለውታል። መቸኮላችን ዋጋ እያስከፈለን ነው፥ ሰው እስከ ማስገደል ድረስ ወንጀል የሚያሠራው ይህ ችኮላ ነው። አምላካችን አሏህ ሰውን ከመጉዳት እና ከሕሊና ጸጸት ይጠብቀን! ተረጋግተው በማስረጃ እና በዕውቀት ከሚያረጋግጡት ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ነገ ቅዳሜ በቲክ ታክ እንገናኝ። ኢንሻላህ!
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.