cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ጤናችን

የጤና መረጃ ✍️🫀🫁👨‍⚕️👩‍⚕️🧠🚑

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
6 152
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-287 أيام
-15930 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from PULSE
Photo unavailableShow in Telegram
ለጤናማ አዲስ አመት ተግባራዊ መፍትሄዎች ዛሬ እንጀምር መስከረም ሲጠባ ብዙዎቻችን በህይወታችን ላይ ከባለፈው አመት በተሻለ አወንታዊ ለውጦችን ለመተግበር እንነሳሳለን፤ የበለጠ ጤናማ ለመሆን እንመኛለን። በዚህ አመት ልንወስዳቸው ከሚገቡ ቀዳሚ ውሳኔዎች (new year resolution) መካከል በጤና ላይ ያተኮሩ ቢሆኑ መልካም ነው። ከምኞት ያለፈ ተግባራዊ ለውጦችን ለመፈጸም ቃል መግባት ከመቸውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው። ጤናዎ በጣም ውድ ሀብትዎ ነው። ሰውነትዎን እና አእምሮዎትን የሚያለመልሙ ጤናማ የአኗኗር ምርጫዎችን በማድረግ ይህን ከገንዘብ በላይ የሆነ ውድ ሃብት ይጠብቁት፤ ይንከባከቡት። በ2017 አዲስ አመት ስኬታማ እንዲሆን ስናቅድና ስናልም ጤናችንን መጠበቅና ማበልጸግ ቅድሚያ የሚሰጠው የህይዎታችን አካል ማድረግ አለብን። ጤናዎትን ቅድሚያ ሰጥተው ከጠበቁ እራስዎን እየተስፉፉ ከመጡት ስኳር ህመምና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አስቀድመው መከላከል ይችላሉ። ጤናን መጠበቅ ከሁሉም ኢንቨስትመንቶች የበለጠ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ ነው። ጤና ካለ ሰርተን መክበር፣ ነግደን ማትረፍ፣ ሮጠን ማሸነፍ፣ ታግለን መጣል፣ ተምረን ተመራምረን አዲስ ግኝት መፍጠር፣ ወልደን መሳም፣ ወልደን ማሳደግና ለወግ ማእረግ ማብቃት፣ ጸልዬን መዳን፣ አርጅተን ታሪክ ማውጋት እንችላለን። መጪው አዲስ ዓመት ጤናዎን የሚጠብቁበት እና ለጤናማ ረጅም እድሜ እንዲሁም ደስተኛ ህይወት መሰረት የሚጥሉበት ጤናማ አዲስ ጅምሮች ጊዜ እንዲሆንልን እመኛለሁ። የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዛሬው እለት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው እትም ማንበብ ይቻላል። Read its full web version /pdf in Amharic Read its full web version /pdf in Afaan Oromoo https://vm.tiktok.com/ZMromAHpE/ - 💚💛❤️ Melaku Taye, M.D. Let us connect at Blog | TikTok | Telegram | Rate me
إظهار الكل...
2
Repost from PULSE
የአፍሪካ ሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል (ሲዲሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ (mpox) በሽታ የአፍሪካ አስቸኳይ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለማችን ተላላፊ በሽታዎች አስጊ የሆነ ወረርሽኝ እያስከተሉ መጥተዋል። የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። አሁን ደግሞ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በአፍሪካ አንዳንድ ክፍሎች በማንሰራራት ለህብረተሰብ ጤና ስጋት ደቅኗል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወረርሽኙ ከአፍሪካ ውጪም እየተከሰተ ሲሆን ይህም ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ፈጥሯል። የአፍሪካ ሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል (ሲዲሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ (mpox) በሽታን የአፍሪካ አስቸኳይ የጤና ስጋት መሆኑን ከቀናት በፊት አውጇል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ (mpox) በሽታ ምንድን ነው? አዲሱ የዝንጀሮ ፈንጣጣ (mpox) በሽታ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1950ዎቹ በዝንጀሮዎች ላይ ነበር የተገኘው። ይህ በሽታ ዘር፣ ሃይማኖት፣ እድሜና ጾታ ሳይለይ ማንኛውንም ሰው ሊይዝ ይችላል። ደግነቱ ብዙ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ይድናሉ፣ አንዳንዶቹ ግን በጸና ሊያምና ሊከፋባቸው ይችላል። በሽታው በተለይ ህጻናት፣ ነፍሰ ጡር እናቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች ላይ ይበረታል። የዝንጀሮ ፈንጣጣ እንዴት ይተላለፋል? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተላላፊ ህመም ሲሆን በሽታው ካለበት ሰው ወይም እንስሳ በንክኪ ሊይዘን ይችላል። በበሽታው ከተያዘ ሰው የመተንፈሻ አካላት ብናኞች፣ የቆዳ ቁስል ወይም የሰውነት ፈሳሾች አማካኝነት በቅርብ ንክኪ፣ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት እና በቆዳ ለቆዳ ንክኪ ይተላለፋል። እንዲሁም የተያዘ ሰው ተጠቅሞባቸው ከተበከሉ ልብስ፣ የቤት እቃዎችንና ሌሎች ግኡዝ ነገሮችን በመንካት ሊተላለፍ ይችላል። ነፍሰ ጡር አናቶች ቫይረሱን ወደ ጽንሱ ሊያስተላልፉ ይችላሉ። የበሽታው ምልክቶች ምንድን ናቸው? የበሽታው ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት አንድ ሰው ለቫይረሱ ከተጋለጠ ከሳምንት በኋላ ሲሆን አንዳንዴ በቶሎ ወይም ሌላ ጊዜ ዘግየት ብሎ ሊጀምር ይችላሉ። የተለመዱ ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የመገጣጠሚያ ህመምና ድካም ጨምሮ የጉንፋን ዓይነት ምልክቶች ነው። ቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስል / ሽፍታ ዋነኛው መገለጫው ነው። ይህ የቆዳ ምልክቶች መጀመሪያ ላይ ጠፍጣፋ ቀላ ያለ ሽፍታ ሆኖ ይጀምርና ከዚያ አብጦ ፈሳሽ ይቋጥራል። በመቀጠልም ይፈርጥና ይቆስላል። ይህ ቁስል በፊት ላይ፣ በአፍ ውስጥ፣ እና እንደ እጆች፣ እግር፣ ደረት፣ የመራቢያ አካላት ወይም ፊንጢጣ ያሉ ሌሎች የአካል ክፍሎች ላይ ሊወጣ ይችላል። ቁስሉ ሲቆይ ይደርቅና ተቀርፍቶ ይወድቃል። ከዚያም በአዲስ ቆዳ ይተካል። በተጨማሪም የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚዎጡ ንፍፊቶች ማበጥ ያሳያል። ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ከ2-4 ሳምንታት ይቆያሉ። ከቁስሉ ላይ ናሙና በመውሰድ በላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ ይችላል። ህክምናው ምንድር ነው? ህክምናው በዋናነት የተያዘውንን ሰው ኳራንቲን ማድረግ ነው። ለታማሚው ቀላል ማስታገሻዎች ይበቁታል። የትኩሳት ማብረጃ መድሃኒት መውሰድ ወይም የህመም ማስታገሻ መዋጥ በቂ ሊሆን ይችላል። ቁስሎች እስኪድኑ እና አዲስ ቆዳ እስኪወጣ ድረስ ኳራንቲን መቀጠል አለበት፣ ይህ ከ 3-4 ሳምንታት ሊወስድ ይችላል። በሽታው የተገኘበት ሰው ሊያደጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች 👉ከተቻለ በቤት በተለዬ ክፍል ውስጥ ኳራንቲን በማድረግ ከሌሎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ። 👉እጅን በተደጋጋሚ በሳሙና እና በውሃ ይታጠቡ ወይም በሳኒታይዘር እጅ ማጽዳት። 👉ማስክ ማድረግ። 👉ከሌሎች ጋር የምንጋራቸው እቃዎች መኖር የለበትም። የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት መውሰድ ኢንፌክሽንን ለመከላከል ይረዳል። ክትባቱ በተለይም በሽታው ካለበት ሰው ጋር በተገናኘን በ4 ቀናት ውስጥ መሰጠት አለበት። ለማጠቃለል የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ስርጭቱ አስጊ ደረጃ ቢደርስም መደናገጥ አያስፈልግም። በበሽታው የተያዙ አብዛኛዎቹ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ይድናሉ። አብዛኛውን ጊዜ ለሞት የሚዳርግ አይደለም። በተገቢው የግንዛቤ እና የመከላከያ እርምጃዎች እራሳችንን እና ማህበረሰባችንን መጠበቅ እንችላለን። አንዴት እንደሚተላለፍ በመረዳት፣ ምልክቶቹን በማወቅ እና የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ቫይረሱን ለመከላከል፣ ስርጭቱን ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚረዱን ዘዴዎች በእጃችን ናቸው። ማስታወሻ፦ በዚህ መጣጥፍ ላይ የተካተቱት ይዘቶች ወይም ሀሳቦች ለአጠቃላይ መረጃ ብቻ ናቸው። ለግል ምርመራ ወይም ህክምና የጤና ባለሙያዎን ያማክሩ። ተጨማሪ ምክር፣ እርምት ወይም ግብረ መልስ ለመስጠት በኢሜል፦ [email protected] እና ስልክ፦ +251921720381 ማግኘት ይችላሉ። ለግል ህክምና ዶ/ር መላኩ ጋር መመካከር ይችላሉ። ይህን መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት ለሌሎች ያጋሩ። - 💚💛❤️ Melaku Taye, M.D. Let us connect at Blog | TikTok | LinkedIn | Telegram | Rate me
إظهار الكل...
👍 4
Repost from PULSE
ለስኳር ታካሚዎች ሩዝን ወዲያውኑ እንደበሰለ በትኩሱ (Fresh Rice) መመገብ ይሻላል ወይስ ፍሪጅ ቀዝቅዞ አድሮ እንደገና አሙቀን (Cooled and Reheated Rice) መመገብ? በዚህ ሳምንት በቲክቶክ ትሬንዲንግ ከሆኑት የጤና መረጃዎች መካከል አንዱ ሩዝን አቀዝቅዞ መመገብ ስኳር ያስተካክላል ቦርጭ ያጠፋል የሚል መረጃ እየተተራመሰ እንደሆነ አስተውለናል። በዚህ ትምህርታዊ መጣጥፍ ይህን ጉዳይ የምናይ ይሆናል። ሩዝ 80% ያህል ይዘቱ ስታርች (starch) የሚባለው ካርቦሃይድሬት ነው። በዚህ ከፍተኛ የካርቦሃይድሬት ይዘቱ ምክንያት ሩዝን በተመገብን ከመቅጽበት የደም ስኳር መጠን በከፍተኛ መጠን እንዲያሻቅብ ሊያደርግ ይችላል (high glycemic index)። ከፍተኛ ግላይሰሚክ ኢንዴክስ አለው ማለት ሩዝ እንደበላን በፍጥነት አንጀት ወስጥ በቀላሉ በመፈጨትና ወዲያውኑ ወደ ደም በመስረግ ስለሚዋሃድ ድህረ ምግብ የግሉኮስ መጠን በድንገት እንዲጨምር ያደርጋል ማለት ነው። ትኩስ የበሰለ ሩዝ (freshly cooked rice) በቀላሉ ሊፈጩና ሊዋሃዱ በሚችሉ ስታርቾች የበለፀገ በመሆኑ ወዲያውኑ እንደበላን የደም ውስጥ የግሉኮስ መጠን ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ያስከትላል። ትኩስ የበሰለ ሩዝ ጣፋጭ መሆኑ በፍጥነት ደም ውስጥ ወደ ግሉኮስ እንደሚቀየር ማሳያ ነው። ለጤነኛ ሰው ይህ የሩዝ ባህሪ ብዙ አሳሳቢ ላይሆን ይችላል። የስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ግን ይህ አደገኛ የደም ስኳር መጠን መጨመር (post-prandial hyperglycemia) ያስከትላል። ለረጅም ጊዜ ሲቆይ ደግሞ ለበርካታ የስኳር ህመም ተያያዥ ችግሮች ያጋልጣል። ስለሆነም ሩዝ ለስኳር ታካሚዎች እንዳሻቸው እንዲመገቡት የሚመከር አይደለም። ይህ ሲባል ግን ሩዝ መብላት ለስኳር ታካሚ የማይቀመስ ግዝት ምግብ ነው ማለት አይደለም። በሌላ በኩል፣ ሩዝ ከ12 እስከ 24 ሰዓት ፍሪጅ ቀዘቅዞ ከመብላቱ በፊት እንደገና የሚሞቅ ከሆነ የተለየ ባህሪ ይይዛል። ሩዝ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ የተወሰኑት ስታርቾች ወደ የማይልም የስታርች ዓይነት (resistant starch) ይለወጣሉ። የማይልም ስታርች አንጀት ውስጥ በከፊል የማይፈጭ ና የማይሰባበር ስለሆነ ወደ ደም ውስጥ አይሰርግም። ይህም ማለት የስኳር መጠናችን ቶሎ አይጨምርብንም ማለት ነው። ቢፈጭ እንኳ በጣም በዝግታ ስለሚሆን የፈጠነ የስኳር መጨመር አያስከትልም። የስኳር ታካሚዎች ስኳራቸው በሃይል ሳይጨምር እንዴት ሩዝን መመገብ የሚያስችሉ ተግባራዊ ምክረ ሃሳቦች እነሆ። የመጀመርያው ሩዝን በብልሃት የመብላት ጥበብ የበሰለ ሩዝዎን አቀዘቅዞ አድሮ ክዚያ እንደገና አሙቆ መብላት ነው። ሩዝን ካበሰሉ በኋላ ወዲያውኑ አይበሉት። ይልቁንም ለብዙ ሰዓታት እስከ 24 ሰዓት ፍሪጅ ውስጥ በ 4 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እንዲቀዘቅዝ ያድርጉት። መብላት ሲፈልጉ በሚቀጥለው ቀን እንደገና ያሙቁ እና ይብሉት። ይህን ቀላል ነገር ማድረግ ሩዝን መመገብ የስኳር ልኬታችን እንዳያሻቅብ ለመገደብ በመጠኑም ቢሆን ይረዳል። ከላይ እንደተጠቀሰው የበሰለ ሩዝ በሚቀዘቅዝበት ጊዜ የሩዝ ስታርች ባህሪ ስለሚቀይር አንጀት ውስጥ ምግብ የሚያደቁ ኤንዛይሞችን በመቋቋም በቀላሉ የማይልምና የማይፈጭ ጸባይ ይይዛል። ስለሆነም የደም ስኳር መጠን ቶሎ እንዳይጨምር ይከላከላል። ሌላኛው ወሳኝ ዘዴ ደግሞ መጠናችንን መገደብ ነው። ቀዘቀዞ የተሞቀ ሩዝም አንኳ ቢሆን አብዝተን ከበላን የስኳር መጠን ከፍ ያደርጋል። ያው በዝግታም ቢሆን ተፈጭቶ ወደ ስኳር መቀየሩ አይቀርማ! ሁሌም ቢሆን የምግባችንን መጠን መመጠን (Portion control) ይገባል። የስኳር ታካሚ ቢበዛ ቢበዛ ከግማሽ አነስተኛ ጭልፋ በላይ ሩዝ በቀን ቢመገብ ስኳር ከቁጥጥር በላይ እንዲወጣ ሊያደርገው ይችላል። በሌላ አነጋገር ሩዝን እንደግዝት ከምግብ ምርጫችን ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አስፈላጊ ባይሆንም ከበዛ ግን መዘዙ አይለቀንም። ከትኩስ የበሰለ ሩዝ ከመጠቀም ይልቅ የበሰለ ሩዝን አቀዝቅዞና እንደገና አሙቆ መመገብ በንጽጽር የተሻለ ነው ለማለት ነው እንጅ የቀዘቀዘ ሩዝ ለስኳር መጠን መጨመር በጭራሽ አስተዋጽኦ አያደርግም ተብሎ መተርጎም የለበትም። በዝግታና በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ስኳር ይጨምራል። በተለይ አብዝተን ከበላን ስኳር ከፍ ማለቱ አይቀርም። [It does not mean that cooled-reheated rice does not contribute to the rise in sugar levels, but it contributes less and very slowly to the rise in blood sugar levels compared to freshly cooked rice]. ሶስተኛው የሩዝ አመጋገብ ምክረ ሃሳብ ደግሞ ሩዝን ብቻውን ሙሉ ማዕዳችን ከማድረግ ይልቅ ከሌሎች ፕሮቲን እና በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች ጋር አብሮ መብላት ነው። እንዲህ ከከፍተኛ ፋይበር ያላቸው አትክልትና ገንቢ ምግቦች ጋር አብሮ ሲበላ የምግብ እንሽርሽሪት ሂደት እንዲረጋጋ ስለሚያደርጉ የደም ስኳር መጠን በፍጥነት እንዳይጨምር ያዝ ያደርገዋል። በቀላሉ ለማጠቃለል ያህል የበሰለ ሩዝ በትኩሱ ወዲያውኑ ከመመገብ ይልቅ አቀዝቅዞና እንደገና አሙቆ መብላት የሩዝ ስታርቾች ወደ የማይልም የስታርች ዓይነት (resistant starch) ስለሚለወጡ አንጀት ውስጥ በከፊል የማይፈጭ ና የማይደቅ ከሆነ ወደ ደም ውስጥ እንዳይሰርግ ይሆናል። ስለሆነም የስኳር መጠናችን ቶሎ አይጨምርብንም። ቢፈጭ እንኳ በጣም በዝግታ ስለሚሆን የፈጠነ የስኳር መጨመር አያስከትልም። ይህ ማለት ግን የቀዘቀዘ ሩዝ ምንም ካሎሪ የለውም ስኳርም በፍጹም አይጨምርም ማለት አይደለም። ማስታወሻ፦ በዚህ መጣጥፍ ላይ የተካተቱት ይዘቶች ወይም ሀሳቦች ለአጠቃላይ መረጃ ብቻ ናቸው። ለግል ምርመራ ወይም ህክምና የጤና ባለሙያዎን ያማክሩ። - 💚💛❤️ Melaku Taye, M.D. Let us connect at Blog | TikTok | LinkedIn | Telegram | Rate me
إظهار الكل...
👍 5
Repost from PULSE
አብዝቶ መቀመጥ - ሲጋራ ከማጨስ ያልተናነሰ የጤና ጠንቅ! ለሰው ልጆች ሁሉ ደህንነትና ጤና ትልቅ ስጋት ከጋረጡ ፈተናዎች አንዱ ዘመናዊነትና ከተሜነት ያመጣብን የአብዝቶ መቀመጥና ውዝፍነት አደገኛ ልማድ ነው ብንል ማጋናን አይሆንም። ከቀደሙ አያቶቻችን ጋር ሲነጻጸር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሯችን የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሚገድቡ ብቻ ሳይሆን ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ በሚጠይቁ ሁኔታዎች ውስጥ መኖር አስገዳጅ እየሆነ መጥቷል። በቤት ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣ የመጓጓዣ መንገዶች፣ ማህበራዊና ሌሎችም የአኗኗር ለውጦች በባህሪያችን ላይ ተጽእኖ አምጥተዋል - እንዳንቀሳቀስና ቁጭ እንድንል! የቢሮ ወንበራችን ላይም ይሁን መኪና ውስጥ አሊያም ቤታችን ሶፋ ላይ ሲብስም ገንዘባችን አውጥተን ጊዜ ለመግደል በየቡና ቤቱ ዘለግ ላለ ሰዓት መዘርፈጥ የየእለት ህይወታችን አንዱ አካል ሆኗል። ለመሆኑ ለረጅም ጊዜ መቀመጥ (prolonged sitting) እና ውዝፍነት (sedentary lifestyle) ሲባል ምን ማለት ነው? በዚህ የጤና ዘርፍ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው Sedentary Behavior Research Network (SBRN) የተባለው አለምአቀፍ የምርምር ተቋም እንደሚለው ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ ካለእንቅስቃሴ በተቀመጥንበት፣ ጋደም ባልንበት ወይም በተኛንበት ለአንድ ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ መቆየት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ውዝፍነት የሚባለው ደግሞ ይህ አብዝቶ መቀመጥ ወደባህሪ እድጎ ልማድ ሲሆንብን ነው። ልክ ሲጋራ እንደ ማጨስ፣ ከመጠን በላይ ውዝፍነት ለውፍረት፣ ቦርጭ፣ ስኳር ህመም፣ ልብ ሕመም፣ ካንሰር እንዲሁም ሌሎች እልቆ መሳፍርት የሌላቸው ስር የሰደዱ የበሽታ አይነቶች አጋልጦ የሚሰጥ ክፉ ልማድ ነው። ውዝፍነት ካለእድሜ ያሰረጃል ያጃጃል። በተጨማሪም አብዝቶና አዘውትሮ መቀመጥ ካለአድሜ የመሞትን እድል በእጅጉ እንደሚጨምር በዋና ዋና የህክምና መጽሄቶች ላይ የሚወጡ አያሌ ጥናቶች ያረጋገጡት አሌ የማይባል ሃቅ ሁኗል። ለዚህም ነው ለረዥም ሰዓት መቀመጥ በሚያስከትለው መዘዝ ምክንያት ‘the new smoking’ ተብሎ እየተጠራ ያለው። ‘ውይ የኛ ሃኪሞች! ሟርተኞች እኮ ናቸው! እንደናንትስ ወሬ ቢሆን ስንት መዓት በመጣብን ነበር! እሁን ደሞ ማን ይሙት መቀመጥ በምን ሳይንስ ነው ጎጂ የሆነበት ምክንያት?’ ለምትሉ እንደሚከተለው ነው። የሰውነታችንን ተፈጥሯዊ ስርዓተ እንሽርሽሪት (ሜታቦሊዝም) ሂደት ስለሚረብሽ ነው! ለረዥም ሰዓት በምንቀመጥበት ጊዜ ጡንቻዎቻችን እንቅስቃሴ-አልባ ይሆናሉ፣ የበላነው ምግብ (ካሎሪ) አይቃጠልም፣ የደም ዝውውራችንም እንደኤሊ ያዘግማል፣ ሙሉ የሰውነት ህዋሶቻችን ዱዝ ይሆናሉ። ይህ ውፍረት ያመጣል፤ የኢንሱሊንን ስራ ያስተጓጉላል (Insulin resistance)። በሂደትም ለብዙ ከባድ የጤና ችግሮች ያመቻቸናል። ስለዚህ ወዳጄ ሟርት አይደለም - መቀመጥ በሽታ ጎታች መሆኑ ያፈጠጠ ያገጠጠ እውነት ነው። የዚህን ትምህርታዊ ጽሁፍ ሙሉዉን መረጃ በዛሬው እለት የታተመዉ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወይም በአዘጋጁ ብሎግ ያገኙታል። - 💚💛❤️ Melaku Taye, Let us connect at Blog | TikTok | Facebook | LinkedIn |Telegram | Rate me
إظهار الكل...
👍 19😱 1
Hey there, future Hamster Warrior! 🐹💥 Join the Hamster Combat squad and score a whopping #5000,000 #coins daily! It’s time to unleash your inner fur-rocious fighter. Ready to roll? 🐾✨ Let’s conquer !
إظهار الكل...
3👍 2
01:38
Video unavailableShow in Telegram
ዶክተር - አብራሪም ነኝ.mp4 25 years Today , Professor Asrat Woldeyes Passed away.
إظهار الكل...
2.76 MB
11
Repost from PULSE
የታሸገ ውሃ እና የፕላስቲክ ብክለት ስጋት የፕላስቲክ ብክለት ዓለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ጥምን ለመቁረጥ ለብዙዎቻችን ተመራጭ የሆነው የታሸገ ውሃ ግን በፕላስቲክ ብክለት ምክንያት ለጤና አስጊ ነገር ይኖረዋል ብለው አስበው ያውቃሉ? በቅርቡ በአሜሪካ የሳይንስ አካዳሚ ያወጣው ጥናት በእያንዳንዱ ሊትር የታሸገ ውሃ ውስጥ ያለውን የፕላስቲክ ብናኝ መጠን በመለካት አስደንጋጭ መረጃ አውጥቷል። በአማካይ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ የማይክሮ ፕላስቲክ ብናኝ (Microplastic contaminations) አንዳላቸው አረጋግጧል። በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች የፕላስቲች ብናኞችን ለመለካት የተጠቀሙበት መንገድ በጣም የተራቀቀ hyperspectral stimulated Raman scattering (SRS) የሚባል አውቶሜትድ መለያ ሲሆን በጣም ጥቃቅን የፕላስቲክ ብናኞችን ልቅም አድርጎ በቅንጣት ደረጃ መለየት የሚችል መመርመርያ መሳርያ ነው። ይህ መንገድ ከዚህ በፊት የታሸገ ውሃ ደህንነት ለመፈተሽ ከምንጠቀምባቸው የኬሚካል ምርመራዎች በእጅጉ ይልቃል። ይህን መመርመሪያ ዘዴ በመጠቀም የታሸጉ የዉሃ ናሙናዎች ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የፕላስቲክ ብናኝ ብክለት እንዳለው ታውቋል። በአማካይ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ የማይክሮ ፕላስቲክ ብናኝ አንዳላቸው አረጋግጧል። ይህም ማለት እያንዳንዳችን ከእያንዳንዱ ሊትር የታሸገ ውሃ በአማካይ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ የማይክሮ ፕላስቲክ ብናኝ እንጠጣለን ማለት ነው። እነዚህ የፕላስቲክ ብናኞች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤና ስጋቶችን አስነስቷል። መርዛማ ናቸው ተብሎ ይታመናል። ፕላስቲኮች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ በሁሉም ቦታ ተስፋፍተው እንደመገኘታቸው መጠን ይህን ተጋላጭነት ለመቀነስ ምን ማድረግ ይሻላልል ይላሉ? እስኪ ሃሳብዎትን እና የመፍትሄ አማራጮችን ያጋሩን። ዋቢ Qian et al. Rapid single-particle chemical imaging of nanoplastics by SRS microscopy. Proc. Natl. Acad. Sci. 2024; 121 (3) e2300582121. https://doi.org/10.1073/pnas.2300582121
إظهار الكل...
👍 18 2😱 2🙏 2👎 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.