cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

PULSE

Quality health information for all! https://twitter.com/PulseEvents2015 https://www.facebook.com/pulseevents2015

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
222
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
👍 4
Health news: New Minister for the MoH-Ethiopia Today, Dr. Mekdes Daba has been appointed as the Ethiopia's new Health Minister replacing Dr. Lia Tadesse, who held the position since 2020.
إظهار الكل...
የስክሪን ጊዜ ገደብ ለአዋቂዎች ስክሪን ላይ አፍጦ ረዘም ላለ ጊዜ መቀመጥ ለውፍረት፣ ስኳር ህመም፣ ለልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎች እና ለአንዳንድ የካንሰር አይነቶች ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። ከመጠን ያለፈ የስክሪን ጊዜ አካላዊ የጤና ችግሮች ያስከትላል ለምሳሌ የዓይን ድካም፣ ራስ ምታት፣ የአንገት ህመም (texting neck syndrome), የጀርባ ህመም እና የፖስቸር መዛባት ያመጣል። በተጨማሪም ከስክሪኖች የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን እንቅልፍ ሊያስተጓጉል እና አጠቃላይ የእንቅልፍ ጥራትን ሊጎዳ ይችላል። ጤናን ብቻ ሳይሆን በጊዜ አጠቃቀም ላይም ጣልቃ ሊገባ ይችላል። በዋና የህይወት ተግባራችን ላይ ያለንን ትኩረትን ስለሚሰርቅ ስራችንን በጊዜ እንዳናጠናቅቅ እንቅፋት ይሆናል። ባስ ሲልም ከትዳር ጓደኛ፣ ቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ በመሻማት አለመግባባትና ጠብ ያመጣል። #WeArePulse. #WeInform&Engage. @PulseEvents
إظهار الكل...
የስክሪን ጊዜን ለመቀነስ ምን እናድርግ? 1. የስክሪን ማያ ጊዜያችንን መከታተልና ስንት ሰዓት እንደምናቃጥል ማወቅ የመጀመርያው እርምጃ ነው። ይህን ለማድረግ ስልኮቻችን ላይ ያሉ መከታተያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም በየቀኑ ስልክ ላይ ምን ያህል ጊዜ እናጠፋለን የሚለውን ማወቅ ይቻላል። 2. የስልክ መጠቀሚያ ጊዜ ገደብ ማስቀመጥ። ለምሳሌ የመዝናኛ ማያ ጊዜን መገደብ። ጊዜ ገደቡ ሲያልቅ አላርም እንዲጮህ ወይም ስክሪኑ እንዲጨልም በማድረግ ከስክሪን እረፍት እንድናደርግ ሊያስታውሰን ይችላል። 3. ስክሪን ስንጠቀም በማስተዋል ይሁን (Mindful Screen Use): ስክሪን እንዴት እና ለምን እንደምንጠቀም ማስተዋል ይገባል። በልማድ ወይም ከመሰላቸት እንዲሁ ጊዜ ለማቃጠል (mindless scrolling) ሳይሆን ፈልገን አስበንና ፈቅደን እየተጠቀምን እንደሆነ እራስን መጠየቅ ይገባል። ስናይም እንዲሁ የመጣልንን ሳይሆን እራሳችን የምንፈልገውን መረጃ ብቻ መርጠን ማየት ያስፈልጋል። 4. አንዳንድ የቤት ክፍሎቻችንን ከኤሌክትሮኒክስ ነጻ ዞን ማድረግ ለምሳሌ መመገቢያ ክፍሎች፣ አልጋ ክፍሎች ወይም ማንበቢያ ክፍሎች ውስጥ ምንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ይዞ አለመግባት። #WeArePulse. #WeInform&Engage. @PulseEvents
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለህጻናት እና ለአዋቂዎች የስክሪን ጊዜ ገደብ መመሪያ የስክሪን ጊዜ ገደብ ለልጆችና ታዳጊዎች ከልክ በላይ የስክሪን ጊዜ በልጆች አካላዊ እንቅስቃሴያቸው፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው እና ጤናማ የእንቅልፍ ስርዓታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያመጣል። የአእምሮ እደገትም ያዘገያል። የአይንና እይታቸው እድገት ላይም ተጽእኖ አለው። አሁን አሁን በርካታ ልጆች የእይታ መነጽር እምዲጠቀሙ ያስገደደው አንዱ ምክንያት ከልክ ያለፈ በልጅነት ኤሌክትሮኒክስ ስክሪን ላይ ማፍጠጥ እንደሆነ የሚጠቁሙ ጥናቶች እየተሰሙ ነው። ስለሆነም በተልቻለ መጠን ልጆች ስክሪን ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መገደብ ይገባል። ለልጆችና ታዳጊዎች የስክሪን ጊዜ ገደብ መመሪያ ምን ያህል ነው? ከሁለት አመት በታች ያሉ ህጻናት ምንም አይነት ኤሌክትሮኒችስ ስክሪን ፈጽሞ ማየት የለባቸውም። ከሶስት እስከ አስራ ስምንት አመታ ያሉ ልጆች ደግሞ የስክሪን ጊዜያቸው ከሁለት ሰዓት መብለጥ የለበትም። የልጆቻችንን የስክሪን ጊዜ ለመቀነስ ምን እናድርግ? ህጻናት ለአጠቃላይ እድገታቸው መሳለጥ መጫወት፣ ማንበብ እና ከቤተሰብ ጋር ማህበራዊ መስተጋብር መፍጠር እንጅ ስልክ፣ ቴለቪዥን እንዲሁም ቪዲዮ ላይ እንዲያሳልፉ መፍቀድ የለብንም። የልጆችን ስክሪን ጊዜ ገደብ (screen time curfew) በማበጀት ልጆችን መቆጣጠር ያስፈልጋል። ነገር ግን ልጆችን በመከልከል መቆጣጠር ከባድ ነው። በዋናነት የሚማሩት ወላጆችን በማየት ስለሆነ ወላጆች ህጻናት ባሉበት ስልክ ባለመነካካት፣ ቴሌቪዥን በማጥፋት ለልጆቻቸው አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል። #WeArePulse. #WeInform&Engage. @PulseEvents
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ክብደት የሚቀነሰው ኩሽና ውስጥ ነው፤ ጂም ለቅርጽ ነው። Lose weight in the kitchen; get fit in the gym! “በየቀኑ ስፖርት እሰራለሁ ግን ክብደቴ አይቀንስም” የሚል ቅሬታ ብዙ ጊዜ እንሰማለን። ብዙ ሰዎች የሚዘነጉት ነገር ‘መጥፎ አመጋገብን በስፖርት ማካካስ እንደማይቻል’ ነው። ስፖርት እስከሰራሁ ድረስ ተብሎ ያገኙትን መብላት ትችላለህ የሚል የተለመደ የተሳሳተ ግንዛቤ አለ። ክብደት የሚቀነሰው ኩሽና ውስጥ ነው ሲባል አመጋገብ ማስተካከል ዋነኛው እርምጃችን ነው ለማለት ነው። ‘በኋላ ላይ ስፖርት መስራቴ ስለማይቀር እስኪ ዛሬ ኬክም ሌላም ጣፋጭ እንደሻተኝ ልብላ’ እንላለን። ነገር ግን ደቂቃ በማትሞላ ጊዜ የበላናት ኬክና ዶናትን ለማቃጠል በርካታ ቀናትን የሚፈጅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ይፈልጋል። ‘ይህችንማ አሁን ጂም ስገባ ዶጋ አመድ ነው ማደርጋት’ ማቀድ አንደምናስበው ቀላል አይደለም። ስፖርት ማዘውተር ያለገደብ ለመብላት ሰበብ መሆን የለበትም። ስፖርት ስለምሰራ ብለን ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ካዘወተርን የምንፈልገውን ያክል ክብደት መቀነስ አይቻልም። የአንድ ሰአት ሩጫ በአንድ ደቂቃ ምግብና ድራፍት ሊቀለበስ ይችላል። ምንም ያህል ብንሞክር ጤናማ ያልሆነ አመጋገብን በስፖርት ብዛት መብለጥ አዳጋች ነው። ለዚህም ነው ክብደት የሚቀነሰው ኩሽና ውስጥ ነው፤ ጂም ለቅርጽ ነው የሚባለው። #WeArePulse. #WeInform&Engage. @PulseEvents
إظهار الكل...
👍 3
ለመሆኑ የጥንካሬ ስፖርት በሳምንት ስንቴ መስራት ይመከራል? • በሳምንት ከ2-3 ጊዜ የጥንካሬ ስፖርት መስራት በቂ ነው። • የጥንካሬ ስፖርት መስራት ይህን ያክል ከፍተኛ ጠቀሜታ ካለው የሳምንቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎ ውስጥ የጥንካሬ ስፖርት ማካተት አለብን። የጥንካሬ ስፖርት ለመስራት ብዙ መዋዕለ ንዋይ አይፈልግም። ማስታዎሻ፡ ከመጠን በላይ ስፖርት በመስራት የሚከሰት ጉዳትን ለመከላከል ከዝቅተኛ ክብደት ጀምሮ እና ቀስ በቀስ እየጨመሩ መሻሻል ይመከራል። #WeArePulse. #WeInform&Engage. @PulseEvents
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የጥንካሬ ስፖርት (Resistance exercise) አስፈላጊነት የጥንካሬ ስፖርት ሲባል የጡንቻ ጥንካሬን የሚጨምሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን መስራት ማለት ነው። ጡንቻን በማጠንከርና በማጎልበት የጡንቻን ብቃት የሚያሻሻል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ነው። የጡንቻን አቅም፣ ሃይልና ጥንካሬ የሚያፈረጥም ስፖርት ነው። የጥንካሬ ስፖርት የሚባሉን የትኞቹ ስፖርቶች ናቸው? በቤት ውስጥም ሆነ በጂም ጡንቻዎትን ለማጠናከር የሚሰሩ በርካታ የስፖርት አይነቶች አሉ። በመሳሪያ ወይም ካለመሳርያ (የእራስዎ የሰውነት ክብደት በመጠቀም) ሊሰራ ይችላል። • የእራስዎ የሰውነት ክብደት መጠቀም - ስኳት፣ ፑል-አፕ፣ ፑሽ-አፕ እና ቺን-አፕ የመሳሰሉትን መስራት • ክብደትን ማንሳት፡ የክብደት ማሽኖች, dumbbells, ክብደት ያላቸው ኳሶች የመሳሰሉትን መስራት • የሚወጠሩ የጎማ ባንዶች • የእግር ጉዞ ስናደርግ ወይም ስንሮጥ ተለባሽ ክብደት (weighted vest) ማድረግ በአንድ ጊዜ ኤሮቢክና የጥንካሬ ስፖርት ለመስራት ያስችላል። የጤና ጠቀሜታቸው ምንድን ነው? • እነዚህ የስፖርት አይነቶች ናቸው በዋናነት ቦርጭን ድራሽ አባቱ የሚያጠፉት። ጠንካራ ጡንቻዎችን በመገንባት በስብ መልክ የተከማቸን በጣም ከፍተኛ ካሎሪና ስብ ለማቃጠል ይረዳል። ስኳርን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል የማይተካ ሚና ይጫወታል። በካንሰር የመያዝ እድልን በእጅጉ ይቀንሳል።
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
‘’ጤና ላይ ኢንቨስት ማድረግ ከሁሉም የላቀ ትርፍ ያስገኛል’’ ይህ አባባል የራስ፣ ቤተሰብና ማህበረሰብ ጤና ላይ ኢንቨስት ማድረግ፤ ዋጋና ትኩረት መስጠት ስላለው ጠቀሜታ ይናገራል። ጥሩ ወለድ የሚያስገኝ ጠቃሚ ኢንቨስትመንት መሆኑን ይጠቁማል። ጤናችንን ከጠበቅን ጊዜ፣ ጥረት እና እውቀትን ተጠቅመን ሓብት ማፍራት እንችላለን። ማለም መስራት ማሳካት እንችላለን። በጤና ማጣት ምክንያት ለህክምና የምናወጣውን ከፍተኛ ወጪ እናስቀራለን። ለዚህም ነው ጤናን ለመጠበቅ ኢንቨስት በማድረግ የሚገኘው ጥቅም ከሌሎች የፋይናንሺያል ኢንቨስትመንቶች ከሚገኘው ጥቅም እንደሚበልጥ የሚታመነው።
إظهار الكل...
1. ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ በተለይም ከአንድ ሰዓት በላይ ካለእንቅስቃሴ አለማሳለፍ ዘመናዊ ህይወታችን በቴክኖሎጅ ቀላል እየሆነ ስለመጣ ብዙዎቻችንን ስንቅስቃሴ አልባ የአኗኗር ዘይቤ እንድንከተል ተገደናል። ካለእንቅስቃሴ ብዙ መቀመጥ ከበርካታ የጤና ችግሮች መንስኤ እንደሆነ ይታመናል። ለረጅም ሰአታት መቀመጥ ለበርካታ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን በእጅጉ ይጨምራል። ስለዚህ ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ በተለይም ከአንድ ሰዓት በላይ ካለእንቅስቃሴ አለማሳለፍ ይመከራል። 2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክሰስ (exercise snack) ማዘውተር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ 'መክሰስ' ሲባል በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን አጭር የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራትን ነው። በተቻላችሁ ጊዜ በቤት ውስጥ ወይም በስራ ቦታ የመንቀሳቀስ እድሎችን መፍጠር እንደማለት ነው። በተለይም ስራ በዝቶብን ለስፖርት ጊዜ ስናጣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክሰስ ‘መብላት' ባለንበት ቦታ ለትንሽ ደቂቃ ብናፍታታ አስገራሚ የጤና ጥቅሞችን ያስገኛል። ለምሳሌ ቢሮኣችን ጸሃፊያችንን ወረቀት አምጭልኝ ብለን ከማዘዝ እራሳችን ተንቀሳቅሰን ኮፒ ማድረግ፣ ደረጃ ወጣ ወረድ ማለት ሊሆን ይችላል። ወደ ምሳ ለመሄድ መኪና ከምንይዝ በእጋራችን የስፖርት ስናክ ማድረግ ማለት ነው። ስልክ ስናወራም እየተንቀሳቀስን ቢሆን ይረዳል። ከወዳጅ ጋር ስንቀጣጠር አንድ ቦታ ቁጭ ከማለት ወዳሉበት በእግር መሄድም ሊሆን ይችላል። አውቶቡስ ከተሳፈሩ ቀደም ብሎ ከፌርማታ ይውረዱ እና ቀሪውን መንገድ ይራመዱ። 3. በየቀኑ ከአስር ሺህ እርምጃ የማያንስ በእግር መጓዝ በቀን ከ10,000 እርምጃዎች በላይ መንቀሳቀስ ጤናማ ለመሆን ይረዳል። በስልካችን ወይም የእጅ ሰዓታችን የእንቅስቃሴ መከታተያ በመጫን በየቀኑ ምን ያህል እርምጃ እንደተጓዝን በማየት በየጊዜው ለማሻሻል መትጋት ጠቃሚ ነው። 4. በየቀኑ ከ30 ደቂቃ የማያንስ እስኪያልብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በተለይም መካከለኛና ከዚያ በላይ ኃይለኛ የኤሮቢክ እንቅስቃሴ እና ጡንቻን የሚያጠናክሩ ልምምዶችን መስራት ይመክራል። 5. የበለጠ በሰራን ቁጥር የላቀ የጤና ጥቅም እናገኛለን። Source: Bull, F.C., S.S. Al-Ansari, S. Biddle, et al., World Health Organization 2020 guidelines on physical activity and sedentary behaviour. Br J Sport Med 2020;54(24):1451-1462
إظهار الكل...
👍 3
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.