cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
5 930
المشتركون
+424 ساعات
+187 أيام
-1330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለወሰን ማስከበር ስራ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካሳ መክፈሉን ገለጸ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለፈው የ2016 በጀት ዓመት ባከናወናቸው የመንገድ ግንባታ ሳቢያ ለተነሱ መሰረተ ልማቶች እና የመኖሪያ ቤቶች 1.8 ቢሊዮን ብር የካሳ ክፍያ መፈጸሙን ገለጸ። ➡️ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዘንድሮው በጀት ዓመት በሚገነባቸው መንገዶች እና ከሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ 546 የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች እንደሚነሱ አስታውቋል።  ➡️ መስሪያ ቤቱ ይህንን ያስታወቀው፤ ያለፈውን አመት የስራ አፈጻጸሙን እና የ2017 ዓ.ም. በጀት ዓመት እቅድ አስመልክቶ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 9፤ 2017 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው። ➡️ የአዲስ አበባ ከተማን የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲገነባ እና እንዲጠግን በአዋጅ ኃላፊነት የተሰጠው መስሪያ ቤቱ፤ በ2016 በጀት ዓመት 1,140 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ማከናወኑን በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል።  ➡️ በመንገድ ግንባታ እና ጥገናው ሳቢያ 682 ቤቶች እንዲነሱ መደረጋቸውን የገለጸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ከ1,200 በላይ በሆኑ የመብራት እና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል። ➡️ ቤቶቹ እና መሰረተ ልማቶቹ እንዲነሱ የተደረጉት፤ መንገዶች በሚገነቡበት “ወሰን ውስጥ የሚገኙ” በመሆናው ምክንያት መሆኑን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።  🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር Binance‼️ Binance የራሱን Mine app Launch አድርጎዋል ።ብዙ የተንዛዛ አሰራር የለውም። በጣም ቀላል እና ግልፅ ነው። Game ተጫውቱ 6 እድል አላቹ - Game'u እያለሙ Timing ጠብቆ ቢጫ ኮይኖቹን ማግኘት ነው - እንደየ Sizeአቸው የተለያየ Point ይሰጣሉ፡፡ (ጥቁሮቹን ከነካቹ point ይቀንሳል) - DAILY CHECK IN አርጉ - TASK ስሩ የBINANCE ACC አገናኙ እድላቹ ሲያልቅ በየ4 ደቂቃው እየገባቹ ተጫውቱ! ለመጀመር👇👇👇 https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_728604522&startapp=ref_728604522&utm_medium=web_share_copy
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በደቡብ ጎንደር ዞን ከሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ለቀው ወጡ በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ከ2016 ዓ.ም ማብቂያ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ዘግባለች።   የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እስቴ መካነ ኢየሱስ፣ አንዳቤት፣ ሙጃ፣ ስማዳ እና ታች ጋይንት ከሚባሉ ወረዳዎች ከነሐሴ ዕኩሌታ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ባሉት ጊዜያት ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ተገንዝባለች።  የመንግስት ኀይሎች ለምን ከአካባቢው እንደወጡ በይፋ አልተናገሩም። በወረዳዎቹ የነበሩ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሙሉ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር ወደ ዞኑ መቀመጫ ደብረታቦር ገብተዋል። ይህን ተከትሎም በወረዳዎች ኹሉም ዓይነት የመንግሥት አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን፣ በፖሊስ እና በሚሊሻ የሚሰጡ አገልግሎቶችም በተመሳሳይ ቆመዋል።  በአንጻሩ በእነዚህ ወረዳዎች ባንኮች እና የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ነው ተብሏል። ትምህርት ቤቶች እስካሁን ምዝገባ አላከናወኑም።  የአማራ ክልል መንግስት የኮምኒኬሽን ቢሮ ስለጉዳዩ ላቀረብንለት ጥያቄ ጉዳዩን መመለስ የሚችለው የኮማንድ ፖስቱ ነው ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከወረዳዎቹ ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ በቦታው የተተኩት የፋኖ ታጣቂዎች የራሳቸውን የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት ጥረት እያደረጉ ነው። በአንጻሩ የዞኑ ዋና መቀመጫ ደብረታቦር እንዲሁም ንፋስ መውጫ፣ ፎገራ እና ደራ ወረዳዎች ዋና ከተሞቻቸው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ስር ይገኛሉ። ሆኖም በዞኑ ዋና ከተማ ደብረታቦር ዙሪያ ታጣቂዎች በብዛት እንደሚገኙ ሰምተናል።  በሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችም ሰሞኑን በኹለቱ ኃይሎም መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ ቆቷል።  ሰሞኑን በመንግስት ወታደሮች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆኑት በጎንደር እና በደባርቅ ከተሞች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ ሲካሄድ ሰንብቷል። ይህን ተከትሎም በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ተገንዝበናል። በክልሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ግጭት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞትና ለአካል ጉድት መዳረጋቸውን ብሎም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ።   Via ዋዜማ 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
" ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት ትከታተላለች አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ተገቢውን ምላሽ ትሰጣለች " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በመግለጫቸው ፥ " የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ልዩ ትኩረት ይሰጣል " ሲሉ ጠቁመዋል። " ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ በበጎ መንፈስ የተቃኘ ዘላቂ ዲፕሎማሲ ላይ አተኩራ ትሰራለች "ም ብለዋል። " የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴም ሊቆም ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል። ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል። አምባሳደር ነቢያት ፥ ➡️ ከአውሮፓ ህብረት፣ ➡️ ከአሜሪካ ➡️ ከተመድ ልዩ መልዕክተኞች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቁመዋል። " ለሁሉም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ሆኖ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል " ብለዋል። #EPA 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 98.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ ኢትዮ ቴሌኮም መሪ የእድገት ስትራቴጂ በሚል የሶስት ዓመት እቅድ ያወጣ ሲሆኑ እቅዱ የማክሮ ኢኮኖሚ    ጭማሪውን  ታሳቢ  ያደረገመሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ  የሆኑት ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።በ2017 በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ውስጥ በቴክኖሎጂ  ሁሉንም ዘርፍ የሚያነቃቃ እና በጅማሬ ላይ ያሉ እንዲሁም አዳዲስ ቢዝነሶች የሚያድጉበት እና ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ከእቅዶቹ መካከል ቀዳሚ መሆኑን መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ሰምቷል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው ስራዎች 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን እንዲሁም በርካታ አዳዲስ ስራዎችን  እንደሚሰራም ተጠቁሟል። ተቋም በ2016 በጀት ዓመት 98.7 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን  በ2017 በጀት ዓመት ገቢውን ወደ 163.7 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱን አስታውቋል። በሌላ በኩል በዓመቱ  መሰረተ ልማቶችን  ማጠናከር እንዲሁም አዳዲስ መገንባት እና  የሞባይል ሽፋን አሁን ካለበት የተሻለ ለማድረግ 1298  አዳዲስ የሞባይል ጣቢያ በመገንባት አሁን ካለው በ15.6 በመቶ ለማሰደግ  እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ። እቅዱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ላይ የሞባይል  አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግን ያካተተ ሲሆን በዓመቱ የደንበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊዮን ለማድረስ የታቀደ መሆኑም ተጠቁሟል። 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
👍 1
በሊባኖስ በቀናት ልዩነት ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰ የኮሙኒኬሽን መሳሪያ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲገደሉ 450 ያህሉ ቆሰሉ በሊባኖስ ውስጥ በገመድ አልባ የመገናኛ መሳሪያዎች በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 20 ሰዎች ሲገደሉ ከ450 በላይ ቆስለዋል ሲል የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በዋና ከተማይቱ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች፣በካአ ሸለቆ እና በደቡባዊ ሊባኖስ እንደ ምሽግ በሚታዩ አካባቢዎች ታጣቂው ቡድን ሂዝቦላ የሚጠቀምባቸው የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች ላይ ፍንዳታው ደርሷል። ፍንዳታው የተከሰተው ማክሰኞ የሂዝቦላህ አባላት ላይ ፔጀርስ ፈንድተው የተገደሉ 12 ሰዎች በቀብር ስነ-ስርዓት ወቅት ነው። ለዚያ ጥቃት ሂዝቦላህ እስራኤልን ተጠያቂ አድርጓል። እስራኤል በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም። ጥቃቶቹ የደረሱት የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት “በጦርነቱ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ” መጀመሩን ካስታውቁ እና የእስራኤል ጦር ክፍል ወደ ሰሜናዊ ክፍል እንዲሰማራ ትዕዛዝ ከሰጡ በኃላ ነው። የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሊባኖስ ቡድን ሂዝቦላህ ትእዛዝ ማስተላለፊያ የኮሙኒኬሽን መስመር ላይ በታይዋን የተሰሩ 5 ሺ ፔጃሮች ውስጥ አነስተኛ መጠን ያለው ፈንጂ በመትከል  የማክሰኞው ፍንዳታ እንዲሳካ ማድረጉን የሊባኖስ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ ገልጿል። ይህ ሴራ ብዙ ወራትን ያስቆጠረ ነው። ጥቃቱ በሂዝቦላህ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በሊባኖስ የሚገኙ ሆስፒታሎችን እንዲጨናነቅ አድርጓል ። አንዳንድ ተጎጂዎች ለዓይነ ስውርነት ሲዳረጉ ሌሎች ደግሞ የሰውነት አካል መቆረጥ ያስፈልጋቸዋል ።በሊባኖስ እና በሶሪያ ከተከሰቱት ገዳይ ፍንዳታዎች ጋር የተገናኘው የታይዋኑ ፔጀርስ አምራች ጎልድ አፖሎ ፔጀሮቹ የተሰሩትየጀሮ ማ በአውሮፓውያን ባሲ ድርጅት ነው ብሏል። የታይዋኑ ኩባንያ ፔጀሮቹ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ላይ መቀመጫውን ላደረገው ባሲ ምርቱን እንዲሰራ ፍቃድ ሰጥቶታል። ፔጀር የሬዲዮ ዌቭ የሚጠቀም የመገናኛ ዘዴ ነው። ሰዎች መረጃ ሲልኩ የሚተላለፈውም የሬዲዮ ፍሪክዌንሲ በመጠቀም ነው። መልዕክት የተላከለት ሰው መልዕክቱ እንደደረሰው በንዝረት መልዕክት መስጠት የሚችል ሲሆን አጭር የጽሑፍ ወይም የድምፅ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ይችላል።እ.አ.አ 1980ዎቹ እንዲሁም 90ዎቹ በስፋት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ የግንኙነት መሳሪያ አሁን ላይ በሞባይል ስልክ ቢተካም አሁንም ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ጥቅም ላይ ይውላል። 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
" ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አቅዷል " - በህወሓት ጉባኤ ያልተሳተፉት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በህወሓት ጉባኤ ላይ ያልተሳፉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በጋራ መግለጫ አውጥተዋል። በዚህም " ህገመንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን ሌላውን የማባረር ሞራልና ስልጣን የለውም " ብለዋል። ከሰሞኑን በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን አቶ ጌታቸውን ጨምሮ 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትን ማባረሩ ይታወሳል። የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ " ህገ-መንግስትና ህገ ድርጅት በመጣስ ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ሌላውን የማባረር ህጋዊና ሞራላዊ ስልጣን የለውም " ከማለት ባለፈ " መፈንቀለ መንግስት ለማካሄድ ማቀዱን ደርሰንበታል " ብለዋል። " የህገወጡ ቡድን መሪ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጄኖሳይድ ፍትህ እንዲያገኝና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ መታገል ሲገባው ጉዳቱ ወደ ቁጥር ጨዋታ በማውረድ የህዝብ መስዋእትና የወጣቶች ጉዳት ዋጋ እያሳጣው ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል። ከሰሞኑን ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል " ኒው ሆራይዘን " ከተሰኘ የማህበራዊ ሚድያ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። በዚህ ወቅትም " By the way ከአንድ ሚልየን በላይ አለቀ የሚለው ፤ ማስረጃ የለው፣ ጥናት የለው ፣ ለማስፈራርያ ነው የሚውለው። ተጨፍጭፈናል ለማለትም አይደለም ፣ ጄኖሳይድ ተፈፀመብን ለማለትም አይደለም። አመራሩ አስጨረሰን ይላል ፤ አመራር ለመምታት ፣ ስልጣን ለመያዝ የማይሰራ ነገር የለም። " ሲሉ ተናግረው ነበር። በኃላም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ " በህዝባችን ላይ የተፈፀመው ጄኖሳይድ አሁንም በርካታ በወራሪዎች ስር ያሉ የትግራይ አከባቢዎች ነፃ ባለመውጣታቸው ምክንያት የተሟለ መረጃ መስጠት ባይቻልም የደረሰው እልቂት ግን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ መሆን እንደሚችል ለመግለፅ እፈልጋሎህ " የሚል ማስተባበያ ለመስጠት ሞክረዋል። የአቶ ጌታቸው ቡድን ህገ-ወጥ ሲል የሚጠራውን የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድንን " ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ሸምጥጦ በመካድ የዓለም ማህበረሰብ የተከራከረለትና የመሰከረውና የህዝብ እልቂት ወደ ጎን በመተው ዋጋ የሌለው እንዲሆን ወሰኖ ጥላሸት በመቀባት ላይ ይገኛል " ሲል ከሷል። " ህገወጥ ቡድኑ ቡድናዊ የስልጣን ፍላጎቱ በፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ፣ በማሰፈራራትና ሃሳቦች በማፈን ለመጫንና ለማሳካት ላይ ታች በማለት ይገኛል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ይባስ ብሎ የመንግስት መዋቅር አንዲፈርስና ትግራይ መንግስት አልባ ሆና የረብሻና ግርግር ማእከል እንድትሆን እየሰራ ነው " ሲል አሳውቋል። " ህገወጥ ቡድኑ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ማቀዱ ግልፅ ሆኗል " ያለው የማእከላዊ ኮሚቴው " ጊዚያዊ አስተዳደሩና ህዝቡ ከአደገኛ አካሄዱ ሊያስቆሙት ይገባል " በማለት አክለዋል። 50 ዓመት ያስቆጠረ ድርጅት እንደ አዲስ እንዲመዘገብ በማድረግ የትግራይ ህዝብ ትግል የካደው ቡድን ህዝቡና የዳያስፓራ አባላት እንዲታገሉት ጥሪ አቅርቦ የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ለማስመለስ ፓለቲካዊ ውይይት መጀመሩን አመልክቷል። መላው ህዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርቧል። በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ባካሄደው 14ኛው ጉባኤ ያልተሳተፉና ሂደቱን የተቋወሙት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት " ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነታቸው አባርሪያለሁ " ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል። 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
አስቴር አወቀ እና መአዛ ብሩን ጨምሮ ሶስት ሴት ኢትዮጵያውያን ሊሸለሙ ነው ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ እና ሌሎች ሶስት ሴት ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው። በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር ተሸላሚዎች ታውቀዋል። ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ሥነስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ሲሆን እስካሁን አራት ጊዜያት ተካሂዷል። ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች አምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያንን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተሰምቷል:። የዚህ አመት ተሸላሚዎች በሙሉ ሴቶች ሲሆኑ በስነ ጥበብ ዘርፍ ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀና አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ በስፖርቱ ዘርፍ የማራቶንና የ5 ሺህ ሜትር የዓለማችን ክብረወሰን ባለቤቶች ትዕግስት አሰፋና ጉዳፍ ፀጋይ እንዲሁም በቢዝነስ ዘርፍ ርብቃ ሀይሌ ተሸላሚዎች ይሆናሉ። በዕለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረጋላቸው በርካታ እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል። ተሸላሚዎቹ ከግዛቶቹና ከተማዎቹ ተወካዮች የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል። በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የሙዚቃ ዝግጅት በወጣቷ ድምፃዊት ራሄል ጌቱና በታዋቂው መሳሪያ ተጫዋች ሰላም ስዩም የሚቀርብ ይሆናል። የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያውያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል እሁድ በፈረንጆቹ ጥቅምት 13 ቀን 2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት ይካሄዳል። አራዳ ኤፍኤም 95.1 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
👍 5
ሰበር Binance‼️ Binance የራሱን Mine app Launch አድርጎዋል ።ብዙ የተንዛዛ አሰራር የለውም። በጣም ቀላል እና ግልፅ ነው። Game ተጫውቱ 6 እድል አላቹ - Game'u እያለሙ Timing ጠብቆ ቢጫ ኮይኖቹን ማግኘት ነው - እንደየ Sizeአቸው የተለያየ Point ይሰጣሉ፡፡ (ጥቁሮቹን ከነካቹ point ይቀንሳል) - DAILY CHECK IN አርጉ - TASK ስሩ የBINANCE ACC አገናኙ እድላቹ ሲያልቅ በየ4 ደቂቃው እየገባቹ ተጫውቱ! ለመጀመር👇👇👇 https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_728604522&startapp=ref_728604522&utm_medium=web_share_copy
إظهار الكل...
👍 3
ሰበር ዜን☄️☄️ የቱርክ ባሕር ሃይል መርከቦች ወደ ሶማሊያ ሰርጥ በሰልፍ መግባት መጀመራቸው ተዘግቧል። ኢትዮጵያን ለመውረር ደጋግማ የሞከረችው የቀድሞዋ ኦቶማን ተርኪ ዳግም የተወለደች ይመስላል ያለው ዘገባው ቱርክ የሶማሊያን አንጦራ የማዕድን ሃብት አውጥታ በመጠቀም በምትኩ የሶማሊያን ዳር ድንበር ማስጠበቅ በሚል የፈጸመችውን ስምምነት ለመተግበር ነው ጦሯን ያሰማራቸው ብሏል። በዚህም መሰረት የቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ምርምር መርከብ በቱርክ የባህር ኃይል መርከቦች ታጅቦ በሜዲትራኒያን ባህር አቋርጦ ወደ ሶማሊያ ወደብ መግባቱን የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ወደ ሶማሊያ የተላከው ጦር ባራክታየር የተባሉትን የቱርክ ድሮኖችን በገፍ የታጠቀ መሆኑን ያስታወሰው ይሄው ዘገባ የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር ጦሩ የተላከው በሶማሊያ የተገኘውን የፔትሮሊየም ማዕድን ቁፋሮ ሲካሄድ ለሚፈጠሩ ያልተጠበቁ ጥቃቶች እና አደጋዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ብሎም ጥበቃ ለማድረግ ነው የሚል ምክኒያት ነው ያስቀመጠው። የቱርክ ባህር ሃይል ግዙፍ ጦሩን ወደ ኢትዮጵያ መገኛ ሶማሊያ የላከው ከግብጽ ጋር በሚስጥር የተያዘ ዝግ ስብሰባ ካደረገ በኋላ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ። አሁን በቱርክ ልሳን የምትናገረው ግብጽ ሆናለች። 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 🎆 ⚡️አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ          ✨  Telegram :- https://t.me/berbirmereja                                           ✨  Facebook--› https://www.facebook.com/berbirmereja/            ✨  YouTube: -, https://youtube.com/@BerbirMereja
إظهار الكل...
👍 6
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.