cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

GSFGBC፡ ጎሮ ሰፈራ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ

ይህ የቴሌግራም ቻናል በኢትዮጽያ ሙሉ ወንጌል አማኛች ቤተክርያን የጎሮ ሰፈራ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ፣የሚከናወኑና የሚተገበሩ ፕሮግራምዎችን መከታተያ page ነው፡፡ this is official page of goro sefera full gospel believers church... If you have any question Contact: @Kirubel76 @pastor_sisay

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
370
المشتركون
-124 ساعات
+47 أيام
+2930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

“እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ በተናገረኝ ጊዜ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በኮሬብ በቆምህበት ቀን ዓይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አስታውቀው።” — ዘዳግም 4፥9-10
إظهار الكل...
“ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።” — ዘፍጥረት 18፥19
إظهار الكل...
“አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።” — ዘፍጥረት 26፥5
إظهار الكل...
ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻውን ትምህርት—ዮሐ 14-16—እንዲህ በማለት ጀመረ፤ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ" (14፥1)። ከደቀ መዛሙርቱ የሚለይበት፣ ይልቁንም ደግሞ ሊሰቀል አንድ ቀን ብቻ የቀረበት ጊዜ ስለነበር እንዳይጨነቁ አሳሰባቸው። አለመጨነቅ በማመንና በመታመን ካልተተካ፣ ጭንቀት ውስጥ ተመልሶ መግባት አይቀርም። ጌታ የማዘናቸው ምክንያት እየሆነ—ስለሚለያቸው—የመጽናናታቸውም ምክንያት ሆኗል። የትኛውም ሁኔታ የጭንቀት ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በእግዚአብሔርና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ግን መረጋጋትንና ከሥጋት ነጻ መሆንን ያጎናጽፋል። ማመን ማወቅን ይጠይቃል። አምላካቸውንም የሚያውቁ እየታመኑበት ይቀጥላሉ።
إظهار الكل...
1
የዕለቱ ሐሳብ መታመን የሁልጊዜ እውነታ እንጂ ውስን ልምምድ አይደለም። በሁለት ምክንያት ሀልጊዜ እግዚአብሔርን እንታመናለን፤ የመጀመሪያው ውስንና ደካማ መሆናችን ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እርሱ የዘላለም መታመኛ መሆኑ ነው። ነቢዩ እንዲህ አለ፤ "በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐምባ ነውና" (ኢሳ 26፥4)። እርሱ በርግጥ ለየትኛውም ሁኔታና ዘመን ዐምባ ነው። ጥበቃውና ከለላነቱ በማንኛውም ረቂቅ ጥቃት የማይጣስ ስለሆነ፣ በርሱ የሚታመኑትን ከቶ አያሳፍራቸውም።
إظهار الكل...
አገልግሎት የጀመርኩት አሥመራ አማኑኤል ቃለ ሕይወት ነው። የሕጻናት የእሁድ ትምህርት በማስተማር። ሕጻናትን ማስተማር ሁሌም ፈገግ ያሰኛል፤ ያስቃልም። ከዚያ ወዲህ ሁሌም የሕጻናትን ቃላት እለቃቅማለሁ። የራሳችንንም ልጆች። የአባታችን ሆይ ጸሎት ውስጥ ከተለያዩ ልጆች ከሰማኋቸው ውስጥ አንድ ላይ አድርጌ ላካፍል። በፀባይ የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይከደን፤ መንግሥትህ ትምታ፤ ፍቃዷ በፀባይ እንደሆነች፥ እጅጌ በምክር ትሁን፤ የሌለ እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ በድናችንን ቅበርልን፤ ሆድ ፈተና አታግባን፤ ከግፉ አድነን እንጂ፤ መንግሥቱና ኃይሉ ያንተ ናቸው፤ ዘላለምም፤ አሜን። እነዚህ ልጆች ናቸው። አዋቂዎችስ የሉም? እግዚአብሔርን በፀባይ ሊያኖሩ የሚሹ? የሚያስፈራሩት። ማርያም የማይሆን ጥያቄ ጠይቃው ኢየሱስ፥ 'አይሆንም!' ሲላት፥ 'እነዚህን ጡቶቼን እቆርጣቸዋለሁ!' ስትለው፥ 'በቃ ይሁን።' ብሎ እንደመለሰላት የተአምረ ማርያም ተረት። እግዚአብሔርን ፀባይ ሊያስገዙ ብቻ ሳይሆን እጁን ጠምዝዘው ሊወስዱ የሚከጅላቸው የሉም? የሚያስፈራሩትስ? በሕጻናት ስቀን እንደምናርማቸው በነዚህ ገና ስንስቅ እጅጌያቸውን አጥፈው ሲመጡብን ምን ይባላል? ያኔ፥ በፀባይ የምትኖር ሳይሆን በፀባይ የምንኖር መሆን ግድ ይላል! በድናችንን ቅበርልን ተመችቶኛል። ምንጭ በዘላለም መንግሰቱ ተጻፈ
إظهار الكل...
የመልዕክት አቅራቢ: ጋሽ ንጉሴ ቡልቻ የመልዕክት ክፍል: (ያዕቆብ መልዕክት 4:1-17) ቁ1-9 መግቢያ ጠብ እና ጦርነት ከየት ይመጣል? ከሚለው ጥያቄ ይጀምራል። ምን ያጣላናል? የፍጅት መንስኤው መነሻውን መመርመር ያስፈልጋል። ከውጭ ከሚታየው አይደለም የጀመረው፣ በውስጣችሁ ብልቶቻችሁ ይፋተጋሉ ይላል። መመኘት ፣  ያልተገራ ፍላጎት ነዉ ወደ ጠብ የሚመራው። ምቾቶችሁ ወይም  ፍላጎቶቻቸሁ አምጣ የሚል ስሜት ያላቸው ውጊያ ናቸዉ። ትመኛላችሁ ፣ ትገድላላችሁ ፣ ትፈልጋላችሁ ፣ ትዋጉማላችሁ የሚለው በቃኝ አለማወቅን ነው። ለመሆኑ የሰው ፍላጎቶች ምንድን ናቸው? - የድሎት ፍለጋ፣ በልቶ ለመጥገብ፣ ለብሶ ለመዋብ ፣ የገንዘብ ወይም ሀብት የማካበት ፍለጋ፣ ታዋቂ የመሆን ፍለጋ ናቸዉ። - አመንዝሮች የሚለዉ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ቦታ ለሌሎች አማልክት መስጠትን፣ ከጌታ ውጪ ሌላን መውደድን ነዉ። - እናንተ ለእግዚአብሔር በኪዳን የታጫችሁ ሆናችሁ ሳላችሁ፣ ፍቅረ-እግዚአብሔርን ከድታችሁ ከአለም ጋር አንድ ሆናችሁ እያለ ነዉ። ምናለበት እግዚአብሔርንም አለምንም ብወድ ለሚለው የሰው ልብ ከቶ እንደማይታሰብ ነው አጥብቆ የሚናገረው። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ብቸኛ እና ሙሉ ፍቅር ነዉ ሊሆን የሚገባው ፣ ግማሽ  የአለም ፍቅርን አያካትትም። አብዛኛው የሰላም እጦት የ2ቱ ፍቅር ሽሚያ ነው። እግዚአብሔርን ስንወድ አለምን አብረን ማስተናገድ አንችልም ፣ የርሱ አግላይ ፍቅር ስለሆነ ነዉ። በፍጹም ልብህ፣ ነፍስህ፣ ሀይልህ ውደድ። ዮሀንስ በ1ኛው መልዕክቱ ላይ የአለምን ገጽታ በ3ት ከፍሎ ያየዋል። 1. የስጋ ምኞት 2. የገንዘብ  ትምክህት 3. የአይን አምሮት ናቸው እግዚአብሔር በውስጣችን ያሳደረው መንፈስ ቀናተኛ መንፈስ ነዉ። አለምን በመውደድ ምክንያት ልንገዳደረው አይገባም። ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 4:12-13 ይህን ይላል፡ ''ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብም፣ ባገኝም ሆነ ባጣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ኑሮዬ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ። ኀይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።'' በማለት የእርካታን ልክ ይናገራል። የበቃኝነት ሚስጥር ነው። እግዚአብሔር ሁሉን  ሰጪ ነው። በርሱ ያገኘነው ደስታ ሰላም እና እርካታ ግን ከሁሉ ይበልጣል። 2ቆሮ 5 ላይ ''ብንኖር ወይም ብንሞት ለርሱ እንቀናለን'' አለ። በእግዚአብሔር ደስ ይበለን። ዮሀ 13፡- ጌታ ኢየሱስ የደቀመዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ሲነሳ አባቱን እና አምላኩን ማወቁ ነዉ። ትህትና ከእውቀት ይጀመራል። እግዚአብሔር ለትሁታን ጸጋ ይሰጣል። ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እውነተኛ ንስሀ ጸጸት አለው። አልቅሱ የሚለው ይሄን ነው።
إظهار الكل...
ያዕቆብ 4 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ² ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ³ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ⁴ አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል። ⁵ ወይስ መጽሐፍ፦ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን? ⁶ ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። ⁷ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ ⁸ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ⁹ ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። ¹⁰ በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ¹¹ ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም። ¹² ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? ¹³ አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። ¹⁴ ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። ¹⁵ በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። ¹⁶ አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው። ¹⁷ እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።
إظهار الكل...
02:43
Video unavailableShow in Telegram
2.53 MB
👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.