cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethio Construction

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
26 646
المشتركون
+1024 ساعات
-57 أيام
-16330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

"በሕንጻ ግንባታ ሥራ selective material ከመጠቅጠቁ (ከመረምረሙ) በፊት ውኃ የሚጠጣው ለምንድነው? የጎንዮሽ ተጽእኖስ አለው ይላሉ?" 🏷የአፈር መጠቅጠቅ ሂደት ቅንጣቶች በመካከላቸው ያለውን ክፍተት ለመቀነስ የሚደረግ የመጫን ጉልበት (compaction) ትግበራ ነው። 💫በጣም የታመቀ፣ የተጠቀጠቀ አፈር የቅንጣቶችን ክፍተት በመቀነስ አፈሩ በጣም ጥቂት ቦታን (ስፋትን) እንዲይዝ ያግዘዋል። ⭐️ነገር ግን ይህንን የመጠቅጠቅ (ጥግግት) ደረጃ  የምናገኘው ጥሩ የእርጥበት መጠን ካለው  ነው። አፈሩ በጣም ጥሩ እርጥበት የሌለው ከሆነ የአፈር ቅንጣት ጥግግት በሚፈለገው ልክ ሊከናወን ስለማይችል ውስጥ ውስጥ  ያሉትን ክፍተቶች በሙሉ ለመሙላት አስቸጋሪ ይሆናል።  የተደፋው አፈር (Back filled or selective material) ሁሉም አካሉ በቂ እርጥበት እንዲኖረው ቢያንስ ከአንድ ሌሊት በፊት ቀደም ብሎ  ውኃ መጠጣት አለበት። 🌟የተወሰነ ጊዜ ቀድሞ ማጠጣት (አንደኛ) በሰዓቱ መርዘም የተነሳ የውኃውን የስርገት ሂደት በመጨመር እና ሁሉንም አካል የማግኘት (የማዳረስ) ዕድሉን በማስፋት ሁሉም የአፈር ቅንጣት በቂ እርጥበት እንዲያገኝ ያደርገዋል። 🌟(ሁለተኛ) የአፈሩ የመጠቅጠቅ ሂደት አስቀድሞ በውኃው ስርገት የተነሳ እየተከናወነ እንዲቆይ ያድርጋል። ያ ማለት የመጠቅጠቂያ ጉልበትን ይቀንሳል። ⚡️ሆኖም ግን የተመረጠው አፈር በቂ የሆነ የኮረት፣ የጓል እና የደቃቅ አፈር መዋጮ የሌለበት ከሆነ ውኃ ሲጠጣ የባሰ የላመ አፈር (silty) የመሆን እድሉን ስለሚጨምር ከሚፈለገው አገልግሎት አንጻር ጉዳት እንዳይደርስበት የውኃውን መጠን እና የሚጠጣበትን የጊዜ ርዝማኔ እንደአፈሩ አይነት እና እንደአካባቢው አየር የመመጠን ሥራ ከአንድ መሐንዲስ የሚጠበቅ የውሳኔ አካል ነው። https://t.me/ethioengineers1
إظهار الكل...
👍 30 3🔥 3
የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ 1. መስጂድ አል-ሀራም፡- መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል።  መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል። 2. መስጂድ አል-ነበዊ፡- በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው። የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል። 3.ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው። 4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡- በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል።  etconp የኦቶማን አርክቴክቸር ድንቅ ስራ ነው። 5. ሀሰን II መስጂድ፡ በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው። 6. አልሀምብራ፡ በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው። ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል። 7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው።  etconp ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል። 8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው።  ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት። ❤️መልካም ዒድ😇
إظهار الكل...
👍 16 14
Photo unavailableShow in Telegram
✅ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል!
إظهار الكل...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
የቻይና መሃንዲሶች ለትራንስፖርት ተስማሚ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት የሚያግዳቸው ተራራማ፣ ኮረብታማ እና ጎበርባጣ መልከዓ ምድር የለም ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። https://t.me/ethioengineers1
إظهار الكل...
👏 56👍 27 3🤔 3
Photo unavailableShow in Telegram
👍 23🙏 6 4👏 1
ኮንስትራክሽን ክሌም           የኮንስትራክሽን ክሌም ለመስራት የውሉ የክፍያ መንገድ ላምፕ ሰም ወይስ አድሜዠርመንት የሚለውን መለየት ግድ ነው። የውሉ አይነትም ዲዛይን ቢድ ቢዩልድ(DBB) ወይም ዲዛይን ቢዩልድ(DB) ስለመሆኑ  መለየት ይገባል። DBB እና DB የተለያየ ጀኔራል ኮንዲሽን ይጠቀማሉ።ለምሳሌ FIDIC 2017 Red Book ለDBB እና Yellow Book ለDB መጠቀም ይቻላል። የክፍያ መንገዱ ላምፕ ሰም ወይም አድሜዠርመንት መሆኑ ግን የጀኔራል ኮንዲሽን እንድትቀይር አያስገድድም። ለምሳሌ ፒፒኤ 2011 ቨርሽን ለሁለቱም የክፍያ መንገዶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ስፔሻል ኮንዲሽን ላይ የተለወጠ የጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ ያለ እንደሆነ ማረጋገጥም ቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት። ከዚህ በኋላ ለክሌሙ አግባብነት ያለውን የውል ድንጋጌ፣የህግ ድንጋጌ እና የጀኔራልና ስፔሻል ኮንዲሽን ድንጋጌ መለየትና መስፈርቱን የሚያሟላ ክሌም ማዘጋጀት ይቻላል። ከዚያም ክሌሙ ለአማካሪ፣ለዲስፒውት ሪቪው ቦርድ፣ለአርቢትሬሽን ወይስ ለፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባው ለመለየት ጀኔራል ኮንዲሽኑን እና በዋናነት ስፔሻል ኮንዲሽኑን ማየት ይገባል። በጉባዔ አሰፋ https://t.me/ethioengineers1
إظهار الكل...
👍 18 2
ጥያቄ ✅በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው?
መልስ
በኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጮች  (Sub contractors) በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው። https://t.me/ethioengineers1
إظهار الكل...
👍 40 3
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ግዙፍ የአፓርትመንት ኮምፕሌክስ መጠሪያ ስሙ Novy Okkervil ይባላል፤ በሩሲያ ነው የሚገኘው። 🏷እ.ኤ.አ በ2015 የተገነባው የመኖሪያ መንደር ከአለማችን ከሚገኙ ተመሳሳይ ግንባታዎች በቀዳሚነት እንደሚገኝ ይነግርለታል። 💫በዚህ መንደር ውስጥ ወደ 18 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ይኖርበታል። ⭐️እያንዳንዱ ሕንፃ ባለ 25 ወለል ሲሆን፣ በጠቅላላው ወደ ሕንፃው ለመግባትም ሆነ ለመውጣት 35 በሮች አሉት። https://t.me/ethioengineers1
إظهار الكل...
👍 19 3💯 3
🌟Training (With Discount)           🌟Online Class (With Certificate) 1. ETABS Price = 2000birr 2. Ms Project Price = 2500birr 3. Quantity Survey Price = 2000birr 4. Civil 3D Price =2500birr 5. Etabs With Safe Price = 3000birr 6. Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000 7. Structural Design in ProtaStructure Software 8. Autocad Price = 2500birr 9. Sap2000 Price = 2500birr 10. Autodesk Revit Architecture 11. WatrGems 🫵 If u take More than 2 Course u will have Big Discount 🚧Prepared by Engineering Solution Abel Muluken 🫵For Registration - 0948552002 Or 0933575753 or @AbelMuluken 🚧Telegram Channel - https://t.me/AbelMulukenEngineeringSolution 🚧YouTube Channel - https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2B
إظهار الكل...
Engineering Solution

Youtube link -

https://youtube.com/channel/UCNxyykElOiXVKVlA4jXI2BA

👍 11 2
የአለማችን ረጅሙ የእንጨት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በአሜሪካ ሊገነባ ነው በአሜሪካ ዊስኮንሲን ግዛት ውስጥ የሚገነባው 55 ፎቅ ያለው አዲሱ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የዓለማችን ረጅሙ የእንጨት ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ይሆናል ተብሏል። የሕንፃው ነዳፊ የሆነው ሚሼል ግሪን አርክቴክቸር (ኤምጂኤ) መስራች በአሜሪካ የዘመናዊ የእንጨት ግንባታ ፈር ቀዳጅ ሲሆን፣ በሰሜን አሜሪካ ታዋቂ በሆኑ ትላልቅ የእንጨት ግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መሥራቱም ታውቋል። አዲሱ ሰማይ ጠቀስ የእንጨት ሕንፃ ሰፊ አረንጓዴ እና በርካታ ቴራሶች  የያዘ ሲሆን፣ አጠቃላይ ወጪው ከ700 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ይሆናል። ሕንፃው እስከ 750 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች፣ 17,600 ካሬ ሜትር የቢሮ ቦታ፣ 3,700 ካሬ ሜትር ቦታ የንግድ ሱቆች፣ 300 የሆቴል ክፍሎች፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና  ክፍት የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች እና የእግረኛ መንገዶችን ያካተተ እንደሚሆን ታውቋል።  ሰማይ ጠቀስ ሕንፃው በግንባታ ሂደት ውስጥ የትኛውንም ኮንክሪት እንደሚጨምር እርግጠኛ አይደለንም የሚሉት ነዳፊዎቹ፣ ነገር ግን ቁመቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የተወሰነ ኮንክሪት እንደሚካተት እናምናለን ይላሉ። ሰዎች ከእንጨት የተሠራ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በቀላሉ በእሳት ሊያያዝ ይችላል የሚል ስጋት ሊኖራቸው ይችላል፣ ነገር ግን ከባህላዊው እንጨት በተለየ፣ በዘመናዊው ሁኔታ ለግንባታ የተዘጋጀው ጠንካራ የእንጨት ምሰሶ ከብረት ይልቅ እሳትን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም የሚችል ነው ተብሏል። በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ 25 ፎቆች ብቻ  የሚረዝመው የዓለማችን ረጅሙ በእንጨት የተገነባ ሕንፃ የሚገኘው በተመሳሳይ ዊስኮንሲን ግዛት ውስጥ ነው። https://t.me/ethioengineers1
إظهار الكل...
👍 30👏 3 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.