Addis Powerhouse
A Feminist Media committed to amplifying women’s voices and creating participatory spaces for women in Ethiopia.
إظهار المزيد- المشتركون
- التغطية البريدية
- ER - نسبة المشاركة
جاري تحميل البيانات...
جاري تحميل البيانات...
Dear Feminist and Women's Rights Advocates, Please select the most pressing current issue you believe women's rights advocates should prioritize in Ethiopia:
ይህ ዘጋቢ ፊልም በደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በምትገኘው ወላይታ ሶዶ፣ አራት ቆራጥ ሴቶች ስለመሰረቷት አይዳሚያ የምትባል ንቅናቄ ታሪክ እና የትግል ጉዞን የሚቃኝ ነው፡፡ እነዚህ ሴቶች ከሕዝባቸው ጥያቄ እና ከራሳቸውን ሕልም በመነሳት፣ የጋራ ድምጻቸውን ወደ አቅም በመቀየር፣ ሴት ልጅ በማህበረሰብ ጉዳዪች ላይ እንድትሳተፍ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ስራዎችን ሲሰሩ አንደቆዩ በዝርዝር ያሳያል። ይህ በእህትማማችነት የተቃና የመብት ትግል የአይዳሚያ ሴቶች ታሪክ ነው። እንደምትወዱት ተስፋ እናደርጋለን። This documentary explores the history and struggle of the Aydamiya movement, founded by four determined women in Wolayta Sodo, southern Ethiopia. It shows in detail how these women, starting from their people's demands and their own dreams, turned their collective voice into power. This is the story of Aydamiya women's struggle for rights through sisterhood. We hope you are inspired by it.
ለዚህ season የመጨረሻዋ በሆነችው የአጅሪት ፖድካስት ክፍላችን ስለገንዘብ እና የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ ተደራሽነት እና እውቀት እንጫወታለን። አክለንም ስለሴቶች የባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ዘርፎች ውስጥ ያላቸው የውሳኔ ሰጭነት፣ እና ተጠቃሚነት የፌሚኒስት መነፅራችንን አድርገን ከዛሬዋ አጅሪታችን ሊያ ዳንኤል እና እንግዳችን ሀዊ ዳዲ ጋር በመሆን ቃኝተናል፡፡ ቪድዮን ከወደዳችሁት like, follow, share and subscribe ማረግ እንዳትረሱ። በዚህ ክፍልም ሆነ season ባጠቃላይ በነበሩን ክፍሎች ላይ በተወያየንባቸው ጉዳዮች ዙርያ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ ከስር ፃፉልን፣ ለመመለስ ዝግጁ ነን!
በዚች አጀሪት ፖድካስት ክፍላችን ሴቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወስጥ ስላላችው ትሳትፎ እና ስለሚሰጣቸው ቦታ፣ ፖለቲካ ውስጥ ያሉ ሴቶች የግል እና ማህበራዊ ሕይወት፣ አያይዘንም የፖለቲካ አክቲቭስም ምን አይነት ገፅታዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ተጫውተናል። የዛሬዋ አጅሪታችን ጽዮን እንግዳዬ ከራሷ የፖለቲካ ገጠመኞች ተነስታ እንግዳችን እና የዞን ዘጠኝ የፖለቲካ አክቲቭስት ቡድን መስራች አባላት መሃከል ካለችው ሶልያና ሽመልስ ጋር እየተወያየች ቆይታለች። ቪድዮን ከወደዳችሁት like, follow, share and subscribe ማረግ እንዳትረሱ። በተወያየንባቸው ጉዳዮች ዙርያ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ ከስር ፃፉልን፣ ለመመለስ ዝግጁ ነን!
በደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በምትገኘው ወላይታ ሶዶ እምብርት ላይ አራት ቆራጥ ሴቶች ከሕዝባቸው ጥያቄ እና ከራሳቸውን ሕልም በመነሳት፣ አይዳሚያ የምትባል ንቅናቄ ለሴት እህቶቻቸው አበርክተዋል፡፡ ንቅናቄው ወላይታ ውስጥ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማጎልበት ሲባል አባታዊ ስርአት ላይ በማመጽ የተመረኮዘ ቢሆንም፣ ፣ የፍትህ ጥያቄዎቻቸው በወላይታ ሶዶ ማንነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ስራቸው ውጤታማ ሊሆን ችሏል፡፡ ይህ የንቅናቄያቸው ታሪክ በመብት ትግላቸው ዉስጥ ያሳለፏቸዉን ጥቃቶች፣ እስር፣ ብሎም እስከ ሞት ድረስ ያጋለጧቸዉንከባባድ ፈተናዎች በአብሮነት እና በእህትማማችነት እንዴት እንደተቋቋሙ ያወሳል፡፡ ከነሱ ጋር በቆየንበት ጊዜ የሰራነው ገላጭ ፊልም በቅርብ ይለቀቃል። ዮትዮብ ላይ ይጠብቁን።
በዚች የአጅሪት ፖድካስት ክፍል ሁለት ሴት ጓደኛሞች በብዛት ስለሴቶች ግንኙነት ማህበረሰባችን ያለውን አመለካከት እና እውነተኛውን የእህትማማችነት/ የሴቶች ሴት (girls’s girl) የመሆን ትርጉም ከራሳቸው ሕይወት፣ ከንቅናቄያቸው እና ከየተለያዩ ጥናቶች ተነስተው ያወጋሉ። በ popular culture (በሚድያ ፣ ፊልሞቻች/ ዘፈኖች፣ እና እውቅና ያላቸው ሰዎች በሚመሯቸው ባህሎች) ውስጥ ሴቶች ግንኙነቶች የሚሳሉባቸው እና እንዲጫወቱ የምፈቀዱላቸው ገፀ-ባህሪዎችን ዳሰን፣ ወደራሳችን ዓለም እንጋብዛቹሀለን። የዛሬዋ አጅሪት ማህሌት ውብሸትስትሆን፣ አብራት በፀሎትከፈለኝ ትቆያለች። ቪድዮን ከወደዳችሁት like, follow, share and subscribe ማረግ እንዳትረሱ። በርዕሳችን ላይ ወይም በተወያየንባቸው ጉዳዮች ዙርያ ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላችሁ ከስር ፃፉልን፣ ለመመለስ ዝግጁ ነን!
تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.