cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

ሸገር 102.1 መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ሸገር የእናንተ ነው! https://bit.ly/33KMCqz

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
34 302
المشتركون
+1624 ساعات
+807 أيام
+35330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 9፣2017 ኢትዮጵያ ከ5 ዓመት በፊት ‘’የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ’’ የተሰኘ ሰነድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ማጸደቋ ተነግሯል፡፡ በዚህ ሰነድም ኢትዮጵያ እንዴት አማራጭ ወደቦችን መጠቀም እንደምትችል ጭምር የያዘ መሆኑን ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡ የጂቡቲ፣ የላሙ፣ የፖርት ሱዳንን እንዲሁም ፖለቲካው ከተረጋጋ ደግሞ የአሰብ እና ምጽዋን ጭምሮ ሌሎች አማራጭ ወደቦችን ምን ያክል እንጠቀም የሚል ሰነድ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሎጂስቲክስ መምህር የሆኑት ማቲዮስ ኢንሰርሙ(ዶ/ር)  ነግረውናል፡፡ ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው የወጪ እና ገቢ ንግዷ በጂቡቲ ወደብ ላይ የተመሰረተ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ወደብ በተጨማሪ አማራጭ ወደቦችን ማፈላለጓ የሚያመጣላት ጥቅም ምን ይሆን? ለገበሬው፣ ለነጋዴው፣ ለአስመጪው ለላኪው ለገዢው እና ለሻጩስ ጥቅሙ ምን ይሆን? ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/2sreffrw ያሬድ እንዳሻው
إظهار الكل...
👍 4😢 2
መስከረም 9፣2017 ሸገር ስፖርት የእነ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ክስ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ.. ኮሚቴው በፍርድ ቤት በድጋሚ እግድ ተጣለበት! https://youtu.be/T6V1SB9os0I
إظهار الكل...
Sheger Sport - የእነ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ክስ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ / ኮሚቴው በፍርድ ቤት በድጋሚ እግድ ተጣለበት!

መስከረም 9፣2017 Sheger Sport - የእነ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ክስ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ / ኮሚቴው በፍርድ ቤት በድጋሚ እግድ ተጣለበት! shegerfm,sheger fm news,sheger maleda,sheger,sheger sport,shegernews,shegercafe,shegerradio,shegershelf,shegerfmyoutube,shegermeaza,shegermekoya,shegerchewata,shegerdrama,shegersport,shegermeazabirru,shegercafenew,shegerabdualihigera,shegerwerewoch,shegerprograms shegerbestradio,shegertizitazearada,102.1``,manchister city,esheteassefaprogram,sport,chewata,``yechewataengida,sport news,yealemquanqa,kidamechewata,mekoya on youtube,news,“ethiopia”,radio,mekoya mekoya,mekoya new,new mekoya,shegermekoya,kidame mekoya,mekoya mark felt,sheger mekoya,sheger radio mekoya,mekoya on youtube,mekoya jeffrey epstein,shegermeaza,kidamechewata,chewata,shegercafe,shegerradio,shegerchewata,victor manuel,eshete asseafa,news,jeffrey epstein,eshete assefa youtube,shegernews የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Telegram: t.ly/Sheger Website: t.ly/ShegerFM YouTube: t.ly/SHEGER Tiktok:

https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger FM 102.1 Radio is The First Private FM Radio Station in Ethiopia የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

👍 10 3
መስከረም 9፣2017 የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ። ዛሬ ከረፉዱ 3 ሰዓት ሳሪስ አደይ አበባ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ አሸኛኘት ተደርጓል። ከዚያም በሚሊኒየም አዳራሽ የተለያዩ የሽኝት ፕሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ተገኝተዋል። የቀብር ስርዓታቸውም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በአዲስ አበባ በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል። በቀብር ስርዓቱ ላይም ቤተሰቦቻቸው፣ የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል። ፖለቲከኛው እና መምህሩ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። አብዛኛውን የህይወት ዘመናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተማር ያሳለፉት ፕሮፌሰር በየነ በፓለቲካ ተሳትፏቸው በሰላማዊ ትግል አራማጅነታቸው ይታወሳሉ። ፕሮፌሰር በየነ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ የመድረክ እንዲሁም ኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ(ኢሶዴፓ) ሊቀመንበርም ነበሩ፡። በ75 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፕሮፌሰር የሁለት ወንድ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ናቸው። ሸገር በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል። ንጋቱ ሙሉ
إظهار الكل...
👍 7🔥 2 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 9፣2017 ከ14 ዓመታት በላይ ንግግር ሲደረግበት የቆየው የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ አለም አቀፍ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የሚያስችለውን ድምፅ ከወር በፊት ከደቡብ ሲዳን ማግኘቱ ይታወሳል፡፡ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ በሀገራት መፈረም የጀመረው ከ14 ዓመት በፊት ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ፈራሚ ሀገራትም ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ነበሩ፡፡ በህግ አውጭ አካሎቻቸውም አፀድቀውታል፡፡ ብሩንዲም ኋላ ላይ እነ ኢትዮጵያን ተቀላቅላለች፡፡ የውሃ ምህንድስና ባለሞያው ጥሩ ሰው አሰፋ(ዶ/ር)፤ 6ኛ ሀገር ስምምነቱን ባጸደቀች በ60 ቀኑ የናይል ተፋሰስ የትብብር ኮሚሽን የሚባለው እውን ይሆናል ብለዋል፡፡ የሚቋቋመው የናይል ተፋሰስ የትብብር ኮሚሽን ቀዳሚ ስራው ምንድነው? እንዴት ይሰራል? ገንዘብስ ከየት ያመጣል? ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/mr9thrh5 ንጋቱ ሙሉ ተያያዥ ዘገባዎችን ያድምጡ … (1) https://tinyurl.com/ycru5s9m (2) https://tinyurl.com/3atc7k3j #The_Nile_Basin_Cooperative_Framework_Agreement #የአባይ_ተፋሰስ_ሀገራት
إظهار الكل...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 9፣2017 የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎችን ለመቆጣጠር አስመጭዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እያደረግኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ። ከዚህ ቀደም የኤሌክትሮኒክስ አስመጪዎች፤ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በሚያስገቡበት ሰዓት ምን እና ምን ያህል በሚለው ላይ በቂ የቁጥጥር ሥርዓት ባለመኖሩ ከፍተኛ የቆሻሻ ክምችት እንዲኖር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል። በኢትዮጵያ ካለው የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ክምችት ቀዳሚውን የሚይዘው በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ እንደሆነም ሰምተናል። ዘወትር የምንጠቀምባቸው እንደ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና መሰል የኤሌክትሮኒክ እቃዎች አገልግሎት ሲያቆሙ የአወጋገዳቸው ነገር ከፍተኛ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ እንዲሁ መሬት ላይ የሚጣሉ ከሆነ አፈርና ውሃን ለመበከል ከሰውና ለእንስሳት ጤና ጠንቅ የሚሆኑ የኤሌክትሮኒክ ቆሻሻዎችን በአግባቡ ለማስወገድ የአሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጓል ተብሏል፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መጠን ለማወቅና አገልግሎታቸውን የጨረሱ ኤሌክትሮኒክስ በአካባቢው ተከማችተው ብክለት እንዳያስከትሉ አስመጭዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የማድረግ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት ነውም ተብሏል። ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/8vdpbdab ፍቅሩ አምባቸው
إظهار الكل...
👍 7
መስከረም 9፣2017 ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የንግድ ስራ አብዛኛው የቤተሰብ ቢዝነስ እንደመሆኑ ከትውልድ ትውልድ ውጤታማ ሆኖ እንዲሸጋገር፣ የማስተማር ስራ እየከወነ መሆኑን ኤችኤስቲ(HST) የተሰኘው አማካሪ ድርጅት ተናገረ፡፡ የቢዝነስ አስተዳደር እና ፋይናንስ አማካሪ ተቋም የሆነው የHST ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ግዛው እንዳሉት በአብዛኛው የቤተሰብ ንግድ እውቀት ባለው ባለሞያ እንዲመራ ስለማይደረግ የመዳከም እና የመክሰም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ ይህንንም በመረዳት ቤተሰባዊ የሆነው የንግድ ስራው ቀጣይነትን ያለውና ውጤማ እንዲሆንም የማማከርና የማስተማር ስራ እየከወንን ነው ይላሉ፡፡ የቤተሰብ ቢዝነስ መክሰምም ለሃገር ኢኮኖሚ ጭምር ጫና ስለሚፈጥር እንዲበረታ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ተቋማቻው በየአመቱ የቤተሰብ ንግድን በተመለከተ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችል ውይይት እንደሚያዘጋጀ ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡ ትናንትም ይሄንኑ የተመለከተ ውይይት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ማድጉን ነግረውናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ንግድ የቤተሰብ መሆኑንም ጠቅሰው ነገር ግን አብዛኞቹ ማደግ የማይችሉት በዚህ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡ የቤተሰብ ንግዶች እውቀት ባለው ሰው እንዲመሩ ከተደረገና ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላኛው ውጤታማ ሆነው መሻገር ከቻሉ የሚፈጥሩት ሀብት እና የስራ እድል የሃገር ኢኮኖሚም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/2hhyvvyd ተያያዥ ዘገባን ለማድመጥ… https://tinyurl.com/53rz6dn2
إظهار الكل...
በኢትዮጵያ የንግድ ስራ አብዛኛው የቤተሰብ ቢዝነስ ውጤታማ ሆኖ እንዲሸጋገር፣ የማስተማር ስራ እየከወነ መሆኑን HST የተሰኘው አማካሪ ድርጅት ተናገረ

መስከረም 9፣2017 ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የንግድ ስራ አብዛኛው የቤተሰብ ቢዝነስ እንደመሆኑ ከትውልድ ትውልድ ውጤታማ ሆኖ እንዲሸጋገር፣ የማስተማር ስራ እየከወነ መሆኑን ኤችኤስቲ(HST) የተሰኘው አማካሪ ድርጅት ተናገረ፡፡ የቢዝነስ አስተዳደር እና ፋይናንስ አማካሪ ተቋም የሆነው የHST ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ግዛው እንዳሉት በአብዛኛው የቤተሰብ ንግድ እውቀት ባለው ባለሞያ እንዲመራ ስለማይደረግ የመዳከም እና የመክሰም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ ይህንንም በመረዳት ቤተሰባዊ የሆነው የንግድ ስራው ቀጣይነትን ያለውና ውጤማ እንዲሆንም የማማከርና የማስተማር ስራ እየከወንን ነው ይላሉ፡፡ የቤተሰብ ቢዝነስ መክሰምም ለሃገር ኢኮኖሚ ጭምር ጫና ስለሚፈጥር እንዲበረታ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡ ተቋማቻው በየአመቱ የቤተሰብ ንግድን በተመለከተ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችል ውይይት እንደሚያዘጋጀ ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡ ትናንትም ይሄንኑ የተመለከተ ውይይት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ማድጉን ነግረውናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ንግድ የቤተሰብ መሆኑንም ጠቅሰው ነገር ግን አብዛኞቹ ማደግ የማይችሉት በዚህ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡ የቤተሰብ ንግዶች እውቀት ባለው ሰው እንዲመሩ ከተደረገና ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላኛው ውጤታማ ሆነው መሻገር ከቻሉ የሚፈጥሩት ሀብት እና የስራ እድል የሃገር ኢኮኖሚም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን

👍 3 1
መስከረም 9፣2017 ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ በጀት ዓመት በቴሌኮምና በዲጅታል አገልግሎት የተሻለ አቅም ለመፍጠር ለመሰረተ ልማት ግንባታ አንድ ቢሊዮን በላይ ዶላር በጀት መመደቡን ተናገረ። አምና 93.7 ቢሊየን ብር ገቢ ያገኘው ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ በጀት አመት 163.7 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስረድቷል። ይህም ከአምናው ሲነፃፀር የ70 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ታውቋል። አሁን 78 ሚሊየን ደንበኞች ያሉት ኩባንያው በእቅዱ መሰረት የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 83 ሚሊዮን ለማድረስ አቅጃለሁ ብሏል። የቴሌብር ደንበኞችም ከ47.5 ሚሊየን ወደ 55 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ ማቀዱን ተናግሯል። ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር ከተደረገው የፋይናንስና የገንዘብ ስርዓት ለውጥ ጋር በተጣጣመ መልኩ የ2017 እቅድ መንደፋንም ሰምተናል። ኩባንያው ከመንግስት ፖሊሲ እና ከተለያዩ የቢዝነስ ስራና ጠባይ ጋር የሚስማማ እቅድ ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን አስረድቷል። በዚህ የአንድ ዓመት የስራ ዘመን እቅድና የ3 ዓመት ጉዞ እቅድ አለም አቀፍ የቴሌኮም ባህሪና የሀገር ውስጥ የማክሮ ኢኮኖሚውን ማሻሻያ ያካተተ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች ነግረዋል። በቴሌኮምና በዲጅታል ፋይናንስ የውደድር ገበያው የተረጋጋ እንደሚሆን ኩባንያው በእቅዱ ታሳቢ አድርጓል። ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/3c46fswb
إظهار الكل...
መስከረም 9፣2017 - ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ በጀት ዓመት በቴሌኮምና በዲጅታል አገልግሎት የተሻለ አቅም ለመፍጠር ለመሰረተ ልማት ግንባታ ከ1 ቢሊዮን በላይ ዶላር በጀት መመደቡን ተናገረ

ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ በጀት ዓመት በቴሌኮምና በዲጅታል አገልግሎት የተሻለ አቅም ለመፍጠር ለመሰረተ ልማት ግንባታ አንድ ቢሊዮን በላይ ዶላር በጀት መመደቡን ተናገረ።አምና 93.7 ቢሊየን ብር ገቢ ያገኘው ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ በጀት አመት 163.7 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስረድቷል።ይህም ከአምናው ሲነፃፀር የ70 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ታውቋል።አሁን 78 ሚሊየን ደንበኞች ያሉት ኩባንያው በእቅዱ መሰረት የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 83 ሚሊዮን ለማድረስ አቅጃለሁ ብሏል።የቴሌብር ደንበኞችም ከ47.5 ሚሊየን ወደ 55 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ ማቀዱን ተናግሯል።ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር ከተደረገው የፋይናንስና የገንዘብ ስርዓት ለውጥ ጋር በተጣጣመ መልኩ የ2017 እቅድ መንደፋንም ሰምተናል።ኩባንያው ከመንግስት ፖሊሲ እና ከተለያዩ የቢዝነስ ስራና ጠባይ ጋር የሚስማማ እቅድ ቀር

👍 4🤩 2
መስከረም 8፣2017 ትምህርት ሚኒስቴር በየጊዜው የማወጣቸው ፖሊሲዎችን ውጤት ለመገምገም ጥናት እያደረግሁ ነው አለ፡፡ ፖሊሲዎች ማውጣት አልያም የሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያዎች አድርጎ ወደ ስራ ማስገባት ብቻ ስኬት አይደለም የሚለው የትምህርት ሚንስቴር መሬት ላይ ያመጣውን ውጤት መታወቅ አለበት ይላል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ኮራ ጡሽኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከትምህርት ጋር በተያያዘ እየወጡ ያሉ ፖሊሲዎች ወይም ማሻሻያዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ ናቸው፡፡ አንዳንዴ በትምህርት ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በስራቸው ደስተኛ አለመሆናቸው ይታያል ትምህርት ሚኒስቴርም እነዚህን ችግሮች በጥናት አስደግፎ ለመፍታት ይሰራል ነገር ግን ሁሉንም ችግሮች መፍታት ግን አይቻልም ሲሉ አቶ ኮራ ነግረውናል፡፡ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ተደጋጋሚ የአሰራር ማሻሻያ ሲደረጉ ታይቷል ያሉት አቶ ኮራ ጡሽኔ እነዚህ ማሻሻያዎች ምን ለውጥ አመጡ? የሚለውን ለመመልከት ትምህርት ሚኒስቴር ጥናትና ምርምር ያደርጋል ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተደረጉ የአሰራር ማሻሻያዎች በዚህ ወቅት ለውጥ እያመጡ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ ባለፈም በጦርነት ምክንያት ውድመት ደርሶባቸው የነበሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አሁን ላይ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል የሚሉት የትምህርት ሚንስትር ዴዕታው አቶ ኮራ ነገር ግን የደረሰው ውድመት ሙሉ ለሙሉ ጠግኖ ወዲያው ተቋማቱን መጀመሪያ ወደ ነበረበት መመለስ ከባድ ነው ይላሉ፡፡ አሁን በትምህርት ሥርዓቱ ላይ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችና ማሻሻያዎች ውጤታቸው የሚታየው ከጊዜ በኋላ ነው የሚሉት አቶ ኮራ ይህም የሚረጋገጠው በጥናትና ምርምር እንጂ በምልከታ ብቻ አይደለም ብለዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/3kf3at35 በረከት አካሉ
إظهار الكل...
ትምህርት ሚኒስቴር በየጊዜው የማወጣቸው ፖሊሲዎችን ውጤት ለመገምገም ጥናት እያደረግሁ ነው አለ

መስከረም 8፣2017 ትምህርት ሚኒስቴር በየጊዜው የማወጣቸው ፖሊሲዎችን ውጤት ለመገምገም ጥናት እያደረግሁ ነው አለ፡፡ ፖሊሲዎች ማውጣት አልያም የሥርዓተ ትምህርት ማሻሻያዎች አድርጎ ወደ ስራ ማስገባት ብቻ ስኬት አይደለም የሚለው የትምህርት ሚንስቴር መሬት ላይ ያመጣውን ውጤት መታወቅ አለበት ይላል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ኮራ ጡሽኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከትምህርት ጋር በተያያዘ እየወጡ ያሉ ፖሊሲዎች ወይም ማሻሻያዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ ናቸው፡፡ አንዳንዴ በትምህርት ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በስራቸው ደስተኛ አለመሆናቸው ይታያል ትምህርት ሚኒስቴርም እነዚህን ችግሮች በጥናት አስደግፎ ለመፍታት ይሰራል ነገር ግን ሁሉንም ችግሮች መፍታት ግን አይቻልም ሲሉ አቶ ኮራ ነግረውናል፡፡

👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 8፣2017 የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(IGAD) የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን አባል ሀገራት በጋራ መሰረተ ልማት እንዲያለሙ ያግዛል ተባለ። የኢጋድ(IGAD) አባል ሀገራት የበለጠ ከዘርፉ ለመጠቀም ከፈለጉ #የቪዛ_አገልግሎታቸውን ወጥ እንዲሆን ኢጋድ ፍላጎት አለው ተብሏል። የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ በኢጋድ አባል ሀገራት የእርስ በእርስ የቱሪስቶች ጉብኝት ዝቅተኛ ነው ብለዋል። የውጪ ሀገራት ጎብኚዎችም ቢሆን ቀጠናው ካለው የቱሪዝም ሃብት ጋር ሲተያይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። ይህም የሆነው የአባል ሀገራት የእርስ በእርስ #የቱሪዝም_መረጃ ዝቅተኛ መሆን፣ የመሰረተ ልማት ጥራት አነስተኛ መሆንና የጋራ ቪዛ አገልግሎት አለመጠቀም ተጠቃሽ ናቸው። አሁን ኢጋድ ያዘጋጀው ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን እነዚህ ችግሮች ከመፍታት ባለፈም ቀጠናው የተሻለ የቱሪዝም ፍሰት እንዲኖረው ያደርጋል ተብሏል። ይህ እውን እንዲሆን በቀጠናው በየጊዜው የሚነሳው #ግጭትና የሰላም እጦትም ችግር ሊፈታ ይገባልም ተብሏል። የቱሪዝም ሚንስትሯ ናሲሴ ጫሊ የ10 ዓመቱ የኢጋድ ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን በአባል ሀገራት መካከል የጋራ የእርስ በእርስ ግንኙነት ያሳድጋል፤ በተለይም ቀጠናው ያለው የቱሪዝም ሀብት በጋራ አልምቶ ለመጠቀምና የተሻለ መሰረተ ልማት ለመገንባት ይረዳል ሲሉ ተናግረዋል። የአፍሪካ የእርስ በእርስ የቱሪዝም ፍሰት 12 ከመቶ ብቻ ሲሆን ይህንን ወደፊት ማሻሻልና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችን ቁጥር ማሳደግ ይገባል ለዚህ ደግሞ በሀገራቱ መካከል መረጃ መለዋወጥ ያስፈልጋል ተብሏል። የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ሚንስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያ እያስተናገዳች ሲሆን መስከረም 9 የኢጋድ የቱሪዝም ማስተር ፕላን ላይ ይፋ ይደረጋል። በረከት አካሉ
إظهار الكل...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 8፣2017 15 አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም እንድታደርግ ጫና እንዲደረግባት ጠየቁ፡፡ በእስራኤል ላይ አለም አቀፍ ጫና እንዲበረታባት ከጠየቁት አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች መካከል ኦክስፋም፣ ሴቭ ዘ ቺልድረን እና ክርስቲያን ኤድ የተወሰኑት እንደሆኑ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡ የረድኤት ድርጅቶቹ የጋዛውን ጦርነት ለማስቆም በእስራኤል ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብም እንዲደረግባት ጠይቀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በጦርነቱ ምክንያት ወደ ጋዛ መድረስ የነበረበት 85 በመቶ እርዳታ መስተጓጎሉ ተጠቅሷል፡፡ ከጦርነቱ በፊት በየቀኑ 500 የጭነት መኪና እርዳታ ሲገባ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን በየእለቱ የሚገባው ሰብአዊ እርዳታ ከ69 የጭነት መኪና አይበልጥም ተብሏል፡፡ #ShegeWerewoch #Gaza_Strip #Israel_Hamas_War
إظهار الكل...
👍 5
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.