cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኢስላማዊ ግጥሞች الشعر الإسلامي لسيد أبو ذر

አድናቆትን ዝናን ስምን ፈልጌ ሳይሆን አሏህ በሰጠኝ እዉቅና ወንድምና እህቶቼን ለማገልገል አንድ ጊዜ ተፈጥሪያለዉ እናም ዱኒያ አኼራዬን እንዲያሳምርልኝ በዱዓ አግዙኝ ለማንኛዉም ጥያቄ 👇 👇 @seidabuzerbot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 294
المشتركون
-124 ساعات
-77 أيام
-1130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
ሲደወል ስልኩን የማታነሱለት፣ ሲጽፍ ቴክስቱን የማትመልሱለት፣ ሲመጣ ፊት የምትነሱት፣ ሲናገር የማታዳምጡት፣ ላግኝህ ሲላችሁ ዝም የምትሉት  … ያለ አንዳች ጥቅምና የተለየ ዓላማ በቅንነት የሚቀርባችሁ አንድ ችላ የምትሉት ሚስኪን ሰው፤ የሆነ ጊዜ ትዕግስቱ አልቆ የማይሸሻችሁ ይመስላችኋልን!!?፡፡ አዎ አንድ ቀን ይመጣል፡፡ እሱም በተራው ስልካችሁን እያየ ዝም ይላል፣ ቴክስታችሁን አይመልስም፣ ወሬያችሁን አያዳምጥም፣ ለጥሪያችሁ መልስ አይሠጥም፡፡ እንደኮራችሁ፣ እንደተፈለጋችሁ፣ እንደተናፈቃችሁ፣ እንደተወደዳችሁ የምትዘልቁ መስሏችሁ አትሳሳቱ፡፡ ሰዎች አለመፈለጋቸው ሲገባቸው፣ ክብራቸው የተነካ እንደሆነ ሲሰማቸው … ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጓዛቸዉን ሸካክፈው ከቀልባችሁ ለመውጣት ጨካኝ እንደሚሆኑ አትጠራጠሩ፡፡  ያኔ ታዲያ  እናንተም ፈላጊ ትሆናላችሁ፣ ይከብዳችሁ የነበረ ድምጽ ይናፍቃችኋል፣ የሚሰለቻችሁ ቴክስት ሩቅ ይሆናል፡፡ እናሳ … እናማ ተወደድን ብላችሁ አትኩሩ እሺ ተፈለግን ብላችሁም አትዘንጡ። t.me/muselimnegn
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
አባቷ ሙተው ዱንያ ብትጨልምባት የአባቷ ቀብር ወደሚገኝበት ስፍራ ሂዳ ከተቆለለው አፈር እፍኝ ዘገነች። ፋጢማ ረዐ ከቀብሩ የዘገነችውን እፍኝ አፈር እያሸተተች፦ ዘግኖ ያሸተተ የአህመድን አፈር ለዘመናት ሽቶን አያሸትም ነበር ሀዘኖቼ በዝተው የተደራረቡት በቀን ላይ ቢሰፍኑ ሌሊት ባደረጉት ተራራዬ ነበርክ በጥላህ ምጠለል ዛሬ ትተኸኝ ሄድክ ከጠላቶች መሀል _____ የአባቷን የቀብር ስነ ስርዐት ያስፈፀሙት ሰሀባዎች ከቀብር ሲመለሱ ልጅት ፋጢማ መንገድ ላይ ጠብቃ ቀባሪዎቹን፦ «በረሱል አካል ላይ አፈር መልሳችሁ ስትመጡ እንዴት ነፍሳችሁ ፈቀደች?» ንግግሯን ቀጠለች፦ የሰማይ አድማሳት ደብዝዘው ከረሙ ፀሀይም ደም ለብሳ ቀትሮች ጨለሙ ነቢ ካሸለቡ ምድር ከስራ ዋለች በሞታቸው ሀዘን ተሰምቷት ዋለለች _____ እመት ፋጢማን የሀዘን ሰራዊት በናፍቆት አርጩሜ እየገረፈ በትዝታ እስር ቤት ውስጥ በሩን ዘግቶ ሲፈትናት፦ ነፍሴ ታስራ ዋለች በሲቃ ወህኒ ቤት ምነው ባሸለበች እዝያው ባለችበት ከርሶ መሞት ወድያ መኖርስ ለምኔ! መኖር ስለማልችል ሳይኖሩ ከጎኔ ሌት ተ ቀን ማነባው ተሎ ለመሞት ነው _____ ሀዘን ደረጃው ቢለያይም የመለየት ሀዘን ውስጥ ውስጥን ለዘለዐለም የሚሰረስር ህመም አለው ኡመቱ የሚያሳልፋቸውን የመሪር ሀዘን ህመም ለማስተናገድ አቅም በሚያንሰው ግዜ መልዕክተኛው እንዲህ ብለው አቅጣጫ ጠቁመዋል። «አንዳችሁን ሀዘን በገጠማችሁ ግዜ፤ በኔ ሞት የገጠማችሁን ሀዘን በማስታወስ ተፅናኑ። » ዳርሚይ ዘግበውታል። t.me/islamawigetem
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ተረጋግቼ እንድኖር ከሚያደርጉኝ ነገሮች መካከል አንዱ ቀደር ነው። ዝምብለን እንብሰከሰካለን እንጂ ዱንያ አላህ ከፃፋት ልክ አታልፍም። አላህ የፃፈልኝን ነገር ብጓጓለትም ባልጓጓለትም የትም አያመልጠኝም። ያልፃፈልኝ ነገር ብወጣ ብወርድም በኔ ድካም አይለወጥም ። ቢሆንም ግን ከመልፋት አልቦዝንም። አላህ የፃፈልኝን ነገር የትም ይሁን የት አገኘዋለሁ፣  በመካከላችን ያለ ርቀት አይገድበዉም። በርግጥም ጌታዬ ጽፎልኝ ከሆነ እሩቁ ነገር ቅርብ ይሆናል፣ የማይቻለዉም ይቻላል። ግና አንድ ነገር መርሃችሁ ይሁን፣ በአላህ ቀደር እና በነፍሳችሁ ፍላጎት መካከል ብትማረጡ የአላህን ቀደር ምረጡ። አላህ ሁልጊዜም ለናንተ መልካሙን ይመርጣልና። t.me/muselimnegn
إظهار الكل...
እዚህ ቤት አንድ ቀን .... ከጎህ መቅደድ ኋላ ከረፋዱ በፊት፣ አንድ ሰው ነበረ አንድ አባት ነበረ ባለ በሻሻ ፊት:: ንጋቱ ላይ ቆሞ ያ'ብራኮቹን እጣ የልጆቹን ቀትር፣ በህልሙ ማስዋቢያ ቅዠቱን ተርጉሞ በንቅልፉ የሚጥር:: የሆነ ሰው ነበር.. ሰውነቱን ረስቶ ልጅነታቸውን ሲያስብ የነበረ፣ ሲወድ የነበረ አንድ ሰው ነበረ ፤ አንድ አባት ነበረ:: ለውሀል መህፉዝ ቀድሞ ሁን ያለበት ቀደር፣ ከመኖሩ በፊት የቀረ በነበር፤ አንድ አባት ሰው ነበር:: ለማን ይታዘናል ለማን ይለቀሳል?፣ የእንባ ጠብታ የልቦናን ደዌ ቁስሉን ያብሳል:: ማን ይሄን ይመኛል?፣ አባትነት መክኖ የናት ጫንቃ ደቋል:: ባ'ጋር ማጣት ህመም ቻይነቷ ረግቧል :: ታድያ.. ማን ማልቀስ ይጠላል ?? ልጆቹ... በፍቅረ ልፋቱ ከትንሽ ልባቸው በፍቅር የሳለው፣ አባታችሁ ጀግና አብሯችሁ ነው ያለው:: ያኔ የተናገረው... እየመላለሰ እየደጋገመ በነ'ርሱ ብራና በክብር ያተመው፣ ቃሉ ስላልጠፋ ስዕሉ ስላላቸው፤ ማን ደፍሮ 'ኣባታችሁ ሞቷል ይበላቸው???:: አሁን ወላጅ አልባ የቲም ሲል ይጥራቸው???:: ማን??? ከለቅሶው ድንኳን ጋር ቤቷ የፈረሰው ያቺ ምስኪን ባልቴት፣ ከቀብሩ ሽፋን ጋር ልቧ የበረደው ፍፁም አፍቃሪ ሴት፤ የመርዶው ነጋሪት ያልጎሰማቸውን ልጆቿን ታቅፋ ፤ ትዞር ትሄድበት ትገባው ቢጠፋ፤ ከሀዘኗ እጥፍ ችግር ድህነቱ ማጣቱ ቢሰፋ፤ ታጎርስ ታለብሳቸው ታስተምር ባታገኝ፤ ይረዷት ያስጠጓት ያኖሯት ብትመኝ፤ ሰውነት ትርጉሙ ከገንዘብ ያነሰ በሆነት ዘመን፤ እሷነት ስስ ሆነ ድሎት ባደለበው ባይናቸው ሲመዘን:: ስለዚህ.... በልፋቱ ሰበብ የጤዛው ቸነፈር ንጋት ያደመቀ አባት ስለጠፋ፣ በጠራራ ቀትር በሰው ማጣት ህመም ሜዳቸው ተዳፋ:: መኖሩ ለብቻው በወበቅ ላይ ሙቀት ይሰጥ የነበረ አባት ስላለፈ፤ ላቦቱ ያፀዳው የልጆች ገፅታ ላይጠራ ጎደፈ:: ሚስትነቷን ያጣች ምስኪንነት ወርሷት ከሜዳ ብትወጣ፣ የሠው አይን ማየት ሀዘን አልጠቀመ ቀድሞ ያልነበረ የሌለ ላይመጣ:: እንደዚህ ነው ዕጣ!!! t.me/islamawigetem
إظهار الكل...
ኢስላማዊ ግጥሞች الشعر الإسلامي لسيد أبو ذر

አድናቆትን ዝናን ስምን ፈልጌ ሳይሆን አሏህ በሰጠኝ እዉቅና ወንድምና እህቶቼን ለማገልገል አንድ ጊዜ ተፈጥሪያለዉ እናም ዱኒያ አኼራዬን እንዲያሳምርልኝ በዱዓ አግዙኝ ለማንኛዉም ጥያቄ 👇 👇 @seidabuzerbot

#አባት_ከአምስት ሴት ልጆቹ ጋር ይኖራል ለትዳርም ስለደረሱ አባት ከታላቋ ጀምሮ በቅደም ተከተላቸው #እንዲያገቡለት ይፈልጋል ነገር ግን ታላቋ አባቷን መንከባከብ በመፈለግ ማግባት አልፈቀደችም ታላቋ ብቻ ስትቀር አራቱ ልጆቹ አገቡ,እሷም አባቷ አጀሉ ደርሶ እስኪሞት ድረስ ተንከባከበችው አባት ከሞተ በኃላ ግን ይቺ ሴት ብቻዋን ቀረች ። የአባታቸውንም ኑዛዜ አገኙ እሱም " አደራ ራሷን መስዋዕት ያደረገችው እህታችሁ ሳታገባ ቤቱን እንዳትካፈሉ " የሚል ነበር... ነገርግን አራቱ እህቶች የትልቅ እህታቸውን ጉዳይ ቦታ ሳይሰጡ ተሽጦ,መከፋፈልን ፈለጉ ። ትልቋ እህታቸው ቤቱን እንደሚሸጡት ስትረዳ ለመግዛት ለተስማማው ሰው በመደወል ከምትኖርበት ቤት ውጭ ሌላ እንደሌላትና ያለውን ሁኔታ አስረድታ ነገሮችን እስክታስተካክል ድረስ ጊዜ እንዲሰጣት አስፈቀደች ቤቱን የሚገዛውም ሰውም ፍቃደኝነቱን ገለፀላት ቤቱ ተሽጦ ለአምስቱ እህቶች ተከፋፈለ ከተከፋፈለ በኃላ አራቱ ወደ ትዳራቸው ተመለሱ ታላቋ እህታቸው ከቤት ቀረች ይቺ ሴት ወላጇን በመንከባከብ ባሳለፈችው ጊዜ አላህ ልፋቷን በዱንያም ከንቱ እንደማያስቀርባት ተማምና በአላህ ተስፋ አድርጋለች ወራት አለፉ ቤቱን ከገዛው ሰው ስልክ ተደወለላት ቤቱን እንድትለቅ መልክት እንደሚያስተላልፍ በመገመት በፍራቻ 'ይቅርታ እስካሁን ቤት አላገኘውም' አለችው። እሱም ችግር የለም! የደወልኩትም ለሱ ሳይሆን ቤቱን 'መህር' አድርጌ እንድታገቢኝ ልጠይቅሽ ነው ፍቃድሽ ከሆነ ባልሽ እሆናለው ፍቃደኛ ካልሆንሽም ችግር የለም! ቤቱ ግን ያንቺ ነው አላት ። ይቺ ሴት አለቀስች! ተስማማችም አላህም የመልካም ሰሪዎችን ምንዳ ከንቱ አያስቀርምና በመልካም ተካሰች አባቷን በተንከባከበችበት ቤት ትዳር ይዛ ባሏን መንከባከብ ጀመርች ጌታችን ሆይ ! በየቤቱ ያንተን ተስፋ ብቻ የሚጠባበቁ እህቶች አሉና መልካምን_ትዳር ወፍቃቸው t.me/muselimnegn
إظهار الكل...
muselim negn

አድናቆትን ዝናን ስምን ፈልጌ ሳይሆን አሏህ በሰጠኝ እዉቅና ወንድም እና እህቶቼን ለማገልገል አንድ ጊዜ ተፈጥሪያለዉ እናም ዱኒያ አኼራሄን እንዲያሳምርልኝ በዱዓ አግዙኝ ለማንኛዉም ጥያቄ ============ 💌👇 👇 💌 @seid_abuzerbot 👳👳👳👳👳👳 ነብያት እና ህዝባቸዉ ነብዩም ሶሀቦቻቸዉ ስለ እስልምና የለፉ ሙስሊም ነን በለዉ አለፉ

Photo unavailableShow in Telegram
🔹🔸 የእብዱ ኹጥባ 🔸🔹 በጁሙዐ ቀን ኹጥባ የሚያደርጉት የመስጅድ ኢማም በጊዜ አልመጡም ነበርና አንድ እብድ መጣና ሚንበሩ ላይ ወጣ። የተወሰኑ ሰዎች ሊያስወርዱት ሞከሩ በመስጅዱ ውስጥ ሀላፊነት ካላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ባለበት እንዲተውትና ኹጥባ እንድያደርግ አዘዘ። እብዱም ኹጥባ ማድረግ ጀመረ:-"ምስጋና ለአሏህ ይገባው! ያ ከሁለት አይነት የፈጠራችሁና ለሁለት አይነት አድርጎ ለከፈላችሁ። ከናንተ ውስጥ ልታመሰግኑ ዘንድ ሀብታሞችን አደረገ። ከናንተም ውስጥ ትታገሱ ዘንድ ድሆችን አደረገ። ከናንተ ውስጥ ሀብታም የሆነውም አላመሰገነ፣ ድሀ የሆነውም አልታገሰ።የአሏህ እርግማን በሁላችሁም ላይ ይሁን! ቁሙ ወደ ሶላታችሁ!" አለ ይባላል😁 ንግግሩ ሀቅ አለው! #አመስጋኝ እና #ታጋሽ ሁኑ!! ቻናላችንን ለወዳጅዎ ያጋሩ t.me/islamawigetem
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ያ ረሱለሏህ! እንወድዎታለን ~ይቀበሉናል? እኛ እርሶን ስንወድ በእርግጥ የፊትዎን ፍካት ለመመልከት እድል አግኝኝተን አይደለም። ወይም የድምፅዎን መስረቅረቅ በጆሮዎቻችን አዳምጠን አይደለም እኛ እርሶን ስንወድ ከጎንዎ ሰይፍ አንግተን ከሙሽሪኮች የመፋለም እድል ኖሮን አይደለም።አልያም በኡሑድ ዘመቻ ከእርስዎ ተሰልፈን ተዋግተንም አይደለም። እኛ እርሶን ስንወድ ቤት ንብረታችንን  ትተን ከርሶ በረሀ ለበረሀ ተሰደን አይደለም። አልያም እርሶ ሲሰደዱ ስንቅ አመላልሰንም አይደለም። ወይም እርስዎ ሲሰደዱ ለርሶ መከታ ሆነን ተቀብለንዎትም አይደለም። ነገር ግን ያ ረሱለሏህ! እኛ ወሏሂ እንወድዎታለሁ። ይቀበሉናል? ምን እናድርግ!  ፍቃዱ የኛ ባልሆነበት ጉዳይ ላይ ከርሶ ዘመን ዘግይተን ተፈጠርን።በወላጆቻችን ላይ አላህ በዋለው የእስልምና ፀጋ እኛም ተቋደስን፤ ስለ እርሶም እየሰማን አድገን ጎረመስን፤ ስለ እርሶ እያሰብንም በናፍቆት አነባን። ዘመንዎን ደርሰን ሳናይ በዘመንዎ የኖርንበት ያህል እየናፈቀን ያልኖርንበትን ዘመን ዳግም በተመለሰ ብለንም ተመኘን። እርሶ በዘመንዎ ሁነው የኛን ዘመን ናፍቀው እንዳነቡት ሁላ እኛም በዘመናችን ሁነን የርሶን ዘመን እየናፈቅን በማንባት የመገናኛ ቀጠሮአችንን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን። ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ያ ረሱላሏህ እንወድዎታለን t.me/muselimnegn
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
¶¶የረሱል ውዴታ ¶¶ የረሱል ውዴታ ካለ በልባችን ለምንድነው ታዳ የሳቸውን ፈለግ ሸሽተን መሄዳችን የረሱል ውዴታ የረሱል ሙሀባ እንዴት ይገለፃል  በመውሊድ ጭብጨባ እረሱል ሳያዙን ቢድአ እየፈጠርን መዉሊድ ማለታችን አመት እየቆጠርን ምንድነው ሚስጥሩ ማስረጃው የት አለ መዉሊድ በየአመቱ ማን አክብሩ አለ ተከታዮች ከሆን የነብዩን ሱና እሳቸው ካሉት ውጭ መጨመር መቀነስ ማን ፈቀደውና ረሱል ሀቢቢ  የአለሙ መብራት ሌት ተቀን የለፉት አላህን በመፍራት ለኛ ብለው ያኔ ብዙ ተሰቃይተው ኡማቸው ጀሀነም እንዳይገባ ፈርተው ነበር ያስተማሩት እያስጠነቀቁ ምን ይሉታል ዛሬ ከመስመር መልቀቁ እናም ወገኖቼ  ሙስሊም የሆናችሁ የጀሀነም ቅጣት የሚያስጨንቃችሁ ዛሬው ተመለሱ ወደ አላህ አልቅሱ ተወበትን ተቀባይ ረሂም ነው እሱ ላኢላህ ኢለላህ ከገባን ትርጉሙ ይቅርብን ቢድአ ወንጀል መፈፀሙ እውነት ፍቅር ካለ የረሱል ውዴታ ሱናን በመከተል ሁሌም እንበርታ t.me/islamawigetem
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.