cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ስለ ኢየሱስ እና መሐመድ

ይህ ቻናል ስለ ኢየሱስ እና ስለ መሐመድ በቅ እውቀት ይሰጣችኋል! ጥያቄ እና ሀሳብ ካላችሁ @aleazer2cj

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
155
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሻሎም ሻሎም የእግዚአብሔር ልጆች ሰላምና ጸጋ ይብዛላችሁ ❗
إظهار الكل...
ሻሎም ቅዱሳን በ ከዚህ በኋላ ስለ ሌሎች አስተምህሮ የሚንመለከት ይሆናል❗ 1,የኦርቶዶክስ አስተምህሮ በኢየሱስ ላይ❗ 2,የእስልምና አስተምህሮ በኢየሱስ ላይ❗ 3,የይሖዋ ምስክሮች አስተምህሮ በኢየሱስ ላይ❗ እና ሌሎችም❗
إظهار الكل...
ዮሐንስ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁷ አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ⁵⁸ ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ⁵⁹ ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።
إظهار الكل...
#ኢየሱስ_ያሕዌ_ነው።
إظهار الكل...
ኢየሱስ ቃል ነው ወይንስ በቃል የተፈጠረ? የዮሐንስ 1፡14 ትክክለኛ ትርጓሜ ሙስሊም ሰባኪያን እንደ ልማዳቸው በማያውቁት ጉዳይ ገብተው በግምትና ያለ ዕውቀት ማማሰላቸውን ቀጥለውበታል። ከሁሉም የሚገርመው ግን የአዲስ ኪዳንን ግሪክ እንደሚያውቅ ሰው ከሌሎች ኑፋቄያዊ አንጃዎች የቀዱትን በስህተት የተሞላ ሰዋሰው የግላቸው ጥናት አስመስለው በኩራት የሚያቀርቡት ነገር ነው። በዚህ ተግባር ከሚታወቁት ሙስሊም ሰባኪያን መካከል አንዱ የጻፈውን ላስነብባችሁ። እንዲህ ሲል ይጀምራል፡-  ዮሐ.1:14 Καὶ ὁ Λόγος σὰρξ ἐγένετοቃልም ሥጋ ሆነ፤  ነጥብ አንድ ቃል Λόγος እዚህ ጋር የተጠቀሰው ቃል ስፐርማቲኮስ ሎጎስማለት የንግግር ቃል*speech* ሲሆን ፈጣሪ ሁሉንነገር ያስገኘበት፣ ከራሱ አፍ የሚወጣ የራሱ *ሁን* የሚልበት ባህርይ ነው፦ ኢሳ.55:11፤ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤የምሻውን ያደርጋል፥ መዝ.33:9 እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ጸኑም። መዝ.148:5 እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑም፤ እርሱምአዝዞአልና፥ ተፈጠሩም፤ ዮሐ.1:3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳያለ እርሱ አልሆነም። ዘፍጥረት 1.3 እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለብርሃንም ሆነ  ምላሻችን በመጀሪያ ደረጃ፣ ሎጎስ “ንግግር” አይደለም። በጥንታዊ ግሪክ ቋንቋ ይቀርበዋል የሚባለው ትርጉም “Reason” ነው። ሆኖም Λόγος ሎጎስ ወይም “ቃል” እኛ በ 21ኛው ምዕተ ዓመት ውስጥ ሆነን እንደምናስበው ዝም ብሎ የንግግር ቃል አይደለም። ሎጎስ ዮሐንስ ወንጌሉን ከመጻፉ ከብዙ ዘመናት በፊት በብዙ የግሪክ ፍልስፍናና እምነቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ውሎ ነበር። ትርጉሙም ሰፊ ነው። የቃሉን ትርጉም በትክክል ለመረዳት ዮሐንስ ወንጌሉን በጻፈበት ዘመን የነበረውን ግንዛቤ ማወቅ ወሳኝ ነው፡፡ 1. ሔራቅሊጦስ (Heraclitus) 535-475 ዓ.ዓ. ከሶቅራጦስ በፊት በኤፌሶን ይኖር የነበረ የግሪክ ፈላስፋ ነበር። ይህ ፈላስፋ “ሎጎስ” የሚለውን ቃል “The principle which controls the Universe”(አፅናፈ ዓለምን የሚቆጣጠር ፕሪንሲፕል ወይንም መርህ) ብሎ ያስተምር ነበር። 2. እስጦይቆች የተሰኙ የፍልስፍና ግንዶች ደግሞ ሎጎስን “Anima Mundi” ብለው ይገልፁ ነበር። ይህም ማለት “የዓለማችን ሕይወት ወይንም የሕይወት ምንጭ” (Soul of the World) ማለት ነው። 3. ማርቆስ አውራሊዮስ (Marcus Aurelius) ከ 121 -180 ዓ.ም. የኖረ ሮማዊ ባለ ሥልጣን እንዲሁም ፈላስፋ ነበር። እርሱም Spermatikos Logos (የዓፅናፈ ዓለም አስገኚ ፕሪንሲፕል ወይንም መርህ) የሚል ፅንሰ ሐሳብ ይጠቀም ነበር። ይህም “ሎጎስ” የዓለማችንን የመፍጠርና የመራባትን ሕግ የሚቆጣጠር (Generative principle of the Universe) ነው፡፡ በሌላ አባባል ወይም ፍልስፍናዊ ባልሆነ ቋንቋ ሲገለፅ “አምላክን” የሚወክል ማለት ነው። 4. አይሁድ ሊቃውንት ደግሞ በእብራይስጥና በአረማይክ ቋንቋዎች የእግዚአብሔርን ቃል “ሜምራ” (Memra) በሚል ፅንሰ ሐሳብ ገልፀውታል፡፡ ይህም በዕብራውያን መረዳት መሠረት እግዚአብሔርን የሚገልፅ ነው። ለምሳሌ በታርጉማቸው ውስጥ ስለ ኦሪት ዘዳግም 26፡17-18 ሲጽፉ “Ye have appointed The MEMRA (logos) a king over you this day, that he may be YOUR GOD” (ሜምራን (ሎጎስን) በራስህ ላይ ንጉሥ አድርገህ ሹመሃል፤ ይህም አምላክ እንዲሆንህ ነው) ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዘፍጥረት 28፡20-21 ላይ በአረማይክ ታርጉም ያዕቆብ እግዚአብሔር አምላኩ እንደሚሆን ከመናገር ይልቅ የእግዚአብሔር ቃል (ሜምራ) አምላኩ እንደሚሆን ስዕለትን ሲሳል ይታያል፡፡ በዚሁ የአረማይክ ታርጉም ውስጥ ዘዳግም 4፡7 ሲብራራ የእግዚአብሔር ቃል (ሜምራ) በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የሰዎችን ጸሎት እንደሚቀበል ተገልጿል፡፡ በዮሐንስ ዘመን የነበረው የሎጎስ ፅንሰ ሐሳብ ይህንን የሚመስል እንደነበረ ከተረዳን ዘንዳ ሎጎስ የሚለውን ቃል ለምን መረጠ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልገናል፡፡ ዮሐንስ ይህንን ወንጌል ሲጽፍ ኖስቲሳውያን (GNOSTICS) የሚባሉ ቡድኖች እንዲሁም ዲሲፕሊን ኦፍ ቫሌንቲነስ (Discipline of Valentinus)  የተሰኘ የኑፋቄ አስተምህሮ ተነስቶ ነበር። እነኚህ ቡድኖች “ሎጎስ” የተባለ አካል ኤዮን (Aeions) ከሚባሉ የመጀመሪያ ፍጡሮች አንዱ ሲሆን “ዞዪ” (Zoe) ከምትባል ሌላ “ኤዎን” ጋር በመሆን ሌሎች ፍጡሮችን ማስገኘት እንደጀመረ ይናገራሉ። እነኚህ ቡድኖች የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮ በማዛባትና ከነሱ በፊት የነበረውን የሎጎስ ትርጉሞች በመጠቀም የራሳቸውን ሐሰተኛ ወንጌል መስበክ በጀመሩ ጊዜ ነው ዮሐንስ መጻፍ የጀመረው። እናም ዮሐንስ “የሎጎስን” ፍልስፍና በሚያውቅ ማሕበረሰብ ውስጥ ነው ይህንን ስያሜ ለኢየሱስ የተጠቀመው። ይህንን ቃል ሲጠቀም ግን የነሱ ትርጉም ትክክል ነው ብሎ እንደወረደ አልተጠቀመም። ይልቁንስ ሎጎስ የተፈጠረ አምላክ ሳይሆን እራሱ ዘላለማዊና ፈጣሪ መሆኑን ለማሳየት ዮሐንስ 1፡1 “ኤን አርኬ” ብሎ ጀመረው። ከዛም “ቃሉም በመጀመሪያ ከእግዚያብሔር ጋር ነበር” በማለት “ተፈጠረ” የሚለውን ሐሳብ አፈረሰ። ዘላለማዊ መሆኑን ደግሞ የሚያሳየው  “ቃሉም ከእግዚያብሔር ጋር ነበር፣ ቃሉም እግዚያብሔር ነበር” ብሎ የተጠቀመበት የግሪክ ትርጉም  καὶ ὁ Λόγος ἦν πρὸς τὸν Θεόν, καὶ Θεὸς ἦν ὁ Λόγος ሲሆን  ἦν (ነበር was) የሚለው ቃል “Imperfect` ነው። ይህ ማለት ደህሞ በግሪክ መጀመሪያው የማይታወቅ ወይም ዘላለማዊነትን የሚያሳይ ነው። ከዚህ በኋላ ነው ዮሐንስ 1፡14 ላይ “ቃልም ሥጋ ሆነ” ብሎ የደመደመው። ይህ ማለት አንድ አስቀድሞ የነበረ አካል በማንነቱ ላይ ሥጋን ጨመረ ማለት ነው። ምክንያቱም ቃሉ መጀመሪያውኑ የነበረና ኋላ ላይ ግን ሥጋ የሆነ እንጂ ሥጋ በሆነበት ሰዓት ወደ መኖር የመጣ አይደለምና። ከዚህ ውጪ ቃሉ ንግግርና ተፈጣሪ ነው የሚል አዝማሚያ በዮሐንስ ምዕራፍ 1 ላይ ፈፅሞ አይገኝም።  References Barnes note on John 1:1 Iraneus Against Heresies Bk 1, Ch 1. Michael L. Brown, Answering Jewish Objections to Jesus – Volume 2: Theological Objections, 2000, pp. 18-22 ይህ አብዱል ቀጥሎ የጻፈውን እንመልከት (ጥቅሶቹ ለሙግቱ ብዙም ጠቃሚ ስላልሆኑ አንዳንዱን ዘልያለሁ)፡- “ነጥብ ሁለት ሥጋ σὰρξ በቅድሚያ ሥጋ ሰው ለማለት እንደተፈለገሊሰመርበት ይገባል ፦ ዘፍጥረት 6፥13 እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፦የሥጋ σὰρξ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል፥….. ኤርምያስ 32፥27 እነሆ፥ እኔ የሥጋ σὰρξ ሁሉአምላክ እግዚአብሔር ነኝ፥ ፦ ይህ ሥጋ  በድንግል ማርያም ማህጸን የተዘጋጀፍጡር ነው፦ ዕብ.10:5 ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ። መሥዋዕትንናመባን አልወደድህም ሥጋን ግን *አዘጋጀህልኝ*፤ ሐዋ.17:31 ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን*ባዘጋጀው* ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅሊፈርድ አለው፤ ፦ ተዘጋጀ ማለት ተፈጠረ ማለት ነው ፣ አምላክ ፀሓዩንናጨረቃ፣ ደመናትን፣ ዓለሞችን አዘጋጀ ማለት ፈጠረማለት እንደሆነ ሁሉ፦ መዝ.74:16 ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን *አዘጋጀህ*። ምሳ.8:28 ደመናትን በላይ *ባዘጋጀ* ጊዜ፥ የቀላ
إظهار الكل...
ሻሎም ቅዱሳን❗
إظهار الكل...
አሁን የቁርአንንና የመልዕክተኛው ተግባር እንዴት እንደሚጣረስ ቃል በቃል አሳያችኋለሁ።አደራ ስድብ እንዳትሉኝ ይህ የሀይማኖት መወያያ ግሩፕ ነውና ሁላችንም በማስረጃ መወያየት እንችላለን።በቅን ልቦና ተከታተሉኝ። 1ኛ አልበቀራህ 256 በሀይማኖት ማስገደድ የለም።ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ።ልብ በሉ🙋 2ተኛ አል ኢምራን 20 ቢከራከሩህም ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ።የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸው።ለእነዚያም መፅሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሀይሞቹ ሰላማችሁን በላቸው ቢሰልሙም በእርግጥ ተመሩ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው። ተመልከቱ 👉አንደኛው ላይ በአልበቀራህ ሀይማኖት በግዳጅ የለም ቅኑ መንገድ ከጠማማው መንገድ ተለየ ይላል ይህ ሲብራራ ሰው የፈለገውን መከተል ይችላል። የግዴታ ሙስሊም ካልሆንክ ተብሎ መታረድ የለበትም።ለራሱ ጥሩ እድንበታለሁ ብሎ ባመነበት መንገድ መሄድ ይችላል።ሃይማኖትህን ካልቀየርክ ተብሎ መገደድ የለበትም ሀይማኖት የፍቃድ እንጂ የግዴታ አይደለም።አላህ ፍታዊ አምላክ ነው ሰው እስከ ቂያማ ቀን የፈለገውን መንገድ መከተል ይችላል ነው። 2ተኛ አል ኢምራን 20 ቢከራከሩህም ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ።የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸው።ለእነዚያም መፅሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሀይሞቹ ሰላማችሁን በላቸው ቢሰልሙም በእርግጥ ተመሩ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው አላህም ባሮቹን ተመልካች ነውና። 2ተኛ 2ተኛ አል ኢምራን 20 ቢከራከሩህም ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ።የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸው።ለእነዚያም መፅሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሀይሞቹ ሰላማችሁን በላቸው ቢሰልሙም በእርግጥ ተመሩ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው አላህም ባሮቹን ተመልካች ነውና። ይሄ ሲብራራ ደሞ ለመካ ሰዎች ሄደክ ስለእስልምና አስተምህሮ ንገራቸውና ተቀብለው ከተከተሉህ መልካም ነው ካልሆነ ግን አንተ የሚጠበቅብህ መልእክቱን ማድረስ ብቻ ነው አለቀ መልእክተኛ ነህ እንቢ ካሉ ሰላማችሁን ብለህ ሂድ።ከአንተ የሚጠበቅበቀው መልእክት ማድረስ ብቻ ነው በግድ ጨፍጭፍ ካልተቀበሉ ግደል አይልም ታድያ ይህ የቁርአን አንቀጽ እንኳ ቃሉን ብቻ አድርሱ በሰይፍ ሳይሆን በአስተምህሮ ብቻ እንጂ በሰይፍ አታሳምኗተው ካለ መልእክተኛው ኬት አምጥቶ ነው ያንን ሁላ ክርስቲያንና አይሁዳውያን ለዛውም በዩኑስ 94 ላይ ያልገባችሁን ከአይሁድና ክርስቲያን ጠይቁ ያለውን ዘንግቶ ለምን ጨፈጨፋቸው ?በግዴታ ሳይሆን በውዴታ ንገራቸው እንቢ ካሉህ አንተ አያገባህም እኔ ተናግሬያለሁ ምርጫው የናንተ ነው ብለህ ሂድ ብሎታል እኮ ታድያ ረሱል ለምንድን ነው ይህንን ትእዛዝ ያላከበሩት ?የአላህን ቃል አለማክበራቸው ነው ወይስ ቁርአኑ ተሳስቷል ?
إظهار الكل...
ወዳጆቼ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ❗ ዛሬ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ከሚያረጋግጡልን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንዱን እናያለን። #ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ #ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” — ሉቃስ 2፥11
إظهار الكل...
#የዮሐንስ_ወንጌል ተከታታይ ጥናት ክፍል ፪ Part -1 #ከአባቱ_ዘንድ_እንዳለው_ክብር “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” — ዮሐንስ 1፥14 🔷 #ቃልም_ሥጋ_ሆነ የሚለን “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ብለን የተማርነውን ነው🙏 — ዮሐንስ 1፥1 #ቃል በመጀመሪያው የነበረ ነው ✅ #ቃል በእግዚአብሔር እቅፍ የነበረ ነው✅ #ቃል ራሱ እግዚአብሔር የነበረ ነው✅ 🔷ስለዚህ በመጀመሪያ የነበረው በእግዚአብሔር እቅፍ የነበረው ራሱ እግዚአብሔር የነበረው #ቃል ስጋ ሆነ። #ስጋ የሆነው #ቃል #ኢየሱስ ነው። #ኢየሱስ በስጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው። “እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ #በሥጋ_የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16 🔷 #ጸጋንና_እውነትንም_ተሞልቶ_በእኛ_አደረ “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።” — ማቴዎስ 1፥23 🔷 #አንድ_ልጅም_ከአባቱ_ዘንድ_እንዳለው_ክብር የሆነው #ክብሩን_አየን'' የሚለው ሃሳብ ኢየሱስ የነበረውን ከእግዚአብሔር የሚስተካከል ክብርና መልክ የሚያሳይ ነው። “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥” — ፊልጵስዩስ 2፥6 🔷ስጋ የሆነው ኢየሱስ ክብሩ ከአባቱ ጋር የሚስተካከል ነው እርሱ በአብ ዘንድ የነበረ ነው እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፦ “ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤” — 1ኛ ዮሐንስ 1፥2 🔊ኢየሱስ የሁለት ሺህ አመት ታሪክ ያለው በእግዚአብሔር የተላከ ነብይ ብቻ ሳይሆን እርሱ ከአብ ዘንድ ወጥቶ እኛን ስለማዳን በስጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው። በወንድም ሳሚ @JesusIsMyDay 👈 ይቀላቀሉን ሼር ለሌሎች t.me/jesusmiracl
إظهار الكل...
JESUS MIRACLES (የኢየሱስ ታምራት)

✝ የኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ ታምራት ፣ምስክርነቶች፣አስተማሪ መልዕክቶችና የመስቀሉን ፍቅር በጥልቀት የምንገነዘብበት ቻናል ነዉ። ✝ ይህን ድንቅ የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል በእርሱ በማመን አስደናቂ ሰላምና ፈዉስ ወደ ቤትዎ ይጋብዙ ከመቅበዝበዝ ህይወት አሁኑኑ ይገላገሉ!! ⚗ #

// እስልምና በቃኝ// ☞የእህታችን Fatuma Rifkaa ምስክርነት ለእስልምና ከነበረኝ ፍላጎትና ለነብዩ ሙሐመድ ከነበረኝ ትልቅ ፍቅር የተነሳ ቁርኣንንና ሀዲስን ለማንበብ ተገደድኩ! የነብይ የሙሐመድን ፈለግ ለመከተን እሳቸው በህይወት በነበሩበት ዘመን ያደረጉትን ለማድረግና ለመከተል ወሰንኩ! ግን ስለ ነብዩ ሙሐመድ ያገኘዋቸው ታሪኮችን ልከተል ይቅርና በፍፁም መቀበል ቀበደኝ. ከነዚያ መካከል፦ *ነብዩ ሙሐመድ ጥቁር ድንጋይ ስመው ለድንጋይ ሰግደዋል! ሳሂህ አል ብኋሪ ቅፅ 2 መፅሀፍ 26 ቁጥር 673-680 "ሳሊም እንደተረከው፦የአላህ መልክተኛ(ሙሀመድ) ወደ መካ መጥቶ ተውፊድ ሲያደርግ በመጀመሪያ የጥቁር ድንጋይ ጠርዝ ከሳመ በኋላ ከሰባቱ ዙር ሶስቱን ዙሮች ራማ አደረገ!" ልብ ይበሉልኝ ሙሐመድ የአላህ ነብይ ነኝ ብሎ ጥቁር ድንጋይ ሳመ. የመሀመድ መዘዝ በዚህ አላበቃም. ዑመርንም አስቶታል ሳሂህ አል ቡኋሪ ቅፅ 2 መፅሀፍ 26 ቁጥር 667 "አቢስ ቢን ራቢያ እንደተረከው፦ ዑመር ወደ ጥቁር ድንጋይ ቀረብ ብሎ # ድንጋዩን_በመሳም እንዲህ አለ፦"አንተ ድንጋይ እንደሆንክ ማንንም ልትጠቅም እንደማትችል አውቃለሁ ግን ነብዩ ሙሀመድ ስለሳመህ ብቻ እስምሀለው!" ልብ በሉልኝ. ሙሐመድ ጥቁር ድንጋይ ስሞ ዑመርንም አሳተው! ይሄን ሳነብ በጣም አፈርኩ! ተናነቀኝ እንባ! ይባስ ብሎ ሙሐመድ እንዲህ ሲል ፈቅዶልናል!፦ ቁርኣን ሱራ/ምዕራፍ 4፥24 "ሙሐመድ ለተከታዮቹ ከማረኩዎቸው ባሪያዎች ጋር ግንኙነት እንዲፈፅሙ ፈቅዷል!" ይሄኛው ደግሞ ጭራሽ አስደነገጠኝ! ሙሐመድ እውነተኛ ነብይ ከሆነ ለምን እንደዚህ አይነት ነውረኛ ነገር ፈቀደ?? የሙሐመድ ሚስቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም! እኔ የነብዩ ሙሐመድ ተከታይ መሆን አልፈልግም! ሙሐመድ ሞቶ በመቃብር ቀረ! ከሞት ማምለጥ አልቻለም! እራሱንም ማዳን አልቻለም! ውስጤ በጣም አዘነብኝና አንድ ነገር አሰብኩ፦ ቁርኣን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ይላል ብዬ ማፈላለግ ጀመርኩ! የሚገርም ነገር አገኘሁ፦ *ቁርኣን ከማንኛቸውም የታወቁ ሰዎች ይልቅ ለኢየሱስ የበለጠ ከፍተኛ ስሞች ይሰጣል! 1፡ እርሱ ተአምር ነው ( ቁርኣን 19፡21፣ 21፡19) ደግሞም ተጠባባቂ (ቁርኣን4፡171)ተብሏል. በቁርአን ውስጥ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ በአክብሮት ነው የሚናገረው። *በቁርአን ውስጥ በኢየሱስ ላይ የተሰነዘረ ምንም ነቀፌታ ያለም! በቁርአን ኢየሱስ የእግዚአብሄር ሐዋርያ፣ የእግዚአብሄር ቃል (ካሊማ) እና የእግዚአብሄር መንፈስ (ሩህ)ብሎ ይጠራዋል ( ቁርኣን 4፡171) በቁርአን ውስጥ "በሻር" የተባለው የአረብኛ ቃል ያሚያመለክተው የመናፍስትን አለም ሳይሆን አንድ ሟችን ነገር ነው የሚያመለክተው። # ሙሐመድ ልክ እንደሌሎቹ ተራ ሰው ነው!( ቁርኣን 18፡ 110፣41፡6) ሌሎቹም ነብያት ልክ እንደዚው ሟች ተራ ሰው ናቸው። ስለዚህ በሻር(ሟች) የሚለው ቃል ኢየሱስን በተመለከተ አለመገኘቱ እንግዳ ነገር ነው! በተጨማሪ 1፡ኢየሱስ የተወለደው ከድንግል ነው(ቁርኣን19፡20-22) 2፡ኢየሱስ ጉድለት የለውም(ቁርኣን19፡19) 3፡ ኢየሱስ ታላቅ ፈዋሽ ነበር(ቁርኣን 3፡49፣5፡110) 4፡ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዐረገ(ቁርኣን 4፡158) 5፡ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል(ቁርኣን3፡45፣43፡61) 6፡ ኢየሱስ የመፍጠርና ህይወት የመስጠት ሀይል አለው(ቁርኣን 3፡49) ሞት ያልያዘውን መቃብር ፈንቅሎ የተነሳውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ወሰንኩ! እርሱ የአለም ብርሀን ነው! ከክርስቶስ ሌላ አዳኝ የለም! እርሱ በሁሉ ላይ አንደኛ ጌታ ነው! # ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ ፤ የእዳዬን ፅህፈት በደሙ አስወግዶ ፤ምስኪን መስሎ መጥቶ ፣ ዲያቢሎስን ቀጣ፤ በጨለማ ለነበርኩት ለኔ # አዲስ_ብርሀን_ወጣ ! Share share አድርጉ! እግዚአብሄርን አመስግኑልኝ! t.me/Jesusmiracl
إظهار الكل...
JESUS MIRACLE CHURCH

✝ የኢየሱስ ክርስቶስ ድንቅ ታምራት ፣ምስክርነቶች፣አስተማሪ መልዕክቶችና የመስቀሉን ፍቅር በጥልቀት የምንገነዘብበት የJesus miracle ቤተከርስቲያን ቻናል ነዉ ✝ ይህን ድንቅ የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመቀበል በእርሱ በማመን አስደናቂ ሰላምና ፈዉስ ወደ ቤትዎ ይጋብዙ ከመቅበዝበዝ ህይወት አሁኑኑ ይገላገሉ!! ⚗ #

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.