cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ልሳነ ግእዝ ⛪

📚 ከዚህ ገጽ የትም የሌሉ የብራና መጻሕፍት ያገኛሉ YouTube 👇👇 https://youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow Buy ads: https://telega.io/c/geeztheancient

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
16 246
المشتركون
-2124 ساعات
+1417 أيام
-8030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✝✝✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ ✝✝✝ ✝መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +" በዓለ ስዕለ አድኅኖ "+ ✝ይህች ቀን በቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ስዕላት የሚነገርባት ክብርት ቀን ናት:: 'ስዕለ አድኅኖ' ማለት 'እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት: አንድም በቅዱሳኑ አማካኝነት ጸጋ የሚገኝበት: የሚያድን ስዕል' ማለት ነው:: +ስለዚህ ነገር አንዳንዶቹ ሊነቅፉን ይፈልጋሉ:: እኛ ግን ከማን እንደ ተማርነው እናውቃለን:: ከመነሻው እኛ ስዕልን አናመልክም:: ይልቁኑ አምልኮን እንፈጽምበታለን እንጂ:: ስዕልን ለሰው ልጆች የሰጠ ራሱ ባለቤቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሠክራል:: +እንዲያውም የመጀመሪያው ሰዐሊ ራሱ አምላካችን ነው:: አዳምን እንደ መልኩ: በምሳሌው ሲፈጥረው መላእክት የእግዚአብሔርን ምስል አዳም ላይ አይተዋልና:: (ዘፍ. 1:26) ለሙሴም ስዕለ ኪሩብን እንዲስል ያዘዘ ራሱ ነው:: (ዘጸ. 25:22) በዚያም ላይ ሆኖ ሙሴና አሮንን ሲነጋገራቸው ኑሯል:: +በመቅደሰ ሰሎሞንም ተመሳሳይ ነገርን እናገኛለን:: (2ዜና. 7:12, 1ነገ. 9:1) በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ስዕለ ኪሩብ ያለበትን መቅደስ ቤቴ (ማቴ. 21:13): የአባቴ ቤት(ዮሐ. 2:16) ሲለው: በቅዱስ ሰውነቱ ሲመስለውም (ዮሐ. 2:21) እንመለከታለን:: ቅዱስ ዻውሎስ ለገላትያ ሰዎች ስለ ስዕለ ስቅለት ሲያስታውሳቸው (ገላ. 3:1): ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በደም የተረጨች ልብስ ብሎ ያላትን መተርጉማን ያትታሉ:: (ራዕይ. 19:13) +በትውፊት ትምሕርት ደግሞ የመጀመሪያው ስዕል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተሳለ ሲሆን ስዕሉም የእመቤታችን ነው:: "ሚካኤል በክነፊሁ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቃርዮስና ለቬሮኒካ (12 ዓመት ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት) መልክአ ገጹን ሠጥቷቸዋል:: ('ቬሮኒካ' በላቲን 'ቬሮን-ኢኮን' 'እውነተኛ መልክ' እንደ ማለት ነው) +ቀጥሎም ዮሐንስ ወንጌላዊ ለጢባርዮስ ቄሣር ስዕለ ስቅለቱን ሲስልለት ቅዱስ ሉቃስ ደግም የእመቤታችን 'ምስለ ፍቁር ወልዳን' ስሏል:: ከዚያም ሲያያዝ ይሔው ከእኛ ደርሷል:: +ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ ቅርጾች በዝተዋልና ይሔ አላስፈላጊ መዋስ (ያውም ከመናፍቃን) ቢቀር መልካም ነው ባይ ነኝ:: ኋላ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ከባድ ነውና:: +" ጼዴንያ "+ +በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሳላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ስዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሃብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት:: +ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ስዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የስዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር:: (እርሱ ምን ያድርግ! እኔም ብሆን ይህንኑ ነበር የማደርገው) +ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች:: ይህቺ ክብርት ስዕለ አድኅኖ የአሁን መገኛ 4 መረጃዎች አሉ:- 1.ያለችው ኢትዮዽያ ውስጥ (ደብረ ዘመዳ በሚባል ገዳም) ነው:: የመጣችውም ከግማደ መስቀሉ ጋር ነው:: 2.ያለችው በቀደመ ቦታዋ ነው:: 3.የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ወስደዋታል:: 4.በፈጣሪ ጥበብ ተሰውራለች:: +" ልደታ ለማርያም "+ +በግብጽ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት በአንዱ: ማለትም በአስቄጥስ ደብረ አባ መቃርስ የእመቤታችንን ዜና ሕይወት የሚናገር 1 መጽሐፍ አለ:: መጽሐፉ እንደሚለው እመ ብርሃን ድንግል ማርያም የተጸነሰችው ታሕሳስ 17 ቀን ነው:: በዚህ ሒሳብ መሠረት ደግሞ እመ አምላክ የተወለደችው መስከረም 10 ቀን ነው:: ዓለማቀፍ ትውፊቱ ግን ነሐሴ 7 ተጸንሳ: ግንቦት 1 ቀን መወለዷን ያሳያል:: +" ተቀጸል ጽጌ / አጼ መስቀል "+ +'ተቀጸል ጽጌ' ማለት 'መስቀል ሆይ! በአበባ አጊጥ' እንደ ማለት ሲሆን 'አጼ መስቀል' ደግሞ አጼ ገብረ መስቀልን: አንድም አፄ ዳዊት ቀዳማዊን ይመለከታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +በሃገራችን ኢትዮዽያ የነገረ መስቀሉ ትምሕርት ከመጣ ጀምሮ መስቀል ይከበራል:: በአደበባባይ ግን እንዲከበር ያደረጉት የቅዱስ ካሌብ ልጅ አፄ ገብረ መስቀል ናቸው:: በወቅቱ ንጉሡ: ሠራዊቱ: ዻዻሱና ሕዝቡ በተገኙበት ቅዱስ ያሬድ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር-መስቀል ከሁሉ ነገር በላይ ነው: ከጠላትም ያድነናል" እያለ ይዘምር ነበር:: +የአበባ ጉንጉንም ለመስቀሉና ለንጉሡ ይቀርብ ነበር:: ከ800 ዓመታት በሁዋላም አፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ባስመጡ ጊዜ መስከረም ቀን ተተክሎ ታላቅ በዓልም ሆኖ ተከብሯል:: +" ንግሥተ ሳባ "+ +ይሕቺ ደግ ኢትዮዽያዊት ከ3 ሺ ዘመናት በፊት የነበረች ደግ እናት ናት:: በሥጋዊ ደረጃ ከታንዛንያ እስከ የመን ያስተዳደረች ስመ ጥር ንግሥት ስትሆን በመንፈሳዊው ደረጃ ደግሞ እግዚአብሔር የቀባውን ሰው ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች:: +ከዚያውም አምልኮተ እግዚአብሔርን ከሥርዓተ ኦሪት ጋር አምጥታለች:: ድንግልናዋን ለታላቁ ንጉሥ ሰሎሞን ሰጥታ ምኒልክን ወልዳለች:: ይህቺ ንግሥት በጌታችን (በፈጣሪ) አንደበትም ተመስግናለች:: (ማቴ. 12:42) በስምም "ሳባ: አዜብና ማክዳ ተብላ ትታወቃለች:: ዛሬ ዕለተ ዕረፍቷ ነው:: +እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን: ከስዕሏም ረድኤት ትክፈለን:: የቅዱሳኑም ክብር አይለየን:: +መስከረም 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም 2.በዓለ ስዕለ አድኅኖ 3.ቅዱስ እፀ መስቀል (ተቀጸል ጽጌ) 4.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ 5.ቅድስት ማርታ ዘጼዴንያ 6.ቅድስት ዮዲት ጥበበኛዋ 7.ንግስተ ሳባ / ማክዳ / አዜብ 8.ቅድስት መጥሮንያ ሰማዕት 9.አፄ ዳዊት ንጉሥ 10.ቅድስት አትናስያና 3 ልጆቿ =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ++"+ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር:: ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? +"+ (ገላ. 3:1) ‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ›››› ©ከዝክረ ቅዱሳን ገጽ የተወሰደ
إظهار الكل...
3🙏 1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ መቅድም ይህ መጽሐፍ የቅዱስ ዞሲማስንና የቅድስት ማርያም ግብጻዊትን ገድል የያዘ ነው፡፡ ሁለቱም በዮርዳኖስ በረሓ የተጋደሉና በተመሳሳይ ዘመን የነበሩ ታላላቅ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ቅዱስ ዞሲማስ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን ካገለገለ በኋላ ከዚህ ዓለም ነገር ሁሉ ተሰውራ ለአርባ ሰባት (፵፮) ዓመታት ያህል ብቻዋን በበረሓ ስትጋደል የኖረችውን ቅድስት ማርያም ግብጻዊትን ወደ ተጋድሎዋ ፍጻሜ ዘመን ላይ አግኝቷታል፡፡ እርሷም በበረሓ ከሚኖሩ ስውራን ፈላስያን ባሕታውያን አንዷ ነበረች፡፡ የቅዱስ ዞሲማስ ዜና ሕይወት በውስጡ ከእርሱ ሕይወት ጋር አስደናቂ የሆነውን የብሔረ ብፁዓንን ዜና ሕይወት ይዟል፡፡ በብሔረ ብፁዓን የሚኖሩት እንደ እኛው ሰዎች ሲሆኑ ነገር ግን በእነ ኤርምያስ ነቢይ ዘመን በእግዚአብሔር ቸርነት ከዚህ ዓለም ወደ ብሔረ ብፁዓን የተወሰዱ ናቸው፡፡ ብሔረ ብፁዓን ከአምስቱ ዓለማተ መሬት (ሲዖል፤ ይህች እኛ ያለንባት ምድር፣ ብሔረ ሕያዋን እና ገነት) መካከል አንዱ ነው፡፡ ብፁዓውያን ወደ ብሔረ ብፁዓን ከመወሰዳቸው በፊት በዚህ ዓለም ሳሉ ሥጋ ከመብላትና ወይ ከመጠጣት ቤት ከመሥራትና ከመሳሰለው የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ርቀው በገዳም ይኖሩ ነበር፡፡ ይህ ታሪካቸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትንቢተ ኤርምያስ ላይ ትንሽ ፍንጭ በሚሰጥ ሁኔታ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል፡- እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፡- የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፥ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናልና፤ እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ፡፡ በምትኖሩባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እንድትኖሩ፥ በዕድሜአችሁ ሙሉ በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ እንጂ ቤትን አትሥሩ፥ ዘርንም አትዝሩ፥ ወይንም አትትከሉ .. አንዳችም አይሁንላችሁ፡፡ እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም ሚስቶቻችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም፣ የምንቀመጥበትንም ቤት አልሠራንም፣ የወይን ቦታና እርሻ ዘርም የለንም፣ በድንኳንም ውስጥ ተቀምጠናል፥ ታዝዘናል፥ አባታችንም ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ አድርገናል።'' ኤር.35፡1-10 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ የተመለከተው የእነዚህ የብፁዓውያን ፍጻሜያቸውና መዳረሻቸው ምን ነበር? ወዴት ሄዱ? እንዴትስ ሄዱ? የሚሉት ጥያቄዎች የብዙዎች የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቃውንት ጥያቄዎችና ለማወቅ የሚያጓጉ ምሥጢሮች ናቸው፡፡ ቅዱስ ዞሲማስም እነዚህን ብፁዓውያን ለማየትና አኗኗራቸውን ለማወቅ ከፍተኛ መንፈሳዊ ፍላጎት ስላደረበት እግዚአብሔርን እነርሱን ያሳየው ዘንድ በጾምና በጸሎት ብዙ ጊዜ ደጅ ሲጸና ኖሮ የለመኑትን የማይነሳው ቸር አምላክ ፈቃዱን ፈጽሞለት ወደ ብሔረ ብፁዓን ደርሶ እነርሱን አይቶ ዜናቸውን መዝግቦ ይዞልን መጥቷል፡፡ ይህ የብፁዓውያንና የቅዱስ ዞሲማስ ዜና ሕይወት አንድ በመሆኑ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በአንድ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ የቅድስት ማርያም ግብጻዊት ገድልም እንዲሁ ተተርጒሞ በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ ቀርቧል፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን (ቅዱስ ዞሲማስና ቅድስት ማርያም ግብጻዊት) በዘመነ ተጋድሏቸው የተገናኙና ዜና ሕይወታቸውም የተዛመደ ስለሆነ የሁለቱም ቅዱሳን ገድል በአንድ ላይ ሆኖ መቅረቡ ተገቢ ስለሆነ እንዲሁ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የቅዱስ ዞሲማስና የቅድስት ማርያም ግብጻዊት፤ እንዲሁም የብፁዓውያን በረከታቸው ይደርብን፤ አሜን። share https://t.me/geeztheancient Subscribe our YouTube 👇 https://youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow
إظهار الكل...
ገድለ_ቅዱስ_ዞሲማስ_ወቅድስት_ማርያም_ግብጻዊት.pdf20.23 MB
ዝ ውእቱ መጽሐፈ ሥዕል ዘየሐትት በእንተ ሥዕለ አድኅኖ https://t.me/BiranaEthio
إظهار الكل...
ታሪክ በከመ ጸሐፈ አሐዱ መነኮስ.pdf19.31 MB
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ፤ እመ ፱ ለመስከረም በዛቲ ዕለት ኮነ ሰማዕተ ቅዱስ ቢሰሮ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀገረ መጺል። ወዝንቱ ቅዱስ ኮነ ኤጲስ ቆጰሰ ላዕለ ሀገር መፍቀሪተ እግዚአብሔር መጺል እምብሔረ ግብዕ። ወሶበ ነግሠ ዲዮቅልጥያኖስ ከሐዲ ኰነኖሙ ለክርስቲያን ወፈተወ ዝንቱ ቅዱስ ከመ ይክዓው ደሞ በእንተ ስሙ ለክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡ ወአስተጋብአ ኵሎ ሕዝበ፡፡ ወአቀሞሙ ቅድመ ቤተ መቅደስ ወአዘዞሙ ትእዛዘ ጽድቅ። ወእምድኅረዝ አይድዖሙ ውእቱ ይፈቅድ ከመ ይክዓው ደሞ በእንተ ክርስቶስ፡፡ ወሰሚዖሙ በከዩ ላዕሌሁ ዓቢዮሙ ወንኡሶሙ ወይቤልዎ ለምንት ተኀድገነ እጓለ ማውታ ወንሕነሰ ኢነኀድገከ ከመ ትሑር፤ ወፈቀዱ ከመ የአኀዝዎ ወኢተክህሎሙ፡፡ ወእምዝ ኀደግዎ ወአማ ዕቀቦሙ ኀበ ክርስቶስ ወተአምኆሙ። ወወፅአ እምኀቤሆሙ ወእሙንቱ አስተፋነውዎ እንዘ ይበክዩ፡፡ ወሖሩ ምስሌሁ ፫ቱ ኤጲስ ቆጶሳት እሉ እሙንቱ ቢስኮስ ወፍናቢኮስ ወቴዎድሮስ፡፡ ወሖሩ ኅቡረ ኀበ ሀገረ መኰንን ወተአመኑ በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወኰነኖሙ መኰንን ኵነኔ ዓቢየ ወአፈድፈደ ኵነኔሆሙ ወእግዚእነ ያጸንዖሙ በውስተ ኵነኔ ዓቢይ። ወሶበ አእመረ መኰንን ከመ እሙንቱ ኤጲስ ቆጶሳት ፅኑዓን በትዕግሥት አበዊሆሙ ለክርስቲያን አዘዘ ይምትሩ አርእስቲሆሙ በሰይፍ ወነሥኡ አክሊለ ስምዕ ወመተርዎሙ በመንግሥተ ሰማያት ወሥጋሁሰ ለቅዱስ ቢሰሮ እስከ ይእዜ ይነብር በሀገረ ምሲል ዘማዕዶት በረከቶሙ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን። አርኬ
ሰላም ለቢሰሮ ዓቃቤ መርዔቱ ለልዑል፤ ኤጲስ ቆጰስ ዘሀገረ መጺል፤ ወሰላም ካዕበ ለእለ ምስሌሁ መድበል፤ ቢስኮስ ወፍናቢስኮስ ወቴዎድሮስ ኃያል፤ ዘተሰ ነዓዉ ኅቡረ በገድል።
፯. ወበዛቲ ዕለት ኮኑ ሰማዕታት እልፍ ወ፵፻ ወ፯፻ ወ፴ ዕደው ወ፯ቱ አንስት ምስለ ቅዱስ ፋሲለደስ በረከቶሙ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን። ፰. ወበዛቲ ዕለት ኮነ ተዝካረ ተአምር ውስተ ብሔረ ሮምያ በሀገር እንተ ስማ ፍሩምያ። ፱. ውእቱኬ እስመ ሰብእ እምብሔረ ዮናናውያን ቀንኡ ፈድፋደ በቅንአተ ሰይጣን በእንተ ተአምራት ወመንክራት ዘያስተርእዩ ውስተ ቤተ ክርስቲያኑ ለመልአክ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላእክት ወፈቀዱ ይሚጥዎ ዘይውኅዝ ለፈለገ ማይ ላዕለ ቤተ ክርስቲያን ከመ ያጥፍእዋ ወለመጋቢሃ ምስሌሃ። ወሶቤሃ አስተርእዮ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ለናርጢኖስ መጋቤ ቤተክርስቲያን ወቀርበ ኀቤሁ ወይቤሎ ጽናዕ ወኢትፍራህ ወዘበጦ ለኰኵሕ በበትሩ ወተሠጥቀ ኰኵሕ ከመ መስኮት። ፲፩. ወአንከሩ እለ ርእዩ ዘንተ ወሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ወአክበርዎ ለሊቀ ኀይላተ ሰማይ ሚካኤል ክቡር ወእስከ ዮም ሀሎ ውእቱ ፈለግ እንዘ የኀልፍ በውስተ ኰኵሕ ወኢቀርበ ኀበ ቤተክርስቲያኑ ለሊቀ መላእክት፡፡ ትንብልናሁ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን። አርኬ ሰላም እብል ለዓቢይ መንክሩ፤ ዘተከሥተ ዮም በውስተ ደብሩ፤ ፈለገ ማይ ይሚጡ እንዘ ይመክሩ፤ ተሠጥቀ ኰኵሕ እንተ ዓላውያን አንበሩ፤ ሶበ ሚካኤል ዘበጦ በበትሩ። ሰላም ለቂርቆስ ለነቢረ ገዳም ዘአፍቀራ፤ እንዘ ይሰቲ ሐሊበ ቶራ፤ ድኅረ አመከሮ ሰይጣን በዘዘዚአሁ መከራ፤ አዕይንቲሆሙ ለኤጲስ ቆጶሳት ነፀራ፤ በጊዜ ዕረፍቱ ዘኮነ ነከራ። ፲፪. ወበዛቲ ዕለት አዕረፈ ያሳይ ንጉሥ ዘፈጸመ ገድሎ መልዕልተ ኦም ወአሥመሮ ለእግዚአብሔር ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን። ሰላም ለያሳይ እመንግሥተ ምድር ዘተድኅለ፤ መንግሥተ ሰማያት ያድምዕ ወዘኢየኀልፍ ብዕለ፤ ውስተ ጕንደ ዕፅ ይቡስ ጊዜ ተለዓለ፤ ዘትሩፋቲሁ ከመ ያርኢ ኀይለ፤ አሥረፀ ሶቤሃ ወአውፅአ ቈጽለ። share https://t.me/geeztheancient
إظهار الكل...
3🥰 1
ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፰ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ስምንት በዚች ቀን የዓመቱ ወሮች መቍጠሪያ የሚሆን የመጀመሪያ ኮከብ ይወጣል ይኸውም መናዝል የሚለው የዐሥራ ሁለቱ ወር ኮከቦች ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ መገብተ አውራኀ አሉ፤ ምግብ ናቸውን ፈጽመው በዚች ቀን እንደ ገና አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው ። በዚችም ቀን የበራክዩ ልጅ ካህንና ነቢይ የሆነ የከበረ ዘካርያስ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ካህን ስለ ልጁ ዮሐንስ መወለድ የመላእክት አለቃ ገብርኤል በነገረው ጊዜ ነገሩን አምኖ አልተቀበለም ። ስለዚህም ሕፃኑ እስቲወለድ ዲዳ ትሆናለህ አለው ። አርኬ
ሰላም እብል እንበለ እከዩ ወሕሠሙ ። ለዘአቅተለቶ ምሸራብ እንዘ ኢያምሕራ ድካሙ። አመ ተዋቀሰ አምላክ በሞተ ነቢያት ኵሎሙ። አሌ ለኪ ይቤላ ለአቤል እምደሙ። እስከ ደመ ዝንቱ ጻድቅ ዘካርያስ ስሙ ።
ሰላም ለዘካርያስ ለእግዚአብሔር ቅዱሱ። ወለዮሴፍ አበ መንፈሱ። ዓቅመ ፴ ወመንፈቀ ሥሱ። በእንተ ብዙኅ ጻሕቁ ወበእንተ ፍድፉድ ማኅሠሡ ። መንፈቀ ኃጥአን ቄዐ ለገሀነም ከርሡ።
አርኬ
ሰላም እብለ ለዘሰገደ ወአስተብረከ። መልዕልተ ዕፅ ነጺሮ በነደ እሳት መልአከ። መፈውሰ ቍስል ሙሴ ዘእምደዌ ምድር ተነስከ። ወእስከ ተሠይመ በላዕለ ፈርዖን አምላከ። ስብሐተ ቅዱሳን አድምዐ ወዝክረ ብሩከ።
መስከረም ፰ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት ፪.ቅዱስ ዘካርያስ ካህን (ጻድቅ ነቢይ) ፫.ቅዱስ አሮን ካህን ፬.ቅዱስ ዲማድዮስ ሰማዕት ከመቅረት መዘግየት ይሻላል ።
إظهار الكل...
1
ግእዝ ጉባኤ ቃና ሐንካሳን፡አልዐሉ፡እደዊሆሙ፡ኅቡረ፤ እስመ፡ገሠጾሙ፡አብ፡ከመ፡ኢያንሥኡ፡በትረ። ትርጉም አንካሶች በአንድነት እጆቻቸውን አነሱ፤ በትር እንዳያነሱ አባት ተቆጥቷቸዋልና። ምስጢር ለመማታት በትር ያነሱ ጎበዞች/ ወጣቶች አባታቸው በተቆጣ ጊዜ እጆቻቸውን ወደላይ አንስተው በትር አለመያዛቸውን ለአባታቸው ያረጋግጣሉ ። እንዲህም የጎበዞቹ / የወጣቶቹ ምሳሌዎች የሆኑ አንካሶች ከበሽታቸው ከዳኑ በኋላ ያለበትር ሔዱ ማለት በቅኔው ምስጢር ተገልጧል። ሼር.. @geeztheancient
إظهار الكل...
7
ግእዝ ክብር ይእቲ
በበለስ፡ዘሐመ፡ አድኀነ በበለስ፤ እግዚአብሔር፡ዘሰብእ፡ወዘመላእክት፡ አፍራስ። እምቅድመ፡ዝኒ፡ተገብረ፡በሀገረ፡ሮሜ፡ወፋርስ። በሦክ፡ዘሐመ፡ አምጣነ በሦክ ይትፈወስ።
ትርጉም የሰውና የመላእክት/ፈረሶች እግዚአብሔር በበለስ የታመመውን በበለስ አዳነ ። (ይህ) ከዚህም በፊት በሮምና በፋርስ አገር ተደርጓል። በሾህ የታመመ በሾህ ይድናልና። ምስጢር « እሾህ በእሾህ ይነቀላል፤ በደል በካሣ ይመለሳል » እንዲሉ፡በእንጨት የታመመው ሰው በእንጨት እንደሚድን ፤ በበለስ ቅጠል መብል የወደቀ አዳምን ክርስቶስ በእንጨት መስቀል አዳነው ማለት በቅኔው ምስጢር ተገልጧል። በሽተኞች የበለስን ደም እየተቀቡ ይድኑ ነበር ። ከዚህም የተነሳ ኤርምያስ አቤሜሌክን ለድውይ የሚቀባ የበለስ ቀንበጥ እንዲያመጣ ልኮታል። ሐማ መርዶክዮስን ለመስቀል ረዥም እንጨት በበሩ አቁሞ በዚኽም ላይ የመርዶክዮስ ወገኖች ኹሉ እንዲጠፉ ከንጉሥ አርጤክስስ አስፈቅዶ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፤ የንጉሡ ሚስት አስቴር የመርዶክዮሰን ልቅሶ ሰምታ የሦስት ቀን ጾምና ጸሎት ከነወገኖቿ በጥብቅ አደረገችና ለንጉሡ በግብዣዋ ላይ ግፉን አስረዳች። ስለዚህም ንጉሡ ልመናዋን ተቀብሎ ሐማን ለመርዶክዮስ በአዘጋጀው እንጨት ላይ ሰቅሎታል (አስቴ.3-8)። መጽሐፈ ቅኔ የሥነ-ጥበብ ቅርስ ላይ የተወሰደ። @geeztheancient
إظهار الكل...
ድርሳኖሙ ለ፬ቱ እንስሳ (1).pdf11.23 MB
ድርሳነ አርባዕቱ እንስሳ
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.