cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

AHADU RADIO FM 94.3

አሐዱ ራድዮ 94.3 Your source for top local and international news and analysis. "Voice of Ethiopian" የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
19 230
المشتركون
+1324 ساعات
+477 أيام
+10030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መሰረታዊ መብት እየተሸረሸረ ነው አለ መስከረም 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአሁኑ ወቅት ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መሰረታዊ መብት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸረሸረ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ገልጿል። ማዕከሉ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ "በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው እስር፣ ወከባ፣ እንግልት እንዲሁም ዛቻና ማስፈራሪያ እየጨመረ መምጣቱ በእጅጉ አሳስቦኛል" ብሏል፡፡ ድርጊቱ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 29 የተደነገገውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መሰረታዊ መብትን የሚሸረሽር እንደሆነም አንስቷል፡፡ "ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና የሰሉ ትችቶችን፣ የተለዩ አመለካከቶችን እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ የሚቀርቡ ዘገባዎችን ከመገደብ ባለፈ፤ ሕገ-መንግሥቱንም የማያከብር ድርጊት ነው" ሲል በመግለጫው አጽንኦት ሰጥቶበታል፡፡ ይህ የዘፈቀደ እስራት፣ ማስፈራራት እና ዛቻ እንዲሁም እየተባባሰ የመጣው በጋዜጠኞች ላይ በሚደርስ ጫና፤ ገሚሶቹን ሥራቸውን እንዲተዉ እያስገደደ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡ ማዕከሉ አክሎም የሲቪል ማኅበረሰብ አባላት በሚደርስባቸው የተለያዩ ጫናዎች ከሀገር ለቀው እንዲሰደዱ ማስገደዱን አመላክቷል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችንና ጋዜጠኞችን እስርን ጨምሮ በተለያዩ ጫናዎች ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ በሀገሪቱ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ምህዳር የሚያጠብ፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን፣ የሃሳብ ብዝኃነትን እና የማኅበረሰቡን መረጃ የማግኘት መብትን የሚገድብ መሆኑንም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል በመግለጫው አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡ በዳግም ተገኘ ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
"በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎች ለድርድር ፍቃደኛ አይደሉም ተብሎ የሚነሳው ቅሬታ ከእውነት የራቀ ነው" የክልሉ የሰላም ካውንስል "በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎች ለድርድር ፍቃደኛ አይደሉም" ተብሎ የሚነሳው ቅሬታ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የክልሉ የሰላም ካውንስል ለአሐዱ ገልጿል፡፡ በመንግሥትና በታጠቁ ሀይሎች መካከል እየተደረገ የሚገኘውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በተመለከተ አሐዱ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ዋና ሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠን አነጋግሯል። በክልሉ የተፈጠረውን አጠቃላይ የጸጥታ ችግር ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ያነሱት ዋና ሰብሳቢው፤ "በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎች ጋር በተደረገዉ ንግግር ለሰላማዊ ድርድሩ ዝግጁ መሆናቸዉን አረጋግጠናል" ብለዋል። ይህ በሆነበት ሁኔታ "ለድርድር ዝግጁ አይደሉም፤ የሚደራደር አካልም የለም" በሚል የሚሰራጨዉ መረጃ ከእውነት የራቁ ስለመሆኑ አቶ ያየህይራድ ተናግረዋል። በክልሉ የተከሰተው ግጭት እያደረሰ ያለው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ዋና ሰብሳቢው፤ ሁሉም አካላት ለተጀመረው የሰላም ጥረት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። በታሪኩ አለሙ ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
👍 6 1
Photo unavailableShow in Telegram
በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ሁለት መምህራን በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ መስከረም 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ረቡዕ ገበያ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ሁለት መምህራን ትናንት መስከረም 8 ቀን 2017 ዓም በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የተፈጸመባቸዉ መምህራን መ/ር ጌታ እንዳለ አንማውና መ/ር አትንኩት ሁነኛው ሲሆኑ፤ በስናን ወረዳ ረቡዕ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት ሙያ ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸዉ ተብሏል። የታጠቁ ኃይሎች እነዚህን የቀለም አባት እንቁ መምህራን በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈጸሙባቸዉ በ2017 ዓም የትምህርት ዘመን ለመማር ማስተማር እንቅስቃሴ አድርጋችኋል፤ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ለምን ትገባላችሁ? በሚል እንደሆነም ተገልጿል። "ይህ ድርጊት እንደባለፈዉ ዓመት ሁሉ ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይመለሱ፤ የአማራ ህዝብ ተማሪዎች ከሌሎች እኩዮቻቸዉ ተነጥለዉ እንዲቀሩና የትዉልድ ክፍተት እንዲፈጸም ታልሞ የሚሰራ ስራ ነው" ሲል የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር አስታውቋል። ስለሆነም ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና መላዉ የዞኑ ማህበረሰብ ድርጊቱን በማዉገዝ የ2017 ዓ.ም የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል። ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
👍 4😢 4
ኢትዮ ቴሌኮም በተለያየ የሀገሪቷ ክፍሎች የሚስተዋለውን የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በተመለከተ ይቅርታ ጠየቀ መስከረም 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ እንደ አማራ እና ኦሮሚያ እንዲሁም ሌሎች በፀጥታ ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎችን በተመለከተ ይቅርታ ጠይቋል። ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ የጠየቀው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅዱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ በተመለከተ "ኢትዮ ቴሌኮም በጉዳዩ ላይ ሃላፊነቱን ባይወስድም እንደ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ግን ይቅርታ እንጠይቃለን" ብለዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን በተመለከተ (ማን እንደሆነ ያልገለጹት) ሃላፊነትን የሚወስድ እና ምላሽ መስጠት ያለበት የሚመለከተው አካል መሆኑን አመላክተዋል። አያይዘውም ደንበኞች የገዙትን የአገልግሎት ጥቅል ሳይጠቀሙበት የሚፈጸም ምንም አይነት ክፍያ አይኖርም ሲሉ ገልጸዋል። ነገር ግን በአንዳንድ አካባቢዎች ጥቅም ላይ የዋለና እና ያልዋለውን ለመለየት የሚያስቸግርበት ሁኔታ መኖሩን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አክለዋል። በኢንተርኔት መቋረጥ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትሰለፍ መሆኗ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅዱን ይፋ ባደረገበት በዚሁ መድረክ፤ በተያዘው በጀት ዓመት በመላ ሀገሪቱ 1 ሺህ 298 የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎችን ለመገንባት፣ በ500 ከተሞች የ4ጂ እንዲሁም በ15 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ማቀዱን አስታውቋል። በፍርቱና ወልደአብ ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 5 2😁 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዋግ ኽምራ ዞን በመሬት መንሸራተትና በጎርፍ አደጋ ምክንያት 29 ሰዎች መሞታቸውንና በሰብል መሬት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ መስከረም 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዋግ ኽምራ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት እና በጎርፍ አደጋ ምክንያት 29 ሰዎች መሞታቸውንና 9 ሺሕ 7 መቶ 92 የሚሆን የሰብል መሬት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን ከሐምሌ 11/2016 ዓ ም እስከ አሁን ባለው መረጃ በጎርፍና መሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት 29 ሰዎች መሞታቸውንና 9 ሺሕ 7 መቶ 92 የሚሆን የሰብል መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና አስተባባሪ አቶ ምህረት መላኩ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ ክረምት ከገባ እስከ ሐምሌ 11 አካባቢ መጠነኛ የሚባል ዝናብ እንደነበረ አንስተው ነገር ግን የመሬት መንሸራተቱና የጎርፍ አደጋው ከሐምሌ 11 አካባቢ ጀምሮ እየተባባሰ በመምጣቱ የሰዎች ሕይወት ፤የሰብል መሬቶች እንዲሁም ብዛት ያላቸው እንሰሳቶችም የአደጋው ሰለባ እንደሆኑ አክለው ተናግረዋል፡፡ በአደጋው የተፈናቀሉና ለተጎዱ ጊዜያዊ መጠለያ የሚሆን ሸራና አልባሳትን ድጋፍ ማድረጋቸውን አንስተው፤ ለመልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ግን ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዋናነት በጎርፍና በመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸው በ6 ወረዳዎች ላይ እንደሆነና በአጠቃላይ የመልሶ ማቋቋሚያዉ ከአቅም በላይ በመሆኑ ምን ያክል ያስፈልጋል የሚሉ ሐሳቦችን ለሚመለከተው አካል ለመስጠት ጥናት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአደጋው የተጎዱ ማህበረሰቦችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ጥናት በማድረግ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ መፍትሔ እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ምህረት ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ በዓለምነው ሹሙ ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

😢 3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት 500 ከተሞችን የ4G ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ መስከረም 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅዱን በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዕቅዱም መሰረት በተያዘው በጀት ዓመት 500 ከተሞችን የ4G ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል፡፡ በዚህም በ2017 ዓ.ም የ4 ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽ ያልነበሩ 500 ከተሞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱን የቴሌኮሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል። እንዲሁም 15 ተጨማሪ ከተሞች የ5 ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2016 ዓ.ም 100 የገጠር ቀበሌዎችን የማገናኘት ሥራ መሰራቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም 496 የገጠር ቀበሌዎችን ለማገናኘት ይሰራል ብለዋል። በዚህም ወደ 4 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ባደረገው ዕቅድ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እና ማስፋፊያዎችን ለመስራት ዕቅድ መያዙን አስታውቋል። በፍርቱና ወልደአብ ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
👍 8👏 1
የ42 ዓመት አንዲት እናት አራት ሕፃናትን በሠላም ተገላገሉ መስከረም 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዕድሜያቸው 42 ዓመት የሆኑት አንዲት እናት በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ህፃናትን በሠላም መገላገላቸው ተሰምቷል። ወይዘሮ አደባባይ የሺነህ የተባሉት እኚህ እናት ነዋሪነታቸው በአዊ ብሔረሰብ ዞን ጃዊ ወረዳ አሊኩራንድ ቀበሌ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል ሦስት ወንድና አንድ ሴት በድምሩ አራት ሕፃናትን በሰላም መገላገላቸውን ከወረዳው መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል በአሁኑ ሰዓትም ጨቅላ ህፃናቶች በሰባት ወራት ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ ስለሆነ በህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል። ወላጅ እናት የአሁኑን ጨምሮ ለስድስተኛ ጊዜ የወለዱ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በሰላም እንዲገላገሉ ለረዷቸው ለሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎችና የፓዊ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ላደረጉላቸው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ! ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
إظهار الكل...
👍 7👏 1🙏 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.