cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የኛ ግጥም 😍😄❤🥰🥺

እንኳን ደና መጡ🙏 በዚህ ቻናል #ግጥሞች #ቀልዶች እንዲሁም ሀገርኛ ወጎችን አዝናኝ መረጃዎችን በለዛ እናገኛለን ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ስራዎን ማቅረብ ከፈለጉ ወይም cross ከፈለጉ በዚህ ያናግሩኝ 👉 @berii34 እዚህ ለይ ደሞ👇 @ethiopianye👈join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ for any comment👉 @berii34

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 987
المشتركون
+1624 ساعات
+307 أيام
+8430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እኔና አንቺ! ( በረከት በላይነህ). በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤ ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ። እኔና አንቺን እኮ! አበቦቹ ያጅቡናል፣ ፍራፍሬው ይከበናል፤ ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል። ወፎቹ! እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤ ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ። ኮከቦቹ! " ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤ ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ። በቀቀኖች እንኳን! ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤ ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ። ‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ! በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣ እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣ ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።    @ethiopianye @ethiopianye
إظهار الكل...
3
#እሷ :- ዛሬ እኮ የተጋባንበት ሶሰተኛ አመታችን ነው። ለምን በግ አታርድም??? #እሱ :- እኔ ባጠፈሁት ለምን በጉ ይቀጣል🤷‍♀??? 😁😁😁 ደና እደሩ ቤተሰብ 🥱😴 @ethiopianye
إظهار الكل...
😁 6🤣 4
ሆድ አደር ፀሎቱ ፃምን ጦመን ነበር ከስጋ ከወተት 55 ሲመጣ ፋሲካው ሲጎተት ........አብረን ልንንጓተት ፃምን ጦመን ነበር ችግር እንዲርቀን ሞልቶ እንዲያድርልን ጎደሎይቱን ቀን ... ...  ... ...ለካ ከስፍር ስንሰፍር የመጦም ውላችን ችግራችን ሆኖ ስጋ ማጣታችን ለመንነው ፈጣሪን እስከ ጊዜው ጦመን .....ጎደሎው ሲሞላ..... እንኳን ለሁዳዴ በነነዌያችን ልንሰቅል ጎመን አይገርምም ፃምን ጦመን ነበር ስጋ እንዲ'ሰጠን ፀሎቱ ነው አሉ ድሮስ የሆድ አደር...😢 #ephi777✍ [@ephicr7] @ethiopianye
إظهار الكل...
😁 7
ርዕስ:   🎤ሁለት መንገድ😞 ገጣሚ:  naftanan & sonrisa ድምፅ:   naftanan & sonrisa ለአስተያየት;  comment 👇👇                @ethiopianye
إظهار الكل...
ሀለት መንገድ.mp38.13 MB
4👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🥰 7😁 2
ርዕስ:   🎤ያልፋል በሉኝ😞 ገጣሚ:  ናፍታናን ድምፅ:   ናፍታናን ለአስተያየት;  @nafii_junior7   ''ሁሉም ያልፋል'' ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ👇      #share                  @ethiopianye
إظهار الكل...
ያልፋል በሉኝ.mp31.58 MB
👍 5
አንተ ነህ መስከረም (በሠዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ) ማለቂያ በሌለው ደማቅ ሰማያዊ፣ ከሩቅ ያለው ጋራ ተነክሮ ሐምራዊ፡፡ በዚያ ላይ ደመናው እንደ ጥጥ ተነድፎ፣ እየተራራቀ ሲያንጃብብ ተቃቅፎ፡፡ አንተ ነህ መስከረም፣ የሐምሌን ጨለማ የነሐሴን ዝናም፣ የሻርከው አንተ ነህ፣ በብርሃን ውበትህ፡፡ በክረምቱ ወራት ሰማዩን ያስጌጠው፣ የማርያም መቀነት በቀለም ያበደው፡፡ ጤዛው አርሶታል መሬቱ ላይ ለቆ፣ በቀይና ብጫ መስኩ ተለቅልቆ፡፡ ወንዝና ጅረቱ ድንጋይና አፈሩ፣ ሀገሩ ውብ ሆኗል ሜዳው ሸንተረሩ፡፡ ዕንቁጣጣሽ አንተ ስጦታህ የበዛ፣ ለሰው መታሰቢያ ውበት የምትገዛ፡፡ በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፣ ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን፡፡ ከምረው ዘመኑን ካበው ባመት ባመት፣ በወሩ ደረጃ ፍጥረት ይጓዝበት፡፡ ፍየሎች ይዝለሉ ቅጠል ይበጥሱ፣ ከተሰደዱበት ወፎች ይመለሱ፡፡ ይልቀሙት አህሉን፣ ይስሩ ቤታቸውን፣ ይስፈሩበት ዛፉን፣ የደስደስ ያሰሙ ንቦች ይራኮቱ፣ ይንጠራሩ አበቦች ይንቁ ይከፈቱ፡፡ አንበሳና ግልገል በመስኩ ይፈንጩ፣ ከብቶች ሣሩን ይንጩ፡፡ ሕፃናት ይሩጡ ይሳቁ ይንጫጩ፣ ዛፎች ይተንፍሱ፣ የነፋሱ ጠረን፣ ይሰራጭ በቦታው ያውደው አገሩን፡፡ ዓደይ አበባ ነህ የመስቀል ደመራ፣ ጠረንህ አልባብ ነው አየርህ የጠራ፡፡ ያገር ልብስ አንተ ነህ ነጭ እንደበረዶ፣ ሰው የሚያጌጥብህ ጥበብህን ወስዶ፡፡ ቡቃያ ነህ እሸት ጓሚያ የበሰለ፣ አረንጓዴ ልብስህ በጌጥ የተሳለ፡፡ ጥቁር አረንጓዴ፣ ብጫማ አረንጓዴ፣ ቀለም ! ቀለም ! ቀለም ! የሚያስተካክልህ የሚያስንቅህ የለም፡፡ ኀዘን የምታርቅ የገነት ምሳሌ፡፡ ይታደል ወለላህ ጠጁ በብርሌ ይስከር በደስታ ሕዝቡ ይሳሳቅ፣ ድምፁ እየተማታ ሙዚቃው ይፍለቅ፡፡ ዕንቁጣጣሽ ብለን እንስጥህ ሰላምታ፣ ይጭብጨብ ለዝናህ፣ ይጭብጨብ ለስራህ ይጭብጨብ ለመልክህ አንተ ነህ መስከረም፡፡ ዘመን የምታድስ አስጊጠህ በቀለም፡፡ @ethiopianye
إظهار الكل...
👍 6
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለመውሊድ ባህል በሰላም አደረሳችሁ ❤️❤️
إظهار الكل...
🔥 3🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
' ለጋ የልጅነት ወራቴን ፍም አፍላ ወጣትነቴን ሂያጅ'ና መጭ እኔነቴን ዛሬ ነገ ትናንቴን ፤ ያስናፈቅሽኝ ያስወደድሽኝ ያስመኘሽኝ 'ኔን ከ'ኔ ያዋሃድሽኝ ያነጋሽኝ ያፈካሽኝ ጣፋጭ ምሽት ቀን የኾንሽኝ ፤ አንቺ እንደ ኾንሽ የህይዎት ቃና ... ከረሜላ ፤ ፡ አንቺን ሳይሽ ረዥም ዕድሜ እንደምናፍቅ ብዙ መኖር እንዲኖረኝ እንደምመኝ ፤ ድምፅሽ ከጆሮዬ ስር እንዳይበርድ ምስልሽ ከውስጤ እንዳይፋቅ ቶሎ ቶሎ እንደማስብሽ ነይ'ንጅ ልይሽ ልሳምሽ ልደባብስሽ እንደምልሽ ፤ ተከፍዬ ተሰንጥቄ ቢታይብኝ የደበቅኹት ዘር ዘርቼ አለምልሜ በልቤ እርሻ ያበቀልኩት ያንቺ ፍቅር እንደኾነ ሰው አድርጎ 'ሚያራምደኝ በሌት በቀን አሳስቆ ከመኖር ጋር ያላመደኝ እንደ ትኩስ ለብላቢ ቁስል ደጋግሜ 'ማስተውልሽ የምታምሚኝ... በህመምሽ የምታሰክሪኝ ፤ አምመሽኝ መኖሬን የምትነግሪኝ ! አንቺ እንደኾንሽ የዕድሜ ቁስል የማትደርቂ የማትድኚ እርሺኝ ቢሉሽ የማትረሺ ፤ ቆይ እኔ ስንቴ ልንገርሽ እሺ !? #ቴዎድሮስ_ካሳ @ethiopianye
إظهار الكل...
7
.. ለገላዋ እራፊ ፡  ብጣሽ አልገዛሁም፤ እረዥም ታሪኳን ፡  ቁጭ ብዬ አልሰማሁም ምኞት ፍላጎቷን ፡  ለይቼ አላወኩም የእግሯን ወለምታ ፡ አሽቼ አላዳንኩም፤ አሞሌ ጭንቀቷን ፡ በሳቅ አላሟሟው፤ ያመቃትን ስቃይ  ፡ ጠጋ ብዬ አልሰማው ፡ ከድርብርብ ውጥረት አስሮ ከደበቃት፤ ሽሮ ለመላቀቅ  ፡ ቀልዴ ለሚበቃት ማድያት ሽፍታ  ፡ ሲያጨላልም መልኳን፤ ተራራ ሆኖብኝ  ፥ "ምነው?" ማለት እንኳን ፈገግታ እድሜዋን ፡ ጊዜ ሲከረክም፤ የትም እንደማትሄድ ፡ የኔን ብቻ ሳክም ለእንስፍስፍ አንጀቷ ፡ ላይሆን መቀነቻ ወኔዬም ፣ ጀብዱዬም ፡ "ወዳታለው" ብቻ። ይቅርታ.. እማ። @ethiopianye @ethiopianye
إظهار الكل...
💔 7
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.