cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Land Related Laws(Ethiopia)መሬትና መሬት ነክ ህጎች በኢትዮጵያ

This channel helps to access land related laws in Ethiopia!! ከመሬትና መሬት ነክ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችንና የህግ ማዕቀፎችን በመወያየት ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን ማቃለልና ግንዛቤ መፍጠር ነው፡፡ መልዕክት መቀበያ፡http://t.me/landinfo_bot ለበለጠ መረጃ: 0918712839 ላይ ይደውሉ ።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
518
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በጣም አሳፍሪና አሳዛኝ ድርጊት አንድን የ9 ዓመት ህፃን ለሁለት ከደፈሩ በኃላ አፍኖ መግደል። ይህ የተፈፀመው ባህርዳር ላይ ነው። እባካችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን ከአውሬ ወንዶች ጠብቁ። ሴት ህፃናት ብቻ ሳይሆን ወንድ ህፃናትን የዚህ ጥቃት ሰለባ ናቸውና ህብረተሰቡ አካባቢውን ይጠብቅ። ልጆች ጨዋታ ላይ ሲሆኑ የልጆች ወላጆች በተራም ቢሆን ልጆቹ ጨዋታ ቦታ ላይ በመገኘት ጥበቃ በማድረግ ከዚህ አሳዛኝና ዘግናኝ ድርጊት መጠበቅ ይቻላል። የህፃኗን ነፍስ ፈጣሪ በገነት ያሳርፍልን መልዕክቴ ነው ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን መልካም ምሽት
إظهار الكل...
00:55
Video unavailableShow in Telegram
የjackMa ምክር በቲክቶክ እየሰማው የሚገርም ምክር ነው። የሚለውን ምክር በገባኝ አግባብ @ከ20 እስከ 30 ዓመት እድሜህ ጥሩ አለቃ ያስፈልግሃል ምክንያቱም ከጥሩ አለቃ ብዙ ነገሮችን ትማራለህ ። የወደፊት ህይወትህ የሚሆን ልምድና እውቀት ትወስዳለህ ። @ከ30-40 ባለው እድሜህ ስራዎችን በራስህ ለመስራት ሞክር @40-50 ባለው እድሜህ 20 ዓመት የሰበሰብከውን ልምድና ተሞክሮ ተጠቅመህ መልካምና ጥሩ ነገሮችን ስራ @ከ50- 60 ዓመት ብዙውን ግዜህን ወጣቶችን በማገዝ አሳልፈው። ምክንያቱም እውቀት ከልምድ ጋር አካብተሃል ለማለት ነው። @ከ60 ዓመት በኋላ ብዙውን ግዜ ከልጅ ልጆችህ ጋር አሳልፍ። መልካም ምሽት!!
إظهار الكل...
4.95 MB
በአማራ ክልል 668 ከተሞች በመዋቅራዊ ፕላን እየተመሩ ነው ተባለ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 668 ከተሞች በፕላን የሚመሩ እንዲሆኑ መደረጉን የክልሉ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ በሰላም ይመኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ በአማራ ክልል ከሚገኙ 683 ከተሞች ውስጥ 668 ከተሞች በፕላን የሚመሩ ከተሞች እንዲሆኑ ተደርጓል። አንድን ከተማ፤ ከተማ የሚያሰኘው በፕላን መመራቱ ነው ያሉት ሀላፊው÷ የከተሞችን ፕላን መነሻ በማድረግ ሌሎች የከተማ ልማት ስራዎችን ማከናወን እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ በተለይም ከተሞችን በፕላን መምራት ከተሞቹ ውብ፣ ጽዱና ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ እንደሚያደርግም ጠቅሰዋል፡፡ የከተማ ፕላን አንድ ጊዜ ተዘጋጅቶ የሚያበቃ አለመሆኑን በመጥቀስም እንደየከተሞቹ ባህሪ በ10 አመት ወይም በ20 አመት እንደሚከለስም አስረድተዋል፡፡ ለአብነትም በክልሉ የባህር ዳር ከተማን የ30 አመት እጣ ፋንታ እንዲወስን ተደርጎ ካለፈው አመት ጀምሮ የተተገበረ መዋቅራዊ ፕላን ተጠናቆ ወደ ትግበራ መገባቱን አስታውሰዋል፡፡ በተለይ የትላልቅ ከተሞች ፕላን ሲዘጋጅ የሌሎች ሀገራትን እንዲሁም በኢትዮጵያ የተሻሉ ከተሞችን ተሞክሮ ተወስዶ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል፡፡ ሁሉም ከተሞች ፕላናቸውን ለመተግበር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልጸው÷ የከተማ ፕላን ትግበራ ሂደትን የሚፈታተኑ ጉዳዮች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡ ሕገ ወጥ ግንባታዎች፣ ሕገ ወጥ የመሬት ወረራ እንዲሁም ከግንባታ ዲዛይን ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች የከተማ ፕላን ተግባራዊ እንዳይሆን የሚፈታተኑ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል፡፡ ቢሮው በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ችግሮች የሚፈቱበትን አሰራር በመዘርጋት እየሰራ እንደሚገኝም ሀላፊው አመላክተዋል፡፡ በሌላ በኩል አዳዲስ ፕላን ያልተሰራላቸው ከተሞችን በማጠናቀቅ ፕላን የሌለው ከተማ በክልሉ እንዳይኖር ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቅሰው÷የከተማ ፕላን በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ህዝቡ በንቃት እንዲሳተፍ አሳስበዋል፡፡ በየሻምበል ምሕረት
إظهار الكل...
00:30
Video unavailableShow in Telegram
እድገታቸውን ከየትም አላመጡትም!! ከስራ፣ከታታሪነትና ስነ ምግባር ነው!!
إظهار الكل...
11.58 MB
ለቸኮለ! ረቡዕ ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች የአዲስ አበባ አስተዳደር ለመኖሪያ ቤት ግንባታ በአጋርነት ለመስራት የመረጣቸው የግል ሪል ስቴት አልሚዎች ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሊጀምሩ መኾኑን ሪፖርተር ዘግቧል። አስተዳደሩ በቀረጸው 70/30 የመንግሥትና የግል አጋርነት የቤት ግንባታ መርሃ ግብር እንዲሳተፉ የመረጣቸው 68 ሪል ስቴት አልሚዎች ናቸው። መኖሪያ ቤቶቹን ለመገንባት ከተመረጡት መካከል፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ፍሊንትስቶን ሆምስና ጊፍት ሪል ስቴት እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል። የከተማ አስተዳደሩ ድርሻ ከሊዝ ነጻ የኾነ የመኖሪያ ቤት መገንቢያ መሬት ማቅረብ ሲኾን፣ አልሚዎቹ ደሞ ቤቶቹን ገንብተው ማጠናቀቅና 30 በመቶውን ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከብ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል።[ዋዜማ]
إظهار الكل...
ለተነሽ አርሶ አደሮች የሚሰጠው ትክ ቦታ የድልድል ስራው ተጠናቆ የብሎክ እጣ እያወጡ መሆኑ ተገለፀ። ሀምሌ 18/2015 (ባህርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን) በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ለቤት ማህበር ቦታ ለተወሰደባቸው ተነሽ አርሶ አደሮች ትክ ቦታ ለመስጠት የተጀመረው የሽንሸና ተግባር ተጠናቆ የብሎክ እጣ የማስወጣት እና ቦታቸውን የማስረከብ ስራ መሰራቱን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይለየሱስ ፀጋየ ገልፀዋል። እንደ አቶ ኃይለየሱስ ፀጋየ ገለፃ ከተማ አስተዳደሩ ለማህበር ቤት ለመስጠት በተሸነሸኑ 3 ሳይቶች ማለትም በዘንዘልማ ፣ በአርሴማና ገድሩ ላይ ለሚነሱ 216 ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ከሚነሱበት አካባቢ ሳይርቁ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራቸው ሳይቃወስ በህግ የተወሰነላቸውን የ500 ካሬ ቦታ የሽንሸናና ብሎክ የማሰር ስራውን በማጠናቀቅ እጣ በማስወጣት ርክክብ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል። ተነሺ አርሶ አደሮች በበኩላቸው ቦታው ተለክቶ እንዲነሱ በተወሰነበት ጊዜ ባለመነሳታቸው ቅር ተሰኝተው የቆዩ ቢሆንም እንሆ በአሁኑ ወቅት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ባልራቀ መልኩ የሚገባቸውን ቦታ እያገኙ መሆኑንና በተለይም ቋጥኝና ገደላማ ቦታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ድልድል በመሰራቱ መደሰታቸውን ገልፀዋል። https://youtube.com/@bahirdarcitycommunicationo1028
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በዚህ ተቋም የነበረው የህዝብ ጩህት በጣም ከፍተኛ ነበር። ሰራተኞችም ሊፈተሹ ይገባል። #NewsAlert የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣናቸው ተነሱ። የኢሚግሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩህተስፋ ሙልጌታን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ም/ዳይሬክተሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ዋዜማ ሰምታለች:: በተያያዘ ዜና ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል። አዲሷ ተሿሚ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ከዚህ ቀደም የቱሪዝም ሚንስትር ዲዔታ ፣ በውጪ ጉዳይ ሚር የዲያስፖራ አገልግሎትና በውጪ ሀገር በዲፕሎማቲክ ሚስዮን ውስጥ ይሰሩ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🎯 #የኢትዮጵያ መሬት ስፋት ከሀገራት ጋር ሲነፃፀር ❓ እንግሊዝ + ጀርመን + ጣልያን + ጃፓን #ኢትዮጵያ ላይ አይደርሱም 🇪🇹 #ኢትዮጰያ #Ethiopia መልካም ምሽት 🙏 #JOIN US 👉 https://bit.ly/38jVJkC #JOIN US 👉 https://bit.ly/38jVJkC
إظهار الكل...
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በ6ኛው ዙር፣2ተኛ ዓመት ፣6ተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት የከተማና መሰረተ ልማት ዘርፍ ሪፖርት በ2015 በጀት ዓመት ከልማት እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ የመልካም አስተዳደር ችግር መፍቻ እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር በመግባት ከተለዩ 570 የመልካም አስተዳደር ችግሮች ውስጥ 433 መፈታታቸውን ተናግረዋል። በዞንና በከተማ ደረጃ ከመሬት ይዞታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ 21 ሺ የሚደርሱ ጉዳዮች እና ከግንባታ ኘሮጀክቶች አስተዳደር ጋር የተያያዙ 1 ሺ ጉዳዮች ምላሽ መሰጠቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ገልፀዋል ፡፡ 135 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች፣ 80 የአገልግሎት ዘርፍ ማስፋፊያ ጥያቄዎች እና 21 የአምልኮ ቦታ ጥያቄዎች ውሳኔ መሰጠቱን፤ በ84 ከተሞች በስታንዳርድ የሚለካ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን፤ የሌብነትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በተነሳባቸው አመራሮች እና ባለሙያዎች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ይልቃል ቀጥለውም ከመሰረተ ልማት፣ ከመኖሪያ ቤትና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የከተሞችን የፋይናንስ አቅም ማሳደግ ወሳኝ ተግባር ተደርጎ መሰራቱን ፤በ2,373 የቤት ስራ ማህበራት ለ45,896 ተጠቃሚዎች 1.43 ሺህ ሄ/ር መሬት ማስተላለፍ መቻሉን፤ በበጀት ዓመቱ 81 ሺ የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የመኖሪያ ቤት ችግር ለማቃለል ታቅዶ በሪል ስቴት 145፣ በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማኀበራት 17,700፣ በግለሰቦች 15,763፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 1,353 በጠቅላላው 34,961 ቤቶች መገንባታቸውን አንስተዋል ፡፡ በከተማ ልማት ስራዎች የሚስተዋሉ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል እና የተሳለጠ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል ፡፡ መረጃው የክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ ነው!
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.