cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Wazema Media / Radio

Wazema Radio other contents are available either in our website/social media or FM radio stations in Ethiopia. www.wazemaradio.com

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
39 121
المشتركون
+11224 ساعات
+6027 أيام
+2 74230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ለቸኮለ! ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሐካን ፊዳን፣ ቱርክ በኢትዮጵያ እና ሱማሊያ መካከል ሦስተኛውን ዙር ንግግር ከመጀመራ በፊት ከአገራቱ ጋር የተናጥል ውይይት ማድረግ እንደምትፈልግ ተናግረዋል። ፊዳን፣ ከሁለቱ አገራት ጋር በተናጥል መነጋገር የፈለጉት፣ አገራቱ በባሕር በር ዙሪያ የገቡበትን ውዝግብ በማጥበብ እንደኾነ ገልጸዋል። በቱርክ አሸማጋይነት አንካራ ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው ሦስተኛው የሁለቱ አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ቀጥተኛ ያልሆነ ንግግር በይፋ ባልተገለጠ ምክንያት እንደተሰረዘ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ፣ በኹለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ፣ በቱርክ አሸማጋይነት የተካሄዱት ሁለት ቀጥተኛ ያልኾኑ ንግግሮች ውጤት አላመጡም። 2፤ በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር መቀመጫ በኾነችው ደባርቅ ከተማ በሳምንቱ መጀመሪያ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ውጊያ በትንሹ 20 ያህል ሰዎች እንደተገደሉ አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ነግረውኛል ሲል የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል። ባለሥልጣኑ አብዛኞቹ ሟቾች ሰላማዊ ሰዎች መኾናቸውን እንደገለጡ ዘገባው አመልክቷል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የደባርቅ ሆስፒታል ምንጮች፣ በተኩስ ልውውጡ በትንሹ 10 ሰዎች እንደተገደሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የሆስፒታሉ ምንጮች፣ 35 ያህል የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል ተብሏል። 3፤ በአማራ ክልል ለ2017 ዓ፣ም የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 7 ሚሊዮን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን የተመዘገቡት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተማሪዎች (21 በመቶዎቹ) ብቻ ናቸው። ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት፣ ባለፈው ዓመት ተዘግተው የከረሙ በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ለዘንድሮው የትምህርት ዘመንም እስካኹን ምዝገባ አላከናወኑም። የአንዳንድ ወረዳ የትምህርት ጽሕፈት ቤቶች፣ በገጠር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለማስጀመር ሕዝቡ የፋኖ ታጣቂዎችን እንዲያስፈቅድ መጠየቃቸውን ዋዜማ ተረድታለች። የክልሉ መንግሥት በገጠር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለማስጀመር ፈተና የኾነበት፣ ታጣቂዎች መምህራንን ስለሚያግቱ እንደኾነ ታውቋል። መምህራን ምዝገባ ለማከናወን በሞከሩባቸው አካባቢዎች፣ ድብደባና እገታ የተፈጸመባቸው መምህራን መኖራቸውን ዋዜማ ሰምታለች። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና፣ በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር፣ ስናን ወረዳ ውስጥ በምትገኝ ረቡዕ ገበያ በተባለች ከተማ ታጣቂዎች ትናንት ባደረሱት ጥቃት ኹለት መምህራን "በአሰቃቂ ኹኔታ" እንደተገደሉ አስታውቋል። በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት፣ መምህር ጌታ እንዳለ እና መምህር አትንኩት ኹነኛው ሲሆኑ የረቡዕ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት መምህራን እንደነበሩ የዞኑ አስተዳደር ገልጧል። ታጣቂዎቹ በመምህራኑ ላይ ግድያ የፈጸሙት፣ ትምህርት ቤቱ በ2017 ዓ፣ም የትምህርት ዘመን የማስተማር ማስተማር ሂደት እንዲጀምር እንቅስቃሴ አድርጋችኋል በማለት እንደኾነ ጠቅሷል። የዞኑ አስተዳደር፣ በንጹሃን መምህራን ላይ ግድያ መፈጸምና ፍርሃት እንዲሰማቸው ማድረግ ለሕዝብ ካለማሰብ የሚመነጭ "እኩይ ድርጊት ነው" በማለት አውግዟል። 4፤ የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን፣ ከሱዳኑ ጦርነት ሽሽተው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሱዳናዊያን ስደተኞችና የኢትዮጵያዊያን ተመላሾች ብዛት 60 ሺሕ 61 መድረሱን ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። ከጥር ወዲህ ብቻ 17 ሺሕ 112 ሱዳናዊያን ስደተኞችና ተመላሾች በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ኮሚሽኑ ገልጧል። ከሱዳኑ ጦርነት መቀስቀስ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት መካከል፣ 11 ሺሕ 771 ያህሉ ኢትዮጵያዊያን ተመላሾች ናቸው ተብሏል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል ከገቡት ሱዳናዊያን ስደተኞች መካከል፣ ከሐምሌ ጀምሮ 3 ሺሕ 500 ያህሉ ወደ አዲሱ ኡራ መጠለያ የተዛወሩ ሲኾን፣ በአማራ ክልል ውስጥ ደሞ ኩመር እና አውላላ መጠለያዎች ውስጥ ተጠልለው የነበሩ 7 ሺሕ ያህል ስደተኞች ወደ አዲሱ አፍጥጥ መጠለያ እንደተዛወሩና ኩመር እና አውላላ መጠለያዎችም ሙሉ በሙሉ እንደተዘጉ የድርጅቱ መረጃ አመልክቷል። 5፤ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሞሐመድ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ትናንት ያወጣውን መግለጫ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት ተችተዋል። ሙስጠፌ፣ ኦብነግን በስም ባይጠቅሱም፣ በአፍሪካ ቀንድ የጅዖፖለቲካ ክስተት በተፈጠረ ቁጥር አንድ ፓርቲ ሰማሁት ባለው ያልተጣራ መረጃ ላይ ተመስርቶ መግለጫ አውጥቷል በማለት ወቅሰዋል። ኦብነግ ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የሱማሌ ክልል ባንዲራን ለመቀየር እንዳቀደ ጭምጭምታ መስማቱን ጠቅሶ፣ ይህ ድርጊት እውን ከሆነ የሱማሌ ሕዝብን ማንነት ለማጥፋት ያለመ ይሆናል በማለት ተቃውሞውን ገልጦ ነበር። ኦብነግ፣ በኢትዮጵያ እና ሱማሊያ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ፣ የሱማሌ ክልል ሕዝብ ተጎጂ መኾን የለበትም በማለት አቋሙን መግለጡን ዋዜማ ትናንት መዘገቧ ይታወሳል። 7፤ ኢትዮ ቴሌኮም፣ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅዱ ለቴሌኮምና ለዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋፊያዎች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በጀት መመደቡን አስታውቋል። ኩባንያው በበጀት ዓመቱ፣ 1 ሺሕ 298 የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያዎችን እንደሚገነባም ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጧል። ኩባንያው የቴሌብር ደንበኞቹን ቁጥር በ15 ነጥብ 7 በመቶ ለመጨመርና 55 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን የገለጠው ኩባንያው፣ ከሃዋላ አገልግሎት የውጪ ምንዛሬ መጠኑን ወደ 282 ሚሊዮን ዶላር ለማሳደግ ማቀዱንም ጠቅሷል። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 40👏 3👎 1
ለቸኮለ ማለዳ! ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ የፋኖ ታጣቂዎች በደቡብ ጎንደር ዞን አምስት ወረዳዎችን እንደተቆጣጠሩ ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች ተረድታለች። ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና የወረዳና ቀበሌ አመራሮች ወረዳዎቹን ለቀው ከዞኑ ዋና መቀመጫ ደብረታቦር ገብተዋል። የፋኖ ታጣቂዎች ከጳጉሜ መጨረሻ ጀምሮ ባሉት ቀናት በተቆጣጠሯቸው ታች ጋይንት፣ እስቴ፣ አንዳቤት፣ መካነእየሱስ፣ ስማዳ እና ስዴ ሙጃ ወረዳዎች፣ የራሳቸውን አስተዳደራዊ መዋቅሮች የመዘርጋትና ግብር የመሰብሰብ ሙከራ እያደረጉ እንደኾነም ዋዜማ ሰምታለች። link- https://tinyurl.com/avw5rdu8 2፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከሕወሓት ጉባዔ ራሳቸውን ያገለሉ 16 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል የሚመሩት ቡድን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ መፈንቅለ ሥልጣን ለማድረግ አቅዷል በማለት ከሷል። የጌታቸው ቡድን ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ የደብረጺዮን ቡድን ሌሎችን ከፓርቲው የማሰናበት ሕጋዊ ሥልጣንም ኾነ ሞራል የለውም በማለትም የቡድኑ አባላት ከፓርቲው ስለመባረራቸው የተላለፈውን ውሳኔ አጣጥሏል። የደብረጺዮን ቡድን፣ በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳልተፈጸመ ጭምር በመካድ በትግራይ ሕዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደቶችን እየፈጸመ ይገኛል በማለት ይሄው ቡድን ወቅሷል። ቡድኑ፣ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት ለማስመለስ አደርገዋለሁ ባለው ፓለቲካዊ ድርድር፣ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ከጎኑ እንዲቆሙም ጥሪ አድርጓል። 3፤ በሶማሌ ክልል ዋርዴር ከተማ ውስጥ ባንድ መስጊድ ላይ ትናንት በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ ከነዋሪዎችና ባለሥልጣናት መስማቱን ጠቅሶ ቪኦኤ ዘግቧል። በጥቃቱ የተገደሉት፣ የእስልምና ሃይማኖት ተማሪዎች እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል። ጥቃቱን የፈጸሙት፣ የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው ግለሰቦች ናቸው በማለት የአካባቢው ባለሥልጣናት መናገራቸውንና በቅርቡ ባካባቢው ተከስቶ ከነበረ የጎሳ ግጭት ጋር የተያያዘ አይደለም የሚል እምነት እንዳላቸው መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። የክልሉ መንግሥት፣ በመስጊዱ ላይ ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃትና ሰዎች ተገድለዋል ስለመባሉ በይፋ ያለው ነገር የለም። 4፤ ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በ2016 የትምህርት ዘመን በተሰጠው የ12ኛ ክፍል አገር ዓቀፍ ፈተና ከ500 እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን አወዳድሮ ነጻ የትምህርት ዕድል ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል። ዩኒቨርሲቲው፣ 200 ተማሪዎችን ለመምረጥ የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥና ብቃትን፣ ብዝሃነትንና ፍትሃዊነትን ማዕከል አድርጎ ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን እንደሚቀበል ገልጧል። ዩኒቨርሲቲው ነጻ የትምህርት ዕድል ለሚሰጣቸው ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ጭምር እንደሚሰጥ አመልክቷል። 5፤ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ፣ እስራኤል በኃይል የያዘቻቸውን አካባቢዎች ባንድ ዓመት ውስጥ እንድትለቅ ትናንት በድምጽ ብልጫ ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ኢትዮጵያ ድምጸ ተዓቅቦ አድርጋለች። ጠቅላላ ጉባዔው ውሳኔውን ያሳለፈው፣ በ124 የድጋፍ ድምጽ ነው። አሜሪካን ጨምሮ 12 አገራት የተቃውሞ ድምጽ ሲያስመዘግቡ፣ 43 አገራት ደሞ ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል። እስራኤል በወረራው ሳቢያ በፍልስጤማዊያን ላይ ላደረሰችው ጉዳት ካሳ እንድትከፍል ጭምር ጠይቋል። በእስራኤል ወረራ ሥር የሚገኙት፣ ዌስት ባንክና ምሥራቅ እየሩሳሌም ናቸው። የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ አስገዳጅነት የለውም። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 88 12👎 7😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ከ2016 ዓ.ም ማብቂያ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ተረድታለች። የመንግስት ኃይሎች ለምን ከአካባቢው እንደወጡ በይፋ አልተናገሩም። አንብቡት-https://tinyurl.com/avw5rdu8 📷 FILE
إظهار الكل...
👍 14 14👏 3👎 2
Student.webp0.42 KB
*በአማራ ክልል ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 7 ሚሊዮን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን የተመዘገቡት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ ናቸው። *ዋዜማ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ባደረገችው ማጣራት በ2016 የትምህርት ዘመን ተዘግተው የከረሙ በርካታ ትምህርት ቤቶች ለዘንድሮው የትምህርት ዘመንም እስካሁን ምዝገባ አላከናወኑም። *ክልሉ ባጋጠመው የጸጥታ ችግር ምክንያት ባለፈው ዓመት የትምህርት ዘመን ከ4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ሙሉ ዓመቱን ሳይማሩ አሳልፈዋል። ዝርዝሩ ይኸው- https://tinyurl.com/y262w9uy 📷 Unicef
إظهار الكل...

👍 13😢 13👌 2😁 1
ለቸኮለ! ረቡዕ መስከረም 8/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ ኢጋድ፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በባሕር በር ውዝግብ ዙሪያ የገቡበትን ውጥረት በድርድር ለመፍታት ጥረት እንደጀመሩ ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል። ኢጋድ ሁለቱ አገሮች ውጥረቱን በውይይት እንዲፈቱ ለማስቻል ከተጀመረው ጥረት ጀርባ፣ የጂቡቲ፣ የኬንያና የአሜሪካ መንግሥታት ድጋፍ እንዳለ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ ሰሞኑን ወደ ሞቃዲሾ አቅንተው ከሶማሊያ ባለሥልጣናት ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ከሴማሌላንድ ጋር በተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በድርድር ለመፍታት ኢጋድ አዲስ ጥረት የጀመረው፣ በቱርክ አሸማጋይነት የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች አንካራ ውስጥ በሁለት ዙሮች ያደረጓቸው ቀጥተኛ ያልኾኑ ንግግሮች ውጤት ሳያስገኙ መቅረታቸውን ተከትሎ ነው። ትናንት አንካራ ውስጥ ሦስተኛው ዙር ንግግር ይጀመራል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢኾንም፣ ቱርክ በይፋ ባልገለጠችው ምክንያት ንግግሩ ሳይጀመር ቀርቷል። 2፤ በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ እና ዳባት ከተሞ በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ውጊያ ዘጠኝ ሰዎች እንደተገደሉ መስማቱን ጠቅሶ እንግሊዝኛው ቪኦኤ ጣቢያ ዘግቧል። ደባርቅ ሆስፒታል ብቻ ሕጻናትንና ተዋጊዎችን ጨምሮ 30 ያህል ሰዎች ቁስለኞችን ማከሙን እንደተናገረ ዘገባው አመልክቷል። በውጊያው ሳቢያ በሁለቱ ከተሞች የንግድ መደብሮችና የመንግሥት ቢሮዎች ሰኞ እና ማክሰኞ'ለት ተዘግተው እንደዋሉ ተገልጧል። በጎንደሩ ውጊያ በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ከነዋሪዎች መስማቱን ጠቅሶ የዘገበው ደሞ ዶቸቨለ ነው። አዘዞ አካባቢ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሦስት ሰዎች እንዲኹም ቡልኮ በተባለ አካባቢ በከባድ መሳሪያ ተኩስ ሁለት ሕጻናት መገደላቸውን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። 3፤ ኦብነግ፣ በኢትዮጵያና ሱማሊያ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ የሶማሌ ክልል ሕዝብ ተጎጂ መኾን የለበትም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። በሶማሌ ክልል ባሁኑ ወቅት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተበራክቷል ያለው ኦብነግ፣ ክልሉ "በወታደራዊ አስተዳደር ሥር" ሊወድቅ እንደሚችልና ይህም የሶማሌ ሕዝብን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደሚሸረሽር ገልጧል። ኦብነግ፣ ፌደራል መንግሥቱ በሶማሌ ክልል ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች በሕገመንግሥቱ በአንቀጽ 39 የተደነገገውን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚጥሱ ናቸው በማለትም ከሷል።  4፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ ፌደራል መንግሥቱ የትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ ያገዱ እንቅፋቶችን እንዲቀርፍ ዛሬ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክን መቀሌ ውስጥ ባነጋገሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ጠይቀዋል። ጌታቸው የኤርትራ ሠራዊት በምሥራቃዊ ትግራይ በተለይ በኢሮብ ወረዳ እስካሁን መኖሩ፣ በኢሮብ ብሄረሰብ ሕልውና ላይ አደጋ ደቅኗል ማለታቸውንም የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተንና መልሶ የማዋሃድ ጉዳይ፣ መሬት ላይ ባለው የጸጥታ ኹኔታ ሊወሰን ይገባዋል በማለት ጌታቸው እንዳሳሰቡ ዘገባው አመልክቷል። አምባሳደር ላሜክ፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ባግባቡ ሊተገበር እንደሚገባው አሳስበዋል ተብሏል። 5፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ2013 ዓ፣ም እስከ ጥር 2016 ዓ፣ም ባሉት ዓመታት 144 የድሮን ጥቃቶች እንደተተፈጸሙ ማረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል። የፖለቲካ ግጭቶችንና ተቃውሞዎችን የሚመዘግበው "አርምድ ኮንፍሊክት ሎኬሽን ኤንድ ኤቨንት ዳታ" (አክሌድ) የተባለው ዓለማቀፍ ተቋም፣ በአማራ ክልል እስከ ጥር 2016 ዓ፣ም ድረስ 49 የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙ መመዝገቡን ዘገባው ጠቅሷል። በኦሮሚያ ክልል ደሞ 28 የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙ የአክሌድ መረጃ እንደሚያሳይ ዘገባው አመልክቷል። በአክሌድ መረጃ መሠረት፣ ከታኅሳስ 2013 ዓ፣ም እስከ የካቲት 2016 ዓ፣ም ባሉት ጊዜያት 139 የተረጋገጡ የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙ እንደሚያመለክት ተገልጧል። መንግሥት፣ በድሮን ጥቃት "ጽንፈኛ ኃይሎችን' እንጂ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ አላደረኩም በማለት ቀደም ሲል ማስተባበሉ አይዘነጋም። 6፤ ለበርካታ ወራት በእስር ላይ የቆዩት የበይነ መረብ ጋዜጠኞቹ በላይ ማናዬ እና በቃሉ አላምረው ባለፈው ሳምንት ከአገር መሰደዳቸው ተሰምቷል። ጋዜጠኞቹ የመሰደድ የተገደዱት፣ የመንግሥት የጸጥታ አባላት “ለሕይወታቸው የሚያሰጋ" ማስጠንቀቂያ እንደሰጧቸው እና "ክትትል" እንደሚያደርጉባቸው በመግለጽ እንደኾነ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። በአማራ ክልል ታውጆ ከነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ለእስር የተዳረጉት በላይ እና በቃሉ፣ ከእስር የተፈቱት ከሦስት ወራት በፊት ነበር። "አልፋ ሚዲያ” የተሰኘ የበይነ መረብ ጣቢያ መስራችና አዘጋጅ የኾነው በቃሉ ለዘጠኝ ወራት አዋሽ አርባ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ውስጥ ታስሮ የነበረ ሲኾን፣ የ"ኢትዮ ኒውስ” የበይነ መረብ ጣቢያ መስራችና አዘጋጅ በላይም በተመሳሳይ ቦታ ለሰባት ወራት እንደታሠረ ይታወሳል። 7፤ የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት አመራሮች በሕዝቡ ላይ ለምን የቦሮ ፓርቲን ዕጩዎች በሰኔው ምርጫ መረጣችሁ በማለት ዛቻና ማስፈራሪያ ሰንዝረዋል በማለት ከሷል። ፓርቲው፣ የክልሉ መንግሥት ለዚህ ድርጊት ሕዝቡን ባስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል። በአመራሮቹ፣ በአባላቱና ደጋፊዎቹ ላይ እስራትና ድብደባ እንደሚፈጸምባቸውና በሕገወጥ መንገድ ከሥራ እንደሚዛወሩ የገለጠው ፓርቲው፣ የክልሉ መንግሥት አካሄዱን እንዲያርም አሳስቧል፡፡ የክልሉ መንግሥት ድርጊቶቹን ካላረመ፣ ከመንግሥት ጋር አብሮ ለመስራት ያሳለፈውን ውሳኔ በድጋሚ ለማጤን እንደሚገደድ ፓርቲው አስጠንቅቋል። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 87 8😍 1
ለቸኮለ ማለዳ! ረቡዕ መስከረም 8/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ በመንግሥት ወታደሮችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተቀሰቀሰው ውጊያ ሳቢያ፣ በጎንደርና ባሕርዳር እንዲሁም በጎንደር እና በወረዳ ከተሞች መካከል የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ዋዜማ ሰምታለች። ኹለቱ ወገኖች ሰኞ'ለት በሰሜን ጎንደር ዞን ባካሄዱት ውጊያ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ላጭር ጊዜ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና መቀመጫ ደባርቅ ከተማን ተቆጣጥረው እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል። በውጊያው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች መረዳት ችላለች። 2፤ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል "ኒው ሆሪዞን" ከተባለ የበይነ መረብ ጣቢያ ጋር ሰሞኑን ያደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በሰሜኑ ጦርነት በተገደሉ ሰዎች ዙሪያ የሰጡት አስተያየት ከቁጥር ጋር የተያያዘ ውዥንብር እንደፈጠረ መረዳታቸውን ገልጸዋል። ደብረጺዮን በቃለ ምልልሳቸው፣ በጦርነቱ 1 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል የሚባለው ነገር በጥናት ላይ ያልተመሠረተና ማስረጃ የሌለው አመራሩን ተጠያቂ ለማድረግ ሲባል ብቻ የሚነገር ነገር እንደኾነ ተናግረው ነበር። ኾኖም ደብረጺዮን ትናንት ምሽት ላይ በሕወሓት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ በኩል በሰጡት ማብራሪያ፣ በእያንዳንዱ የትግራይ ቤተሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተፈጸመ በመግለጽ የወንጀሉ ሰለባዎች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ ይችላል ብለዋል። የዘር ማጥፋት ወንጀሉ አኹንም ቀጥሏል ያሉት ደብረጺዮን፣ በውስጣችን የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግና በዘር ማጥፋት ወንጀሉ ተጠያቂ መኾን ያለባቸው ሌሎች አካላት እንዳይጠየቁ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ በማለት ከሰዋል። ደብረጺዮን በቃለ ምልልሱ ላይ ማስረዳት የፈለጉት የእነዚህን በስም ያልጠቀሷቸው አካላት ድርጊት እንጂ በዘር ማጥፋት ወንጀሉ የጠፋውን የሰው ሕይወት ብዛት አይደለም በማለት አስተባብለዋል። 3፤ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሁለት የመንግሥት ሠራተኞች እንደተገደሉና ሌላ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ እንደቆሰለ ዶቸቨለ ዘግቧል። ሠራተኞቹ ጥይት የተተኮሰባቸው፣ በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት፣ ሦስቱ ግለሰቦች ከኪረሙ ወረዳ ወደ ስሬዶሮ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደኾነ መስማቱን የጠቆመው ዘገባው፣ ጥቃቱን ያደረሱት የፋኖ ታጣቂዎች ናቸው በማለት የአካባቢው ምንጮች መናገራቸውን ጠቅሷል። 4፤ ብሄራዊ ባንክ፣ "ሰን ፔይ ሶሊዩሽን" የተሰኘውን የፋይናንስ አስተዳደር እና ክፍያ ሥርዓት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ፍቃድ እንደሠረዘ ሸጋ ሜዲያ ዘግቧል። ኩባንያው ከሁለት ዓመት በፊት የፋይናንስ ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት ከባንኩ ፍቃድ ወስዶ ነበር። ባንኩ የኩባንያውን ፍቃድ የሠረዘው፣ ኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ መሾም አለመቻሉን፣ የንግድ ፍቃዱን አለማሳደሱንና የአክሲዮን ባለድርሻዎች ስብሰባ ማካሄድ አለመቻሉን በመጥቀስ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። የኩባንያውን ከፍተኛ ድርሻ የያዘው፣ የታዋቂው የሪል እስቴትና ኮንስትራክሽን ኢንቨስትመንት ባለሃብት የሳሙዔል ታፈሠ ልጅ ዮናስ ሳሙዔል እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። 5፤ ቱርክ፣ በሱማሊያ ባሕር ዳርቻ የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ለመጀመር አንዲት መርከብ በቀጣዩ ወር ወደ ሱማሊያ የባሕር ዳርቻ ልትልክ መኾኗን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ቱርክ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፈላጊ መርከቧን ደኅንነት የሚጠብቁ ቢያንስ ሁለት የባሕር ኃይል መርከቦችን ጭምር በሱማሊያ የውቅያኖስ ጠረፍ ለማሠማራት እንዳቀደች ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ቱርክ፣ እያንዳንዳቸው አምስት ሺሕ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ባላቸው ሦስት ቦታዎች ላይ የጋዝ ፍለጋ እንድትጀምር ከሱማሊያ ፍቃድ ማግኘቷን ገልጣለች። ቱርክና ሱማሊያ ባለፈው መጋቢት የጋዝ ክፍፍል ስምምነት ተፈራርመዋል። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 97👎 4 1
ለቸኮለ! ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከትናንት ሌሊት ጀምሮ እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአገር ውስጥ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ዛሬ አዘዞ፣ ቀበሌ 18፣ አዲስ ዓለም፣ አይራ እና ዓለም በር በተባሉ የከተማዋ አካባቢዎች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ መዋሉን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በውጊያው በርካታ ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉም ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በተመሳሳይ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ ደባርቅ፣ በዳባት ወረዳ በዳባት እና በወገራ ወረዳ በአምባ ጊዮርጊስ ከተሞች፣ ዛሬን ጨምሮ ሰሞኑን ውጊያ ሲደረግ መሰንበቱና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪሎች መገደላቸው ተዘግቧል። 2፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ከቦሌ ወደ መቀሌ ሊበር በነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ሁከት በመፍጠር ክስ የተመሠረተባቸው ስድስት ተከሳሾች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን የአገር ውስጥ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ዓቃቤ ሕግ በግለሰቦቹ ላይ የመሠረታቸው ክሶች፣ ከአውሮፕላን አንወርድም በማለት አውሮፕላኑን ያለአግባብ የመያዝ ወንጀል፣ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ ግዴታውን እንዳይወጣ ማስተጓጎልና አለመታዘዝ የሚሉ ናቸው፡፡ አንደኛ ተከሳሽ ዮሃንስ ዳንዔል፣ የአየር መንገዱን መልካም ስም በሚያጎድፍ መልኩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በኮምፒውተር ሥርዓት አማካኝነት አሠራጭቷል የሚል ክስ ጭምር እንደተመሠረተበት ይታወሳል። ተከሳሾቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች ተደራራቢ መኾናቸውን ጠቅሶ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ፣ ክሱን ጥቅምት 4 ለመመልከት ቀጠሮ እንደሰጠ ተገልጧል። 3፤ ፖለቲከኛ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ በ74 ዓመታቸው ዛሬ ጧት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ፕሮፌሰር በየነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ ዓመታት በባዮሎጂ አስተማሪነትና በባዮሎጂ ትምህርት ክፍል ሊቀመንበርነት ያገለገሉ ሲኾን፣ በዘርፉ በርካታ የምርምር ሥራዎችን እንደሠሩ ይነገርላቸዋል። ፕሮፌሰር በየነ፣ በሽግግር መንግሥቱ ዘመን ምክትል የትምህርት ሚንስትር ኾነውም አገልግለዋል። በፖለቲካው ዓለም የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረትን እና "መድረክ" የተባለውን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ለዓመታት የመሩት ፕሮፌሰር በየነ፣ እስከ'ለተ ሞታቸው ድረስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን በሊቀመንበርነት የመሩና ለዓመታት በሽግግር መንግሥቱ ምክር ቤትና በፌደራሉ ፓርላማ አባል የነበሩ ናቸው። ፕሮፌሰር በየነ፣ እስከ ሕልፈታቸው ድረስ የመንግሥታዊው ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ነበሩ። 4፤ የብር ምንዛሬ ከዶላርና ሌሎች የውጭ ምንዛሬዎች አንጻር በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ደረጃ መዳከሙን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምንዛሬ መረጃ አመልክቷል። ንግድ ባንክ ዛሬ አንድ ዶላር እየገዛበት ያለው ዋጋ፣ ወደ 112 ብር ከ39 ሳንቲም ያሻቀበ ሲኾን፣ የመሸጫ ዋጋው ደሞ ወደ 124 ብር ከ75 ሳንቲም ከፍ ብሏል። ባንኩ አንድን ዶላር ዛሬ የሚገዛበት ዋጋ ከትናንቱ ጋር ሲነጻጸር ከ4 ብር በላይ ጭማሪ ያሳየ ሲኾን፣ መሸጫው ደሞ 5 ብር ጭማሪ አሳይቷል። አንድ ፓውንድ ዛሬ በ141 ብር ከ63 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ157 ብር ከ94 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሚገኝም ባንኩ ገልጧል። በተመሳሳይ፣ አንድ ዩሮ በ125 ብር ከ01 ሳንቲም እየተገዛ፣ በ138 ብር ከ76 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል። 5፤ ደቡብ ሱዳን፣ ነዳጇን በፖርት ሱዳን በኩል ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንድትቀጥል ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ጀኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ዛሬ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው በሱዳኑ ጦርነት ጉዳት ደርሶበት፣ ደቡብ ሱዳን ላለፉት አራት ወራት ነዳጅ ለውጭ ገበያ ማቅረብ አልቻለችም። ከፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ለመወየት ትናንት ጁባ የገቡት ጀኔራል ቡርሃን፣ በነዳጅ ማስተላለፊያው ቧንቧ ላይ ሲደረግ የነበረው ጥገና ተጠናቋል በማለት ተናግረዋል። ሁለቱ መሪዎች ይህን ይበሉ እንጂ፣ ከፊሉ ቧንቧ የሚያልፈው የሱዳን ፈጥኖ ደራሹ ኃይል በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች እንደኾነ ይታወቃል። 6፤ ሜታ ኩባንያ፣ የሩሲያውን ቴሌቪዥን ጣቢያ "አር ቲ" "ሐሰተኛ መረጃ በማሠራጨት ያልተገባ ተጽዕኖ" ለመፍጠር ሲሞክር ቆይቷል በማለት ከፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አግዶታል። አሜሪካ፣ በሩሲያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኘው "አር ቲ" ለአንድ ተቋም 10 ሚሊዮን ዶላር ከፍሎ የሩሲያ መንግሥትን ድብቅ መልዕክቶች ለማስተላለፍ ሞክሯል፤ ጣቢያው የሩሲያ ስለላ ተቋም አካል ኾኗል በማለት ክስ አሰምታ ነበር። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 81 11👎 1😢 1👌 1😍 1
ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ የሚገኙ በርከት ያሉ ቦታዎችን አኹንም እንደተቆጣጠረ መኾኑን ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ካገኘችው መረጃ ተረድታለች። በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ኹለት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉና ሌሎች ኹለት ቀበሌዎች በከፊል በኤርትራ ይዞታ ሥር እንደሚገኙና የባንክ፣ ስልክና ትራንስፖርት አገልግሎቶች እንደተቋረጡ መኾኑ ታውቋል። በአራቱም ቀበሌዎች፣ 16 ሺሕ ሕዝብ የጤና አገልግሎት እንደማያገኝ ዋዜማ ሰምታለች። በኤርትራ ሥር ለመተዳደር ፍቃደኛ እንዲኾኑ ወይም አካባቢውን እንዲለቁ ምርጫ ከቀረበላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል፣ ወደ አዲግራት የመጡ መኖራቸውንም ምንጮች ተናግረዋል። የዛላንበሳ ከተማም ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ቁጥጥር ሥር ስትኾን፣ ከከተማዋ የተፈናቀሉ ነዋሪዎቿም ነጻ በኾነው ጉሎመሃዳ ወረዳ ውስጥ ተጠልለዋል ተብሏል። 2፤ ሕወሓት፣ ምክትል ሊቀመንበሩን ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 16 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ማባረሩንና ከድርጅታዊ ሃላፊነታቸውና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካላቸው ውክልና በሙሉ ማንሳቱን ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው አሰናብቻቸዋለሁ ያላቸውን አባላቱን በሙስና ወንጀል ጭምር እንደሚጠይቃቸው ገልጧል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ከፓርቲ አባልነት አባርሬያቸዋለሁ ያላቸው፣ ጌታቸው ረዳ፣ በየነ ምክሩ፣ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት፣ ሓጎስ ጎዲፈይ፣ ኣልማዝ ገ/ጻዲቅ፣ ረዳኢ ሓለፎም፣ ሰብለ ካሕሳይ፣ ኢሳያስ ታደሠ፣ ሰለሞን መዓሾ፣ ሺሻይ መረሳ፣ ገብረሂወት ገብረእግዜር፣ ርስቁ አለማው፣ ሃፍቱ ኪሮስ፣ ብርሃነ ገ/እየሱስ፣ ሩፋኤል ሽፋረ እና ነጋ አሠፋ ናቸው። የምርጫ ቦርድ እውቅና የሌለው ቢኾንም፣ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ በስም የተጠቀሱትን ግለሰቦች ከማዕክላዊ ኮሚቴ ቀደም ሲል ማገዱ ይታወሳል። 3፤ ግብጽ፣ ኤርትራን ከሕወሓት ጋር ለማስታረቅ በምትችልበት ኹኔታ ዙሪያ ከኤርትራ ጋር እየመከረች መኾኗን የኢምሬቶች ጋዜጣ ናሽናል ዘግቧል። ኤርትራ እና ግብጽ የወታደራዊ ትብብርና የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ አማራጮችን እየፈተሹ እንደኾነም ዘገባው ጠቅሷል። ሁለቱ አገራት ለመፈራረም ያስቡት ስምምነት፣ በቀይ ባሕር አካባቢ የመርከቦችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ርምጃዎችን መውሰድን ያካትታል ተብሏል። የግብጽ ደኅንነት ሚንስትር ጀኔራል ከማል አባስና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብደላቲ ሰሞኑን አሥመራ ውስጥ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። 4፤ ትሬድ ማርክ አፍሪካ የተሰኘው አሕጉራዊ ድርጅት፣ የኢትዮጵያን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን የቦርድ ሊቀመንበሩ አድርጎ ሰሞኑን ሾሟል። ኃይለማርያም የድርጅቱ የቦርድ ሊቀመንበር ኾነው የተሾሙት፣ ለቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት ነው። ትሬድ ማርክ አፍሪካ፣ በአፍሪካ አገራት መካከል፣ የንግድ ልውውጥና የወጪ ንግድ እንዲጨምር የሚሠራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። ኃይለማርያም ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት የተቀላቀሉት፣ ድርጅቱ በአገራት መካከል የሚደረግ የሸቀጦች ዝውውር የሚፈጀውን ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ስትራቴጂክ ግብ በያዘበት ወቅት ላይ ነው። 5፤ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጀኔራል ቡርሃን፣ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ለመነጋገር ትናንት ጁባ ገብተዋል። ጀኔራል ቡርሃንና ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገሩ የጁባ ባለሥልጣናት ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ደቡብ ሱዳን ውስጥ ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ይመለምላሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳለው ተመድ ገልጧል። ደቡብ ሱዳን፣ በሱዳኗ ፓርት ሱዳን በኩል የምታስወጣው ነዳጅ በጦርነቱ ሳቢያ ከተስተጓጎለ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 97 10😁 4👏 3😍 3👎 2
ለቸኮለ! ሰኞ መስከረም 6/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች 1፤ መንግሥትን እና የፋኖ ታጣቂዎችን ወደ ድርድር ለማምጣት የማመቻቸት ጥረት እያደረገ የሚገኘው በአማራ ክልል የተቋቋመው የሰላም ምክር ቤት፣ ዛሬ በአዲስ አበባ የካናዳ አምባሳደር ጆሿ ታባህ ጋር ተወያይቷል። ውይይቱ ሁለቱን ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ጫና እንዲፈጦር ምክር ቤቱ የጀመረው ጥረት አካል ነው። አምባሳደሩ፣ ካናዳ የአማራ ክልልን ሁኔታ በንቃት እንደምትከታተል በመግለጽ፣ የምክር ቤቱን ጥረት እንደሚደግፉ ገለጸዋል። 2፤ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በክልሉ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት አዲስ ሲቪል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ጠይቀዋል። በክልሉ ባሁኑ ወቅት የተፈጠረው ችግር ፖለቲካዊ መኾኑን የገለጡት ፓርቲዎቹ፣ ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ምክር ቤት ያለው ሁሉን አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ሲቋቋም ብቻ እንደኾነ ገልጸዋል። ይህንኑ ጥሪ ዛሬ ያቀረቡት፣ ባይቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ውድብ ናጽነት ትግራይ እና አረና፣ የክልሉ ጸጥታ ሃይሎች በፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነጻ በመኾን በአዲሱ ሲቪል አስተዳደር ሥር በሕግ የሚመሩ እንዲኾኑ ጠይቀዋል። የትግራይ ፖለቲከኞች ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ፣ የክልሉን ሕገመንግሥታዊ ወሰን በማስመለስ እንዲሁም የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ በመበተን እና መልሶ በማዋሃድ ዙሪያ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የደረሱባቸውን ስምምነቶች ለሕዝብ ግልጽ እንዲያደርጉና የስምምነቶቹን የእስካኹን አፈጻጸም ይፋ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። 3፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከመስከረም ወር ጀምሮ በመጪዎቹ ሦስት ወራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኪሎ ዋት እስከ 95 ብር ድረስ ጭማሪ እንደሚደረግበት አስታውቋል። ከተያዘው ዓመት ጀምሮ በሚደረገው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ታሪፍ ማሻሻያ መሠረት፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ እስከ 40 በመቶ ጭማሪ ይደረግበታል፡፡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የማመንጫ ታሪፍ ላይ ቀደሞ ይከፍሉት ከነበረው ሂሳብ በኪሎ ዋት የ42 ሳንቲም ጭማሪ እንደሚደረግ የተቋሙ መረጃ ያሳያል፡፡ ባንጻሩ፣ ከፍተኛ የኃይል ተጠቃሚ የኾኑ ደንበኞች የማመንጫ ታሪፍ በኪሎ ዋት የ81 ሳንቲም ይጨመርባቸዋል። በተመሳሳይ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ከዚህ ቀደም ይከፍሉት ከነበረው ታሪፍ ላይ በኪሎ ዋት 26 ብር ከ34 ሳንቲም ጭማሪ ይከፍላሉ። በከፍተኛ የኃይል ተጠቃሚዎች ላይ ደሞ፣ ቀድሞ ይከፍሉት ከነበረው የኃይል ማስተላለፊያ ታሪፍ ይከፍሉት ከነበረው በኪሎ ዋት 95 ብር ከ87 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጓል። 4፤ ኢዜማ፣ ገዢው ብልጽግና ፖርቲ የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራዎችን መቀላቀልን በማናለብኝነት መንገድ ገፍቶበታል በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል፡፡ ኢዜማ፣ ገዥው ፓርቲ ሰሞኑን ለአባሎቹ ሥልጠና የተጠቀመበትን ሃብትና ንብረት ወደ መንግሥት ካዝና እንዲመለስም ጠይቋል። ዲሞክራሲያዊ ተቋማትም፣ መንግሥትን ተጠያቂ እንዲያደርጉና የአገሪቱን ሃብት ከሙስና እና ምዝበራ እንዲታደጉ አሳስቧል። ገዥው ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ላይ አደጋ እና ስጋት የሚደቅኑ ተግባራትን በተደጋጋሚ በመሥራት ለተጠያቂነት ዝግጁ አለመኾኑን እያሳየ ይገኛል ያለው ኢዜማ፣ ይህ አካሄድ የሚያመጣው መዘዝ ቀላል አለመኾኑ ሊታወቅ ይገባል በማለት አስጠንቅቋል፡፡ ኢዜማ፣ ገዥው ፓርቲ ስህተቱን በማረም የመንግሥትን ሃብትና ንብረት እንዳይባክን እና የመንግሥት መገናኛ ብዙሃንም በገለልተኛነት ይህን ተግባር እንዲያወግዙ አሳስቧል። 5፤ ሱዳን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ያሉበትን አስከፊ ኹኔታ በማስመልከት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ስደተኞቹ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ ባስቸኳይ ወደ አገራቸው እንዲመልሷቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ዘገባው አመልክቷል። በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን፣ ባሁኑ ወቅት ችግራቸውን የሚፈታላቸው አካል ማግኘት እንዳልቻሉም ስደተኞቹ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ገልጸዋል ተብሏል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከሑመራ እና ወልቃይት አካባቢዎች ወደ ሱዳን የተሰደዱት፣ የሰሜኑ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ የሱዳኑ ጦርነት ስደተኞቹ ወደሚገኙበት መጠለያ መቃረቡን በመግለጽ፣ ፌደራል መንግሥቱ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ከሱዳን ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ኹኔታ እንዲያመቻች ከጥቂት ሳምንታት በፊት መጠየቃቸው አይዘነጋም። 6፤ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ፣ ዛሬ ሞቃዲሾ ውስጥ ከሱማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሕመድ ፊቂ ጋር በቀጠናዊ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። የሱማሊያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሕመድ ፊቂም፣ የሱማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እንጂ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጠብ እንደሌለው መግለጣቸውን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ወርቅነህ ወደ ሞቃዲሾ ያቀኑት፣ ፊቂ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር ስምምነት ተግባራዊ ካደረገች፣ ሱማሊያ ለኢትዮጵያ አማጺ ኃይሎች ጦር መሳሪያ ልታስታጥቅ ትችላለች በማለት በተናገሩ ማግስት ነው። [ዋዜማ]
إظهار الكل...
👍 94 10😁 5👎 3
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.