cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ማለፊያ - Malefia

#ማለፊያ ☞ ታሪኮች ☞ ግጥሞች ☞ ሀሳቦች ☞ የጉዞ ማስታዎሻዎች ☞ ተስፋዎች ሰው ከመኖር የሚያተርፈው አንድም #ተስፋን ነው! ሁለትም #የማለፊያ ጥበብን ነው። ለአስተያየት ና ሀሳብ @Adwa1888 [አምባዬ ጌታነህ] ለስራ ከፈለጋችሁ ደግሞ ታችኛውን ተጠቀሙ @Amba_opportunity

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
5 106
المشتركون
-624 ساعات
-327 أيام
-13630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
"አምባ እንዴት ነህ?" የሚል መልዕክት በቴሌግራም አካውንቴ ገባልኝ። የላከችልኝ #ሐምራዊት ነበረች። ሐምራዊት ከእጅ ማስታዎሻዬ ባልተለዬ መልኩ አብራኝ የምትሆን በጣም የቅርብ ወዳጄ የነበረች ናት። ሐምራዊት ታሪክ የምትወድ ግን ታሪክ ማንበብ የሚሰለቻት አስቂኝም ግራ አጋቢም ሴት ናት። ከሐምራዊት ጋር ፒያሳ ማሞካቻ ቁጭ ብለን፣ ኦስሎ በረንዳ ላይ ተቀምጠን፣ የኤኔርኮን ኬክ በልተን ማኪያቶ እየጠጣን ያልዘለፍነው ዘፋኝ፣ ያላማነው ፣ ገጣሚ ፣ ደራሲና ተወዛዋዥ የለም። ሐምራዊት የቲያትር ተውኔት ልዩ ችሎታ አላት። የተዋወቅነው ባቢሎን በሳሎንን ብሔራዊ ትያትር ለመመልከት በሄድኩበት ወቅት ብሔራዊ መናፈሻ ላይ ከጓደኞቿ ጋር ችብስ እየበላች እኔ ደግሞ የ #Robert Frost ተወዳጅ ግጥሞችን በተመስጦ በማንበብ ላይ ሳለሁ ነበር ድንገት መጥታ "Hi" ያለቺኝ። ቀና ብዬ ተመለከትኳትና ማንበቤን ቀጠልኩ "ቢራቢሮ" አልኩ! "አመሰግናለሁ እንተዋወቅ" ስትለኝ እኔ ቢራቢሮ ያልኩት መፅሐፉ ላይ "My butterfly" የሚለውን ግጥም እያነበብኩ ስለነበር ነው"አልኳትና ለሰላምታ የዘረጋችውን እጇን በእርጋታ ጨበጥኳት። ትውውቃችን ከዚህ ነው የሚጀምረው። እና ሐምራዊ በቲያትር ተውኔት መድረክ ላይ ስትተውን እንደ ኤርታሌ እሳት የሚፋጅ ኢነርጂ አላት። ታዳሚውን ልቡንም ቀልቡንም ሰርቃ እስከመጨረሻው የማቆየቱ መክሊቱ አላት። እጇ ሁሉ ነገሯ ይወራጫል። ዳይሬክተሩ ሳይቀር ሁሌም ይገረምባታል። ከመድረክ ስትወርድ ደግሞ #የደጋ ሰው ብርድ ያኮራመታት ሴት ትመስላለች። አንድ ሰውነት ሁለት ማንነት አላት። እናም አብዝታ እኔን የቲያትር ፅሁፎችን እንድፅፍ ታበረታኛለች። የ#ቀጨኔውን አንተ ግን ትንሽ ብቻ ደጋግመህ ብትፅፍ እሳት የላስክ የቲያትር ፅሐፊ ነው የምትሆነው" ትለኛለች።የቀጨኔውን ማለቷ የቀጨኔ መድኃኒዓለምን ለማለት ነው። የትውልድ አካባቢዋ መነን ቢሆንም ከምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ይልቅ የቀጨኔው መድኃኒዓለም ለመሀላ ይቀርባታል። የቀጨኔውን ካለች ሀሳቧ ላይ ጠንካራ መልዕክት እንዳለ እኔም ሆንኩ ሌሎቹ እናውቃለን።"እኔም ተይ ሐምራዊ ለጋ ፅሐፊ ላይ ጠንከር ያለ የአድናቆት ቀንበር አይጫንም። ያለ እድሜዬ ያለ ስራዬ ትልቅ ሀላፊነት አታሸክሚኝ መያዝ ያቅተኛል። ቆይ ትንሽ በመፃፍ ልጠንክር!" እላታለሁ። ከዛ ፈገግ ትልና "ይሁንልህ ግን በቃ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደምትደርስ በብዕርህ አያለሁ። ታውቃለህ ግን ፅሁፍህን ግጥሞችህን ሳስብ ሁሌም እድገትህን የተወለድህበትን ቦታ አየዋለሁ። በተለይ የእናትህን ገራገርነት ደግነት ውበት የእናቱን ማንነት በጥልቀት የሚረዳ ልጅ ምሳሌ አንተ ነህ መሆን ያለብህ"እያለች የምታሞካሸኝ ልጅ ነች። ባጭሩ ሐምራዊት ይቺ ነች። እና እሷ ናት በቴሌግራም መልዕክት የፃፈችልኝ "ሐምራዊ ወዳጄ እንዴት ነሽ?" አልኋት "ሐምራዊት" ከምላት "ሐምራዊ ስላት ምን ያህል ደስ እንደሚላት አውቃለሁ። "እኔ በጣም ደህና ነኝ አንተ ግን ደህና ነህ?" አጠያየቋ በሆሂያት ተሰድረው የተላኩ ቢመስሉም በስሜትም ግን የሆነ ድምፅ አብሮ ያለፈ ያህል ነው። ጠፋህ ወዳጅነቱንም የልብ ወጋችንንም ለነ ኦስሎ ትዝታ አድርገህ ጠፋህ። የቀጨኔውን አሁንኮ እንደድሮ ፒያሳም ፒያሳ አልመስልሽ አለኝ! ድንገት ወደዛ ከሄድኩ ደግሞ እነዛ ውስጠ ወይራ ሀሳቦቻችን በምናነሳቸው ጉዳዮች የምንሰጣጣቸው ጠንካራ መልዕክቶችን ይመጡብኛል። በተለይ ስለ ካህሊል ጂብራን The Profit በሚለው መፅሐፍ ዙሪያ ያወጋናውን ሁሌም አስታውሳለሁ" አለች። "በቃ ሐምራዊ ማለት ይች ናት። ልቧ ላይ አንዳች ነገር ማስቀመጥ አትወድም። ቶሎ ነው ዝርግፍ አድርጋ የምትገላገለው። ለአመት ያህል የያዘችውን ስሜት በአንድ ፅሁፍ ፅፋ ተገላገለች። "ቀጠለችና የመጀመሪያውን መልዕክቷን አምብቤ ሳልጨርስ "ዳሩ ግን አንተ ስልጠና ምናምን እያልክ በጣም ነው የተቀየርክብኝ። እንደ ድሮው #ቀለል ስትል ነው ደስ የሚለው። #ቀለል ስትል ነው የምትመቸኝ😁 ደሞ ግጥሞችህም ናፍቀውኛል" ብላ ፃፈች። ትንሽ አሰብ አደረኩና " ሌላስ?" አልኳት "ቀለል ያለ ሰው ይመቸኛል! አለ አይደል የማያካብድ ረሃ የሆነ ሰው። በቃ አታካብድ አለባበስህም ንግግርህም ሁሉም ነገርህም አንተ አልመስል አልከኝ እኮ " ስትለኝ ግራ ገባኝ።ካለችው ቃል አልገባህ ያለኝ #ቀለል ስትል ማለቷ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት በመሞከሬ ነው። መቅለልን በድጋሚ አነሳቺው "ይቺ ልጅ የምወድልህ እያለቺኝ ያለው #ያለ ስአት ዝም ብዬ መገኘቴን ፣ #ያለምንም አመክንዮ የሚቀጥሩኝ ሰዎችን የማገኘውን፣ ና በዚህ ሂድ በዚህ እያሉ የሚያሽከረክሩትን፣ ከራሱ ደስታ ይልቅ ለሌሎች አብዝቶ በሼም የሚጨነቀውን፣ ያለ ዓላማ ዝም ብሎ የሚጓዘውን፣ የነገውን ህልም ስለማሳካት አይደለም ስለህልም የማያቀውን፣ ከማመስገን ይልቅ አብዝቶ ፈጣሪውን ለምን ድሃ አድርጎ እንደፈጠረው የሚያማርረውን ሰው፣ ህይዎቱን በአሰልቺ መቼትና ግጭት ድግግሞሽ የሚኖረውን ሰው ነው? ይመቸኛል እያለች ያለቺው?" በማለት ራሴን ጠየኩት። እንዴት አሁን አልተመቸኋትም? እሷ የምታውቀው ያለፈ ህይዎቴን ስለሆነ ነው? ምርጫዋስ የለመደቺው ወይስ ትክክሉ ነው? ያለ ህልም መኖርስ ውበት ሆነ ማለት ነው። ለሰዎች የመወደጃ መስፈርትስ ሆነ ማለት ነው? መቅለልስ ወንዳወንድነት ሆነ ማለት ነው? አልገባኝም "አያሌ ጥያቄዎችን አመላለስኩ! "አሁን እኮ በእርጋታ ሀሳቦችን የማሰላስል የሀሳብን ምንነት የተረዳሁ ሰው ሆኛለሁ። አሁን እኮ ከተራ መተቸት ወጥቼ የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማፍለቅ የምታትር ሰዎችን ከመመልከት ይልቅ ራሴን መመልከትን ማንነት ያደረኩ ሰው ሆኛለሁ።! አሁን እኮ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዬን አውቄ የምጓዝ ሰው ሆኛለሁ። እና እንዴት አሁን ከበድኳት? እንዴት አሁን አልቀለልኳትም። የውስጡን ጥያቄ ያልመለሰው የቀድሞው ማንነቴስ እንዴት አልከበዳትም? ራሱን ሳይሆን የሚጓዘው እኔነቴስ ለምን አልከበዳትም? ሰው የሚቀለው ህልም አልባ ሲሆን እንደ ቦይ የሚፈስ ሲሆን ነው ማለት ነው? የሚከብደው ህልም ሲኖረው ነው ማለት ነው? እያልኩ አያሌ ሀሳቦችን እያወጣሁ እያወረድሁ። " ሐምራዊ ወዳጄ በእርግጥ ያነሳናቸው ሀሳቦች የተወያየንባቸው ቁምነገሮችን ሳስብ በወቅቱ የነበረንን የመሻት ግለት አይበታለሁ። የእኛንም ቁመና ማንነት እረዳበታለሁ። ግን ብዙ ደግሞ የዘለልናቸው መሠረታዊ ነገሮች አሉ። ያልመለስናቸው የ "ለምን?" ጥያቄዎችም እንዳሉ ማወቅ አለብሽ። የለመድነው ብቻ ትክክል ነው ማለት ሀሳዊነት ነው " እነሱን መያዝ ስለምፈልግ ነው የምሰለጥነው። ደግሞም ትልቅ ህልም ስላለኝ በዛ በኩል እንገናኛለን።ደግሞም ከድሮው ይልቅ ለወዳጂነታችን የሚመች ሰው የምሆነው አሁን ነው ለማንኛውም #ሔመንን ሳሚልኝ " አልኳት ። ሔመን በልጅነቷ የወለደቻት ልጇ ነች። "አምባ አሁንማ የምናስበውም የምንፈልገውም ሀሳቦቻችንም የተለያዩ ናቸው። መቼም ልንግባባ አንችልም"ብላ መልዕክቶቻችን ሰረዘቻቸው።
إظهار الكل...
" ከስዕሉ ጀርባ " ( በአምባዬ ጌታነህ ) ለመክሊቱ መቅድም አይኑ እያማተረ፣ አንዴ መምህሩን አንዴ ተማሪውን እየቀያየረ ፣ በምትሀት እጆቹ ቁጭ አርጎ እያኖረ፣ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ፦ ስዕል ብቻ ሚስል አንድ ልጅ ነበረ። ከእለታት ባንድ ቀን መምህሩ ሲዞር "ደብተርህን "ሲለው፤ ደብተሩን አሳየው። የስዕል ደብተሩን የሰጠኝ ነው መስሎት፣ መምህሩ ደንግጦ "ሌላ ደብተር" አለው፣ ሌላ ደብተር ሰጠው፣ ይህንም ቢገልጠው፣ ስዕል ብቻ ሆኖ እሱ ያፃፈውን ኖት ማየት ናፈቀው። .... ወደ በሩ በኩል እጁን 'የጠቆመ "ውጣ ከዚህ "አለው። ልጁን አስወጥቶ ደብተሩ ላይ ባሉ ስዕል አፈጠጠ፤ <ስዕል ፩> ሀገር የሚረከብ ሀገርን የሚቀርፅ በመሻት ላይ ያለ ትውልድን ለማነፅ ደፋ ቀና የሚል ከጠመኔው ጋራ የተመሳሰለ፣ ኑሮ ያንገላታው ትጉህ መምህር አለ። <ስዕል፪> የመምህሩን መኖር ከመጤፍ ሳይቆጥር ስልክ ሚጎረጉር ፀጉሩን በጣቶቹ እያፍተለተለ፣ አልፎ አልፎ መምህሩን ቀና ብሎ እያየ ከሱ ጋራ መስሎ ከእሱ ጋ የሌለ፣ የአርሴናልን ማሊያ የለበሰ ወጣት አንድ ተማሪ አለ። <ስዕል ፫> በተደፋ ኩሏ የተንሸዋረረች፣ ያለ እረፍት ከንፈሯን እያሸራመጠች፣ ተገላልጣ ለብሳ ሳትታይ የቀረች፣ በስተመጨረሻ ተስፋ የቆረጠች፣ የምትቁነጠነጥ አንዲት ሴት ልጅ አለች። <ስዕል፬> መምህሩ ሚለውን ከአፉ እየነጠቀ እየተከተለ፣ በደብተሩ ሚያስቀር ትጉህ ተማሪ አለ። <ስዕል ፭> የመምህሩን መውጫ ስአት የናፈቁ፣ ቁራጭ ወረቀት ላይ በተፃፃፏቸው ቃላት የሚስቁ፤ በወንበሩ አሻግረው እግርና እግራቸውን እያነባበሩ፣ ፍቅር ሚጀምሩ፣ በብርድ የሞቃቸው ልጅ እሳት ነበሩ። <ስዕል ፮> በዛ በኩል ደግሞ፣ ሁሉንም ተማሪ እያየ በአርምሞ፣ በድርጊቶቻቸው ከልቡ ተገርሞ፣ "ልሳላቸው ብሎ እየሳለ ሳለ " ድንገት መምህሩ አይቶት ወደ እሱ መጣና፣ " ስዕል ከምትስል ለምን አትማርም በኋላ ሳትማር ለወላጅ ለሀገር  ከምትሆን ሸክም? ብትከታተለኝ ሳይሻል አይቀርም፣" የሚል መምህርና የተማሪው ምስል በስዕሉ ይታያል። ከዛም መምህሩ ይህን ሁሉ ስዕል ተመለከተና፣ "ያለ መክሊቱ ነው የሚማረው?" ብሎ ከልቡ አዘነና፣ የስዕል ስድስትን- መምህር ተግባር ወስዶ፣ " ና ግባ" አለው ልጁን የጥል ግምቡን ንዶ። ይህን ሁሉ ምናብ በስዕል መስሎ በስንኝ ሚሰድር፣ ከስዕሉ ጀርባ ሳይ ገጣሚ ነበር። 09/06/2011 @malefia @malefia
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የወፍ ህግ (አምባዬ ጌታነህ) : አስተውል ሁሉን በአንክሮ አዳምጠው የውስጥህን ጥም፣ ሁሉም ዛፍ ፍሬ አለው ማለት አጥጋቢ ምግብ አይሰጥም። @malefia @malefia @malefia
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#በእምነታችን (አምባዬ ጌታነህ) ፡ በፈጣሪ ፈቃድ የሙሴ ብትሩ ባህርን ገመሰ፣ በአንዲት ወንጭፍ ጠጠር በዳዊት ፊት ወድቆ ጎልያድ አነሰ። አዎ ባህሩም ተገምሷል ጎልያድም ወድቋል። ግን ምንድን ልልህ ነው የሙሴ ብትሩ ባህር ምን ብትገምስም አትበልጥም ከሙሴ ጎልያዶች ሁሉ በእምነታችን እንጂ በጠጠር አይወድቁም ትልሀለች ነፍሴ። @malefia @malefia
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ግራ ስንጋባ መሄጃ ቸግሮን  ሲጠፋብን  መንገድ፣ በእሱ  እንድንፅናና እመ አምላክን ሰጠን አማላጅ ትሆን ዘንድ @malefia @malefia @malefia
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.