167
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
- المشتركون
- التغطية البريدية
- ER - نسبة المشاركة
جاري تحميل البيانات...
معدل نمو المشترك
جاري تحميل البيانات...
🌈⭐️⭐️ ደስታን ላራሳቾችን ስንፈልገው
⭐️ 🌟 አይገኝም ነገርግን ደስታን ለሰው
⭐️ ስንሰጠው ወደ እኛ ተመልሶ
ይመጣል፣ ይህ የደስታ ምስጢራዊ
አስማት ነው። ስለዚህ ባለን አቅም ሁሉ
ደስታን ለሰው እንስጥ የእኛ ደስታ
ከምናስበው በላይ እያደገ እያደገ ይመጣል።
@tinswaa
ደሃው ሞቶ ሞቶ ሀብታም ብቻ ቀረ
ሀብታም ኖሮ ኖሮ ደሃ ሆኖ ቀረ
እርሱም እንደ ደሃው ለሞት ተቃረበ
የሚረዳው አጥቶ ተኝቶ ተራበ
የሚያስታምም ጠፍቶ ሞትንም ተመኘ
ግን እንደምኞቱ ሞትም አልተገኘ
✍ ታምሀዊ
@tinswaa
በአንዷ ህይወቴ ሁለት ምርጫ ይዤ
ነብሴን እየቀጣሁ ለስጋዬ አግዤ
መኖርን መርጬ ከአምላኬ ስጣላ
ወደፊት እየሔድኩ ሳላይ ወደኋላ
ብርቅርቋ ዓለም ሆና ተገላልጣ
ለጊዜያዊ ኑሮ ዘላለሜን ሳጣ
ጨረስኩት እድሜዬን መንገዴን እንዳጣው
ተስፋባገኝ ብዬ ይኸው ደጅህ መጣው
✍ ታምሀዊ
@tinswaa
☞.............አእምሮን ለመደምሰስ እንጂ ለመሙላት
እንዳልመጣሁ የሚያወሱ አንዳንድ አሉታዊ ነገሮች ብቻ
ይነገሩ ይሆናል ፡፡ሆኖም አሮጌዉ አእምሮ ካልተደመሰሰ
አዲሱ ሊፈጠር አይችልም ፡፡ፈጠራ ከጥፋት ዉስጥ
ያንሠራራል፡፡ህይወትም በሞት ዉስጥ ያብባል፡፡..............
☞ እዚህ ያሉ ስራወቼ በሙሉ አእምሮን በመደምሰስ ላይ
ያተኩራሉ ፡፡ የአእምሮ ስሮችን በጣጥሶ በመጣልም
በእያንዳንዱ የህይወት ጊዜያት ነፃነታችሁን ታዉጃላችሁ ፤
እናም ያለ አንዳች ያለፈ ታሪክ መኖር ትችላላችሁ ፡፡ከአለፈ
ታሪክ ጋር መኖር በእስር ቤት ተከርችሞብን እንደመኖር ነው ...
ባግዋን ኦሾ
@tinswaa
“የሰዉ ልጅ በጣም የሚገርም ፍጡር ነዉ፡፡ ገንዘብ
ለማግኘት ሲል ጤናዉን መስዋእት ያደርጋል፡፡ ከዛ መልሶ
ጤናዉን ለማግኘት ያለዉን ገንዘብ በሙሉ ያፈሳል፡፡
ስለነገ በጣም ይጨነቅና ዛሬን መኖር ይረሳል ፣ዉጤቱ
ደግሞ ዛሬንም ነገንም እንዳይኖር ያደርገዋል፡፡ ሰዉ አንድም
ቀን እንደማይሞት አድርጎ ይመላለሳል ነገር ግን አንድም
ቀን ሳይኖር ይሞታል” -
-ዳላይ ላማ--
@tinswaa
ለራስ የሚነገር መልዕክት ___
መልዕክት 1
እራስክን ከማንማ ጋር አታወዳድር፡፡ ይህን ባደረክ ጊዜ
እራስክን በራስህ እንደሰደብክ ቁጠረው፡፡
መልዕክት 2
ቁልፍን ያለመክፈቻ ማንም እንደማይሰራ ሁሉ ፈጣሪም
መፍትሄ የሌለው ችግር እንዲገጥምን አይፈቅድም፡፡
መልዕክት 3
ደስታህን ከራስህ ባራቅህ ጊዜ ሕይዎት በአንተ ላይ
ትስቃለች፡፡ ደስተኛ በሆንክ ጊዜ ሕይዎት ፈገግታዋን
ትለግስሃለች፡፡ ሌሎች እንዲደሰቱ ምክንያት በሆንክ ጊዜ ግን
ሕይዎት የከበረ ሠላምታዋን ታቀርብልሃለች፡፡
መልዕክት 4
ማንኛውም ስኬታማ ሰው ከበስተጀርባው አስቸጋሪ ታሪኮች
እንዳሉት ሁሉ ማንኛውም የችግር(አስቸጋሪ) ታሪክ
መጠናቀቂያው ስኬት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ተቀበልና
ለስኬት ተዘጋጅ፡፡
መልዕክት 5
የሌሎችን ስህተት ለመተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ነገር
የእራስን ስህተት መረዳቱ ላይ ነው፡፡
መልዕክት 6
የተፈጠረልህ መልካም አጋጣሚ ባመለጠህ ጊዜ እዛው
ባለህበት ቁመህ አይንህን በእንባ አትሙላ፡፡ ቀጣዩንና
የተሻለውን መልካም አጋጣሚ እንዳታይ ይከልልሃልና፡፡
መልዕክት 7
ለችግር ፊትን ማዞር ችግሩን አይቀይረውም ችግሩን መጋፈጥ
እንጅ፡፡ በሌሎች ቅሬታን ከማሰማት እራስን ለውጦ ሠላምን
መግዛት፡፡
መልዕክት 8
ስህተት ስህተቱ በተፈጠረበት ወቅት ስሜትን ይጎዳል፡፡
ከዓመታት በኋላ የስህተቶች ድምር የሚፈጥረውና ወደ ስኬት
የሚያመራው ከስህተት መማር ተሞክሮ(ልምድ) እንለዋለን፡፡
መልዕክት 9
የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚሆነው፣
የተጠረበ ድንጋይ ሀውልት እንደሚሆነው ሁሉ፣
አንተም በብዙ ችግር ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን
አትርሳ፡፡ በመሆኑም ስትሸነፍ ጠንካራ ስታሸንፍ የተረጋጋ ሁን፡፡
@tinswaa
اختر خطة مختلفة
تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.