cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የወረታ ወጣቶች ሰለፍያ ጀመዓ ገፅ

በከተማዋ ዉስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የአሕባሽ እና የተክፊር ፈተና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ማስጠንቀቅ!!!⚠️⚠️⚠️ በዚህ bot በመግባት አስተያየትወን መስጠት ይችላሉ @asteyayetmeschabot

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
183
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እኛስ የት እንሆን? ~ "ከዒልም በረከትና ስርአት ውስጥ አንዱ ሚዛናዊነት ነው። ሚዛናዊ ያልሆነ ሰው አልተረዳም፤ አልተገነዘበም።" ኢብኑ ዐብዲል በር [ጃሚዑ በያኒል ዒልም፡ 1/530] https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

➥ ሰውን ከሰለፍያ ማስወጣት ከባድ ነው። ወንድሜ በትላልቅ የዲን ነጥቦች የተወሰነ እውቀት አለኝ በማለት ከመፍጠን ረጋ በል! በተለይ ሰውን ከሱና በማስወጣት (በጀርሕ ወተዕዲል) ጉዳይ ርእሱ ሊመጠንን ሰለማይችል ከፊት እየከነፉ ከመሄድ ወይንም ከፊት የሚከንፉ የፊትና አራጋቢዎችን እየተከተልን አኼራችንን ከምናጨልም ረጋ በማለት በተለይ በዚህ ርእስ ከታወቁ የሱና ዑለሞች ከዘርፉ ባለሟያዎች ሗላ እንሁን ➲ ሰውን ከሱና ማስወጣት ከባድ እንደሆነ ➲ ይህ ርእስ እኛን የሚመጥነን እንዳላይደለ ➲ በዚህ ጉዳይ ወደ ዑለሞች መመለስ እንዳለብን ተወዳጁ የሱና ዐሊም ሸይኽ ሱለይማን አር–ሩሐይሊይ የሚመክሩንን ወርቃማ ምክር እናዳምጥ ____የሸይኹን ንግግር በተወሰነ መልኩ ከዚህ ባታች ወደአማረኛ መልሸዋለሁ__________ ጥያቄ/ ከሰለፊያ የመውጣት ዷቢጥ(ህግ) ምንድን ነው? መልስ/ ➼ ከሰለፊያ ማስውጣት በጣም ከባድ ነገር ነው ወንድሞቼ! ➼ ለዚህም ሲባል በዚህ ጉዳይ ልንቸኩል አይገባም። ➼ ለጣሊበል ዒልምም በዚህ ርእስ ላይ ነፍሳቸውን ፈራጅ አድርገው ሊሰይሙ አይገባም! ➥ ከሚያሳዝነው ነገር እኛ ከፊል ትንሽ ተማሪዎችን በትላልቅ ዑለሞች ላይ ሁክም ሲሰጡ እናገኛለን ➼ አንዳንዴም ወጣቱ –ከራሱ ዘንድ(በሆነ ፍርድ) ማለቴ ነው– በዚያ ሰለፍያን ባስተማረው ሸይኹ ላይ እሱ ሰለፍይ አይደለም ብሎ ፍርድ ይሰጣል ➼ ወንድሞቼ በዚህ ጉዳይ ላይ መቸኮል አይገባም እላለሁ ➼ ይልቁንም ሰው (በዚህ ነጥብ) የመረጋጋት ባለቤት መሆን ይገባዋል ➼ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ዑለሞች ሊመለስ እና ጉዳዩን (ለዑለሞች) አንድን ነገር የሚፈልግ ሳይሆን ሐቅ የሚፈልግ ሰው አቀራረብ ሊያቀርብ ግደታ ይሆናል ➼ ከፊል ሰዎች ምሳሌ ይደውልልኝ እና ጉዳዩን ልክ እንዳለ በትክክል አያቀርብም አንድን ነገር ብቻ የሚፈልግ ሁኖ ያቀርባል…… ➼ ይህ አላህ ዘንድ አይጠቅምም ምክኒያቱም አንተ በዚህ ልቦናህን መታዘዝ እንጅ ጊታህን መታዘዝ አልፈለግክም ➼ በዚህ ርእስ ላይ ታዋቂ ወደሆኑ ዑለሞች መመለስ ጉዳዩንም ለነርሱ ማቅረብ በንደዚህ አይነት ጉዳይ የሚሰጡትን አቅጣጫ(ምክር) መፈለግ ግዴታ ነው _ ➥ ለማንኛውም ዑለሞች ዘንድ አንድ ጥቅል የሆነቸዋ መርህ ➲ ሰለፊያ ተዋቂ የሆኑ መሰረቶች አሏት (በርግጥ አውስተናታል) እርሷን የተኻለፈ ከሰለፊያ ይወጣል ➲ እርሷን (እቺን መሰረት) ያሟላ እርሱ በሰለፎች (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) መንሀጅ ላይ ነው ➲ ነገር ግን ለጣሊበል ዒለሞች በዚህ ርእስ ሊቸኩሉ አይገባም እላለሁ ➲ እንደውም (በዚህ ርእስ) ሊቀደሞ አይገባምም አይፈቀድላቸውምም ➲ ይልቅ (በዚህ ጉዳይ) በግልፅ ወደዑለሞች መቅረብና (እንድሁም) ጉዳዩ እንዳለ በትክክል ለዑለሞች ሊቀርብ ነው የሚገባው __ቀጥታ ከሸይኹ👇 ያዳምጡት_________ https://i.top4top.io/m_1904omnyj1.mp3 ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• ✍ ወንድማችሁ/ ኢብኑ ሙሐመድዘይን 🔗t.me/IbnuMuhammedzeyn
إظهار الكل...

ከዚህ በፊት {በኢስላም ዑዝር ቢልጀህል ስለመኖሩ ግራ ለተጋባችሁ!} በሚል ርእስ ለተክፊሮች መልስ የተሰጠበትን ተከታታይ ፅሁፍ አንድ ወንድሜ «በተወሰኑ አከባቢዎች "በድብቅም ቢሆን" የተክፊሮች እንቅስቃሴ ስላለ ለሁለተኛ ጊዜ ሼር ብታደርገው ፅሁፉ ላልደረሳቸው ይደርሳል በዑዝር ቢልጀህልም ዙሪያ ከተክፊሮች ጋር መወያየት ለሚፈልጉ ወንድሞች ያግዛቸዋል እንድሁም ተክፊሮች ባሉበት አከባቢ በዚህ ርእስ እራሳቸውን ከሹበሃ ለመጠበቅ ሰበብ ይሆናቸዋል» ብሎ በጠየቀኝ መሰረት ከዚህ በታች ከክፍል 1–8 በሊንክ ተዘጋጀተው ቀርበዋል ፅሁፎቹን ሊንኩን እየተጫናችሁ በመግባት አንብቧቸው ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጓቸው (ጀዛኩሙሏሁ ኸይርን) • {በኢስላም ዑዝር ቢልጀህል ስለመኖሩ ግራ ለተጋባችሁ!} ክፍል 1 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/196 ክፍል 2 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/212 ክፍል 3 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/213 ክፍል 4 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/845 ክፍል 5 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/220 ክፍል 6 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/227 ክፍል 7 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/235 ክፍል 8 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/278 • ማሳሰቢይ:- ይህ ተከታታይ ፅሁፍ አላለቀም ኢን ሻአሏህ በተመቼኝና ጊዜ ባገኙሁ ጊዜ ወደፊት ለመጨረስ እሞክራለሁ! ✍ ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድዘይን ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• http://t.me/IbnuMuhammedzeyn
إظهار الكل...
Ibnu Muhammedzeyn

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነው {በኢስላም ዑዝር ቢልጀህል ስለመኖሩ ግራ ለተጋባችሁ!} ኢንሻ አላህ በኢስላም ዑዝር ቢልጀህል እዳለ ቁራኣናዊ ሀዲሳዊ እንድሁም የኡለሞችን ንግግር በተከታታይ ፅሁፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ! ክፍል አንድ ★የቁራኣን ማስረጃ★ በቅድሚያ ወደ ማስረጃ መጥቀስ ከመግባቴ በፊት ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የተወሰኑ ነጥቦችን ላስቀድም 👉 ዑዝር ቢልጀህል ዐቂዳዊ መስአላ (ነጥብ) ነው ወይንስ ፊቂሃዊ ነው የሚለውን እንመልከት!! 👌 ዑዝር ቢልጀህል እንደሌሎች ኢጅቲሃድን እንደሚያስተናግዱ ርእሶች ነው። እንጅ #ከዐቂዳ ርእስ አይደለም!! ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- "#ማሳሰቢያ በዑዝር ቢልጀህል መለያየት እንደሌሎቹ ፊቂሃዊ እና ኢጅቲሃድን ከሚቀበሉ መስአላዎች ነው!" [ሸርሁ ከሽፊ ሹቡሃት: 50)] #ለዚህም ነው የሱና አሊሞች በዚህ ዙሪያ ብዙዎቹ ዑዝር ቢልጀህል አለ ሲሉ! #የተወሰኑት የለም በማለት የተለያዩት። ቢሆንም! ግን አለ የሚሉት አሊሞች የለም የሚሉትን አልጠሉም! #በዚህም ላይ አቋማቸውን አልለያዩም። በተቃራኒውም የለም የሚሉት አሊሞች አለ የሚሉትን አልጠሉም! #ይህ ነገር መፈጠሩ እርስ በእርሳቸው እንዲጠላሉ አላደረጋቸውም ! የዚህን ዘመን አጋፋ የሱና አሊሞች ለአብነት ያክል እንመልከት ሸይኽ ዑሠይሚን፣ ሸይኽ አልባኒ፣ ሸይኽ ሙ/ድ አማን አል–ጃሚ ፣ ሸይኽ አልዐባድ ዑዝር ቢልጀህል አለ ሲሉ። #በተቃራኒው ደግሙ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ እና ሸይኽ ፈውዛን የለም ይላሉ! #ግን በዚህ ምክኒያት አንዳቸው ሌላቸውን አልጠሉም፣ አልተወጋገዙምም! #ሌሎች የቢድዐ አንጃዎች በዚህ ምክኒያት ዑዝር ቢልጀህል አለ በማለት አቋማቸውን የነቀፋቸውን ሁሉ እንደሚያከፍሩትም አንዳቸው ሌላቸውን አላከፈሩምም!! በዚህ ዙሪያ…

ስለ አህባሽ ስለ ጨረቃዎቹና ስለ ዜሮዎቻቼው " አብዱላህ አል-ሀረሪ ጨረቃ ላይ ታይተዋል" የሚለውን ቅጥፈታቸው ፈገግ ያሰኛል
إظهار الكل...
ስለ-ጨረቃዎችና ዜሮዎቹ...!.mp31.74 MB
“በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ ~ ~ ~~ ~ ~~~~ ~~~~~~~~~~ እጅግ ከሚገርሙ ነገሮች ውስጥ አንዱ መጤ ለሆነው መውሊድ ቁርኣንና ሐዲሥ የሚያጣቅሱ ሰዎችን ማየት ነው። ይሄ የሚያሳየው ሰዎቹ ምን ያክል ለቁርኣንና ሐዲሥ ተገቢ ክብር የማይሰጡ፣ ሐያእ የቀለላቸው እንደሆኑ ነው። መውሊድ በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስኮ፦ * ልክ ዛሬ እናንተ እንደምታደርጉት በሶሐቦቹ፣ በታቢዒዮቹ፣ በአትባዑ ታቢዒን፣ በታላላቅ ቀደምት ኢማሞች፣ ይከበር ነበር። * እናንተ እንደምትሉት በሙዞፈር እስከሚጀመር ስድስት ክ/ዘመን መቆየት ሳያስፈልገው በኸሊፋዎቹ ይፈፀም ነበር። * በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ በዚህ ቢድዐ ላይ ውዝግብ ባልተነሳ ነበር። * በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ነቃፊ ዑለማዎች ቀርቶ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣ ዒራቂ፣ ተዝመንቲ፣… ያሉ የመውሊድ ደጋፊዎች ጭምር ቢድዐ ነው ብለው ባልደመደሙ ነበር። ቁርኣንና ሐዲሥ ውስጥ የሚገኝ ጉዳይ “ቢድዐ ይባላልንዴ?!” * በቁርኣንና በሐዲሥ ቢጠቀስ ኖሮ ሶላሑዲን አል አዩቢ የባጢኒያ ሺዐዎችን ስርኣት ሲገረስስ በነሱ የተጀመረውን መውሊድም አብሮ ባላቋረጠው ነበር። እነዚህን እውነታዎች ይዘን ከዚያም እነዚህ አካላት ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናሉ ብለው የሚጠቅሷቸውን የቁርኣን አንቀፆችንና ሐዲሦችን ብንመለከት ስራቸው አይን ያወጣ ማምታት እንደሆነ እንደመድማለን። ምክንያቱም የሚጠቅሷቸው አንቀፆችና ሐዲሦች መውሊድን የሚጠቁሙ ቢሆኑ ኖሮ በዚያ እንቁ ዘመን ይከበር ነበርና። በዚያ ዘመን መውሊድ አለመከበሩ እነዚህ አታላዮች ለአንቀፆቹ የሚሰጧቸው ትርጓሜዎች የተሳሳቱ ለመሆናቸው በቂ ማሳያ ነው። ባጭሩ ለነዚህ አካላት የምንሰጣቸው ጥቅል ምላሽ የትኛውም የቁርኣን አንቀፅ ወይም የሐዲሥ ትርጓሜ ዋጋ የሚኖረው የቀደምቶችን ግንዛቤ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው። ሌላው ቀርቶ የነሱን ቃላት እየተጠቀመ አፈፃፀሙ ግን የነሱን አፈፃፀም ያልተከተለ ከሆነ የሰለፎችን ግንዛቤ አልተከተለም ማለት ነው። ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ ረሒመሁላህ ሱብኪ የተባሉት ሸይኽ የሆነችን የቁርኣን አንቀፅ ከሰለፎች አንድም ባልቀደማቸው መልኩ በመፈሰራቸው የተነሳ ምላሽ ሲሰጧቸው እንዲህ ነበር ያሉት፡- “ይሄ ተቃዋሚ ይህቺን አንቀፅ የፈሰረበት መንገድ በርግጠኝነት ውድቅ ነው። ሐቅ ቢሆን ኖሮ (ቀደምቶቻችን) በእውቀትም፣ በተግባርም፣ በማመላከትም፣ በመምከርም ይቀድሙን ነበር። በየትኛውም አንቀፅ ወይም ሱና ላይ በሰለፎች ዘመን ያልነበረ፣ እነሱ ያላወቁትና ለህዝቡ ግልፅ ያላደረጉት የሆነን ትንታኔ መፍጠር አይቻልም። እንዲህ ማድረግ እነሱ በዚህ ላይ ሐቁን ዘንግተውና ከሱም አፈንግጠው ኖሮ ይሄ ዘግይቶ የመጣው ተቃዋሚ አግኝቶታል ማለት ነው።” [አሷሪሙል ሙንኪ፡ 247] በነገራችን ላይ እንደ ኢብኑ ሐጀር፣ ሲዩጢ፣ ሰኻዊ፣… ያሉ ዓሊሞች መውሊድ በሰለፎቹ ዘመን ያልነበረ ቢድዐ ነው ብለው በግልፅ ሲናገሩ ብዙ ጣጣ ጨርሰውልናል። ምክንያቱም ሰለፎች ለማያውቁት ዒባዳ ቁርኣንና ሐዲሥን ማጣቀስ ስህተት መሆኑ በቁርጥ የሚታወቅ ነውና። ይህንን ከያዝን በኋላ ሱፍዮች ለመውሊድ ቢድዐ ጠንካራ ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱትን የቁርኣን መልእክት እንመልከት፡- {قُلۡ بِفَضۡلِ ٱللَّهِ وَبِرَحۡمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلۡيَفۡرَحُواْ هُوَ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ} [يونس: 58] {“በአላህ ችሮታና በእዝነቱ ይደሰቱ። እርሱ ከሚሰበስቡት ሃብት በላጭ ነው” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 58] እና በዚህ ውስጥ መውሊድን የሚደግፍ ምን መልእክት አለ? ብትሉ “በአላህ እዝነትና ችሮታ እንድንደሰት ታዘናል፤ ከእዝነቶችና ችሮታዎቹ ሁሉ በላጩ ደግሞ የነብዩ ﷺ መወለድ ነው። ስለዚህ መውሊዳቸውን ማክበር በዚች አንቀፅ ውስጥ ተካቷል” ይላሉ። መልስ፡- ===== አዎ አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ችሮታውና እዝነቱ ሲባል ምንድነው የተፈለገው በሚለው ላይ “ቁርኣን”፣ “ዲን”፣ “ኢስላም”፣ “ኢማን”፣ “ከቁርኣን ሰዎች ማድረጉ”፣ “ሱናዎች”፣ “ጀነት” ወዘተ የሚሉ ተፍሲሮችን በቀዳሚነት ብናገኝም ነብያችንንም ﷺ የሚያካትት ይሆናል። ይህንን የሚጠቁም ተፍሲር ኢብኑል ጀውዚ፣ ሲዩጢና ኣሉሲ አስፍረዋል። በርግጥ ሶስቱም በቀዳሚነት ያሰፈሩት ይህንን አይደለም። ሱፍዮች ግን ቀዳሚዎቹን ጥለው እዚህ ላይ ነው የሚያነጣጥሩት። ቢሆንም ብዙም የሚያሳስብ አይደለም። መልእክቱ ጠቅላይ ነውና እዚህ ላይ ከተጠቀሱት ውጭ ባሉ የጌታችን ችሮታዎች ጭምር እንደሰታለን፣ እናመሰግነዋለንም። ነገር ግን፦ 1. የአንቀጿ መልእክት በነብያችን ﷺ ላይ የተገደበ ባልሆነበት እንዲያውም ሌሎቹ ተፍሲሮች ቀዳሚ በሆኑበት ነጥሎ እሳቸውን ብቻ የታሰቡ አድርጎ ማቅረብ ማድበስበስ ነው። 2. በቁርኣን፣ በሐዲሥ፣ በኢስላም፣ በኢማን፣ ... ለመደሰት አመት መጠበቅ እንደማያስፈልገን ሁሉ በነብዩ ﷺ ለመደሰትም አመት መጠበቅ አያስፈልገንም። ይሄ ሱፍያዊ ተርቲብ ነው። አመት ጠብቆ ያልዘለለ ሰው በነብዩ ﷺ መልላክ አልተደሰተም ብሎ ማሰብም የለየለት ብልግና ነው። 3. የአንቀጿ መልእክት ሙሉ በሙሉ ነብዩን ﷺ የሚገልፅ ነው ቢባል እንኳን አመት ጠብቃችሁ መውሊድ አክብሩ የሚል ጭብጥ በቅርብም በሩቅም የለም። እነዚህ አካላት ግን ካልተጨፈረ ካልተዘለለ ደስታ ያለ አይመስላቸውም። በዚያ ላይ የልደት ቀናቸው በቁርጥ አለመታወቁን ጨምሩበት። 4. የአንቀጿ መልእክት ለመውሊድ ማስረጃ ቢሆን ኖሮ ቀደምቶች እየተሰባሰቡ መውሊዳቸውን ያከብሩ ነበር። ይሄ ተግባር በዚያ ዘመን አለመፈፀሙ የቁርኣኑ መልእክት መውሊድን ፈፅሞ እንደማያካትት በቁርጥ ያስረዳል። 5. ሰለፎች መውሊድን ያላከበሩት ስላልተመቻቸው ነው የሚለውን ሱፍያዊ ማምታቻ ለጊዜው ብንቀበል እንኳ ሰለፎቻችን ከተፍሲሮቻቸው ያሰፍሩት ነበር። ልብ በሉ የመውሊድ አክባሪዎች ከዘመናት በኋላ መጥተው መልእክቱን ጠምዝዘው ለዚህ ቢድዐ እስከሚጠቀሙበት ድረስ ይህቺን አንቀፅ ለመውሊድ መረጃ ያደረገ አንድ እንኳን የለም። ሙልሀም እንደሆኑ ከተመሰከረላቸው ዑመር፣ ቁርኣንን እንደወረደ መቅራት የፈለገ ከሳቸው እንዲማር የተነገረላቸው ኢብኑ መስዑድ፣ ቱርጁማኑል ቁርኣን ከተባሉት ኢብኑ ዐባስ፣ ከቁርኣን ሰብሳቢው ዑስማንና ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ ከነ ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ … የሙፈሲሮች ሸይኽ ከሚባሉት ከሙጃሂድ፣ ከነቀታዳ፣ ከነዶሓክ፣ ከነሻፊዒይ፣ ከነማሊክ፣.. እንዴት ተሰወረ? እነዚህ ሁሉ ያላወቁትን ነው ከዚያ በኋላ የመጣ ትውልድ የሚያውቀው?! 6. በነዚህ ሰዎች ስሌት ከተሄደ የሶሐቦችንም መውሊድ ማክበር ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ሶሐቦች አላህ ለኡማው ከዋላቸው ፀጋዎች ውስጥ ናቸው። የነብዩ ﷺ ሚኒስትሮችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች ነበሩ። ሶሐቦች ለዚህ ኡማ ባለውለታ ናቸው። ቁርኣኑም ሐዲሡም ያለነሱ ወደኛ መድረስ አይችልም ነበር። ስለዚህ አላህ ለኛ ከዋለልን ውለታዎች፣ ከትሩፋቱ፣ ከእዝነቱ ናቸው። አላህ ደግሞ በትሩፋቱና በእዝነቱ እንድንደሰት አዞናል። ስለዚህ የእያንዳንዱ ሶሐባ መውሊድ መከበር አለበት። በተለይ ደግሞ ኹለፋኡ አርራሺዲን። ውለታቸውም ደረጃዎቻቸውም ከፍ ያለ ነውና። ኧረ እንዲያውም በአንቀጿ ውስጥ “ትሩፋቱ” ሲባል የተፈለገው ነብዩን ﷺ ለማለት ሲሆን “እዝነቱ” የሚለው ደግሞ “ዐሊይን ነው” የሚል ዘገባ ከኢብኑ ዐባስ እንደተላለፈ አልኸጢብ እና ኢብኑ ዐሳኪር ገልፀዋል። [ሩሑል መዓኒ፡ 6/133] ከነሱ ቀጥሎ የመጡት ታቢዒዮችም እንዲሁ እነሱስ ባይኖሩ
إظهار الكل...
ያቁት አልሐመዊ ከሙዞፈር ጋር አንድ ዘመን የኖሩ በመሆናቸው ዘግይተው መጥተው ስለ ንጉሱ አድናቆት ብቻ ከሰፈሩ ፀሐፊዎች በተሻለ ምስክርነታቸው ሚዛን የሚደፋ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሙዞፈር ፃድቅ እንኳ ቢሆን፣ አይደለም እንጂ መውሊድ በሱ የተጀመረ ቢሆን እንኳ ይሄ ከቢድዐነት አያወጣውም፡፡ ከነቢዩ - ﷺ - ህልፈት በኋላ ስድስት መቶ አመታት ዘግይቶ የሚጀመር አዲስ ፈሊጥ ጥመት እንጂ ፈፅሞ ፅድቅ ሊሆን አይችልም፡፡ እምነታችን ከቁርኣንና ከሐዲሥ የሚቀዳ እንጂ እንደ ሌሎች እምነቶች ማንም እየተነሳ አዳዲስ ነገሮችን የሚለጥፍበት አይደለም፡፡ Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) (ጥቅምት 08/2013) የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ። https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ቻናሉን ይቀላቀሉ። ለሌሎችም ያሰራጩ።

መውሊድ በማን ተጀመረ? በሙዞፈር ወይስ በ“ፋጢሚያ” ሺዐ? ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሰሞኑን አሕባሾች መውሊድን በማስተዋወቅ ላይ ተጠምደው እያየን ነው። ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ መውሊድ “ታላቅ ዓሊም፣ ተቂይ፣ ሷሊሕና ጀግና በነበሩት” ንጉስ ሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚል ነው። ሙዞፈር የሞተው ከ812 አመት በፊት በ630 ሂጅሪያ ነው። ሰዎቹ ሙዞፈር ላይ ችክ የሚሉት እጅግ አፈንጋጭ በሆኑት “ፋጢሚያ” ሺዐዎች ነው የተጀመረው የሚለውን ለመሸሽ ነው። እርግጥ ነው መውሊድ የተጀመረው በሙዞፈር ነው ያሉ አሉ። ሌሎች ደግሞ የለም ትንሽ ቀደም ብሎ በሸይኽ ዑመር አልመላ (571 ሂ.) ነው የሚሉም አሉ። ሁለቱም ሃሳቦች ግን በማንም - እደግመዋለሁ - በማንም ቢጠቀሱ ፈፅሞ ስህተት ናቸው፡፡ ምክንያቱም ከዚያ በፊት በአፈንጋጭ ሺዐዎች እንደተጀመረ የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉና፡፡ ማስረጃ ከቀረበ በኋላ ለማንም ሙግት እጅ አንሰጥም፡፡ ለሐቅ እጅ ለሚሰጡ፣ ከመንጋዊ አስተሳሰብ አግልለው ህሊናቸውን ለሚያከብሩ ሰዎች ብቻ ማስረጃዎቹን አሰፍራለሁ። 1. ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.):— በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ ተጠቅሶ የተገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ነው። የኢብኑል መእሙን አባት የ“ፋጢሚያ” ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር። የታሪክ ፀሐፊው አልመቅሪዚ (845 ሂ.) ኢብኑል መእሙንን በማጣቀስ በ517 ሂጅሪያ የተካሄደውን መውሊድ አስመልክተው እንዲህ የሚል መረጃ አስፍረዋል፡- “የ‘ፊጢሚያ’ ገዢዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዘባቸው ዓውደ-አመታት” ካሉ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- ለፋጢሚያ ገዢዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውደ አመታት አሏቸው። እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ - ﷺ - ልደት (#መውሊድ) ቀን፣ የዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁንና)፣ የፋጢመቱ ዘህራእ ዐለይሃ ሰላም ልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያሉ ይዘረዝራሉ። ከውስጣቸው የፋርስ መጁሳዎች፣ የሺዐና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ትንሳኤ ያሉ በዓላት የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው የተዘረዘሩት። [አልኺጦጥ፡ 1/436] መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ። በሌላ ኪታባቸው ላይም “በረቢዐል አወል ላይ (የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላሉ። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 2/48] ሌላ ቦታ ደግሞ “ረቢዐል አወል ላይ የነብዩን - ﷺ - ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ልምድ ሆኖ ቀጠለ” ይላል። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 3/101] ልብ በሉ! ይህንን መረጃ የሰጠን ኢብኑል መእሙን የሞተው መውሊድን ጀመረ የሚባለው ንጉስ ሙዞፈር ገና በተሾመ በአመቱ ነው፡፡ እያስተዋላችሁ!! 2. ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.):— ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው። ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል። ኋላ በሶላሑዲን አልአዩቢ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል። በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል። በ“ፋጢሚያዎች” መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ ደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል። “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው። ለናሙና ያክል ቀንጨብ ላድርገው፡- ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبي صلى الله عليه وسلم، ومولد أمير المؤمنين علي بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر “ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መስሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ- ﷺ - መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ ዐለይሃ ሰላም መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን - ዐለይሂመ ሰላም - መውሊድና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው፡፡ …” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219] 3. አሕመድ ብኑ ዐሊይ አልቀልቀሸንዲ (821 ሂ.):— ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ጉባዔ ሲያወሩ “ሶስተኛው ጉባዔ በረቢዐል አወል ወር 12ኛ ቀን ላይ በነብዩ - ﷺ - መውሊድ ላይ የሚኖረው ጉባዔ ነው” ካሉ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካሉ፡፡ [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576] ስናጠቃልል የመውሊድ በዓል ጀማሪዎች “ፋጢሚያ” ሺዐዎች እንደነበሩ ለጥርጣሬ ቀዳዳ የማይሰጡ መረጃዎች አሉን ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ! የመጨረሻው የ“ፋጢሚዮች” ንጉስ አልዓዲድ ሊዲኒላህ የሞተው በ 567 ሂጅሪያ ነው፡፡ ሱፍዮች “መውሊድ ጀመረ” የሚሉት ሙዞፈር የተሾመው ደግሞ ከ 19 ዓመታት በኋላ በ586 ሂ. ነው፡፡ ይህንን ተጨባጭ ታሪካዊ መረጃ እያየ “አይኔን ግንባር ያርገው” የሚል ካለ የለየለት ቂላቂል ነው፡፡ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ የሚጠቁሙ ግልፅ ማስረጃዎች እየቀረቡ እያዩ “እከሌ እንዲህ ብለዋል” “እንቶኔ እንዲህ ብለዋል” እያሉ ነገር መዘብዘብ እራስን መሸወድ ብቻ ነው፡፡ “ሙዞፈር ነው የጀመረው” ያሉት እንደ ሲዩጢ ያሉ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ ያጣቀሱት ተጨባጭ ማስረጃ የለም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ መውሊድ በሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚሉ አካላት ኢብኑ ከሢርን ሲያጣቅሱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ኢብኑ ከሢር የሙዞፈርን መውሊድ ከመጥቀሳቸው ውጭ “ጀማሪ ነው” አላሉም፡፡ መቅሪዚ እንደጠቀሱት እነዚህ የሺዐዎቹ መውሊዶች ኋላ ላይ ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋርጠው ነበር፡፡ [አልመዋዒዝ ወልኢዕቲባር፡ 1/432] ኋላ ላይ በተተካው የ“ፊጢሚዮቹ” ንጉስ አልኣሚር ቢአሕካሚላህ (524 ሂ.) ነው የተጀመሩት፡፡ ልብ በሉ! ይህ ዳግም የተጀመረው መውሊድ እራሱ ከሙዞፈር መውሊድ በዓል ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሙዞፈር መወለድም የቀደመ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሱፍዮች መውሊድን ጀመረ የሚሉትን ሙዞፈርን ቅዱስ አድርገው የሚጠቅሱት ወይ ታማኞች ስላልሆኑ ነው፡፡ ወይ ደግሞ በሰውየው ላይ የቀረቡ ሂሶችን ያልተመለከቱ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የሚያደርጉት ለገበያቸው የሚሆናቸውን እየመረጡ ማቅረብ ነው፡፡ ንጉሱ በከፊል የታሪክ ፀሐፊዎች ከመወደሱም ጋር የሰላ ሂስ የሰነዘሩበትም አሉ፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡- ያቁት አልሐመዊ ይባላሉ፡፡ በ626 ሂ. የሞቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁር ናቸው፡፡ ሙዞፈርን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡- “የዚህ ሰውየ ባህሪ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው፡፡ እሱ ሲበዛ በዳይ፣ ህዝቦቹ ላይ ጨካኝ እንዲሁም አግባብ ባልሆነ መልኩ ገንዘቦችን የሚወስድ ነበር፡፡ ይህ ከመሆኑ ጋር ለድሃዎች የሚቸርና ለእንግዶች በብዛት የሚሰድቅ ነበር፡፡ እጅግ በርካታ ገንዘቦችን አፍስሶ ከከሃዲዎች እጅ ምርኮኞችን ነፃ ያወጣ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ባለቅኔው እንዲህ ይላል፡- ‘ልክ እንደዚያች ወጥ ረገጥ በብልቷ ነግዳ ለበጎ ስራ የምትሮጥ መስሚያ ካለሽ ወዮ ላንቺ! ምፅዋትሽ ይቅር ይልቅ አትዘሙቺ፡፡’ ” [ሙዕጀሙዑል ቡልዳን፡ 1/138]
إظهار الكل...
በእኛ እና በአሕባሾች መካከል ክፍል 3 ታላቅ ርእሰ ! "ኢስተቓሣ እና ዱዓእ" የአህሉሱና አቋም ምን ይመስላል? የአሕባሾችና የመሰሎቻቸውሥ? በርእሱ ላይ የሚያቀርቧቸው ሹብሃዎች (ማደናገሪያዎች) ከበቂ መልሦቻቸው ጋር!!! https://t.me/Muhammedsirage/1967
إظهار الكل...
በእኛ እና በአሕባሾች መካከል ክፍል 3.mp312.39 MB
መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ? ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ ቀደም ብየ ገልጬ ነበር። አሁን ደግሞ የጀመሩበትን አላማ ልጠቁም እወዳለሁ። በግብፅ የአስዩጥ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶክተር ሐሰን ኢብራሂም ሐሰን እና በትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትምህርቶች ገምጋሚ የነበሩት ጦሀ አሕመድ ሸረፍ በጋራ በመሆን “አልሙዒዝ ሊዲኒላህ” በሚል ርእስ ስለ“ፋጢሚያዎቹ” ንጉስ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አንድ መፅሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ “አውደ - አመታትና በዓላት” በሚል ርእስ ስር ያሰፈሩት ሃሳብ “መውሊድ ለምን አላማ ታስቦ ነው የተጀመረው?” ለሚለው ጥያቄ ጥሩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡- “(ንጉሱ) አልሙዒዝ በሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ቀን፣ በነብዩ ﷺ መውሊድ ቀን፣ በረጀብ መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በሸዕባን መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በረመዷን መጀመሪያ ቀን ከሚያስተዳድራቸው ህዝቦች ጋር ይካፈል ነበር፡፡ ይህን የሚያደርገው * የሱኒ፞ዮቹን ነፍስ ለማረጋጋት፣ * እንዲሁም በሱኒ፞ዮች መርሆዎችና በሺዐዎች እምነቶች መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ በማሰብ ነው፡፡ * በተጨማሪም ይሄ አልሙኢዝ ሊዲኒላ፞ህ የንግስና ዘመኑን ያሸበረቀባቸውን እነዚህን በዓላት የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ እምነቶችን ለማሰራጨት ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሑሰይንን ዝክር ህያው ለማድረግ የዓሹራእ ቀንን ያከብር የነበረው፡፡ ልክ እንዲሁ የበርካታ አኢማዎችን መውሊድና ስልጣን ላይ ያለውን ገዢ መውሊድ በሚልም (የራሱን ልደት) ያከብር ነበር፡፡ * ልክ በዚህ መልኩ የህዝቦቹን ትኩረት ወደሱ ለመሳብና የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ መርሆዎችን ለማሰራጨት እነዚህን በዓላት እንደ መዳረሻ ይጠቀምባቸው ነበር፡፡” [አልሙዒዝ ሊዲኒላህ፡ 284] ስለዚህ መውሊድ የተጀመረው ለፖለቲካዊ ትርፍ እና የሺዐን እምነት ለማስፋፋት ሲባል ነው ማለት ነው፡፡ የክርስቲያኖቹ ገና፞፣ ሁዳዴ፣ …፣ የራፊዷዎቹ የዓሹራእ በዓል፣ ገዲር ኹም፣ …፣ የእሳት አምላኪ መጁሳዎቹ ነይሩዝ ይከበሩ ከነበሩት በዓላት ውስጥ ነበሩ፡፡ የህዝብን ትኩረት ለመሳብ፣ ቅሬታ ውስጥ ያሉ ሱኒ፞ዮችን ልብ ለማረጋጋት በሂደትም ወደራሱ የሺዐ እምነት ሰዎችን ለማስገባት በማለም ነው፡፡ ቀስ እያለ በጉልበት ወደ ሺዐ እምነት መጣራት እንደተጀመረ ይታወስ፡፡ ስለዚህ አላማቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡትን የህዝብ ግፊቶች በማርገብ ይከተሉት የነበሩትን የኢስማዒሊያ ሺዐ እምነት ማስፋፋት ነበር ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ዛሬ ሱፍዮች እንደሚያስቡት “የወሃብዮች” ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ከላይ እንዳየነው የታሪክ አጥኚዎች ድምዳሜ ነው፡፡ የመውሊድ ስርኣቱ ለእኩይ አላማ የታለመ ስለነበርም ነው ሶላሑዲን አልአዩቢ “ፋጢሚዮችን” አሸንፎ ግብፅን ሲቆጣጠር አስቁሞት የነበረው፡፡ መቼም እሱንም “ወሃቢ ነው” እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የተጀመረው ኋላ በመምሉካውያን ጊዜ ነው፡፡ የመውሊድ ተግባር ዳግም ሲመለስ ሌሎቹ መውሊዶች የሌላ እምነት መሰረት ያላቸው ወይም ሺዐ-ዘመም ስለነበሩ በሱኒ፞ው አለም ገበያ አላገኙም፡፡ ---------------------------------- “መውሊድ፤ ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት” ከሚለው መፅሐፍ ተነካክቶ የተወሰደ አዘጋጅ፦ ሙሐመድ አሕመድ ሙነወር https://t.me/Daru_Sunnah
إظهار الكل...
Daru Sunnah

📚#ليكن هدفنا فهم الكتاب والسنة على منهج السلف والعمل بما فيهما!

ማስታዎሻ ሶፈር/13/1443/ ቀጣዩ ወር ረቢዑል አወል ነዉ በዚህ ወር የሺርክ ሁሉ መነሃሪያ የሆነዉ መዉሊድ ይከበርበታል። ስለሆነም ኡመቱል ኢስላምን ከሺርክ ለማዳን ወሩ ከመግባቱ በፊት መዉሊድን በማስረጃ በማዉገዝ ላይ እንዝመት። ❌መዉሊድ የሙስሊሞች በዓል አይደለም❌
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.