cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Daily News/ዜና

በዚ ቻናል በሀገራችን እና በአለማችን ውስጥ የሚከሰቱ ማንኛውነም ኩነቶችን ያገኙበታል ።you can get any updated news here .📡

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
170
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል። በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ። ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል። ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ። 1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et 2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et 3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot 4) በ9444 SMS ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። (የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ) #Pass_it_on:- tikvahethiopia
إظهار الكل...
💥🔥የጫማ ማስቀመጫ 👌✅ 🥾በር ላይ ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰቀል 🥾 ሚስማር ሳይመቱ በር ላይ የሚሰቅሉት 🥾17 ጫማወችን የሚይዝ 👉 በሚፈልጉት ቁመትና የጫማ ብዛት በትዛዝ እንሰራለን 📞 0970050032 📞0970050025 Telegram @romisdesign
إظهار الكل...
💂‍♀#Bonnet (ሻሽ) 🪅🔥ፀጉርዎ እንዳይሰባበር የሚረዳ 🪅🔥የፀጉር ስታይል እንዲቆይ የሚያደርግ 🪅 🔥 ለፀጉር ድርቀት ጥሩ መፍትሄ 🪅🔥የፀጉር ስታይል ሳይበላሽ እንዲቆይ የሚያደርግ 🪅🔥 የፊት ብጉር እንዳይባባስ የሚረዳ 🪅🔥ውብ የሆኑ ዘመናዊ ሻሾች በማይታመን ዋጋ💸 💠 በብዛት ለሚወስዱ ልዩ ፓኬጅ አዘጋጅተናል❕ ✅ይደውሉ ☎️ +251970050032 ☎️ +251970050025 📥 @romisdesign
إظهار الكل...
ጫማ ሰርቀሻል በሚል ምክኒያት የቤት ሰራተኛቸዉን ቢላ በማጋል ጉዳት ያደረሱ ጥንዶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ በሆሳዕና ከተማ ሴች ዱና ቀበሌ በትዳር ተጣምረው የሚኖሩት ጥንዶች ማሞ ሀይሉ እና አበባየሁ ሀንዴቦ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጫማ ሰርቀሻል በሚል ምክኒያት የቤት ሰራተኛቸዉ የሆነችዉን ማርታ ሱሊቶ ቢላ በማጋል ሰዉነቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የሆሳዕና ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዋና ኢ/ር ካሳ ሊሊሶ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል። ወንጀሉ የተፈጸመው ጥር 4 2014 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ጫማ ሰርቀሻል በሚል ምከንያት ጥንዶቹ የቤት ሰራተኛቸዉን ቢላ በእሳት በማጋል በሰዉነቷ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተጠቁሟል ። በእለቱ ጥቆማ የደረሰዉ የሆሳዕና ከተማ ፖሊስ በቦታዉ በመገኘት ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አዉሏል። በተበዳይ ላይ የደረሰዉ ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ወደ ወላይታ ሶዶ ሆስፒታል ለተጨማሪ ህክምና መላኳን ኢ/ር ካሳ ሊሊሶ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።
إظهار الكل...
🧰 #የቦርሳና_የጌጣጌጥ _መያዣዎች ❇️ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰሩ የጌጣጌጥ እና የቦርሳ መያዣዎች ❇️እጅግ ያማሩ ❇️በፈለጉት ቦታ የሚቀመጥ ❇️በፈለጉት የከለር ምርጫ 📌 በብዛት ለሚወስዱ ልዩ ፓኬጅ አዘጋጅተናል ይደውሉ ☎️ +251 970050032 ☎️ +251 970050025 📩 @ro118l
إظهار الكل...
እንግሊዝ ከኢትዮጵያ የተዘረፉ ታቦታትን አልመልስም ማለቷ ተሰማ በ1860 ዓ.ም. የተካሄደውን የመቅደላ ጦርነት ተከትሎ የተዘረፈ የቤተ ክርስትያን ታቦት ለመመለስ እንግሊዝ አልስማማም ብላለች ተባለ። በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ሙዚየም ተቀምጦ የሚገኘውን ታቦት የኢትዮጵያ መንግስት ለማስመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተከትሎ በቤተ መዘክሮቹ በኩል ቅርሱን በጊዜያዊነት ከማዋስ በስተቀር መመለስ አይታሰብም ማለታቸውን አትላንታ ብላክስታር ዘግቧል። በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንም ሆነ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው 8 ታቦታት በብሪትሽ ሙዚየም የሚገኙ ሲሆን የሙዚየሙ አስተዳደር ቅርሶቹን መመለስ በሙዚየሙ ህግ አይፈቀድም ማለታቸው ተሰምቷል። ይሁን እንጂ ሀሳቡን የተቃወሙ ሰዎች ሙዚየሙ ቅርሶቹን ለባለቤቶቹ በመመለስ የእንግሊዝና ኢትዮጵያን የቆየ ግንኙነት ማጠናከር ያስችላል በማለት እየሞገቱ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በመቅደላ ዘመቻ ወቅት የተዘረፉ የከበረ ዘዉድ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጥንታዊ የእጅ ጽሁፍ ዉጤቶችና መስቀሎችን ከእንግሊዝና ከሌሎች ሀገራትም ማስመለሷ የሚታወስ ነው። ከእዚሁ ጋር በተያያዘ ለቅኝ ግዛት ወደ አፍሪካ ተመው የነበሩ የአውሮፓ ሀገራት ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አጥጋቢ ባይሆኑም ተመሳሳይ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው ተብሏል። (አዲስዘይቤ)
إظهار الكل...
ለአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት በገዋኒ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪት የተፈረጀውን የሕወሓት ቡድን ከአፋር ምድር በማፅዳት ከፍተኛ ጀብድ የፈፀሙት የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት በገዋኒ ወረዳ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ በአፋር ክልል የህወሃት ቡድንን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ተአምራዊ ጥቃት ከፈፀሙት የፀጥታ ኃይሎች መካከል የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት አንደኛው መሆኑ ይታወቃል። ይህ ሰራዊት ህወሃት በሁሉም ጦርነት በከፈተባቸው ግምባሮች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ታላቅ ጀብዱ ሰርቷል። ከአፋር ክልል ከሁሉም ጫፍ፣ ከሁሉም ወረዳዎች የዘመተው ሕዝባዊ ሰራዊት የአያት ቅድመ አያቱን የጀግንነት ታሪክ በመድገም በሁሉም ግምባሮች ታሪክ ሰርቷል ሲል የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል። ሕዝባዊ ሰራዊቱን ወደግምባር ከላኩት መካከል በሆነችው ገዋኒም ታጋዮች በድል ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
إظهار الكل...
በቦረና በተከሰተው ድርቅ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት፣ በዞኑ በሚገኘው ቦረና ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ብርቅዬ የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጸ። በድርቁ ምክንያት በአካባቢው ከፍተኛ የግጦሽና የውኃ እጥረት በመኖሩ እንስሳቱ ለአደጋ መጋለጣቸው ተሰምቷል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ የዱር እንስሳት ፓርኮች እና ኢኮቱሪዝም ዳይሬክተር መሐመድ ኑር ጀማል ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያና ኬንያ ብቻ ከሚገኙ የሜዳ አህያ ዝርያዎች አብዛኞቹ በቦረና ብሔራዊ ፓርክ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ አሁን ላይ በዞኑ ባለው ድርቅ ምክንያት የዱር እንስሳቱ የውኃ እጥረት እንዳጋጠማቸው አመላክተዋል። (አዲስ ማለዳ)
إظهار الكل...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተበታትኖ የወጣውን የጠላት ኃይል እየተከተልን ነው አሉ ሙሉ በሙሉ ሸዋ፣ የኬሚሴ እንዲሁም ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በርካታ የደቡብ ወሎ ዞን አካባቢዎች ነፃ መውጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍም ድሉ ቀጣይ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰራው ጠንካራ ሥራ ጠላት የዘረፈውን አራግና ተበታትኖ ነው የወጣው ሆኖም የጠላት ኃይልን እየተከተልን እየደመሰስነው ነው ብለዋል፡፡ እየከፈልን ያለነው መስዋዕትነት ልንደፍር ልንሰርቅና ሌሎች ወንጀሎችን ልንፈፅም ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማዳን ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ አብዛኛው የአማራ ክልልና የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥቷል፤ ድሉ ይቀጥላል እናንተም ታሸንፋላችሁ ሲሉ የወገን ጦርን አብስረዋል፡፡
إظهار الكل...
ሰበር ዜና! ደሴ፣ ኮምቦልቻና ባቲ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጡ ታሪካዊቷ የደሴ ከተማና የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ፣ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል። በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ በምሥራቅ ግንባር ባቲን፣ቀርሳን፣ ገርባንና ደጋንን ነጻ ያወጣ ሲሆን በሐርቡ ግንባር ደግሞ ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.