cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Abu Hiba (አቡ ሒባ)

❶. የመልካም ቀደምቶቻችንን ፋና በመከተል እስልምናችንን የምንማማርበት፣ ❷. ቁርኣን እና ሐዲሥ ነክ መጣጥፎች፣ ➌. እንዲሁም አጫጭር የሰለፎች ንግግርና ምክሮች።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 934
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+107 أيام
+3830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሶለዋት ➝ የአላህን እዝነት ያስገኛል‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት በውዱ ነብያችን ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረድ በጁሙዓ ዕለት ከሚወደዱ ዒባዳዎች መካከል አንዱ ነው። ሶለዋት ሱና ብቻ ሳይሆን የአላህን ትእዛዝ መታዘዝ ብሎም፤ የቂያም ቀን የርሳቸውን አማልጅነት ማገኛም መንገድ ነው። - በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የአላህን እዝነት ያስገኛል። አላህ ኸይር ነገር በርሳቸው ላይ አወረደ፤ እኛንም ከዚህ ኸይር ተጋሪዎች አደረገን። ኣንድ ሶለዋት ስናወርድ፤ አላህ በእኛ ላይ ዓስር ሶለዋት ያወርዳል። ከአላህ ዘንድ ለፍጥረታት የሚወ'ረድ ሶለዋት ደግሞ ከጨለማ ያወጣል። ብርሓንን ያስገኛል። የኣላህን እዝነትና ውዴታን ያጎናጽፋል። * በጁሙዓ ዕለት፣ ተሽሑድ ላይ፣ የርሳቸው ስም ሲነሳ፣ ኣዛን ሲባልና መስጅድ በምንገባበት ጊዜ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረዱ ይበልጥ ሙስተሓብ ከሚሆኑባቸው ወቅቶች ናቸው። √ ሶለዋት አጭር ድካም ትልቅ ትርፍና የተነባበረ ፀጋ! «በእኔ ላይ ኣንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ ዓስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል።» ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምንጭ:-📒ሙስሊም (384) «مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا.» √ ሶለዋት ከነብዩ ጋር በቀጥታ ሰላምታን ያስገኛል። «ማንም ሰው ለእኔ ሰላምታ (ሶለዋት) ካደረገ፤ አላህ ሩሔን ይመልስና ሰላምታውን እመልስለታለሁ።» ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምንጭ፦📒ሶሒህ አቡ ዳውድ (2041) «ما من أحدٍ يسلِّمُ عليَّ إلَّا ردَّ اللَّهُ عليَّ روحي حتَّى أردَّ عليْهِ السَّلامَ.» √ በተቃራኒው ደግሞ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማድረግን የሰሰተ፤ በራሱ ላይ ኸይር ነገርን ከማግኘት ሰስቷል። በነፍሱ ላይ ነፍጓል። ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦ «ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ፤ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው።» ምንጭ፦📒ሶሒሁ ቲርሚዚ (3546) «البخيلُ الذي من ذُكِرْتُ عندَه فلم يُصَلِّ عليَّ.» ✔️ የሶለዋት ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ አላህ ራሱ እኔ አወርዳለሁ፤ እናንተም ኣማኞች ሁሉ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርዱ የሚል ትዕዛዛዊ–መልክትን በቁርኣን ነግሯል። إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا۝ አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ 📒አል-ኣሕዛብ (56) * ✔️ሶለዋት የምናወርደው እንዴት ነው⁉️ ——— ከዕብ ቢን ዑጅረህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦ إنَّ النبيَّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ خَرَجَ عَلَيْنَا، فَقُلْنَا: يا رَسولَ اللَّهِ، قدْ عَلِمْنَا كيفَ نُسَلِّمُ عَلَيْكَ، ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደኛ መጡ። የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአንተ ላይ ሰላምታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አወቕን። فَكيفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ؟ “ሶለዋት የምናወርደው'ስ እንዴት ነው?” ብለን ጠየቕናቸው። قالَ: فَقُولوا እንዲህ በማለትም አስተማሩን፦ «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.» ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (6357) “አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሐመድ” || የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me//AbuHiba
إظهار الكل...
Abu Hiba (አቡ ሒባ)

❶. የመልካም ቀደምቶቻችንን ፋና በመከተል እስልምናችንን የምንማማርበት፣ ❷. ቁርኣን እና ሐዲሥ ነክ መጣጥፎች፣ ➌. እንዲሁም አጫጭር የሰለፎች ንግግርና ምክሮች።

00:28
Video unavailableShow in Telegram
5.51 MB
✍«ሓቀኛዉ ሞት፣ መራሩ እዉነት ሲጎበኘን እንዳንረሳው ይመስላል። በቅርቧ እንዳንፈዝ፣ እንዳንደነዝዝ፤ ብቅ እያለ ያስታውሳል። ሰርክ ላይ ያለች ነፍስን ይመክራል። ሆኖም ስለሞት ያልታሰበበት ቀን ኩሉ ያሞኛል። ኳስ በመሬት እያለ ያነሆልላል። ይህችን ዓለም ጥቂቶች ብቻ ኣስታዋሽ ሆነው፤ ሕይወትን እንደ መንገድ በድር`ብቡ ይገፏታል፡፡»
إظهار الكل...
✍ከአቡበከር አስ-ሰዲቅ፣ ከዑመር ኢብኑ-ል-ኸጣብ፣ ከዓሊይ ኢብን ኣቢ ጧሊብ፣ ከዑስማን ኢብኑ ዓፋን፤ እንዲሁም ከሰሓባዎች (ረድየል'ሏሁ ዓንሁም) በላይ ነብዩን (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የወደደ የለም። ወደፊትም አይኖርም። ማስተንተን ለቻለ አዕምሮ ላለው ሰው ከዚህ በላይ ማስረጃ አያስፈልግም። መውደድ በመከተል ይገለፃል። ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነዉ። ጥመት ሁሉ የእሳት ነዉ። መውሊድ ሰርጎ ገብ በዓል ነው። መውሊድ ቢድዓነቱ ይነገራል!
إظهار الكل...
00:48
Video unavailableShow in Telegram
ከአካላዊ ልኬት በላይ ጉልበት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍አላህ የሰው ልጆችን ወደ ምድር በብቸኝነት እርሱን ብቻ እንዲያመኩት ከመላኩ ጋር፤ ለሰው ልጅ በአካልም ሆነ በመንፈሳዊ መርዳት ወይ ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለማስተማር አላህ በዚህ ዩኒቨርስ ላይ ብዙ ፍጥረታትን አስገኝቷል። - ጥቃቅን ሆኖም አስደናቂ፣ መጠናቸው ትንሽ ቢሆንም ልዩ የማሰብ ችሎታ ያላቸውና ከአካላዊ ልኬታቸው በላይ የሆነ፣ ጉልበት ያላቸው፤ ተዓምራቱን አመላካች የአላህ ፍጥረታት...🐜 የጉንዳን ትጉነትን፣ የመረጃ ፈጣንነትን፣ የእቅድ አፈፃፀምን፣ ከጉልበት በላይ ብልሃትን፣ ማህበራዊ አወቃቀርን፣ የስራ ስነ-ምግባራቸውንና አንድነታቸውን የሰው ልጅ በትክክል መመልከት ከቻለ፤ በጉንዳን ውስጥ ጥልቅ ግንዛቤ አለ። * በእርግጠኝነትም አላህ በስማቸው አንድን ምዕራፍ በከንቱ አልሰየምም። በቁርኣን ውስጥ ሱረቱ አን-ነምል (የጉንዳን ምዕራፍ) የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ጉንዳኖች፤ በሱራው ላይ አላህ የጉንዳንን አስተዋይ ንግግር እና አርቆ አስተዋይነት በአንድ አንቀፅ አጉልቶት እናገኛለን፦ حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ۝ በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ። ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አንዳይሰባብሯችሁ» አለች። 📒አን-ነምል (18) በዚህ አስደናቂ ንግግሯዋም ጉንዳን፣ ነብዩሏህ ሱለይማንን (ዓለይሂ ሰላም) በሳቅ ፈገግ አሰኝታለች። || የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me//AbuHiba
إظهار الكل...
3.72 MB
➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ክፍል፦ 287 ➊) «በጠዋትም ይሁን ከሰዓት ወደ መስጅድ የሚመላለስ ሰው፤ በተመላለሰው ልክ አላህ ከጀነት የሆነን መስተንግዶ (ማረፊያን) ያዘጋጅለታል።» ምንጭ፦📒ሶሒሁል ጃሚዕ (6399) «من غدا إلى المسجدِ أو راح، أعدَّ اللهُ له نُزُلًا من الجنَّةِ كلما غدا أو راح.» * ➋) «በጀመዓ የሚሰገድ ሶላት፣ በግል ከሚስገደው ሶላት በ27 እጥፍ ይበልጣል።» ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምንጭ፦📒ሶሒሁል ጃሚዕ (3819) «صَلاةُ الجَمَاعَةِ أَفضَلُ مِنْ صَلاةِ الفَذِّ بِسَبْعٍ وَعِشْرِينَ درَجَةً» * ❸) «ከሩኩዕ ወይም ከሱጁድ ላይ ከኢማሙ በፊት ራሱን ቀና የሚያደርግ ሰው፤ አላህ ጭንቅላቱን የኣህያ ጭንቅላት ወይም ገፅታውን የኣህያ ገፅታ እንዳያደርግበት አይሰጋምን?» ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምንጭ፦📒ቡኻሪ (691) «أما يخشى الَّذي يرفَعُ رأسَهُ قبلَ الإمامِ راكعًا أو ساجدًا أن يحوِّلَ اللَّهُ رأسَهُ رأسَ حمارٍ أو صورتَهُ صورةَ حمارٍ.» || የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me//AbuHiba
إظهار الكل...
Abu Hiba (አቡ ሒባ)

❶. የመልካም ቀደምቶቻችንን ፋና በመከተል እስልምናችንን የምንማማርበት፣ ❷. ቁርኣን እና ሐዲሥ ነክ መጣጥፎች፣ ➌. እንዲሁም አጫጭር የሰለፎች ንግግርና ምክሮች።

00:50
Video unavailableShow in Telegram
የላቀ አፈጣጠር‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍የሰው ልጅ ኣፈጣጠር መለኮታዊ ኃይሉንና ጥበቡን የሚያሳይ ከታላላቅ የአላህ ተአምራት አንዱ ነው። አላህ የፈጠረው ነገር ሁሉ ከግዙፉ ኣጽናፍ እስከ ትንሹ ፍጡር ድረስ በጥበብ፣ በዓላማና በውበት የተሞላ ነው። - በዚህ የኣፈጣጠር ውበት ላይ የሰው ልጅ በትክክል ማገናዘብ ከቻለ፤ የፍጥረተ ዓለሙን ውስብስብነትና የአላህን የአፈጣጠር ሃይል ይረዳል። በአፈጣጠሩ ይደነቃል። ፍጹማዊ ብቸኛ ተመላኪነቱንም ያፀድቃል። √ አላህ የሰውን ልጅ አፈጣጠር የእድገት ደረጃዎች ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦ ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ۝ ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡ አል-ሙእሚኑን (14) * እያንዳንዱ የአፈጣጠር ሂደት በአላህ ትእዛዝ የሚመራ ውስብስብ ተዓምራዊ ለውጥ ነው። የሰው ልጅ የሰውነት ክፍል በውስጡ ተዘርዝረው የማያልቁ ተዓምሮችን ይዟል። አላህ የመፍጠር ልሕቀቱን የሚገልጹ አል-ኻሊቕ፣ አል-ባሪእ እና አል-ሙሰዊር የተሰኙ 3 ውብ ስሞች አሉት። በእነዚህ ስሞች መሰረት በዚች ምድር ላይ ሕልውና ያለው ነገር ሁሉ፤ የአላህ ፍጹም ንድፍ ፈቃድ መገለጫ ነው። || የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me//AbuHiba
إظهار الكل...
7.48 MB
በቁርኣን እንተዎወስ‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ክፍል፦141 ✍ዓይን አይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት በሰዎች ልቦና ውስጥ ውል ብሎ የማያውቅ ወስፍ ያላት፤ በሰበብ እና በእዝነቱ እንጅ በስራ የማትገኝ፣ ዓይኖች የማያውቋት የዓይን መርጊያ፤ መግዣ ዋጋ የሌላት ውድ እቃ። #ጀነት! فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّآ أُخْفِىَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَآءًۢ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ۝ «ይሰሩትም በነበረውሩት (ስራ ሰበብ) ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቃላቸውን ፀጋ ማነኛይቱም ነፍስ አታውቅም።» 📒አስ-ሰጀዳህ (17) || የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me//AbuHiba
إظهار الكل...
Abu Hiba (አቡ ሒባ)

❶. የመልካም ቀደምቶቻችንን ፋና በመከተል እስልምናችንን የምንማማርበት፣ ❷. ሐዲሥ እና ቁርኣን ነክ መጣጥፎች፣ ➌. እንዲሁም አጫጭር የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን ያገኙበታል።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Ai) ሕይወትን ለሰው ልጅ ቀላል፣ ምቹና ቀልጣፋ ከማድረጉ ባሻገር፤ ከዚህ በፊት ይታሰቡ የማይመስሉ ስራዎችን ማከናወኑን ቀጥሏል። ኤ.አይ ያልገባባቸው የሕይወት ዘርፎች የሉም ማለት ይቀላል። በተቃራኒው ደግሞ Ai የሰውን ልጅ የማጥፋት አቅም ይዞ እየመጣም ይመስላል። Ai ይዞልን (ይዞብን) እየመጣ ያለው የሰው ልጅ ውስጣዊ ሃይልን ወደ ውጫዊ ማሽናዊ ሕልውናዎች የመተካት አዲስ ዓለም ነው። ከጥቅሙ ጉዳቱ ማመዘኑ ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋ ይገኛል። አሁን አሁን እየመጡ ያሉ የቴክኖሎጅ ውጤቶች ሰው ጠል ናቸው። - ለዚህም ምዕራቡ ዓለም ላይ በAi ብቻ የሚንቀሳቀሱ አውቶነመስ ተሽከርካሪዎችን መመለከት በቂ ነው። የAI እድገት በዚሁ ከቀጠለ ፍፃሜው የሚሆነው፤ አሁን ላይ የሰው ልጅ ደረስኩበት ያለውን ስልጣኔ በሙሉ ኤ.አይ አጥፍቶ፣ ጠቅልሎ ይውጠዋል። √ አላህ ስለ አውሮፓውያን ሲናገር እንዲህ አለ፦ يَعْلَمُونَ ظَاهِرًا مِّنَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ عَنِ الْآخِرَةِ هُمْ غَافِلُونَ۝ «ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡» አር-ሩም (7) * ✔️አምላካችን አላህ እውነትን ተናገረ። አላህ ግልፅ ያደረገላቸውን ስለቅርቧ ዓለም የተወሰነውን ያውቃሉ። ነገር ግን ለምን እንደተፈጠሩ፣ ለምን ወደዚህች ዓለም እንደመጡ አያውቁም።
إظهار الكل...
ሰው ሰራሽ አስተውሎት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Ai) ሕይወትን ለሰው ልጅ ቀላል፣ ምቹና ቀልጣፋ ከማድረጉ ባሻገር፤ ከዚህ በፊት ይታሰቡ የማይመስሉ ስራዎችን ማከናወኑን ቀጥሏል። ኤ.አይ ያልገባባቸው የሕይወት ዘርፎች የሉም ማለት ይቀላል። በተቃራኒው ደግሞ Ai የሰውን ልጅ የማጥፋት አቅም ይዞ እየመጣም ይመስላል። Ai ይዞልን (ይዞብን) እየመጣ ያለው የሰው ልጅ ውስጣዊ ሃይልን ወደ ውጫዊ ማሽናዊ ሕልውናዎች የመተካት አዲስ ዓለም ነው። ከጥቅሙ ጉዳቱ ማመዘኑ ከግዜ ወደ ግዜ እየሰፋ ይገኛል። አሁን አሁን እየመጡ ያሉ የቴክኖሎጅ ውጤቶች ሰው ጠል ናቸው። - ለዚህም ምዕራቡ ዓለም ላይ በAi ብቻ የሚንቀሳቀሱ አውቶነመስ ተሽከርካሪዎችን መመለከት በቂ ነው። የAI እድገት በዚሁ ከቀጠለ ፍፃሜው የሚሆነው፤ አሁን ላይ የሰው ልጅ ደረስኩበት ያለውን ስልጣኔ በሙሉ ኤ.አይ አጥፍቶ፣ ጠቅልሎ ይውጠዋል። √ አላህ ስለ አውሮፓውያን ሲናገር እንዲህ አለ፦ يَعْلَمُونَ ظَاهِرًا مِّنَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ عَنِ الْآخِرَةِ هُمْ غَافِلُونَ۝ «ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡» አር-ሩም (7) * ✔️አምላካችን አላህ እውነትን ተናገረ። አላህ ግልፅ ያደረገላቸውን ስለቅርቧ ዓለም የተወሰነውን ያውቃሉ። ነገር ግን ለምን እንደተፈጠሩ፣ ለምን ወደዚህች ዓለም እንደመጡ አያውቁም።
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.