cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

AY Bible Club Channel

“ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”” — ኢሳይያስ 40፥8

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
848
المشتركون
+124 ساعات
+197 أيام
+5530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ማን ነው?፣ ክፍል ሶስት ============================ 📖“ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?” — መዝሙር 34፥12 በጎ የሆነውን ነገር ሁሉ ያይ ዘንድ የሚናፍቅ ሰው ሊኖሩት ስለሚገቡ ባሕሪያት መመርመር ከጀመርን እነሆ ሶስተኛ ቀናትን ይዘናል። በዛሬው የሕይወት ስንቃችን “ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤” (መዝ 34፥14) የሚለውን እንመለከታለን። የመልካምነት አንፃር የሆነው ራሱ እግዚአብሔር ነው። እኔ እስካሁን በምድር ላይ በኖርኩባቸው ዘመናት የእግዚአብሔርን ክፉነት ለአንድም ቀን ተመልክቼ አላውቅም። ከመልካምነቱና ከፍቅሩ በቅር ሌላ አላየሁም። ይህ መልካም የሆነው አምላክ ታዲያ ልጆቹ መልካም ይሆኑ ዘንድ ይፈልጋል። ዮሐንስ በመልዕክቱ ላይ “ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።” (3ኛ ዮሐ 1፥11) በማለት መልካምነትን አጉልቶ፣ ክፉነትን ደግሞ አኮስሶ ያስቀምጥልናል። በሌላም ክፍል ላይ ስራችን በመልካምነት የተቃኘ ሊሆን እንደሚገባ ተፅፎ እናነባለን። “መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።” (ኢሳ 1፥17) መልካም ተግባራትን መከወን፣ እውነተኛ የሆነውን ፍርድ መበየን፣ ደካማ ለሆኑት ደግሞ መሞገት ጠቢብነት ነው። ስለዚህ “ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ” የሚለው ሕያው ቃል ዘውትር ከጆሯችን አይለይ። ይህ ሲሆን በምድር ላይ ሰማይን መኖር እንችላለንና። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ባሕሪዬ አንተን ይመስል ዘንድ ስለምትወድድ አከብርሃለሁ። “ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ” የተባለውን ቃል እንድታዘዝ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።
إظهار الكل...
4
ማን ነው?፣ ክፍል ሁለት ============================ 📖“ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?”   — መዝሙር 34፥12 በመልካም ሕይወት ለመኖር የሚናፍቅና በጎ የሆነውን ነገር ለማየት የሚወድድ ሰው ሊኖሩት የሚገቡትን ባሕሪያት እያጠናን እንገኛለን። በዛሬው የሕይወት ስንቃችን “ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።” (መዝ 34፥13) የሚለውን እንመለከታለን። "የውሸት አባት" የተባለው ጠላት ባሕሪውን በሰው ልጆች ላይ ማንፀባረቅ ይፈልጋል። ይህንንም እኩይ ሀሳቡን ተፈፃሚ ለማድረግ ነገሮችን ቀባብቶና ኩሎ ለሰው ልጆች ያቀርባል። የሽንገላን ቃል ከአንደበት ማውጣት ጠቢብነት እንደሆነ በማስመሰል ብዙዎችን ያስታል፤ ያደናግራልም። ለዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” (ኤፌ 6፥11) በማለት ምክሩን የሚለግሰን። ሸንጋይ በሆነው ማንነታችን የምንቀጥልና ለመመለስ ፈቃደኞች የማንሆን ከሆነ መጨረሻችን ጥፋት ነው የሚሆነው። “የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ፤” (መዝ 12፥3) ይህም ሕይወታችንን ረብ አልባና ከንቱ ያደርገዋል። ስለዚህ በክርስቶስ የተሰጠውን ፀጋ በመታመን ከንፈሮቻችንን የሽንገላን ቃል እንዳይናገሩ እንግታ። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ውሸት የማያውቅህ ሁሌም እውነተኛ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። ከንፈሮቼ ደግሞ ሽንገላን እንዳይናገሩ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።
إظهار الكل...
ማን ነው?፣ ክፍል አንድ ============================ 📖“ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?” — መዝሙር 34፥12 በሚቀጥሉት አራት ተከታታይ ቀናቶች “ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?” (መዝ 34፥12) ለሚሉት ጥያቄዎች ከቃሉ አንፃር ምላሽን እንመረምራለን። በዛሬው የሕይወት ስንቃችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወት ለመመላለስና መልካም የተባለውን ነገር ለመመልከት አስፈላጊ ከሆኑት ባሕሪያት መካከል አንደበትን ስለ መግራት እንመለከታለን። “አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥” (ቁ 13) "ምላስ አጥንት የላትም ነገር ግን አጥንትን ትሰብራለች" የሚልን አባባል እንደሰማሁ አስታውሳለሁ። የውስጣችንን ስሜት ገልጠን የምናወጣው በአንደበታችን ነው። ለዚህ ነው ከአንደበታችን ለሚወጡት ቃላቶች ልንጠነቀቅ የሚገባን። ዳዊት ይህንን እውነት በመረዳት ነበር “አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።” (መዝ 141፥3) በማለት ሲማፀን የምንመለከተው። ጠቢቡ ሰለሞንም ይህንን ሀሳብ እንዲህ በማለት ያፀናዋል፦ “አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።” (ምሳ 21፥23) “አንደበትህን ከክፉ ከልክል” የሚለው መልካም ምክር በበጎነት የተሞላን ሕይወት እንድንኖር ያስችለናል። ክፋት በበዛበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከወቅቱ ጋር አብረን የምንነዳ ሳይሆን መልካምነትን አስቀድመን ለአፋችን ልጓም ልናበጅ ያስፈልጋል። ስለዚህ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ውስጥ መልካም የሆነውን አምላካችንን በመታመን አንደበታችንን ከክፉ እንከልክል። የሕይወትም ሽታ የሆነን መልካም ቃል እናፍልቅ። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ክፋት የማያውቅህ መልካም ስለሆንክ አከብርሃለሁ። አንደበቴን ደግሞ ከክፉ እንድከለክል በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።
إظهار الكل...
5👍 1
እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም ============================ 📖“እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።” — መዝሙር 34፥4 ስጋዊ አባት የቤተሰብ ምሰሶ ነው። መላ ቤተሰቡን በትክሻው ተሸክሞ ክፉ ቀንን ያሻግራል። ወላጅ አባቴ እኛን ልጆቹን ለመመገብና የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ለማድረግ በመናፈቅ እንጀራን ፍለገ ከእኛ ተለይቶ መሄድ ነበረበት። ጊዜው ለእኛ እጅግ ከባድ ቢሆንም ጠንካራ የሆነችውን ባለቤቱን ተማምኖ አባቴ ተለይቶን ሄደ። ያን ወቅት በደንብ አስታውሰዋለሁ። ከሰው በታች ሳንሆን የሚያስፈልገን ነገር በሙሉ ይደረግልን ነበር። የእኔና የታናሽ እህቴ ፍላጎት ቢሞላም አባታችን ግን ከቤታችን ጎደለብን። በፈለግነው ጊዜ እንዳሻን በስልክ ብናገኘውም በአካል ግን ልናገኘው አንችልም ነበር። አዎን፣ ቀረብን የምንለው አንዳች ነገር አልነበረም። ነገር ግን ባሻነው ቅፅበት አባታችንን ፈልገን በአካል ማግኘት የማይታሰብ ነገር ነበር። ዳዊት በብዙ ውጣ ውረዶች ያለፈ ሰው ነበር። ቀኝ እጄ የሚለውን ወንድ ልጁን አቤሜሌክን ቢፈልገውም፣ ጦር ይዞ ሊገድለው በመምጣት ልጁን አጣው። የበኩር ልጄ ብሎ የሚጠራውና በትረ መንግስቴን ይቀበላል ብሎ የሚያስበውን ልጁን አምኖንን ቢፈልገውም፣ የገዛ እህቱን ትዕማርን በማስነወር አጣው። ከዕለታት በአንዱ ቀን ዳዊት በሰገነት ላይ ሲመላለስ ሳለ አንዲት ቆንጆን ሴት ይመለከታል፤ ቤርሳቤህን። ታዲያ ዓይኑ አይቷት፣ ልቡ ደግሞ ተመኝቷት አልቀረም። ከእርሷ ጋር በመተኛት ራሱን ደግሞ አጣው። ነገር ግን ዳዊት እነዚህን ነገሮች በሙሉ ቢያጣም አንድን አካል ግን አላጣውም። “እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።” (መዝ 34፥4) እግዚአብሔርን ፈለገው፣ አገኘውም። ከገጠሙት መከራዎች ሁሉ አዳነው። እኛም ዛሬ ብዙ ነገሮችን ልክ እንደ ዳዊት ፈልገን አጥተን ይሆናል። መፈለግና ማጣት የሕይወታችን መገለጫ እስኪመስል ድረስ ዝለን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በሙሉ ልባችን ፈልገን ልናጣው የማንችለው አንድ አካል አለ፤ እግዚአብሔር። እርሱን በፍፁም ልባችን ስንሻው ከቶ ልናጣው አንችልም። ለዚህ ነው “እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።” (ኤር 29፥13) በማለት የማረጋገጫን ቃል የሚሰጠን። ስለዚህ በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን እንፈልገው። እርሱም በመገኘቱ ይባርከናል። ከመከራችንም ያሳርፈናል፤ ያድነንማል። መፈለግ -> ማግኘት -> መዳን! 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ “እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።” በማለት ስለ ሰጠኸን የተስፋ ቃል አከብርሃለሁ። በፍፁም ልቤና ሀሳቤ ደግሞ አንተን እንድፈልግህ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።
إظهار الكل...
6
በአፌ ነው ============================ 📖“እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው።” — መዝሙር 34፥1 እጅግ አድርገን የምንወደው ሰው ከአፋችን አይለይም። ስንገባና ስንወጣ ስሙን እናነሳለን። ስለ እርሱም ለሌሎች ለማውራት ምክንያት አያሻንም። በወሬያችን መሐል ይህ ሰው ከአፋችን አይጠፋም። "የልቤ" የተባለው ዳዊት እግዚአብሔርን የልቡ አደረገው። እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው።” (መዝ 34፥1) ዳዊት “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ” ሲል “ሁልጊዜ” ነው። በአምላኩ ፊት ምስጋናውን ይዞ ለመቅረብ ሁኔታዎችን አልተመለከተም። በእያንዳንዱ ቅፅበት አምላኩን ለመባረክ ናፈቀ። ዛሬም እኛ ምስጋናችን በሁኔታዎች ላይ የታጠረ መሆን የለበትም። ነገር ሰመረ አልሰመረ፣ ቀን ጎደለ አልጎደለ እግዚአብሔርን የመባረክ ልምድ ይኑረን። ምክንያቱም እርሱ ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ ነውና። አምላክነቱንና ጌትነቱን የተረዳው ዳዊት እግዚአብሔርን ከአፉ መለየት የፈለገ አይመስልም። ለዚህም ነው “ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው” በማለት ሲናገር የሚስተዋለው። ይህ ለእኛ ትልቅ ትምሕርትን ይሰጠናል። ኃይል ያለው የእግዚአብሔር ስም ላፍታ እንኳን ከአፋችን ሊለይ አይገባም። ምስጋናችንን እርከን አውጥተን የምናቀርብ ሳይሆን አምላካችን ላደረገልን ለእያንዳንዱ ነገር ከልባችን ዘውትር የምስጋናን መስዋዕት የምናቀርብ እንሁን። ምስጋናውም ዘውትር ከአፋችን አይለይ። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ በሕይወቴ ስላደረከው ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ። “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው” እንዳለው ባሪያህ ምስጋናህ ዘውትር በአፌ ይሁንልኝ ስል እፀልያለሁ። አሜን።
إظهار الكل...
5👍 4
አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን ============================ 📖“አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን።”   — መዝሙር 33፥22 የእግዚአብሔር ምሕረት ወደር የማይገኝለት ነው። የወደቀን አንስቶ ዳግም ያቆማል። የሕሊናን ወቀሳ ሽሮ ነፃነትን ይሰጣል። ይህ የእርሱ ምሕረት በኃጢአት ቀንበር የጎበጠውን ማንነት የሚቀይር ነው። በጠላት ማታለያ ውስጥ ወድቀው አንገት የደፉትን ደርሶ ቀና ያደርጋል። በሰይጣን ወጥመድ የተያዙትን ነፃ ያወጣል። እፍረትን በእረፍት ይቀይራል። ጴጥሮስ ከእየሱስ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት የነበረው ደቀ-መዝሙር ነበር። እየሱስን ከሁሉ ይልቅ እንደሚወድደውና ሌሎች እንኳን ቢክዱት እርሱ ከቶ እንደማይክደው በራሱ እርግጠኛ ነበር። ነገር ግን ጌታችን ለሞት ተላልፎ የሚሰጥበት ሰዓት ሲደርስ ልቡ ከዳው። "አላውቀውም!" እያለ ሶስት ጊዜ ከዳው። “ጴጥሮስም፦ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።” (ማቴ 26፥75) ጴጥሮስ የክህደት ተምሳሌት ሆነ! ነገር ግን የጴጥሮስ ሕይወት ፍፃሜው ይህ አልነበረም። እርሱ የክህደት በትሩን በክርስቶስ ላይ ቢያነሳም ጌታችን ምሕረቱን አደለው። ዳግም ሰው አድርጎ በፀጋው አቆመው። ለትልቅ ኃላፊነትም ሾመው። “...ኢየሱስም፦ በጎቼን አሰማራ” አለው። (ዮሐ 21፥17) ከሃዲ የነበረው ጴጥሮስ አደራ ተቀባይ ሆነ። ከሃዲው ጴጥሮስ...ማለቴ ባለ አደራው ጴጥሮስ። አስደናቂ ምሕረት! ለጴጥሮስ የተገለጠው ይህ ምሕረት በዚህ ብቻ መቼ አበቃና። ራስ የሆነው ክርስቶስ የሚመራት ቤተ ክርስቲያን ዓለት ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ተነገረ። “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” (ማቴ 16፥18-19) ዛሬም በእርሱ ዘንድ ይህ ምሕረት ለእኛ ተገልጧል። የወደደ ሁሉ እንዲሁ በነፃ ያገኘዋል። ብቻ ከልባችን እንዲህ ብለን በፊቱ እንቅረብ፦ “አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን።” (መዝ 33፥22) እርሱ ከሃዲን ታማኝ ባለ አደራ ማድረግን ያውቅበታልና በትላንትናው ስህተቶቻችን ራሳችንን አስረን አናስቀምጥ። ይልቁን ምሕረቱን ታምነን ለከበረው ባለ አደራነት እንዘርጋ። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ከሃዲን ታማኝ ባለ አደራ ማድረግን ስለምታውቅበት አከብርሃለሁ። “አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን።” አሜን።
إظهار الكل...
2👍 1
ያያል ============================ 📖“እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በምሕረቱም ወደሚታመኑ፥”          — መዝሙር 33፥18 እግዚአብሔር አምላክ አንዴ ፈጥሮን ብቻ የሚተወን ሳይሆን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ውስጥ አብሮን የሚሆን ወዳጅ ነው። የዚህ ፍቅር ያየለበት ወዳጅነት መሰረቱ እርሱ ራሱ ነው። ምንም እንኳን በዚህ ግንኙነት ውስጥ ብቸኛው ተጠቃሚ የሰው ልጅ ቢሆንም ዝቅ በማለት አጠገባችን ሆነ። ይህ አምላክ በደስታ ጊዜ ብቻ አብሮን የሚሆን ሳይሆን በሀዘናችንም የማይለየን ነው። በመከራ ስናልፍ፣ በችግር ስንገረፍና በማዕበል ስንዋኝ ዝም የሚለን ሳይሆን ያየናል። የስኬት ተራራችን እጅግ የራቀ ሲመስለንና በሸለቆው ውስጥ ሕይወታችንን ስንመራ ከሰማይ ፀባዖት ሆኖ ይመለከተናል። ጎስቋላነታችን ገኖ ማድረግ የማንፈልገውን ነገር ስናደርግ፣ በተቃራኒው ደግሞ ማድረግ የምንፈልገውን ነገር ሳናደርግ ስንቀር ያየናል። እኛ ራሱ በራሳችን ተስፋ ስንቆርጥ ዓይኖቹን እኛ ላይ በመትከል ተስፋችን ይሆን ዘንድ በፍቅር ዓይኑ ያየናል። አዎን፣ ያየናል! እንባችንን ከዓይናችን ለማበስ ያየናል። መከራችንን ሊሽር ያየናል። ስንክ ሳሮቻችንን ሊያጠፋ ያየናል። ከወደቅንበት አንስቶ በሁለት እግራችን ለማቆም ያየናል። የተሰበረውን ልባችንን ለመጠገን ያየናል። የቆሸሸውን ሕሊናችንን ለማጥራት ያየናል። እንደ ደም የቀላውን ኃጢአታችንን እንደ በረዶ ነጭ ለማድረግ ያየናል። ያደፈውን ማንነታችንን ለማንፃት ያየናል። ለጥያቄዎቻችንን ሁሉ መልስ ለመሆን ያየናል። እዝነታችንን በደስታ ለመለወጥ ያየናል። ሁልጊዜ በፍቅር ዓይኖቹ በስስት ያየናል። ታዲያ ይህ የሚሆነው እርሱን ስንፈራና በምሕረቱ ስንታመን ብቻ ነው። “እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በምሕረቱም ወደሚታመኑ፥” (መዝ 33፥18) ይህ ከእርሱ ዘንድ የተሰጠን ዋስትናችን ነው። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ በፍቅር ሳትሰለች ስለምታየኝ አከብርሃለሁ። አንተን ዘውትር በመፍራትና በምሕረትህ በመታመን እኖር ዘንድ በፀጋህ እርዳኝ። አሜን።
إظهار الكل...
6👍 3
ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ ============================ 📖“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ።” — ራእይ 21፥5 በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ሳለ ጊዜ የማይለውጠው ነገር የለም። ሁሉም ነገር በጊዜ ውስጥ የሚከወን ነው። ጊዜ ይጥላል፤ ጊዜ ያነሳል። ጊዜ ጥሩ ዕድሎችን ይዞ ይመጣል፤ መልካም ነገሮችም ከእኛ በጊዜ ይወሰዳሉ። በጊዜ ውስጥ ሀሴት ይኖራል፤ መሪር ሀዘንንም በውስጡ ይይዛል። በጊዜ ውስጥ ሆኖ ነገር ግን ከጊዜ ውጪ የሚሰራ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ምን አልባት በሕይወታችን ሆነው ያለፉ፣ እየሆኑም ያሉ ነገሮች እንደው በአጋጣሚ የሆኑ ሊመስለን ይችላል። ነገር ግን "የጠጉራችንን ቁጥር" እንኳን ሳይቀር የሚያውቀው አምላክ፣ እርሱ ሳይፈቅድ አንዳች ነገር በሕይወታችን አይሆንም። ባሳለፍነው ዓመት ሁላችንም የተለያየ አይነት ይዘት ያለው የሕይወት ጎዳና ውስጥ አልፈን ይሆናል። እግዚአብሔር የጎደለውን ቤታችንን ሞልቶት፣ የሞተውን ነገራችንን ሕይወት ዘርቶበት፣ የተቆረጠውን ሁኔታችንን ተስፋ ዘርቶበት እነሆ እዚህ ደረሰን። በብቸኝነት የነበርን በሕይወት አጋር ተባርከን፣ በትምሕርት ላይ የነበርን ተመርቀንና የእንጀራ በር ተከፍቶልን፣ ወላጅ የሆንን ደግሞ በልጆች ቤታችን ደምቆልን አዲስ ዓመትን አየን። ክብር ሁሉ በላይ በሰማይ ለእርሱ ይሁን! ደግሞም "ሁሌ ፋሲካ የለም" እንደ 'ሚል ተረቱ፣ ይህን ዓመት በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፍን ወገኖች እንኖራለን። እጅግ አብዝተን የምንወዳቸውን ወገኖች በሞት ያጣን፣ የናፈቅነውን ስኬት የተቀማን፣ ሀሳባችን ከሀሳብነት ፈቀቅ ያላለልን፣ የጨበጥነው የተበተነብን፣ የዘራነው የጠወለገብን ወንድምና እህቶች እንኖራለን። ምንም እንኳን ከባድ ዓመትን ብናሳልፍም እግዚአብሔር መልካም ነው። ሁሌም በስራው ትክክልና ፃዲቅ ነው። "ለምን እንዲህ አደረግህ?" ተብሎ የማይጠየቅ ሉዓላዊ ነው። አዲስ ዓመት፣ አዲስ ጅማሮ! እግዚአብሔር ሕይወትን ሰጥቶን እዚህ ቀን ላይ ደርሰናል። ከሚያልፉት ቀናቶች ጋር አብረን ሳናልፍ ዘመንን ለውጠናል። ክብር ለእርሱ ይሁን! እርሱም በዚህ አዲስ ዕለት እንደዚህ ይለናል፦ “እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” (ራእይ 21፥5) አዎ፣ ዛሬ አዲስ ቀን ነው። ያጣናቸውን ነገሮች የምናገኝበት፣ በመክሊታችን የምናገለግልበት፣ በብዙ በረከት የምንጎበኝበት፣ ከኃጢአት የምንፋታበት፣ ወደ ፊት የምንዘረጋበት፣ ፅድቅን የምንጠማበት፣ ክርስቶስን የምንናፍቅበት አዲስ ዓመት! እርሱ ለቃሉ ታመኝ ነውና ሁሉን ነገራችንን አዲስ ሊያደርግልን እነሆ በደጅ ነው። ከፍተን እናስገባው። አሮጌው ነገራችን በአዲስ ይለወጥልን። አሜን! እንቁጣጣሽ! አዲስ ዓመት፣ አዲስ ጅማሮ! መልካም አዲስ ዓመት! መስከረም 1፣ 2017 ዓ.ም
إظهار الكل...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
ሆኑም፤ ጸኑም ============================ 📖“እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።”   — መዝሙር 33፥9 እግዚአብሔር አምላክ ሊመሰገን ለምን እንደሚገባው ዳዊት ምክንያቶችን ይደረድራል። “በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፣ የባሕርን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥ ቀላዮችንም በመዝገቦች የሚያኖራቸው። ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሣ ይደንግጡ። እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።” (መዝ 33፥6-9) ባለ መዝሙሩ ዳዊት ግሩም በሆነ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት ዘመረ። እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፣ በውስጧ ያሉትንም ሁሉ በቃሉ የፈጠረ፣ የሰው ልጆችን በእጆቹ ያበጀ ኃያል አምላክ ነው። "ሁን!" ሲል የሚሆንለት፣ ነገሮች ሁሉ የሚታዘዙለት ሁሉን ቻይ ኤልሻዳይ ነው። እርሱ ሁሉን የፈጠረ፣ በማንም ግን ያልተፈጠረ ሉዓላዊ ነው። በአፈጣጠሩ እንከን የማይወጣለት ግሩም ነው። ቃሉ እውነት ነው። ከእርሱ ዘንድ የሚወጣው ቃል እንዲሁ በከንቱ የሚመለስ ሳይሆን የሞተን የሚያስነሳ፣ ያዘነን የሚያፅናና፣ ነገር የጨለመበትን ደግሞ የሚያበራ ነው። ይህ አምላክ ዛሬም በሕይወታችን ይሰራል። ትላንትና ብቻ ሰርቶ ያለፈ ተረት ሳይሆን ዛሬም የሚሰራ እውን ነው። ወንድሜ፣ ከእርሱ ዘንድ ማግኘት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ በእምነት ጠይቀው። በሕይወትህ ላይ ቃልን በመላክ መልስን ይሰጥሃል። እህቴ፣ ልብሽን በእርሱ ፊት በማፍሰስ ልመናሽን ሁሉ አቅርቢ። ኃያሉ አምላክ የልብሽን መሻት እንደመልካም ፈቃዱ ይሰጥሽ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን ይልክልሻል። “እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።” (ቁ 9) ተብሎ እንደ ተፃፈ። 🛐ፀሎት፡ አምላኬ ሆይ፣ ሁሉን የፈጠርህ ፈጣሪ ስለሆንክ አከብርሃለሁ። በአንተ ዘንድ መሆን የምፈልገውን እሆን ዘንድ ቃልህን ላክልኝ። ድምፅህንም አሰማኝ። አሜን።
إظهار الكل...
👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.