cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
74 759
المشتركون
+8624 ساعات
+3227 أيام
+85630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
የእውቀት፣ የክህሎት እና የጥበብ ቅንጅት! 1. እውቀት ማለት፣ ምን እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚደረግ ያውቃል ማለት ስኬታማ ነው ማለት አይደለም፡፡ ብዙ ሃሳብ መሰንዘር የሚወዱና ተግባር ላይ ግን ብዙም የሌሉበት ሰዎች እዚህ ክፍክ ውስጥ ይመደባሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ምን እንደሚደረግ የማወቃቸውን የመረጃ እውቀት ወደ “እንዴት ይደረግ” ደረጃ ሊያሳድጉት ይገባቸዋል፡፡ 2. ክህሎት ማለት፣ አንድ ነገር እንዴት እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው በአንድ ጉዳይ ላይ ምን እንደሚደረግ ከማወቅ የጽንሰ ሐሳብ እና የመረጃ እውቀት አልፎ፣ እንዴት እንደሚደረግ ተግባራዊ እውቀት ሲኖረው እዚህ ይመደባል፡፡ ሆኖም፣ ምንም እንኳን እንዴት እንደሚደረግ የማወቅ ብቃቱና ልምዱ ቢኖረውም እሱ ብቻውን ረጅም ርቀት ላይሄድ ስለሚችል መቼ እና በምን መልኩ ሊረግ እንደሚገባው ወደማወቅ ደረጃ ማደግ ያስፈልጋል፡፡ 3. ጥበብ ማለት፣ አንድ ነገር መቼ እንደሚደረግ ማወቅ ማለት ነው፡፡ በመረጃ መልክ ወደ ማወቅ የመጣነውን እና ከዚያም አልፈን እንዴት መደረግ እንዳለበት ክህሎቱን ያዳበርንበትን ነገር በወቅቱ መደረግ ይኑርበት እና አይኑበት የመለየት ብልሃት ጥበብ ይባላል፡፡ ምንም አይነት የመረጃም ሆነ ተግባራዊ ክህሎት የመጨረሻ ስኬታማነቱ ያለው በጥበብ ሲያዝ ነው፡፡ መረጃ-ተኮር ከሆነው እውቀት፣ ተግባር-ተኮር ወደሆነው ክህሎት፣ ከክህሎት ደግሞ ብልሃት-ተኮር ወደሆነው ጥበብ ስናድግ ከአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ቀደም ብለን እንገኛለን! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
በአረብ ሃገር ለምትኖሩ ወገኖቻችን ያዘጋጀሁት የነጻ ስልጠና ዛሬ ማታ በኢትዮጲያ አቆጣር 3 ሰዓት ላይ (ከ40 ደቂቃ በኋላ) ይጀምራል፡፡ እስካሁን ስልጠናው የሚጥበትን የግሩፕ ሊንክ ያላገኛችሁ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ መቀላቀል ትችላላችሁ፡፡ https://t.me/+jiVi8fudKrxlYjY0
إظهار الكل...
Dr. Eyob's Arab Training Group

Dr. Eyob Mamo invites you to join this group on Telegram.

👍 40 3
ጥያቄ፡- ሰላም ዶ/ር እባክህን ምክርህን ስጠኝ፡፡ እናት እና አባቴ የ25 አመት ትዳር አላቸው ፊት ለፊታችን ተጨቃጭቀው እንኳን አያቁም እሱ በጣም የስራ ሰው ነው ለቤተሰቡ ብዙ አይጨነቅም እሱ ብቻ ያለው ነው ሚሆነው ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ውጪ ማደር አብዝቷል እና ሳጣራ ስልኩን ተቀብዬ ሌላ ቤተሰብ 3 ልጆች እንዳሉት ደረስኩበት እናቴን ዝምብዬ ሳወራት ማለት እንደማቅ ሆኜ ሳይሆን ሀሳቧን ለማወቅ ሌላ ቤተሰብ እንዳለው እንደምትጠረጥር ነገረችን እና ያሰብሽው ነገር እውነት ቢሆን ምን ታደርጊያለሽ ስላት ለልጆቼ ስል እችላለሁ ግን በሰላም መለያየት ነው አለችኝ እኔ ደግሞ ይሄን እያወቅኩኝ ዝም ማለቴ ከእናቴ ጋር እንዳያቀያይመኝ ፈራሁ ምን ላድርግ እባክህ እንዳታልፈኝ፡፡ መልስ፡- በመጀመሪያ ይህንን የመሰለ ከበድ ያለ ሁኔታ በብልህነትና በእርጋታ ለመያዝ ያለሽን ብቃት ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ አብዛኛዎቹ የወላጆች የእርስ በእርስ ግንኙነት ልጆች ከመወለዳቸው በፊት የሆኑትን ሁኔታዎች ሁሉ የሚያጠቃልልና አውደ-ሰፊ በመሆኑ፣ ከሁሉም በፊት በዚህ ሁኔታ ከልክ ባለፈ መልኩ ስሜታዊ ላለመሆን ሞክሪ፡፡ሞክሪ ያልኩት ስሜታዊ አለመሆን ከባድ ስለሆነ ነው፡፡ ከሁሉም በፊት ይህ ያገኘሽው መረጃ (ማስረጃ) በእውነትም ትክክል መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለብሽ፡፡ እሱን ካረጋገጥሽ በኋላ ሁኔታውን እናትሽ ማወቅ እንዳለባቸው ማሰብሽ ትክክለኛ እሳቤ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ሆኖም፣ ሂደቱ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልግሻል፡፡ ያሉሽ አማራጮች . . . 1. ሁኔታውን በውስጥሽ ይዘሽ በራሱ እስኪወጣ መጠበቅነ ራስሽ ላይ ማተኮር 2. አባትሽን በግል በማነጋገር እውነቱን ለእናትሽ እንዲናገሩና መፍትሄ እንዲፈልጉ መሞገት 3. እናትሽን በግል በማነጋርና ሁሉንም ነገር በመግለጽ ማድረግ የሚፈልጉትን እንዲደርጉ ነጻ በማድረግ እሳቸውን መደገፍ 4. ሁለቱም በግልሽ በማስቀመጥ ሁኔታውን ግልጽ በማድረግ መወያየትና መፍትሄ መፈለግ 5. እናትሽም ሆኑ አባትሽ የሚያከብሯቸው የቤተሰብ አባላት ወይም የእምነት አባቶች በግል በማነጋገር ሁኔታውን እሱ እዲይዙ መነገድ ማመቻቸት እነዚህ መንገዶች በሙሉ የራሳቸው ጠንካራ እና ደካማ ጎን አላቸው፡፡ እሱን የሚወስነው ከእነሱ ጋር ያለሽ ግንኙት፣ ሊደግፉሽ የሚች ሰዎች የመኖራች ጉዳይ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ከገለጽሽልኝ ሁኔታ በመነሳት ስገምተው ግን አምስተኛውን ምርጫ የእንቺ የስሜት ውጥረት ከማርገብ አንጻር፣ የሁኔታውን ከባድነት የሚመጥን እርምጃ ከመውሰድ አንጻርና ሂደቱ ውስጥ የብዙዎች መልካም አሳብ ከማካተት አንጻር ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በመጨረሻ የምመክርሽ ወላጆችሽ አንቺ ከመወለድሽ በፊት ሕይወት እንደነበራቸው ሁሉ፣ ወደፊትም ደግሞ እነሱ ካለፉ በኋላ የአንቺ ሕይወት ስለሚቀጥል ሁታው የወደፊትሽ ላይ ጠባሳ እንዳያሳርፍ ተጠንቀቂ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👍 114😢 15 13😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
አባቴ ሌላ ቤተሰብ እና 3 ልጆች እንዳሉት ደረስኩበት ... ፈራሁ ምን ላድርግ?
إظهار الكل...
👍 8😁 6
ለምንድን ነው? ለምንድን ነው ሰዎች እንደፈለጉ የሚያደርጉኝ? . . . ለምንድን ነው ክልከለ ማድረግ ላለብኝ ነገር እምቢ ማለት የሚያስቸግረኝ? . . . ለምንድን ነው በቀላሉ በሰዎች ቅጥጥርና ጭቆና ስር ስወድቅ ራሴን የማገኘው? . . . ለምንድን ነው ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እኔ ሃላፊነትን የምወስደው? . . . ለምንድን ነው? 1. ሁል ጊዜ በሁሉም ሰው መወደድን መፈለግ በሰዎች መወደድን የሚፈልግ ሰው ማንም ሰው እንዳይቀየመው ስለሚፈልግ ለሁሉም ነገር በመስማማት ሳይወድ በግዱ በሰዎች ቁጥጥር ስር ይኖራል፡፡ ሆኖም፣ ሁል ጊዜ፣ በሁሉም ሰው መወደድ ስማይቻል አንደኛችንን ነጻነታችን ማወጅ ይሻለናል፡፡ 2. የግንዛቤ ጉድለት የግል የቀይ መስመርን አስመልክቶ የተዛባ አመለካከት ወይም ያልበሰለ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች፣ ያንን ማድረግ ያቅታቸዋል፡፡ ይህ የተዛባ ዝንባሌ፣ ከአስተዳደግ ወይም አንዳንድ የሃይማኖት አስተምህሮቶችን በተሳሳተ መንገድ ከመገንዘብ ሊመጣ ይችላል፡፡ ማንኛውም ግንኙነት የቀይ መስመር፣ ማለትም የሚፈቀደውና የማይፈቀደው ነገር ሊለይ እንደሚገባው ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ 3. የዝቅተኛነት ስሜት የበታችነት የሚሰማው ሰው የራሱ የሆነ አመለካከት እና አቋም የመያዝ ችግር ስላለበት ሁል ጊዜ የበላዩ እንደሆኑ በሚያስባቸው ሰዎች ቁጥጥር ስር ራሱን ያገኘዋል፡፡ ከሰዎች ጋር ማንልባት ችሎታ ልንለያይ ብንችልም “በሰውነት” ግን እኩል መሆናችንን መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ 4. አለመግባባትን መፍራት አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት እንደፈጠር ስለማይፈልጉና ስለሚፈሩ፣ ትንሽ ኃይለኛነትን የሚያንጸባርቁ ሰዎች ካጋጠሟቸው ቶሎ ብለው የበታችነቱን ስፍራ በመያዝ ይገዛሉ፡፡ በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ አለመግባባት ሊፈጠር እንደሚችል አምኖ በመቀበል ሁኔታውን ለእድገት መጠቀም የግድ ነው፡፡ 5. ሰዎችን ካለልክ ማመን ሁሉን ሰው እንዲሁ በየዋህነት የማመን ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች ማንም ሰው ይጎዳኛል ብለው ስለማያስቡ ለሁሉ ነገር ተሰማሚዎች ሆነው ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ሰዎችን ማመን መልካም ሆኖ ሳለ፣ ራሳችንን ከመጠበቅ ጋርና ሁሉን በልክ ከማድረግ ጋር መያዝ ተገቢ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👍 135 63🤩 6
Photo unavailableShow in Telegram
ለምንድን ነው?
إظهار الكل...
ጥያቄ፡- ሰላም ዶ/ር ራሴን ለማሻሻል personal development ስልጠና መውሰድ ከጀመርኩኝ አመታት አልፈውኛል፡፡ ብዙ ስልጠና ወስጃለሁ ነገር ግን ወደ ተግባር መግባት በጣም ከብዶኛል፡፡ ልክ ወደ ተግባር ልገባ ሳስብ ሌላ የሞቲቬሽን ስልጠና እፈልጋለሁ፣ እንዲሁም ደግሞ ድብርት ይጫጫነኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ውዝግብ ውስጥ ጨምሮኛልና ምን ላድረግ፡፡ መልስ፡- ይህ ሁኔታ ብዙ ሰዎች የሚታገሉበት ችግር ነው፡፡ በተለይም አሁን ያለንበት ዘመን ብዙ የማነቃቂያ ንግግሮችና ዝግጅቶች የተበራከቱበት ጊዜ በመሆኑ ችግሩ ጎልቶ ይታያል፡፡ የማነቃቂያ ፕሮግራሞች ጠቃሚና ችግር የሌለባቸው ቢሆኑም በጥንቃቄ መያዝ ግን አለባቸው፡፡ የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ጠቃሚ ነው፡- 1. የምንከታተላቸውን አነቃቂ ተናጋሪ ሰዎች በጥንቃቄ መምረጥ አንዳንድ አነቃቂ ሰዎች ስሜትን ከማነሳሳት ያላለፈ እና ከእውነታ ጋር ምንም የማይገናኝ ነገር ከመናገር የዘለለ ነገር የላቸው፡፡ ይህንን አይነት ንግግር ከለመድን በኋላ ልክ እንደ ሱስ ይሆንና ደጋግመን ከመስማት ያለፈ ነገር አይኖረንም፡፡ ስለሆነም፣ ሰዎችን ስንመርጥ የሚናገሩትን በሚገባ የሚያውቁ፣ እንዲሁም በነገሩ ያለፉበትና ልምምዱ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ 2. አነቃቂ ፕሮግራሞችን በመከታተል ብቻ ለውጥን እንደማታመጣ መገንዘብ አነቃቂ ንግግሮች የራሳቸው የሆነ ጥቅም አላቸው፡፡ ሆኖም በሚናገሩት ነገር ያለፉ ሰዎች ከልምዳቸው በመነሳት ተግባራዊ መርሆችን ሲጨምሩበት፣ እኛም ያንን ሰምተን እርምጃ ስንወስድ ነው ለውጥ የሚመጣው፡፡ 3. የግልን ራእይ ከማወቅ መጀመር ማንኛውም አነቃቂ ነገር ስኬታማ የሚሆነው ከተነቃቃን በኋላ ወደ የት እንደምንሄድ ስናውቀው ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም፣ አጠቃላይ የሕይወታችንን ራእይ ከማወቅ መጀመርና ወደዚያ ባለን ጉዞ የሚያነቃቃንን ንግግር መጨመር ጥሩ መንገድ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

👍 93 27🤩 4🔥 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ስልጠና ወስጃለሁ ነገር ግን ወደ ተግባር ልገባ ሳስብ ሌላ የሞቲቬሽን ስልጠና እፈልጋለሁ፣ እንዲሁም ደግሞ ድብርት ይጫጫነኛል፡፡
إظهار الكل...
7👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
“እሺ” እና “እምቢ” ሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደቷን እንድትቀጥልና ሁኔታዎች በራሳቸው መስመር እየያዙ እንዲሄዱ መለማመድ የምንችላቸው ሁለት ልምምዶች አሉ፡፡ እነዚህ ልምምዶች ከለመድናቸው እጅግ ቀላል የሆኑ፣ ካላወቅንበት ግን የሚከብዱ ልምምዶች ናቸው፡፡ 1. ለተገቢው ነገር “እሺ” ማለት፡- በሕይወታችን መልካም ነገሮች እንዲገቡ በሩን የሚከፍተው ቁልፍ! በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንደሆነ ላመናችሁበት ነገር “እሺ” ማለት ሌሎች መልካም ነገሮች እየተወለዱ የሚሄዱበትን መስመር ይከፍትላችኋል፡፡ 2. ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” ማለት፡- በሕይወታችን ጤና-ቢስ ነገሮች እንዳይገቡ በሩን የሚዘጋው ቁልፍ! በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንዳልሆነ ላመናችሁት ነገር “እምቢ” ማለት ደግሞ በሕይወታችሁ መልካም ያልሆኑ ነገሮች እየተበራከቱ እንዳይሄዱ መንገዱን ይዘጋዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ልምምዶች ፍርሃትን አልፎ መሄድን ይጠይቃሉ፡፡ በአንድ ጎኑ፣ “እሺ” ለምንለው ነገር ብቁ ባንሆንስ፣ ባይሳካስ፣ በኋላ ብጸጸትስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ “እምቢ” በማለታችን ምክንያት ችግር ቢደርስብንስ፣ እድል ቢያመልጠንስ፣ ሰዎች ቢቀየሙንስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
👍 183 49
Photo unavailableShow in Telegram
ሻማችሁ እንዳይጠፋ ጠብቁ! ሻማው እስከበራ ድረስ ጨለማው ምንም ብዙና ድቅድቅ ቢሆን፣ “አለሁ” ከማለት ውጪ ያለፈ አቅም የለውም፡፡ ጨለማ ብርታትና አቅም ኖሮት የሚያሸንፈው ሻመው ማብራቱን ወደማቆም ተስፋ መቁረጥ ሲመጣ ብቻ ነው፡፡ በዙሪያችሁ በሚሆነው ነገር ምክንያት የማንነታችሁን ሻማ አታጥፉ፣ ከዓላማችሁ አትመለሱ፣ ከየእለት ተግባራችሁ አትገቱ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
إظهار الكل...
👍 170 69🔥 6😁 2😱 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.