cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ቅድስት ፌብሮኒያ

ይህ ቻናል ስለ ሕይወታችን የምንወያይበት ሁላችንም ሀሳብና አስተያየት የምናካፍልበት ነው ፤ እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ነገሮች ይለቀቁበታል።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 407
المشتركون
+224 ساعات
+87 أيام
+6830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
የጊዜያት ባለቤት እግዚአብሔር ሆይ የጨለማውን ግርማ ገፈህ ብርሃኑን እንድመለከት ሰለረዳህኝ በኃጢአቴ ብዛት በሰውነቴ ክፋት ተስፋ ሳትቅርጥ በእድሜ ላይ ይችን ቀን ለንስሐ ሰለጨመርከኝ አመሰግንሃለሁ ። በመኝታዬም ስለጠበከኝ ከሞት ስለሰወርከኝ እጅ መንሳቴን ለአንተ አቀርባለሁ፡፡ ቸር እረኛዬ ትጉህ የማታንቀላፋ ነህና ሌሊቱን ከእኔ ጋር ሆነህ እንደጠበቅኸኝ ይህንን ማለዳ ባርከህ ቀድስህ የሰላም ውሎ እንድውል ቀኝህ ትርዳኝ፡፡ መንገዴን ሁሉ ከፊት እየሆንክ ምራኝ፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
11
መልካም አዲሷ አመት ይሁንላችሁ ጌታ እግዚአብሔር በእናንተ የሚደሰትባችሁ ለመሆን ያብቃችሁ ክርስቲያን ለመሆን ሁላችንም ያብቃን መልካም አዲስ አመት🤗።
إظهار الكل...
2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዮሐንስ 15 (John) 18፤ ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። 19፤ ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል። 👉@Sleiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
👍 1
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!              ወርሐ ጳጉሜ ወርሐ ጳጉሜ በዓመቱ መጨረሻ የምትገኝ በአገራችን ኢትዮጵያ እንደ 13ኛ ወር የምትቆጠር ናት ፤ወርሐ ጳጉሜ 5 ቀናት ያሏት ስትሆን በ4 ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ሉቃስ መውጫ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ያለው 6ቀን ይሆናል፡፡ ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ተውሳክ 5ቀን፣ ሩብ ፤ከዐውደ ወር ተርፎ በዓመቱ መጨረሻ የተጨመረ ስለሆነ ትርፍ ተጨማሪ ይባላል፤ወርሐ ጳጉሜ ዕለተ ምርያ (የመዳን ወር ) ትባላለች በዚህ ወቅት ጻድቁ ኢዮብ በባህረ ዮርዳኖስ ተጠምቆ በሰውነቱ የነበረው ደዌ ዘለክብር የዳነለት ወቅት በመሆኑ እንዲሁም ብዙዎችም ከህመም የተፈወሱባት ወቅት በመሆኗ ዕለተ ምርያ (የመዳን ወር ) ትባላለች ፤ምዕመናን ይህን ትውፊት መሠረት አድርገው በዚህች ወቅት ፀበል ይጠበሉባታል( ይጠመቁበታል) ፡፡ በወርሐ ጳጉሜ ምዕመናን በፈቃዳቸው ይጾሙባታል ፤መጪው ዘመን እንዲባረክ ፣ስለቀደመው ኃጢአት እያዘኑ በጾም በጸሎት ፈጣሪን እየተማጸኑ ያሳልፏታል፤በትውፊት በዚህች ወር የሚጾመውን ጾም ጾመ ዮዲት ይባላል ፤ሆሊፎርኒስ የተባለ የናቡከደኖጾር ቢትወደድ የእስራኤልን ልጆች ምንጭ ይዞ ሕዝቡን ባስጨነቀ ጊዜ ተስፋ ቆርጠው ለጠላት ምርኮ እንግባ አሉ አግዚአብሔርን የምትፈራ በጾም በጸሎት ተወስና የምትኖር ዮዲት የተባለች ደገኛ ሴት ሕዝቡ እንዲጾም እንዲጸለይ አስደርጋ  ከጠላት ከተማ ገብታ በጥበብ የአስጨናቂዎቻቸውን የሆሊፎርኒስን  ቸብቸቦ( ራስ ቆርጣ) ወገኖቿ ድል እንዲቀዳጁ አደረገች ፡፡ ( መጽ ዮዲ 13፣4-5) ምዕመናን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ፣የዮዲትን የእምነት ጽናት፣የጾም ጸሎትን ጥቅም ተረድተው ስለ ግል ሕይወታቸው ፣ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለ አገር ፍቅር ሰላም ብለው በፈቃዳቸው ወርሐ ጳጉሜን በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ ፡፡ ይቆየን ! ሱላሜ( ዲ/ን ተስፋዬ ቻይ) 👉 @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
1 ቆሮንቶስ 3 (1 Corinthians) 6፤ እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የጳጉሜን ወር ለፍጹም የንስሐ ሕይወት! +++ "ስለ ምን ትሞታላችሁ?" +++ "... ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ። የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ? የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።" ትንቢተ ሕዝቅኤል 18 : 30 - 32 +++ መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። ሰቆቃው ኤርምያስ 3 : 40 +++ @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢዮብ 42 (Job) 5፤ መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ፤ 6፤ ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ። @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
8🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ልደቱ_ለአቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ በትንቢት ‹‹ከአንዲት ሴት ልጅ በጸሎቱ ዓለምን የሚያድን፣ በአማላጅነቱ ነፍሳትን የሚዋጅ ልጅ ይወለዳል›› ተብሎ ከተነገረ ከብዙ ዘመን በኋላ እግዚአብሔርን የምታመልክ ስሟ ማርያም ሞገሳ የምትባል ሴት ልጅ ተወለደች ያችንም ሴት ልጅ እናትና አባቷ ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በዕውቀት አሳደጓት ዕድሜዋም ለትዳር ሲደርስ እናትና አባቷ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ስሙ ደመ ክርስቶስ ለሚባል ሰው ዳሯት በዚያን ጊዜ ስልጣኑ ከሰማይ የሆነና ክብሩ እጅግም የሆነ ልጅ ጸነሰች እርሱን ከጸነሰች ጊዜ ጀምሮ እስክትወልደው ድረስም ልብሷን አትታጠቅም፤ ለወገቧም መቀነትን አትፈልግም ነበር በእናቱ ማኅፀን ተአምራትን እንዳደረገ እንደ ዘካርያስ ልጅ እንደ ዮሐንስ በደስታ እየሰገደ በእናቱ ማኅፀን ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርግ ነበርና እርሷም የመውለጃዋ ቀን እስኪደርስ በጾምና በጸሎት ተወስና ስታገለግል ኖረች። በነሐሴ ፳፯ ቀን በሰው ዘንድ የተናቀ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ይህንን ክቡር ጻድቅ ወለደችው በተወለደም ጊዜ በእናትና አባቱ እንዲሁም በሀገሩ ሰዎችም ዘንድ ደስታ ሆነ እስከ ሰባት ቀንም ድረስ ግብዣ አደረጉ ይህም ጻድቅ ባሕታዊ በተወለደበት (ክርስትና) በተነሳበት ቀን በካህናት አፍ ጸጋ ክርስቶስ ተባለ የኃጢአት ማሠሪያን ሁሉ ያሥርና ይፈታ ዘንድ ጵጵስና በሾመው ጊዜ እግዚአብሔር ያወጣለት ሁለተኛው ስሙ ዘርዓ ቡሩክ ነው ሦስተኛ ስሙ ደግሞ ጸጋ ኢየሱስ (በጸሎት ተደጋግሞ ብዙ ይገኛል) ይባላል። ከልደቱ በኋላ ያንንም ሕጻን አባቱና እናቱ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በአምልኮት እና በዕውቀት አሳደጉት:: ሰባት ዓመት ሲሆነው የሚያልፈውንና የሚጠፋውን ዓለም ሁሉ እንዳያይ ዓይኖቹ ታወሩ የልጃቸው ዓይኖች በጠፉበት ቀን እናትና አባቱ አዘኑ ታውሮም በቤታቸው አንዲት ዓመት ኖረ ከተወለደ ሰባት ዓመት ሲሆነው ረቡዕና ዓርብን መጾም ጀመረ እናትና አባቱም በተወለደ በሰባት ዓመቱ ሲጾም ባዩት ጊዜ ኀዘናቸው ወደ ደስታ ተለወጠ ከዚህም በኋላ በእኒህ እንዲተዳደር ብሎ እንደተናገረው መጽሐፍትን ቢማር ያለበትን ነውር እንደሚሰውር እና በእነዚህም እንዲተዳደር አውቀው የቤተ ክርስቲያንን መጽሐፍት ሁሉ እንዲያስተምረው ለመምህር ሊሰጡት ተማከሩ እርሱ ሲማር እግዚአብሔር ብርቱ መከራንና የሚያስጨንቅ በሽታ አመጣበት አባትና እናቱም በልጃቸው ላይ የሆነውን ነገር አይተው ዓይኖቹ የታወሩ ‹‹ይህ ልጃችን በምን ይተዳደራል? በዚህ ዓለምስ አኗኗሩ እንደምን ይሆናል?›› ብለው ታላቅ ኀዘንን አዘኑ እግዚአብሔርም ከእርሱ (ከእግዚአብሔር) በቀር መጻሕፍትን ሁሉ ከማንም እንዲማር እንዳልፈቀደለት ፈጽመው አስተውለው አላወቁም ነበር ይህ ትንሽ ሕጻን ግን ለአባትና ለእናቱ ሲታዘዝ (ሲያገለግላቸው) ኖረ:: ሐዋርያትም በሲኖዶሳቸው እንዳዘዙት ከተወለደ ፲፪ ዓመት ሲሆነው ይጾም ነበር ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነውም በኋላ የጌታችንን ጾም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ማርያምን ጾም፣ ሐዋርያት የሠሩትን ጾም፣ ሁሉ መጾም ጀመረ አባትና እናቱም በዐሥራ ሁለት ዓመቱ ጾሙን ሁሉ ሲጾም አይተው ተደሰቱ ይህ ሕጻን ልጃቸው በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንደጸና አላወቁም እግዚአብሔር አምላክም ለዚህ ጻድቅ አባት መጻሕፍተ ብሉያትንና መጻሕፍተ ሐዲሳትን፤ መጻሕፍተ ሊቃውንትንና መጻሕፍተ መነኮሳትንም፤ አዋልድ መጻሕፍትንም፤ የመላእክትንና የሰውን ነገር (ፍትኅን ሁሉ፤ የማኅሌታይ የቅዱስ ያሬድንም ዜማ) ገለጠለት፤ እግዚአብሔር ይህንን ድንቅ ተአምራት ለወዳጁ ለብፁዕ አባታችን ለአቡነ ዘርዐ ብሩክ የሰጠው ገና በልጅነቱ ነበር። ለእኛም ፈጣሪያችን እንዲሁ ተአምራትን ያድርግልን፤ በመከራችን ጊዜ ደስታን ያሰማን፤ ለእርሱ እንደገለጠለት መጻሕፍትን ሁሉ ይግለጥልን፤ መታሰብያውን ለምናደርግ፣ ስሙንም ለምንጠራ እና በጸሎቱ ለምንማጸን ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቹ በጻድቁ ጸሎት ነፍሳችንን ይማርልን! #በፍኖተ_ሕይወት ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀ። @Slehiwetwe ይቀላቀሉን።
إظهار الكل...
👍 2 1
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክርስቲያን ቤተሰብ የተወለደ ሰማዕት ነው። አባቱ ዞሮንቶስ እናቱ ቴዎብስትያ ይባላሉ፡፡ አባቱ የዲዮቅልጥያኖስ ሰው ነበር፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአባቱ ሞት በኋላ የአባቱን ሹመት፣ የዓለምን ክብርና ደስታ ንቆ የክርስቶስ ምስከር ሆነ፡፡ በዲዮቅልጥያኖስ ትእዛዝ ብዙ መከራ ቢቀበልም እስከ ሞት ድረስ ጸንቶ ለክርስቶስ ታምኖአል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ መከራና ሞት ያልበገረው የክርስቶስ ምስክር ነው፡፡ በጽናቱ በእምነቱ በትዕግሥቱና በፍቅሩ አብነታችን ነው:: በረከቱ አይለየን፡፡
إظهار الكل...
11
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.