cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Sami Automotive technology

A Professional Automotive Electrician More 10 Years of on Field Experience, We Repair, Maintain, and Install Electric Work on Every Automotive Contact us 0912072874 094732 93 34

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
6 370
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+217 أيام
+13130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
አንድ መኪና ጠዋት ላይ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት እነዚህን 8 ወሳኝ ነገሮችን ማረጋገጥ አለብን። እነሱም፦ 1.የሞተር ዘይት (Engine oil) መጠን ማየት 2.የኩላንት (የራዲአተር ውሃ) በቂ መሆኑን ማረጋገጥ 3.የፍሬን ዘይት (Break fluid) መጠን ማየት 4. የጎማ ንፋስ መጠንን እና ጎማዎቹ መጥበቃቸውን አንድ በአንድ ማረጋገጥ 5. በነዳጅ ታንከር (Fuel tank) ውስጥ በቂ ነዳጅ መኖሩን ማረጋገጥ 6. በዳሽ-ቦርድ ላይ የማስጠንቀቂያ መብራቶች (Warning light) አለመብራታቸውን ማየት 7. የፍሬን ፣ የፊት ፣ የፍሬቻ ፣ የጎን እና የኋላ መብራቶች እንደሚሰሩ ማረጋገጥ 8. በመጨረሻም መኪናውን ያቆምንበት ቦታ ላይ ምንም ዓይነት ፍሳሽ አለመኖሩን ማረጋገጥ አለብን። ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ Telegram: https://t.me/samiauto1 ምን ጊዜም ለመኪናዎት ሴኩሪቲ እና ሴፍቲ ሳሚ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ይምረጡ።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የመጀመሪያው የአለማችን መኪና መቼ እና በማን ተሰራ ◍ ከብዙ ዘመናት በፊት የሰው ልጅ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ ባህላዊ መጓጓዣዎችን ይጠቀም ነበር። ለምሳሌ ያህል እንደ ሰረገላ ፣ በቅሎ ፣ ፈረስ እና የመሳሰሉትን ይጠቀም ነበር ፤ ከነዚህም ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።በፈረንጆች አቆጣጠር በ1886 ዓ.ም በጀርመናዊው ተወላጅ ካርል ቤንዝ ( Karl Benz ) የመጀመሪያዋ መኪና ልትሰራ ችላለች።ይህቺም መኪና የሰውን ልጅ ከባህላዊ መጓጓዣ ወደ ዘመናዊ መጓጓዣ አሸጋግራለች። ባጠቃላይ መኪናዋ ባለ አንድ ሲሊንደር ስትሆን 265 ኪ.ግ ክብደት እና በሰዓት 16 kilometer per hour ትጓዝ ነበረ። ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ Telegram: https://t.me/samiauto1 ምን ጊዜም ለመኪናዎት ሴኩሪቲ እና ሴፍቲ ሳሚ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ይምረጡ።
إظهار الكل...
DPF ( Diesel Particulate Filter ) ምንድነው ? ➾ DPF የናፍጣ መኪኖች ላይ የሚገጠም የበካይ ጭስ ማጣሪያ መሳሪያ ነው። DPF የጭስ ማውጫ ሲስተም ላይ የሚገጠም ሲሆን ከ Catalytic converter በኋላ ወይም በፊት ሊገጠም ይችላል። የ DPF ዲዛይን Honeycomb filter (የንብ እንጀራ ዓይነት ማጣሪያ) ኖሮት በብረት የተሸፈነ ነው። የDPF Honeycomb ማጣሪያ Cordierite wall flow filter ወይም Silicon carbide wall flow filter ከተባሉ ቁሶች የተሰራ ነው። የDPF ዋና ሥራ በናፍጣ የሚሰሩ መኪኖች የሚፈጥሩትን Particulate (ተረፈ ምርት) አስቀርቶ ወደ አካባቢ አየር እንዳይገቡ ማድረግ ነው። እነዚህ Particulate ለመተንፈሻ አካላት በጣም ጎጂ ናቸው። እነዚህ ጎጂ ቅንጣጦች በዓይን በማይታዩ ጥቃቅን ማጣሪያዎች እየተጣሩ ይቆያሉ። ከዛም Regeneration በሚባል ሂደት በሙቀት እንዲጠፉ ይደረጋሉ። ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ Telegram: https://t.me/samiauto1 ምን ጊዜም ለመኪናዎት ሴኩሪቲ እና ሴፍቲ ሳሚ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ይምረጡ።
إظهار الكل...
Sami Automotive technology

A Professional Automotive Electrician More 10 Years of on Field Experience, We Repair, Maintain, and Install Electric Work on Every Automotive Contact us 0912072874 094732 93 34

Photo unavailableShow in Telegram
ቱርቦቻርጀር (Turbocharger)፡ አየር ወደ ሞተር Combustion chamber ውስጥ በሁለት አይነት መንገድ ሊገባ ይችላል(ክፍል 2) 2.Turbine: ይህ ሁለት ክፍሎች አሉት። እነሱም፦ ➣Turbine wheel: ይህ ክፍል በተቃጠለ ጭስ (Exhaust gas) የሚነዳ ነው። ➣Turbine housing: ይህ ክፍል የተቃጠለው ጭስ (Exhaust gas) እንዳይበታተን ቀጥታ ሰብስቦ ወደ Turbine wheel እንዲሄድ ያደርጋል። ይህ ጭስ የ turbine wheel'ን በሚገፋበት ሰዓት ዙር (Rotation) ይፈጠራል ፤ ይህም እስከ 150,000 RPM ድረስ ይዞራል።ያም ጊዜ ከውጪ (Atmosphere) አየር ወደ ውስጥ መግባት ይጀምራል። 3.Shaft: ይህ ክፍል ከ turbine ጋር የተያያዘ ሲሆን በተቃጠለው ጭስ የተፈጠረውን ዙር (rotation) ወደ ኮምፕረሰር የሚያደርስልን ነው። 4.Compressor: ይህ ክፍል ከ Atmosphere አየር የምናስገባበት ነው።ይህም Compressor housing እና Compressor wheel የሚባሉ ክፍሎች አሉት። * Compressor housing አየሩ ከውጪ (atmosphere) በሚመጣበት ጊዜ በቀጥታ ወደ compressor wheel እንዲሄድ ያደርጋል። * Compressor wheel ደግሞ እሽክርክሪት (rotation) ስላለው ወደ ሞተሩ አየር እንዲገባ ያደርጋል። 5.Wastegate valve: ይህ ክፍል በሞተሩ (Engine) ውስጥ ትልቅ ግፊት (Pressure) ያለው አየር በሚገባበት ጊዜ ሲስተሞቹ እንዳይጎዱ pressure'ን የሚቀንስ ነው። 6.Intercooler: ይህ ክፍል አየሩ ወደ ሞተሩ የመቀጣጠያ ቦታ (Combustion chamber) ከመግባቱ በፊት የገባውን ከፍተኛ ግፊት (pressure) እና ሙቀት (temperature) ያለውን አየር በማቀዝቀዝ ወደ ሞተሩ (Engine) እንዲገባ ያደርጋል። ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ Telegram: https://t.me/samiauto1 ምን ጊዜም ለመኪናዎት ሴኩሪቲ እና ሴፍቲ ሳሚ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ይምረጡ።
إظهار الكل...
Sami Automotive technology

A Professional Automotive Electrician More 10 Years of on Field Experience, We Repair, Maintain, and Install Electric Work on Every Automotive Contact us 0912072874 094732 93 34

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የመኪና ባትሪ (Battery)፡ የመኪና ባትሪ የኬሚካል ሀይልን ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል የሚቀይርልን መሳሪያ ነው። (ክፍል 1 ) ➾ ባትሪ በሁለት ቦታ የሚከፈል ሲሆን እነሱም፦ 1.Primary battery (ቻርጅ የማይደረግ)፡ ይህ ባትሪ አንድ ጊዜ ተጠቅመን ሲያልቅ በድጋሚ ቻርጅ የማናደርገው የባትሪ ዓይነት ነው።ለምሳሌ፦ የካሜራ ባትሪ ፣ የእጅ ባትሪ ፣ የሪሞት ባትሪ...... 2.Secondary battery (ቻርጅ የሚታረግ)፡ ይህ የባትሪ ዓይነት በሚያልቅበት ጊዜ በድጋሚ ቻርጅ አድርገን መልሰን መጠቀም የምንችለው የባትሪ ዓይነት ነው።ለምሳሌ፦ የስልክ ባትሪ ፣ የመኪና ባትሪ........ ➲ የመኪና ባትሪ በመኪናው ላይ ላሉ በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ክፍሎች የመጀመሪያ የሀይል ምንጭ ነው። ይህ ባትሪ በመኪና ላይ በዋነኝነት ሞተርን (Engine) ለማስነሳት ያገለግላል ፤ በተጨማሪም ነዳጅን ለማቀጣጠል ፣ ለሬዲዮ ፣ ለመብራት..... ወዘተ የመኪና ባትሪ ወደ አስር የሚሆኑ ክፍሎች አሉት። እነሱም፦ 1.Terminal: በባትሪው የውጨኛው ክፍል ላይ የሚገኙ የ Positive [+] እና የ Negative [-] ኤሌክትሪክ ገመድ ማገናኛ ተርሚናል ይባላል። ፔጃችንን እንደዚህ አይነት ከመኪና ጋር የተገናኙ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎችን ስለሚለቅ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ Telegram: https://t.me/samiauto1 ምን ጊዜም ለመኪናዎት ሴኩሪቲ እና ሴፍቲ ሳሚ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ይምረጡ።

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.