882
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
- المشتركون
- التغطية البريدية
- ER - نسبة المشاركة
جاري تحميل البيانات...
معدل نمو المشترك
جاري تحميل البيانات...
Photo unavailable
ቃል ከረከሰበት ቅጥፈት ከበዛበት
ከኔና ካንተ አለም
የማለልን እንጂ የኖረልን የለም
አላፊ እኔና አንተ ምን ብንዋደድም
ዘላለም በሚል ቃል አንሸዋወድም
ስሞ ያሞካሸኝ ዘላለም ላይረባኝ
እስካሉ መውደድ ነው በጊዜ የገባኝ::
4900
Photo unavailable
"ወዴት ነሽ?"
ኃይሉ ከትናንት ተርፎ ዛሬን ወደሚሰርቀው ትዝታ! መጥፎ ሲሰሩበት ሊረሱት ግድ ወደሚያደርጉት ትዝታ! ሲከብሩበት ወደሚደሰኩሩት ትዝታ! የራስን ክፉነትና መልካምነት ወደሚያንፀባርቁበት አለም... ወደ ኋላ!
3600
ሴትን ልጅ ወደህና ፈቅደህ ወደሂወትህ ካመጣሀት በሆአላ እንደአባት መካሪ እንደወንድም ተቆርቋሪ እንደእናት እንስፍስፍ ሁንላት እንጂ ፈፅሞ ፈፅሞ የእንባዋ መፍሰስ ምክንያት እንዳትሆን ነገ ለልጆችክ የምትነግራቸው ልዩና ዘመን የማይሽረው ፍቅር ና ክብር ይኑርህ::
4100
Photo unavailable
<< በለሆሳስ የሚጮኹ እዬዬዎች አሉ። በፈገግታ የሚግሉ መከፋቶች አሉ። ትኩረት፣ እይታን በመፈለግ ውስጥ፣ በጥልቅ ላለመድከም የታይታ በራስ መተማመን በማሳየት ውስጥ የተሸሸጉ ግራ የሚያጋቡ ሰቃዥ ስሜቶች አሉ። ብዙ ነገሮች እንደምናያቸው አይደሉም። የአንዳንድ ሰዎች ሁኔታ እንዲህ ነው። ስል የሆነ ቢላዋ ላይ ቆሞ እንደ መደነስ፣ በስል ቢላዋ ላይ ሸርተቴ እንደ መጫወት፣ ደም እያንቆረቆሩ ላቤ ምነው ቀላ እንደማለት፣ በጥፍር ዳገትን እንደ መውጣት። >>
4200
የወደድክ ግዜ ጥሎህ የማይሄደውን ውደድ....ፍጥረታትን ስታፈቅር ውዴታህን ከአይንህ አሳልፈህ ለልብህ ስጥ....የአይን ወዳጅህ ከእይታህ ሲርቅ በናፍቆት ይገድልሃል...የልብ ወዳጅ ግን ዝንተዐለም ካንተ ጋር ይኖራል...!
🔗3600
የጊዜ ጉዳይ እንጂ በዳይ በዚህ ምድር ላይ የእጁን ያገኛል፡፡ ዛሬ ቢፈነድቅ ቢደሠት ለጊዜው ነው፡፡ ዛሬን ሳይቀጣ ቢያልፍ እንኳ ነገ ሌላ ኬላ አለበት፡፡ በትንሳኤ ቀን የሚጠብቀው መዓት ከባድ ነው፡፡ በቂያማ ቀን ለምርመራ ዋናው መርማሪ ፊት ይቆማል፡፡ መልካም ምንዳዉን ሁሉ ዐይኑ እያየ ይነጠቃል፡፡ የበደላቸዉን ሰዎች እንዲክስ ይደረጋል፡፡ የሚክሰዉም ዱንያ ላይ ከሠራው የመልካም ሥራ ምንዳው እየተወሰደ ነው፡፡ ዐይን እያየ የራስን መልካም ሥራ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ህመም አለ!!፡፡ በዚህ መልኩ የበደለዉን ሁሉ ይክሳል፤ የሰረቀዉን ሁሉ ሳይወድ በግዱ ይመልሳል፡፡ መልካም ሥራ ከሌለው ወይም ለተበዳዮች ተሠጥቶ ካለ ከተበዳይ መጥፎ ሥራ ተቀንሶ ዕዳ እንዲሸከም ይደረጋል፡፡
በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማ ነው፡፡ በዳይ ሰው ኪሳራው ብዙ ነው፡፡ ማረፊያዉም ጨለማ ነው፡፡ ለበዳይ ሰው እዘንለት እንጂ ተበደልኩ ብለህ አትማረር፡፡ የተበዳይ ዱዓ ምላሽ አለው፡፡ የተበዳይን ጉዳይ አላህ አይረሳም፡፡ አንድ ቀን ይመልስለታል፡፡ እንባዉን በማረ ሁኔታ ያብስለታል፡፡ በደል ጉዳት ቢመስልም ትርፍ አለው፡፡ እናም ምን አሳሰበህ …
@ከአላህ ጋር መጽሐፍ
4500
አካሉ ከአካሌ ቢርቅም ...አብሮኝ እንደሚውል ከሀሳቤ የማይጠፋ ...እንደ ቅርቤ ሁሉ ምቱን የማደምጠው ፥ አለ ሚናፍቀኝ🧡
6000
Repost from N/a
00:45
Video unavailable
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳቹ አደረሰን መልካም የኢባዳ ጊዜ ይሁንልን🌺
IMG_2502.MOV8.87 MB
5600
ሐራም ነገርን በሩቁ መጠየፍን የመሰለ ነገር የለም። ከተጠጉት ግን በሂደት ሳይታሰብ ይዞ ይሄዳል።
እንደ ከባድ ወንጀል ሲታይ የነበረው ለዐይን ይቀላል። ከዚያ መሥራቱ ይገራል። ከዚያ መደጋገሙ ይለመዳል። ከዚያ ከሐላል ጋር ተመሳስሎ መለየቱ ይከብዳል። ከዚያ ኖርማልና ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ እንደ ሐላል ይወሰዳል።
ቀልብ ይበልጥ እየደረቀ ሲሄድ ደግሞ ሐላልና ሐራምን መለየት ይሳነዋል። ይመር የነበረው ይጣፍጣል ፣ ያዝናናል። ከዚያ ሱስ ይሆናል። ከዚያ ማግኘቱ ያጓጋል።
ቀልብ እንዲህ እስክትሆን መጠበቅ የሞት ሞት ነው።
ሙእሚን በወንጀል ሊወድቅ ይችላል፣ ቢወድቅም ወድቆ አይቀርም አፈር ልሶ ይነሳል። ቢሸነፍና ድንገት ስህተት ቢሠራ ጥቂት ቆይቶ ይነቃል። የሚወቅሰው ህሊና፤ የምትቆጣው ነፍስ አለዉና ሽንፈቱን መቀበል ይከብደዋል። አላህም ተፀፃች ባርያውን ያግዛል።
6000
ሳላይህ አመንኩብህ፣
ሳላይህ ሰገድኩልህ፣
ሳላይህ ለመንኩህ፣
ሳላይህ ተመካሁብህ፣
ያየኸኝ እና ያየሁህ ቀን እዘንልኝ፣
ካንተ መገናኘቴን አሳምርልኝ።😢
ያ ረብ።
ሽይኽ ሸዕራዊ።
5200
اختر خطة مختلفة
تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.