cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የሀገሬ ወጎች

2017 ዓ.ም!

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 460
المشتركون
-224 ساعات
-267 أيام
-11330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
የተቀነጨበ ጨዋታ ከሳቅሽ ከለዛ አንደበትሽ ተደማምሮ ሳለ ከተፈጥሮሽ እንጂ ከልብሽ ምን አለ? . . . እንጃልን እኛማ ላወጋልን ሁሉ ለሳቀልን ሁሉ ሞትን ካልንማ። ዮኒ ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan
إظهار الكل...
❤❤የፍቅር ማእበል❤❤        ክፍል 28 እውነት ለመናገር ምንም የማለት ድፍረቱን አላገኘሁም :: ዝም ብዬ ተነስቼ ወጣሁ አልተከተሉኝም ነበር። ወደናቴ ቤት ሄድኩኝና ክፍሌ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ጭንቀት: ድብርት: ሀሳብ የሰፈነበት መኝታ ነበር ። እናቴ የሰሞኑ ሁኔታሽ ምንም ደስ አላለኝም ያስጨነቀሽ ነገር አለ እንዴ አለችኝ ። እኔ ምንም የለም ብዬ ሽምጥጥ አደረኳት። ልዑሌ ደውሎ ቤት ልምጣ እንዴ ቢሮ ስራ የለኝም አለ ?? አይ እኔ እናቴጋ ሄጃለሁ ቤት አደለሁም አልኩት ?? በዛውም ማዘርን  አያቸዋለሁ በቃ መጣሁ አለኝና ቤት መጣ ፈጣሪ ይወቀው ለምን እንደሆነ ግን አንዳንዴ ሳየው ልዑል ያናድደኝ ጀምሯል ። ስለማክቤል ከሰማሁ ቡሀላ ትክክለኛ ስሜቴ ምን እንደሆነ ለማወቅም እየተቸገርኩ ነው ። ልዑል ቤት ሲመጣ ድምፁን ስሰማ እንቅልፍ እንደወሰደው ሰው አይኔን ጨፈንኩ በቃ ይለፍላት ትተኛ ብሎ በሩን ዘግቶ ከክፍሌ ወጣ። ሁኔታዬ ለራሴም አስጠላኝ ግራ አጋባኝ ቆይ ልዑል ምን አደረገ ብዬ እራሴን ጠይቃለሁ?? መልሱ ምንም አላደረገም ከውርደት ነው ያዳነሽ የቤቱንም የልቡንም በር ነው የከፈተልሽ የሚል ሆኖ አገኘዋለሁ ። ልዑሌ እና እናቴ የሞቀ ጨዋታ ይዘው እየተጫወቱ ሳቃቸው  ይሰማል ። እኔም ልቀላቀላቸው ብዬ ተነስቼ ወጣሁ እየተጫወትን እህቴም መጣች ቤተሰቡ ሰብሰብ ብሎ ሲጫወት እናቴ በጣም ደስ አላት ። ሲመሽ እኔና ልዑሌ ወደቤት ለመሄድ ወጣን ። እህቴን ለብቻዋ ጠራኋትና አዲሱን ቁጥሬን ለማክቤል እንድትሰጠው ነገርኳት ግን ለማንም እንዳትናገር አስማልኳት ። ወደ ቤት እዬሄድን አስር ጊዜ አረ መሲ ብቻዋን እቤት ይደብራታል እለዋለሁ። ቆይ ምንድነው ከዚች ልጅጋ እንደዚህ የተቀራረብሽው አለኝ ልዑሌ ። አረ ብታይ ታሪኳንኮ ብታውቅ እንደዚህ አትልም ነበር እንዴት እንደምታሳዝን ። ንገሪኛ ምንድነው አለኝ ??? ይቀጥላል ..... አረ share እያደረጋችሁ አደለም ቆመናልኮ 480ላይ 😂😂😂 ምርትና አግልግሎቶን ለማስተዋወቅ ያናግሩኝ !!! @Ye_Hagere_Wegoch @Ye_Hagere_Wegoch
إظهار الكل...
👍 6
Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
ከትልቅ ይቅርታ ጋር "ተፈላጊ" የተሰኘው ልብወለድ በ ዮኒ ኣታን ቻናል እስከ ቁጥር ሁለት ድረስ ሲተላለፍ የነበረ እንደሆነ ይታወቃል በመሆኑም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ቁጥር ሶስትን ይዞ በ ዮኒ ኣታን፣ ግጥም በኢትዮጵያ እና የሀገሬ ወጎች ላይ መለቀቅ ጀምሮ የነበረው "ተፈላጊ" አሁን ላይ ባጋጠመን ትልቅ ችግር ማለትም የነበሩትን ፋይሎች በሌላ ሰው ስም ተቀናጅተው እየተለቀቁ ስለሆነ ላልተወሰነ ጊዜ ልብወለዱን ገታ አድርገን አየተወያየንባቸው እንገኛለን። ስለዚህም ክቡራት ተከታታዮቻችን ከትልቅ ይቅርታ ጋር ላልተወሰነ ጊዜ አቁመነዋል። የ ዮኒ_ኣታን ቻነል አድሚኖች @Yonny_Athan @Yonny_Athan
إظهار الكل...
👍 1
Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
❤❤የፍቅር ማእበል ❤❤             ክፍል 27 የት ሄዶ ይሆን እያልኩ ወደናቴ ቤት ሄጄ ትንሽ ልረፍ ብዬ ልመለስ ስል የማክቤት አባት የኔ ልጅ የኔ ልጅ እያሉ ከኋላይ እየሮጡ መጡና አስቆሙኝ 5  ደቂቃ ብቻ እንዳወራቸው አጥብቀው ለመኑኝ:: ቅር እያለኝም ቢሆን እሺ አልኳቸው ወደ ውስጥ ገብተን እንቀመጥ አሉኝ እሺ ብዬ ተከተልኳቸው ወንበር አዘጋጅተው አስቀመጡኝ። ምን ሊያወሩኝ እንደሆነ መገመት አልቻልኩም ግን አሁንም ካጠገቡ እራቂ ሊሉኝ ይሆን እንዴ??? ይቅርታ የኔ ልጅ ምን ይምጣልሽ አሉኝ ምንም አልፈልግም እቸኩላለሁ ካላስቸገርኮት ማለት የፈለጉቱን ቶሎ ይበሉኝና ልሂድ አልኳቸው ... እየውልሽ የኔ ልጅ እኔ ስለልጄ ላወራሽ ነበር አሉኝ ቀና ብለው አይኔን ለማየት እየፈሩ እንዴት ብዬ አይኔን በጨው አጥቤ ፊትሽ እንደቆምኩ አላውቅም  ግን በቃ ልጄን መልሽልኝ ማክቤልና የአይኔን ማረፊያ አይኔ እያየ አጥቼዋለሁ አሉ እንባ እየተናነቃቸው። ምነው ማክቤል የሆነው ነገር አለ እንዴ??? (እውነት ለመናገር ደንግጫለሁ ) አዎ ካንቺጋ ከተለያያችሁ ጀምሮ የበፊቱ ማክቤል የለም በስርአት አውርቶኝ አያውቅም ቤትም ሆነ ስራ ቦታ ከስንት አንዴ ብር ሲፈልግ ብቻ ነው ሚመጣው የለበሰው ልብስ እላዩ ላይ ሸቶ እንኳን አይቀይረውም ። ልጄን አተርፋለሁ ብዬ ገደልኩት እየውልሽ የኔ ልጅ እኔ ነኝ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ እሱ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ። ህይወቴን በሙሉ ለፍቼ ሰርቻለሁ ልጄን ለማሳደግ ስል የልጄ እናት በቂ ገንዘብ ስሌለኝ ከኔና ከልጄጋ በድህነት መኖር ስለማትፈልግ ብቻ ነው እኔንም ማክቤልንም ጥላን የሄደችው ። እና ቆይ የኔ ልጅ ከኔ በላይ ገንዘብን መውደድ ያለበት ሰው አለ እኔ አንችና እሱ እንድትለያዩ ያደረኩበትና ምክንያቶች ልጥቀስልሽ በመጀመሪያ እኔ ልጄ የራሱን ቤት በራሱ እስኪገዛ መኪና እስኪኖረው ሀብታም ከሚባሉት ደረጃ እስኪመደብ ድረስ ጠንክሮ እንዲሰራና እንደሱ ሀብታም የሆነችውን መርጦ አግብቶ እኔ እሱን ባሳደኩበት መንገድ ሳይሆን በተለየ መንገድ ነው ልጆቹን እንዲያሳድግ ምፈልገው ሁለተኛ በቃ ስራ ስራ ነው ማክቤል ብዙ ጊዜ እንዲሰራ ያዘዝኩትን ስራ እየተወ አንቺን ለማግኘት ይመጣል አየሽ ዛሬ ገንዘብ በመስሪያው ሰአት አንቺን አንቺን እያለ ነገ የተሻለ ሀብታም ስታገኚ ጥለሽው ብትሄጂስ ብዬ ፈራሁ ሶስተኛ አንቺ ስንት አመት ሙሉ እናትሽ ብቻዋን ለፍታ አስተምራሽ ተምረሽ ከተመረቅሽ ቡሀላ ግን እሷ እየሰራች አንቺ የቤት እመቤት ሆንሽ በዛ ሰአት ለልጄ እነደማትሆኚው ወሰንኩ ቢያንስ እንኳን በርሽ ላይ ሱቅ ነገር ከፍተሽ ሻይ ቅጠል መሸጥ ይሻላልኮ በዚህ ወጣትነት እድሜ ስራ እስካገኝ ነው እያሉ ቤት ከመቀመጥ ግን አሁን የታየኝ ልጄ እናንተጋ ሀብት መስፈርት አልነበረውም ፍቅራችሁ አንዳችሁ አንዳችሁን አምናችሁ ጠብቃችሁ እንድትኖሩ ያደርጋችሁ ነበር ለካ ሁሉም ሴት እንደኔ ሚስት አደለም እኔ ይቺን ግሮሰሪ ይዤ ለልጄ ሚስትነት ስታንሽብኝ የሀብታሞች ሀብታሙ መጥቶ በክብር አንደላቆ አገባሽ የዛኔ ነው ሁሉም ነገር የተገለጠልኝ ። ዛሬ ከረፈደ እንደ እግር እሳት ቢበላኝ ምን ላድርግ ግን በቃ አንድ የመጨረሻ ነገር የምለምንሽ ማክቤልን እንዴትም አድርገሽ ቢሆን ወደራሱ መልሽልኝ ሚስቱ ባትሆኚ እንኳን እህቱ ሁኚው እባክሽ የኔ ልጅ በኔ ጥፋት እሱ አይቀጣብኝ እንደው በወለደችሽ እናትሽ ይዤሻለሁ ይቺን ብቻ እሺ በይኝ አሉ እንባቸው ካይናቸው እየወረደ ይቀጥላል ...... @Ye_Hagere_Wegoch @Ye_Hagere_Wegoch
إظهار الكل...
👍 3 1
Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
👍 1
Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
Repost from ✍ዮኒ-ኣታን
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
👍 2
🌼
إظهار الكل...
4👍 2😁 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.