cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Kolfe education official channel

We are delighted to inform our members about kolfea keranio Education bureau.🇪🇹

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
14 276
المشتركون
+3624 ساعات
+4047 أيام
+1 33530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት አብሮነትንና አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበሩ የትምህርት አመራሩ የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገለፀ። መስከረም 09/2017 ዓ.ም ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በአላትን የአብሮነት አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር በክፍለ ከተማው ሥር የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣ርዕሰ መምህራን፣ሱፐር ቫይዘሮች እና የትምህርት በላሙያዎች ጋር ውይይት የተካሔደ ሲሆን በውይይቱም የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት የሥራ ክፍሎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰይፈሚካኤል በርጠማ አማካኝነት የመስቀልና የኢሬቻ በአላት ሀይማኖታዊና ትውፊቱ ተጠብቆ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በተዘጋጀው የማስፈፀሚያ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሒዶበታል። የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ ሁለቱም የአደባባይ በዓላት እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የትምህርት ማህበረሰቡ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አለብን ያሉ ሲሆን ለዚህም ህፃናት የሚማሩባቸው የትምህርት ተቋማት ያለምንም የፀጥታ ችግር መማር ማስተማሩ እንዲቀጥል እና ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በየአካባቢችን እና በሥራ ቦታን በህዝቦች መካከል የሚያቀራርብ የወንድማማችነት ተግባር ማከናወን ይገባናል ብለዋል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዓላቱ ከዚህ ቀደም እንደተከበሩ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
إظهار الكل...
👍 18
በሞግዚትነት እያገለገላችሁ የነበራችሁ በቅ/መደበኛ ትምህርታችሁን ያሻሻላችሁ መምህራን ስም ዝርዝር ሲሆን የምደባ ደብዳቤ ማክሰኞ ቀን 14/01/2017 ዓ.ም ከኮ/ቀ/ክ/ከተማ ት/ት ጽ/ቤት እንድትወስዱ እናሳስባለን ።
إظهار الكل...
👍 1 1👏 1
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል። ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። 👇👇👇👇👇 https://result.ethernet.edu.et/
إظهار الكل...
👍 7
የተማሪዎች ምገባ በአዲሱ ሜኖ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ በ08/01/2016 ዓ.ም በጄ/ዋቆ ጉቱ ቁ.አንድ እእ በአቡነ ባሲሊዮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመታዘብ ተችሏል።
إظهار الكل...
👍 10🥰 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Update አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ ዛሬ መግለፁ ይታወቃል። እንዴት ማመልከት ይችላሉ? በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ ከሆኑ ያመልክቱ። በ https://portal.aau.edu.et በመግባት Apply for Admission የሚለውን በመጫን መሰረታዊ መረጃዎች ከሞሉ በኋላ Sponsorship ለሚለው Government Scholarship የሚለውን በመምረጥ Other Reason ለሚለው “more than 500 and above” በማለት በክፍት ቦታው ላይ በመፃፍ የ12ኛ ውጤት ያስመዘገባችሁበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማያያዝ ያስፈልጋል፡፡ የማመልከቻ ጊዜ 👇 ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ይህ ጥሪ ከዚህ ቀደም ያመለከቱት አመልካቾች አያካትትም። @tikvahuniversity
إظهار الكل...
👍 13 3
Photo unavailableShow in Telegram
ተማሪዎች እስከ መቼ ማመልከት ይችላሉ ? የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው መረጃ የማመልከቻው ቀን ከዚህ ቀደም በነበረው ማስታወቂያ ዛሬ መስከረም 08/2017 እንደሚያበቃ ቢገለጽም እስከ ነገ መስከረም 09/2017 ድረስ መራዘሙን አስታውቋል። በዚህም በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጾች ፦ ➡️ www.aau.edu.et ➡️ https://portal.aau.edu.et ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል። #ማስታወሻ ፦ ለነፃ የትምህርት እድል ( #ስኮላርሺፕ ) የሚመዘገቡ የተለየ መመዝገቢያ አለመኖሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸው ዩኒቨርሲቲው ከላይ በተጠቀሰው የመመዝገቢያ አማራጭ ብቻ እንዲያመለክቱ መልዕክት አስተላልፏል። @tikvahethiopia
إظهار الكل...
መደበኛ የትምህርት በሬዲዮ መርሀ ግብር የፊታችን ሰኞ መስከረም 13 ዓ.ም ይጀምራል ።
إظهار الكل...
👍 10 2🥰 2
የስልጠና ጥሪ ለመንግስት እና ለግል ቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ በኮ/ቀ/ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የምትገኙ  የመንግስት  እና የግል ቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የቅድመ አንደኛ የእንግሊዝኛ ትምህርት መጽሀፍ ትውውቅ ስልጠና  ለመምህራን ቅዳሜ እና እሁድ በቀን 11_12/1/2017 ጠዋት 2:30 ሰዓት  ጀምሮ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ እንግሊዝኛ መጽሀፍ ከደረጃ 1-ደረጃ 3  የመጽሀፍ ትውውቅ ስልጠና ስለሚሰጥ ከሁሉም የግልና የመንግስት ቅድመ አንደኛ ት/ቤቶች  ከጀማሪ 1 መምህር ፣ከደረጃ አንድ 1መምህር፣ለደረጃ ሁለት ከአንደኛ ክፍል 1 እንግሊዝኛ መምህር በድምሩ ከየት/ቤቱ 3 መምህራን ተለይተው ዝርዝራቸው በሀርድና በሶፍት ኮፒ ይዘው የወረዳ ስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪዎች አርብ ጠዋት 3:00 ሰዓት ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት እንዲገኙ እያሳሰብን የስልጠና ቦታ  ከወረዳ 1-4 ያላችሁ እና ወረዳ 11 አየር ጤና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከወረዳ 5-10 ያላችሁ ደግሞ ወይራ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እንድትገኙ በጥብቅ  እናሳስባለን  ማርፈድም ሆነ መቅረት አይቻልም። #. የአሰልጣኞች ስልጠና የወሰዳችሁ መምህራን እና ባለሙያዎች በቀን 10/01/2017 ከጠዋቱ 3:00 ላይ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኦረንቴሽን ስላለ በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳስባለን ።                     ትምህርት ጽ/ቤቱ
إظهار الكل...
👍 18 2
Repost from N/a

                ቀን 08/01/16
↘️ለ11ዱ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት
   የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ስለመጣ ነገ ማለትም በ 09/01/16 እሰከ 5፡ 00 ፅ/ቤት ሀላፊ ወይም ቡድን መሪ  መጥታቹ እንድትወስዱ እናሳስባለን። #ማሳሰቢያ:-ለመወሰድ የግድ መኪና ሥለሚያስፈልጋችሁ መኪና ማምጣት ይኖርባችኋል።
إظهار الكل...
👍 4🥰 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.