cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Admas University Students' Council (2014 EC — )

The purpose of the student council is to give students an opportunity to develop leadership by organizing and carrying out school activities and service projects. In addition, it works with the university adminstratives in different concerns.

إظهار المزيد
Ethiopia35 179لم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
214
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Please Check your Exit Exam Result using the following Link:https://result.ethernet.edu.et/
إظهار الكل...
2
Sub Saharan Trading PLC is arranging training on (a) how to select a good research topic/title, (b) how to write a good thesis, and (c) panel data analysis. The training is essential especially for postgraduate students and University Lecturers. So, you are invited to take the training. To register, use the following link!!! https://forms.office.com/Pages/ResponsePage.aspx?id=DQSIkWdsW0yxEjajBLZtrQAAAAAAAAAAAAN__iy9p5lUOThPWE1DTjFCSjNSSFQ2NUNPM01RRUE1VC4u
إظهار الكل...
Please fill out this form

👍 2
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምን አሉ ? የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸው ምን አሉ ? - የፈተናው አይነት " የምርጫ ጥያቄ " መሆኑን ገልፀዋል። - የፈተናው ጥያቄ ብዛት በተመለከተ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለፅ፤ የጥየቄው ብዛት ግን ከ50 በላይ እንደሆነ ፤ በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ እንደሚኖር አሳውቀዋል። - በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ ነው ፈተናው ፤ በተወሰኑ መስኮች ምርጫውን ለመሙላት ብዙ ሂሳብ ስለሚሰሩ የጥያቄ ቁጥሩ ከ100 ሊያንስ ይችላል። - ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ ውጤታቸውን ወዲያው መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቢሮርም የመጀመሪያ ቀን የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ቢገለፅ ሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ጫና አንፃር ወይም ፈተናው ቀለል / ከባድ ነው ብሎ እንዳይዘናጋ / እንዳይጨነቅ ወዲያው አይገለፅም። የፈተናው ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና ከተሰጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው። - ውጤት አልፏል ወድቋል ብቻ ሳይሆን ተማሪው ያመጣው ውጤት ይገለፃል። - የጤና ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 30 ይጀምራል እስከ ሐምሌ 8 ድረስ ይዘልቃል። የጤና ተማሪዎች ቀድመው የሚፈተኑበት ምክንያት ቀኑን ሙሉ ፈተናውን ስለሚወስዱ ነው። ጥዋት ላይ ከሙያቸው ጋር የተያያዘውን ይፈታናሉ ፤ ከሰዓት ላይ የመውጫውን ፈተና ይወስዳሉ / በተቃራኒው / ። - ፈተናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የተዘጋጀው ፤ በውስን ኃላፊዎች ብቻ እንዲታወቅ ተደርጓል፤ ስለማይታተም፣ እጅም ስለሌለበት ደህንነቱ አያሰጋንም። - ፈተናውን ከመስጫው ሰከንድ በፊት ማየት የሚችል ሰው አይኖርም። ፈተናው ካለቀበት ሰከንድ በኃላ መስራት የሚችል ሰው አይኖርም። ይህ በማዕከል ነው ቁጥጥር የሚደረገው። - የማለፊያው ነጥብ 50 % እና በላይ ሲሆን ይህን ያላለፉ (ኮርስ ያልጨረሱ) ከ5 / ከ6 ወር በኃላ ጥር እና የካቲት ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መውሰድ ይችለሉ። በዚህም ከለተሳካ ከቀጣይ አመት ተፈታኞች ጋር መውሰድ ይቻላል። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ታቅዷል። - አብዛኛው ተማሪ በመጀመሪያው ዙር ያልፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ካልሆነ ግን በሁለተኛው ዙር ተፈትኖ ያልፋል። ሁለቴ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ እስከሚያልፍ / 50 % እና ከዚያ በላይ ማምጣቱ እስኪረጋገጥ ፈተናውን መውሰድ ይችላል። - ፈተናው ተማሪዎች አልተሳካላቸውም ብሎ የማሸማቀቅ ዓለማ ስለሌለው እስኪያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ። - ምናልባት ያላለፉ ተማሪዎች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ አይጠበቅባቸውም ፤ ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል። - ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች በምረቃ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር የምረቃ ፕሮግራም በተመለከተ በፖሊሲው ላይ እንደማይፅፍ ገልፀዋል። ጉዳዩ የተቋማት ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ በፖሊሲ የሚያስገድደው ግን የመውጫ ፈተናው የስርዓተ ትምህርቱ አካል ስለሆነ ይህን ያላለፈ ዲግሪ/ጊዜያዊ ጭምር፣  ትራንስክሪብት አይሰጠውም። የምረቃ ፕሮግራም ከማዕከል አይመራም ይህ የተቋማቱ ጉዳይ ነው። እኛ የምንከታተለው ፈተናውን ሳያልፉ ዲግሪ እንዳይሰጣቸው ነው። - የምረቃ ጉዳይ እና በዕለቱ በምረቃ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ጉዳይ የሴኔት ነው ትምህርት ሚኒስቴር አይመለከተውም። ነገር ግን የመውጫ ፈተናው እየተሰጠ/ ሳይሰጥ በፊት ምረቃ ማድረግ በፍፁም አይቻልም። - የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ በፍፁም ዲግሪ፣ ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ ሰርተፊኬት እንደማይሰጠው አስገንዝበዋል። @tikvahethiopia
إظهار الكل...
#ይደመጥ የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የ " መውጫ ፈተና " ን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል። በዚህ ማብራሪያ ፦ - የፈተናውን አይነት - የውጤት አገላለፅ - የጤና ተማሪዎች ፈተና / የሙያቸው እና የመውጫው - እንደው ተማሪዎች ፈተናውን ባያልፉ መቼ እና የት ? እስከ ስንት ጊዜ ድረስ ድጋሚ መውሰድ እንደሚችሉ - የፈተናው ደህንነት - የተማሪዎች ምረቃ / ውጤት ያላመጡ ምረቃ ላይ ይሳተፋሉ በሚለው ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አቋም ምን እንደሆነ . . . ሌሎችንም ምላሽ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በዝርዝር ለመላው ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ለተማሪ ወላጆች፣ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አስረድተዋል። ፋይሉ 28.2 MB ነው። Credit : #FBC @tikvahethiopia
إظهار الكل...
በዩኒቨርሲቲ_መውጫ_ፈተና_ላይ_የትምህርት_ሚኒስቴር_የሰጠው_ልዩ_ማብራሪያ.mp328.17 MB
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
የተማሪዎች ምረቃ እና የመውጫ ፈተና ማለፍ / አለማለፍ ለምን አይነጣጠልም ? የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዜዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው ፦ " የ Graduation Ceremony ጉዳይ ፤ በጣም ብዙ ስብሰባ እያደረግን ነው የምንሰራው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ። አንዳንድ ጊዜ መመሪያዎችም ሲወጡ ተሳትፈንበት ፣ ተወያይተን ጠይቀን አንዳንድ ጊዜ compromise አድርገው win win situation እየተደረገ ነው የወጣው። Graduation (ምረቃ) እስከ ዛሬ የነበረው ምን ነበር ? ይሄ የመውጫ ፈተና (exit exam) ታሪክ ከመምጣቱ በፊት፤ በአዋጅ መሰረት አንድ ተማሪ የተወሰነ ፕሬግራሙን አሟልቶ የትምህርት ቤቱ ሴኔት approve አድርጎት ልጁ Graduate ማድረግ ይችላል ሲባል Graduate ያደርጋል ፤ ዲግሪውን ያገኝ ነበር። አንዳንዶቹ ደግሞ ለመርዳት ብሎ walk የሚያደርጉ ይባላሉ ፤ walk የሚያደርጉ ማለት በዛ ዓመት አንድ class ስለቀረችው ልጁ next year ድረስ ከሚቆይ ለበዓሉ አብሮ ይሳተፍ ምክንያቱም አንድ ዓመት ለመሳተፍ ለምን ይቆያል ቤተሰብ አሉት፣ ለቤተሰቡ almost ጨርሻለሁ ብሎ ሊሆን ይችላል አንድ class ነች ያገኛታል ተብሎ ሲታሰብ አብሮ walk እንዲያደርግ ይድረጋል ፤ ይሄም አብሮ ይሳተፋል ፤ የፎቶ ዕድል ያገኛል። ይሄ ማለት ፎቶግራፍ እና ጋዎን ስለለበሰ ልጁ Graduate አድርጓል ማለት አይደለም። የceremonyውን part አብሮ ይሳተፍ ምንም ለውጥ የለውም የሚል ነገር ነበር እኛ ለምሳሌ (ዩኒቲ) walk ማድረግ አቁመናል ቆይቷል እኛ ጋር ለምረቃ የሚገባው ልጅ የሴኔትን approval አግኝቶ የት/ቤቱን ፖሊሲ አክብሮ ከጨረሰ Graduate ያደርጋል፤ ceremony ላይ ይሳተፋል። አሁን exit exam መጥቷል ፤ ይህ ሲመጣ መጀመሪያ ላይ ሲነገር የነበረው ኃላም ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው ' ምረቃ የምትባለዋ ነገር exit exam ላለፈ ልጅ ብቻ ነው ' አሉ ምን ማለት ነው ምረቃ የምትሰጠው ከሆነ ዲግሪውን እየሰጠኸው ስለሆነ ያ የሚሆነው exit exam ሲያልፍ ነው። ስለዚህ exit exam ያለፈ ተማሪ ከሆነ ብዥታ የለም። አሁን Situation የመጣው የexit exam ውጤት ሳይሳካለት ቢቀር / ቢሳካለት የሚለውን ትተን እኛ ceremony ላይ የኛን የሴኔት ጉዳይ የጨረሰ ሴኔት approve ያደረገው ግን exit exam ላይ ያልተሳካለት አብሮ በዓሉ ላይ ቢያከብር ምን አለበት ? የሚል ነው። እኛ ያደረግነው አዎ እነዚህን ሰዎች እናሳትፋቸዋለን፤ የኛን የሴኔት ጉዳይ የጨረሱ ከሆኑ exit exam ብቻ ያለፉትን አናደርግም ለበዓሉ፤ ለበዓሉ አብረው ይሳተፉ። ይሄ ቅርብ ጊዜ ያደረግነው ነው። ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተገናኝነት ለምንድነው exit exam ያለፉትን ብቻ የምታደርጉት እነዚህም ቢሳተፉ ምን አለበት ? ብለን ይሄ የናተ ጉዳይ ነው አለን ትምህርት ሚኒስቴእ እኔ አቋሜ exit exam ተፈትኖ ምረቃ የሚለው ዲግሪ ስትሰጠው ነው አሉ። እኛ የምናደርገው ግን ceremony ይሳተፋል፣ walk ያደርጋል ፤ ዲግሪውን ግን አያገኝም። እንኳን ዲግሪ temporary የሚባለውን አንሰጠውም። በዚህ ተስማምተናል። ምረቃት ላይ ከባችለር ውጭ የexit exam የማይመለከታቸው የማስተርስ ተመራቂዎችም ይሳተፋሉ ፤ በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ላይ የጨረሱ exit exam አይመለከታቸውም እነሱም በሴኔቱ ውሳኔ መሰረት ይሳተፋሉ። ሶስተኛው exit exam ይወስዳል የተባለው ሴኔቱን ካሟላ በምረቃ በዓሉ ላይ እንዲሳተፍ እናደርገዋለን። " @tikvahethiopia
إظهار الكل...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል። የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላት #ማረጋገጥ ችሏል። በዚህ መሰረት ፦ 1ኛ. በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት #በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ኘሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደትም እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስመቅጧል። 2ኛ. በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 /2015 እስከ ሐምሌ 13 /2015 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል። 3ኛ. የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል። በተጨማሪም እንደ አገር ዓመታዊ የትምህርት ካላንደር ከ2016 ጀምሮ ለማስተካከል ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚሁ ማዕቀፍ አንዲያስተካክሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል። ከሀገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የተለያዩ #ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እየሰሙ አለመረጋጋት ውስጥ መግባታቸውን ሲገልፁልን ነበር ፤ በቀጣይም ትምህርት ሚኒስቴር / የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሚሰጡትን ትክክለኛ መረጃ #ብቻ እንድትከታተሉ ፤ በቀረው አጭር ጊዜም ዝግጅታችሁን ታጠናክሩ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን። (ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል #ትክክለኝነቱን ያረጋገጠው ነው።) @tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT
إظهار الكل...
Repost from Admas University
አድማስ ዩኒቨርሲቲ የቃሊቲ ካምፖስ 3ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ አካሄደ። አድማስ ዩኒቨርሲቲ የቃሊቲ ካምፖስ 3ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ አካሄደ። ካምፓሱ ህዳር 17/2015 ዓ.ም "በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስልጠና እና ትምህርት ጥራት" (Technology Supported Quality Education and Training) በሚል ርዕስ ዙርያ ነው። በጥናትና ምርምር ኮንፍረንሱ የጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና ተማሪዎች ተገኝቷል። በጥናትና ምርምር ኮንፈረንሱ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአድማስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ፣ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዳስትሪ ትስስር ዳይሬክተር ተስፋዬ ሙህዬ (ዶ/ር) ሲሆኑ በንግግራቸውም አድማስ ዩኒቨርሲቲ በሚያደርጋቸው የጥናትና ምርምር ተግባራት፣ ግልፅ ዓላማ፣ ችግር ፈቺ እና በተጨባጭ ያሉትን ክፍተቶች የሚሞሉ መሆን ያለባቸው መሆኑን እና ለዚህም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመልዕክታቸውም አሁን በደረስንበት 21ኛው ክ/ዘመን፣ የትምህርት ጥራት ያለ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ትርጉም እንደሌለውና ማሳካትም አዳጋች የሚያደርገው መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ካምፓሱ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግነው ነው ሲሉ አክለዋል፡፡ በመድረኩ ላይ ሶስት ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የመዝጊያ ንግግርና ለመድረኩ ስኬት አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላት በአድማስ ዩኒቨርሲቲ የቃሊቲ ካምፓስ ዲን አቶ ናትናኤል ስዩም የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
إظهار الكل...
إظهار الكل...
National ID Program - Ethiopia

Identity is my right! መታወቅ መብቴ ነው!

I hope most of you need to know it👉👉 https://id.gov.et/
إظهار الكل...
إظهار الكل...
የ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት

የ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት #Etv #EtvEntertainment #EbcEntertainment

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.