cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

ንሴብሖ ለእግዚአብሔር “ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።” — ምሳሌ 9፥9 “ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።” — ሕዝቅኤል 7፥26 በ https://www.tiktok.com/@yaredaweyan

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
8 006
المشتركون
+6324 ساعات
+897 أيام
+12230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✞ ማርያም ብዬ ማርያም ብዬ እዘምራለው እንደአባቶቼ እጠራታለው በያሬድ ዜማ ባዲሱ ቅኔ ልዘምርላት ባዲሱ ቅኔ ማርያም ብዬ በሳት መታጠቂያ ታጥቋል ባለቅኔ ማርያም ብዬ መንፈስ ይማርካል ማህሌት ቸገንቦ ማርያም ብዬ በወርቁ ፅናላይ አርጓል ፀሎቴ ማርያም ብዬ ባአማኑኤል እናት ባንቺው በእመቤቴ አዝ__ ማርያም ብዬ በክብር ደመና ተሞልቷል መቅደሱ ማርያም ብዬ ድንግል ያንቺ ምልጃ ስቦናል ወደሱ ማርያም ብዬ ሆነሽ ተገኝተሻል ሁለተኛ ሰማይ ማርያም ብዬ ጌታ ካንቺ ወቷል የፅድቃችን ፀሀይ አዝ__ ማርያም ብዬ አልጠግብም ስጠራሽ ማር ነሽ ለከንፈሬ ማርያም ብዬ ሳሊለነ እያልኩሽ አለው እስከዛሬ ማርያም ብዬ ፀጋሽ ቤቴን ሞሎቶ ተትረፈረፈልኝ ማርያም ብዬ ሀዘን እና ለቅሶ ከኸላቀረልኝ አዝ__ ማርያም ብዬ የባለጋራዬ ምሽጉ ፈረሰ ማርያም ብዬ በመስቀል ስር ክብሬ እንባዬ ታበሰ ማርያም ብዬ አልፈራም ከንግዲ አለችኝ መከታ ማርያም ብዬ ቁስሌን የምትፈውስ እስሬን የምትፈታ 💚https://t.me/merkorawse💚 💚https://t.me/merkorawse💚
إظهار الكل...
ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

ንሴብሖ ለእግዚአብሔር “ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።” — ምሳሌ 9፥9 “ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።” — ሕዝቅኤል 7፥26 በ

https://www.tiktok.com/@yaredaweyan

❤️ ጼዴንያ ማርያም ❤️ መስከረም ፲ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምትወድና በሚቻላትም ሁሉ የምታገለግላት፣ ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ መነኮስ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አድረው በማግሥቱ ከቤቷ ሲወጡ ማርታ የሚሔዱበትን አገር በጠየቀቻቸው ጊዜ እርሳቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው ቅዱሳት መካናትን እንደሚሳለሙ ነገሯት፡፡ ማርታም ከእርሷ ገንዘብ ወስደው የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ይዘውላት እንዲመጡ ለመነቻቸው፡፡ መነኵሴውም በራሳቸው ገንዘብ ሥዕሉን ገዝተው እንደሚያመጡላት ቃል ገቡላት፡፡ አባ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌም ደርሰው ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ሥዕሏን ሳይገዙ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ?›› የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰምተው ተመልሰው መልኳ ያማረና የተወደደ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ገዝተው በሐርና በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ይዘው እየተጓዙ ሳሉ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ሲደርሱ ወንበዴዎች ተነሱባቸው፡፡ ሊሸሹ ሲሉም ‹‹መንገድህን ሒድ›› የሚል ቃል ከሥዕሏ ወጣ መነኵሴውም መንገዳቸውን በሰላም ተጓዙ፡፡ ሁለተኛም አንበሳ ሊበላቸው በተነሣባቸው ጊዜ ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረላቸው፡፡ አባ ቴዎድሮስ ይህን ኹሉ ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜም ያቺን ሥዕል ለማርታ ከመስጠት ይልቅ ወደ አገራቸው ሊወስዷት ወደዱ፡፡ በመርከብ ተሳፍረው በሌላ አቅጣጫ ሲሔዱም ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያ ወሰዳቸው፡፡ ከመርከብም ወርደው ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ደረሱ፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን ለማርታ አልገለጡላትም፤ እርሷም አላወቀቻቸውም ነበር፡፡ በማግሥቱም ተሠውረው ወደ አገራቸው ሊሔዱ ሲሉ የቅፅሩ ደጃፍ ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ዋሉ፤ በመሸባቸው ጊዜም ወደ ማደሪያቸው ተመለሱ፡፡ ማታ ማታ በሩን ያዩታል፤ ነግቶ መሔድን ሲሹ ግን የበሩ መንገድ ይሠወርባቸዋል፡፡ እንዲህም ኾነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቆዩ፡፡ ማርታም ‹‹አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ኾነህ ነው?›› ሰትል ጠየቀቻችው፡፡ እርሳቸውም ከእመቤታችን ሥዕል የተደረገውን ተአምር ሁሉ ነገሯት፤ ራሳቸውንም ገለጡላትና ሥዕሏን ሰጧት፡፡ እርሷም የእመቤታችንን ሥዕል ተቀብላ የተጠቀለለችበትን ልብስ በፈታችው ጊዜ ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡ ከደስታዋ ብዛት የተነሣም የአባ ቴዎድሮስን እጃቸውንና እግራቸውን ሳመች፡፡ ሥዕሏም ቅዱስ ሉቃስ የሣላት ነበረች፡፡ ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፡፡ በቀንና በሌሊትም የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች፤ ከመቅረዞች ውጭም የሐር መጋረጃን ጋረደች፡፡ ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡ እኒያ መነኰስም እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገሉ ኖሩ፡፡ የሀገሩ ሊቀ ጳጳስም የእመቤታችን ሥዕል ሥጋ የለበሰች ሆና ባገኙና ተአምሯንም በተመለከቱ ጊዜ ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፡፡ ከሥዕሏ ከሚንጠባጠበው ቅባት ቀድተው ለበረከት ሲካፈሉም ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ መላ፡፡ ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜም ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያች አገር በጼዴንያ ትገኛለች፡፡ የሁሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን ትፈውሳለች፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የልጇ፣ የወዳጇ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት አይለየን፡፡ ምንጭ፡ መጽሐፍ ስንክሳር ዘወርኃ መስከረም   ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚https://t.me/merkorawse💚 💚https://t.me/merkorawse💚 💚https://t.me/merkorawse💚
إظهار الكل...
ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

ንሴብሖ ለእግዚአብሔር “ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።” — ምሳሌ 9፥9 “ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።” — ሕዝቅኤል 7፥26 በ

https://www.tiktok.com/@yaredaweyan

🙏 1
🔔✝ ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇 ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዘበነ ለማ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር እዮብ ይመኑ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ 🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
إظهار الكل...
ትምህርቶችን ለማዳመጥ
Photo unavailableShow in Telegram
ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇
إظهار الكل...
ቆየት ያሉ ዝማሬዎች
አዳዲስ ዝማሬዎች
የንስሐ መዝሙሮች
የቸብቸቦ መዝሙሮች
ሁሉንም በአንድ ላይ
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.