cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ደረሳው ሚዲያ

እስላምያላህ ብርሀነው መስመሩን የዘረጋው አላህነውውብያደረገውእሱነው ሚጠብቀው ና እሚከላከልለትአላህነው እኛስራችንን እየጠበቅን ከኢስላም ተጠቅመን የምናልፍሰወችነን የመጠበቅ ግዴታ አለብን እምጠብቀው ኢስላምን በማወቅ ነው ያዘዘንንበመታዘዝ የከለከልንበመከልከል ነው

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
246
المشتركون
+124 ساعات
-57 أيام
-1230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

01:07
Video unavailableShow in Telegram
"መጠጥ እር. ኩስ ነው ማለት ሃጢአት ነው።" ይሄው ቄስ ሌላ ቪዲዮ ላይ "ወይን ቅዱስ ነው" ይላል። . "ይነሳል ቅዱሱ ከጠርሙሱ" የሚለው ዘመቻ ውሃ በላው ማለት ነው። ጠርሙሱ የያዘው መጠጥ ቅዱስ ነው ማለት አይደል? መቼም "ይነሳል ቅዱሱ ከቅዱሱ" አይባል ነገር። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
1.61 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ድሃ እና ሃብታም ~ በመፅሀፍ ቅዱስ ከአስካሪ መጠጥ አንፃር ለድሀዎች ያለው ህግ ለሃብታሞች ካለው የተለየ ነው። 1- ለድሃዎች፦ (ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፤ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድሕነቱንም ይርሳ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ፡፡) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፡6) 2- ለሃብታምስ? (ለነገሥታትና ለሀብታምና ለመሳፍንትም፦ አስካሪ መጠጥ በፍፁም አይገባም፥ ልሙኤል ሆይ፥ ነገሥታት የወይን ጠጅ_ይጠጡ_ዘንድ_አይገባም።) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፥4) ለምን? ለድሃው የተፈቀደው ድህነቱን እንዲረሳ ነው። ሃብታሙ ከዚህ ችግር ነፃ ነው። በመጽሀፉ መሰረት መስከር እንጂ መጠጣት አልተከለከለም። እሺ መጠጣት ከተፈቀደ መጠኑ ምን ያህል ነው? አንዳንዶች እንደሚሉት መለኪያ አይደለም። ይልቁንም ጉዳዩ ለጠጪው የተተወ ይመስላል። እስከሚረካ ድረስ። (ወዳጄ ሆይ ጠጪ እስክትረኪ ድረስ ጠጪ፡፡) (መኀልዬ መኀልዬ ዘሰለሞን 5፡1) ግራ የሚገባው መጽሀፉ ነብያት ሰክረው ወንጀል ፈፀሙ ሲል ነው። ለምሳሌ፦ * የፈጣሪ ነቢይ ኖህ ሰክሮ ራቁቱን ሆነ። (ዘፍጥረት 9:20-21) * በአስካሪ የወይን ጠጅ ስካር ምክንያት ውዱ የእግዚአብሄር ነቢይ ሎጥ ከወለዳቸው ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ሰክሮ ልጆቹ ከአባታቸው ከነቢዩ ሎጥ ዲቃ .ላ ጸነሱ። (ዘፍጥረት 19፡30-36) * አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ። አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው። (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 13፥28) እንደ ኢስላም አስተምህሮት ግን ነብያት ከእንዲህ ዓይነት ሃጢአት ፍፁም እና የተጠበቁ ናቸው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
የወለድ አደጋዎች ~ ዘመናችን በርካታ የቂያማ ምልክቶች የሚታዩበት አስፈሪ ዘመን ነው። ከነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የወለድ መንሰራፋት ነው። ወለድ በቁርኣን፣ በሐዲሥና በምሁራን ኢጅማዕ የተወገዘ እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። ወንጀሉ ምንም እንኳን አደገኛ ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ነው። ከጥፋቱ መስፋፋት በላይ ይበልጥ የሚያሳስበው በተለያዩ ስልቶች የሐላል ቀሚስ ሊያለብሱት አጉል የሚባዝኑ አካላት መኖራቸው ነው። የወለድን ጥፋት ማቃለል በእሳት መጫወት ነው። ለምን? 1. ወለድ ከሰባት ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ ነው። ነብዩ ﷺ “ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ” ይላሉ። “ምን ምን ናቸው እነሱ?” ሲባሉ፡- (الشرك بالله، والسحر، وقتل النفس التي حرّم اللَّهُ إلا بالحق، وأكل الربا، وأكل مال اليتيم، والتّولّي يوم الزّحف، وقذف المحصنات الغافلات المؤمنات) “በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ ጥብቅ ያደረጋት ነፍስ መግደል - በሐቅ ካልሆነ በስተቀር፣ ወለድን መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ በጦርነት ጊዜ መሸሽ፣ ጥብቅና (ከጥፋት) የዘነጉ አማኝ ሴቶችን በዝሙት መወንጀል።” [አቡኻሪይና ሙስሊም] ወለድ ከምን አይነት ወንጀሎች ጋር እንደተቆጠረ ተመልከቱ። 2. ወለድ እንኳን ለአኺራ ለዱንያም አይጠቅምም። ይሄውና አላህ ምን እንደሚል፡- {يَمْحَقُ اللَّهُ الرِّبا وَيُرْبِي الصَّدَقَاتِ} “አላህ አራጣን ያጠፋል። ምፅዋቶችንም ያስፋፋል።” [በቀራህ፡ 276] በየገጠሩ ገበሬውን ባዶውን ያስቀሩት የቁጠባ ተቋማት ናቸው። የወለድ ብድር ውስጥ ገብቶ እንስሶቹ እያለቁ፣ ሰብሉ እየጠፋ፣ ንግዱ እየከሰረ መቀመቅ የገባው እጅግ በርካታ ህዝብ ነው። ወላሂ በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች የወጣ ከዚህ ጋር የተያያዘ ብዙ ለቅሶ ይሰማል። መሬት ላይ ያለው እውነት በቲቪ እንደሚደሰኮረው አይደለም። ነብዩ ﷺ “አንድ ሰው ከወለድ አያበዛም ፍፃሜው መመናመን ቢሆን እንጂ” ይላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5/120] 3. ያለ አስገዳጅ ሁኔታ ከወለድ ጋር የሚነካካ በሁሉም አቅጣጫ የተረገመ ነው። ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- ((لعن رسول الله - صلى الله عليه وسلم -: آكل الربا، وموكله، وكاتبه، وشاهديه))، وقال: ((هم سواء)) “የአላህ መልእክተኛ ﷺ ወለድ የሚበላንም፣ የሚያበላውንም፣ ፀሐፊውንም፣ ምስክሮቹንም ተራግመዋል። ‘ሁሉም በወንጀሉ እኩል ናቸው!’ ብለዋል።” [ሙስሊም፡ 1598] “እኔ ቢቸግረኝ ወሰድኩ እንጂ አራጣ አበዳሪ አይደለሁም” ብለህ እንዳትሸወድ። ያለፈውን ሐዲሥ ተመልከት። በተጨማሪም ነብዩ ﷺ “ወሳጅም ሰጪም እኩል ናቸው” ማለታቸውን ያዝ። [ሙስሊም፡ 1584] ስለዚህ ሙስሊም የሆነ ሰው ሌላው ቀርቶ በወለድ ተቋማት ውስጥ ጥበቃና ፅዳት እንኳን ሊሰራ አይገባውም። 4. ወለድ ውስጥ የገባ ሰው ከአላህ ጋር ጦርነት ውስጥ ነው የገባው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَذَرُوا مَا بَقِيَ مِنَ الرِّبا إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ * فَإِنْ لَمْ تَفْعَلُوا فَأْذَنُوا بِحَرْبٍ مِنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ} “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ። ከአራጣም የቀረውን ተው። አማኞች እንደሆናችሁ (ተጠንቀቁ።) (የታዘዛችሁትን) ባትሰሩም ከአላህና ከመልእክተኛው በሆነች ጦር (መወጋታችሁን) እወቁ።” [አልበቀራ፡ 278-279] ይቺ በነብዩ ﷺ ላይ መጨረሻ ላይ የወረደች አንቀፅ ነች ይላሉ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁማ። [አቡኻሪይ፡ 2086] 5. ወለድ የሚበላ ሰው ከቀብር የሚነሳው ልክ በጂን እንደተለከፈ ሰው እየተሳከረ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسِّ} “እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ከመንካቱ የተነሳ የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጂ (ከመቃብራቸው) አይነሱም።” [አልበቀራ፡ 275] 6. ወለድ ምህረት የለሸ ወንጀል ነው። ነብዩ ﷺ “ምህረት ከማያገኙ ወንጀሎች ተጠንቀቅ። … ወለድን መብላት። ወለድን የበላ ሰው በቂያማ ቀን ሸይጧን የሚጥለው እብድ ሆኖ ነው የሚነሳው” ካሉ በኋላ የላይኛውን አንቀፅ አነበቡ። ስለዚህ ትክክለኛ ተውበት ካልኖነረ ጥፋቱ አደገኛ ነው። 7. ወለድ የከሃዲዎቹ አይሁ.ዳውያን ተግባር ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {وَأَخْذِهِمُ الرِّبا وَقَدْ نُهُوا عَنْهُ وَأَكْلِهِمْ أَمْوَالَ النَّاسِ بِالْبَاطِلِ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ مِنْهُمْ عَذَاباً أَلِيماً} “ከርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣንም በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባብ በመብላታቸውም ሳቢያ (የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው።) ከነሱም ለከሃ .ዲዎቹ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጀን።” [አኒሳእ፡ 161] 8. የወለድ መብዛት የቂያማ ምልክት ነው። ነብዩ ﷺ “ቂያማ ሲቃረብ ወለድ፣ ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ይበዛል” ይላሉ። [ሶሒሑ ተርጊብ ወተርሂብ፡ 1861] 9. ወለድ የሚበላ ሰው አሰቃቂ ስቃይ አለበት። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- “ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎችን አየሁኝ። ወደተቀደሰች ምድርም ይዘውኝ ወጡ። ደም የሚጎርፍበት ወንዝ እስከምንደርስም ተጓዝን። በውስጡ አንድ የቆመ ሰው አለ። ከወንዙ ዳርቻ አንድ ሰው አለ። ከፊት ለፊቱ ድንጋዮች አሉ። ወንዙ ውስጥ ያለው ሰውየ ሊወጣ ሲያመራ ዳር ላይ ያለው ሰውየ አፍ አፉን በድንጋይ እየመታ ወደነበረበት ይመልሰዋል። ሊወጣ በሞከረ ቁጥር ድንጋይ እየወረወረ አፍ አፉን ይመታዋል። ከዚያም ወደነበረበት ይመለሳል። ‘ማነው ይሄ ወንዙ ውስጥ ያየሁት?’ ስል ‘ወለድ የሚበላ ነው’ ይለኛል።” [አቡኻሪይ፡ 2085] 10. ወለድ ከምናስበው በላይ እጅግ የገዘፈ ወንጀል ነው። ነብዩ ﷺ “ወለድ ሰባ ሶስት አይነት ነው። ከነዚህ ውስጥ ቀላሉ አንድ ሰው እናቱ ላይ ዝሙት እንደመስራት ነው” ይላሉ። [ሶሒሑ ተርጊብ ወተርሂብ፡ 1851] 11. የወለድ መብዛት በምድር ላይ የአላህን ቅጣት ያስከትላል። ነብዩ ﷺ “ዝሙትና ወለድ በአንድ ሃገር ላይ ከበዛ በራሳቸው ላይ የአላህን ቅጣት አስወስነዋል” ይላሉ። [ሶሒሑ ተርጊብ ተርሂብ፡ 1859] ወንድሜ! አላህን ፍራ! እህቴ ሆይ! አላህን ፍሪ! ህይወት ማለት የዱንያ ህይወት ማለት አይደለም። ይቺማ ጤዛ'ኮ ናት። ይልቅ ነብዩ ﷺ ምን እንደሚሉ ተመልከት፡- “አንድ ሰው የሚያገኘው ገንዘብ ከሐላል ይሁን ከሐራም ደንታ የማይኖርበት ዘመን በሰዎች ላይ ይመጣል።” [አቡኻሪይ፡ 2059] ልብህ ካልሞተ ይሄ አስፈሪ መልእክት አለው። ሰው እንዴት ራሱን የቂያማ ምልክት ያደርጋል?! ፍጥጥ ባለ መልኩ ሐራም ላይ መግባት ሲኖርስ? ያውም በአራጣ? አላህ ለሸሪዐዊ ትእዛዝ እጅ የምንሰጥ፣ ከዱንያ ይልቅ ኣኺራን የምናስቀድም ያድርገን። ኣሚን። = (ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

00:47
Video unavailableShow in Telegram
ሁሉም የፈለገውን የታየውን መስራት ይችላል! የፈለከውን የታየህን የምታደርገው አልባበስ ላይ እና ምግብህ ላይ ብቻ ነው። .....✍️እኔ እምለው የሀይማኖት አባት ናችሁ የፖለቲካ አባት⁉️ አይ ኢኽዋን⁉️ የተውሒዱ ጠላት የሐቁ ሙደሊስ፡ የሙስሊም ተቋም ነው አሁን ይሔ መጅሊስ? ውሸት የሚናገር ባጢልን ደፋሪ፡ ከሱና የራቀ እጅግ አሳፋሪ!? ተመልከት ኢኽዋንን አጠለቀች ገዋን፡ የትላንቱን ጩኸት ጥላ ነጠላዋን፡ ሁሉም ይቻላል ነው ከተገኘ ወንበር፡ ሰሚ የለም እንጅ ተው ብለን ነበር፡ ስልጣኑን ካጋራን ከተሸጋሸገ፡ የፈለገ ይተው ያክብር የፈለገ፡ በተለይ ለመጅሊሱን ብትጋብዙ ምግቡ፡ እኛ ከናንተ ጋር የለንም ግብግብ፡ ሁላችን አንድ ነን የስልጣን ላይ እርግብ፡ «እርግብግብታም መተታም ኮተታሞች ናችሁ። የታላቁ ጌታ ሀይማኖት ነብያችን صلى الله عليه وسلم ደማቸውን ያፈስሱለትን ዲን ግን የታየህን ልታደርግ ያልተመቼህን ልትተው አትችልም በቃ መብቱ የለህማ። .....✍️ኑረዲን አል አረብ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi
إظهار الكل...
1.32 MB
Show comments
የሞኝ ቀልድ አትቀልድ! ~ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣ በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ … ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:– من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي. "ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም] በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:– لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً. "ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።" አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው የምሩንም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502] = (ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 30/2010) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሐዲሦችን ሐፍዘዋል። 5ሺ አካባቢ የሚሆኑ የደዕዋና የፈትዋ ካሴቶችን አበርክተዋል። ከመቶ የሚበልጡ በሐዲሥ ጥናት ላይ ብቻ ያተኮሩ ኪታቦችን ፅፈዋል። እንዲሁም በሌሎች ኢስላማዊ የእውቀት ዘርፎችም የተፃፉ እጅግ ውድና በርካታ ድርሳናትን ለኡማው አበርክተዋል። በዓለም-አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ተማሪዎችን አፍርተዋል። የነቢዩን ﷺ ሐዲሦችን ደረጃ በማጣራትና በመልእክተኛው ስም የሚወሩ መሰረተ-ቢስና ደካማ “ሐዲሦችን” አበጥሮ በማውጣት ለኡማው ባደረጉት ታላቅ አስተዋፅኦ ኢስላምን ላቅ ባለ ሁኔታ ላገለገሉ ምሁራን የሚበረከተውን አለም አቀፉን የንጉስ ፈይሰል ሽልማት በ1419 ዓመተ-ሂጀራ (1999 እ.ኢ.አ) ተሸላሚ ሆነዋል። ባጠቃላይ ሸይኹ በተለይም በሙስጦለሐል ሐዲሥ (የሐዲሥ ጥናት) ዘርፍ ሑጃ ናቸው ይላሉ ዓሊሞች። በመጨረሻም ጁማደሣኒያ 1419 ዓመተ-ሂጅራ (እ.ኢ.አ. ኦክቶበር 1999) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ረሒመሁላህ ረሕመተን ዋሲዓህ። ስለ ሸይኹልአልባኒይ ታላላቅ ዓሊሞች ምን ብለዋል? ጥቂት ብቻ ልጥቀስ:- 1. ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ባዝ ረሒመሁላህ (የቀድሞው የሰዑዲያ ጠቅላይ ሙፍቲ)፡- “በዚህ ዘመን ከሰማይ በታች እንደታላቁ ዓሊም ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአልባኒይ ሐዲሥን የተገነዘበ ሰው አላውቅም።” በአንድ ወቅት ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፡ “ረሱል ﷺ በሐዲሣቸው በየመቶ ዓመቱ ለዚህ ኡማ አላህ ዲኑን የሚያድስለት እንደሚልክለት ተናግረዋል። በዘመናችን ይሄ ሙጀዲድ (የተሀድሶ አራማጅ) ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ምላሻቸው፡ "እንደኔ እይታ የዚህ ዘመን ሙጀዲድ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአልባኒ ነው፣ ወላሁ አዕለም” የሚል ነበር። 2. ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሠይሚይን ረሒመሁላህ፡- “አልአልባኒይ ከአህለሱና ነው ለሱና ዘብ የቆመ። በሐዲሥም ኢማም ነው። በዘመናችን ከሱ ጋር የሚነፀፀር አንድም አናውቅም።” “የተገናኘነው ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም በተገናኘንበት አጋጣሚ ያስተዋልኩት በዐቂዳም በተግባርም ሱናን ለመተግበርና ቢድዐን ለመዋጋት ወደ ኋላ የማይል እንደሆነ ነው። ሰውየው በዘገባም ይሁን በግንዛቤ እጅግ የገዘፈ ዕውቀት ባለቤት ሲሆን በዒልሙም በመንሀጁም ወደ ሐዲሥ ዒልም ሰዎችን በማዞርም የላቀው አላህ በርካቶችን ጠቅሞበታል። ይህ ለሙስሊሞች ትልቅ ስኬት ነው።” 3. ሸይኽ ሙቅቢል ብኑ ሃዲ አልዋዲዒይ ረሒመሁላህ (የየመን ሀገር ሙሐዲሥ)፡- “ዛሬም በሸይኹልአልባኒይ ኪታቦች ትግላችንን አጠናክረን ቀጥለናል።” “ስለ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአልባኒ አላህ ይጠብቀውና በተደጋጋሚ ተጠይቄያለሁ። በርካታ ሰለፎች ከነሱ ስለሚበልጥ ሰው ሲጠየቁ ይሉ የነበረውን ነው የምለው። 'እኔ ነኝ ስለሱ የምጠየቀው? ወይስ እሱ ነው ስለኔ የሚጠየቀው?!' ችግሩ ያለንበት ዘመን በርካቶች ዓሊምና ጠንቋይ ሙእሚንንና ከ.ሀዲ ሶሻሊስትን የማይለዩበት ዘመን ነው።… አህለ ሱና ያልሆኑ ሰዎች እንጂ በሸይኹልአልባኒይ እውቀት ማንም አይጠራጠርም። እኔ የማምነው ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአልባኒይ ‘አላህ በየመቶ ዓመቱ ለኡማው ዲኑን የሚያድስለት ይልካል' የሚለው ሐዲሥ ከሚያረጋግጣቸው ሙጀዲዶች እንደሆነ ነው።” 4. ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ኣሊሸይኽ (የአሁኑ የሰዑዲያ ጠቅላይ ሙፍቲ)፡- “ሸይኹልአልባኒይ ሐዲሥን በተግባር የሚወድ ለሐዲሥ ጥናት ጥበቃና እንክብካቤ የሚያደርግ ታማኝ የሸሪዐ ምንጭ የሆነ ቅርብ ወንድማችን ነው።” = (ኢብኑ ሙነወር፣ 2001) የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Photo unavailableShow in Telegram
ከዚህ በፊት "ከሚገርመኝ ነገራቸው ውስጥ አንዱ አስካሪውን መጠጥ "ቅዱስ ጊዮርጊስ" ብለው መሰየማቸው ነው። ሃይማኖት ያለው ሰው እንዴት ይህን ለጤናም፣ ለማህበረሰብም ጠንቅ የሆነ ቆሻሻ አተላ "ቅዱስ" ብሎ ይጠራል?!" ብዬ ፅፌ ነበር። አሁን "ይነሳል ቅዱሱ፣ ከጠርሙሱ" የሚል ዘመቻ ሳይ ትዝ አለኝ። "መጠጡ በእምነት ክልክል ካልሆነ ምን ችግር አለው? " የሚል ጥያቄ ግን አጥጋቢ ምላሽ የሚያገኝ አይመስለኝም። የሚገርመው ደግሞ ዘመቻቸውን በቁጭት ለማድመቅ "መሀመድ ቢራ የሚባል አለወይ?" ሲሉ ነው። ምኑን ከምኑ ነው የምታወዳድሩት? በሙሐመድ አስተምህሮ'ኮ አስካሪ መጠጥ ሐራም ነው። መጠጣት የሚያስገርፍ ወንጀል ነው። እናንተስጋ? መፅሀፉ የሚለው "ድሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ።ጕስቁልናውንም ከእንግዲህ አያስብ" ነው። (ምሳ 31፤7-8) ለማንኛውም ለቀጣይ ዘመቻ የሚሆን ርእስ ላስታውሳችሁ። "ቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤትም" ስሙን እንዲቀይር ተንቀሳቀሱ። እንደ መፅሀፉ አስተምህሮት "ዘፋኝ መንግስተ ሰማያት አይገባም።" ቅዱስ ዮሐንስ (St John) የሚል መጠጥም ያለ መሰለኝ። ቡናም በኢ.ኦ.ቤ.ክ "ሐራም" ነው። ለማስታወስ ያክል ነው። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
ታላቁ የሐዲሥ ፈርጥ ከአውሮፓዊቷ አልባኒያ ምድር ~ የዘመናቸው ምሁራን አላህ በየክፍለ ዘመኑ ዲኑን እንዲያድሱ ከሚልካቸው የለውጥ ሰዎች አንዱ እንደሆኑ ያምናሉ። በሐዲሡም በፊቅሁም መስክ የነጠረ እውቀት ያካበቱ ለመሆናቸው ሁለት ሚዛናዊ ሰዎች አይወዛገቡባቸውም፣ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አል አልባኒይ ረሒመሁላህ። ሸይኹል አልባኒይ በ1332 ዓመተ ሂጅሪያ (1914 እ.ኢ.አ) በጊዜው የአልባኒያ ዋና ከተማ በነበረችው አሽቆድራ ተወለዱ። ቤተሰባቸው ድሃ ግን ኢስላማዊ ድባብ ያከበረው ነበር። አባታቸው ሐጂ ኑሕ ከኢስታንቡል የሸሪዐ ተቋም የተመረቁ ሲሆኑ በአካባቢያቸው እውቅ የሐነፊያ መዝሀብ አስተማሪ ነበሩ። በአልባኒህ የልጅነት ዘመን ሀገራቸው አልባኒያ አሳዛኝ በሆነ ታሪካዊ ቀውስ ውስጥ ወደቀች። በጊዜው የሀገሪቱ መሪ የነበረው አህመድ ዛጉ ሀገሪቱን መርዛማ ዝገት አለበሳት። ሀገሪቱ ፅንፈኛና ለኢስላም ጥላቻን የደቀነ ምእራብ-ወለዱን የክህ .ደት ስርዓት/ሴኩላሪዝም የሀገሪቱ ስርዓት አድርጎ አወጀ። የዚህን ጊዜ ነበር የአልባኒይ አባት ሐጂ ኑሕ ከነቤተሰባቸው ኩፍርን ሸሽተው ሂጅራ ያደረጉት፣ እትብታቸው ከተቀበረበት አልባኒያ ወደ ደማስቆ ሶሪያ። ለአላህ ሲባል የተከፈለ ታላቅ መስዋእትነት! አልባኒይ ይሄንን የአባታቸውን ውለታ እንዲህ ሲሉ ደጋግመው ያነሱት ነበር። “ጌታዬ በኔ ላይ የዋለውን ፀጋ ቆጥሬ አልዘለቀውም። ምናልባትም ከዋለልኝ ፀጋዎች ሁሉ ትልልቆቹ የአባቴ ወደ ሻም መሰደድና የሰዓት ጥገና ሙያውንም ለኔ ማስተማሩ ነው።” ሸይኹል አልባኒይ በደማስቆ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በከፍተኛ ውጤት ቢያጠናቅቁም መደበኛው ትምህርት የአባታቸው ፍላጎት አልነበረምና ሳይገፉበት ቀርተዋል። ይሁን እንጂ በቁርኣን፣ በተጅዊድ፣ በነሕውና ሶርፍ እንዲሁም ፊቅህ በሐነፍያ መዝሀብ አጠናክረው ቀጠሉ። ቁርኣንን ካባታቸው ላይ የሐፈዙት ሸይኹልአልባኒይ የሰዓት ጥገና ሙያንም በሚገባ ቀስመዋል። በሙያውም ታዋቂ ከመሆናቸውም በላይ እየጨመረ ለመጣው ዲናዊ ትጋታቸው ጊዜ እንዲኖራቸው አስችሏቸዋል። የሐነፊያን መዝሀብ አጥብቀው የሚከተሉትና ከሱ ውጭ ግራ ቀኝ ማየት የማይፈልጉት የአልባኒይ አባት ልጃቸውም በዚሁ ፈለግ እንዲጓዝ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ በሐዲሥ ጥናት ላይ እንዳይሰማሩ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር። ይሁን እንጂ የአንድን መዘሀብ ጭፍን ተከታይነት በፅኑ ለሚያወግዙት አልባኒይ ይሄ ነገር ፈፅሞ የሚዋጥላቸው አልሆነም። ገና በሀያ ዐመታቸው አካባቢ ነበር የሐዲሥ ጥናታቸውን አፋፍመው የጀመሩት። ለጥናታቸው አጋዥ የሆኑ ኪታቦችን አቅማቸው በፈቀደ እየገዙ ከዚህ ባለፈም ደማስቆ ከሚገኘው “አዟሂሪያ” ቤተ መጻህፍት እየተዋሱ ይጠቀሙ ነበር። በጥናታቸው በገፉ ቁጥር ሱቃቸውን እየዘጉ ሰፊ ጊዜያቸውን በቤተ መጻህፍቱ ማሳለፉን ተያያዙት። ትጋታቸውን ያስተዋሉት የቤተ መጻህፍቱ ሀላፊዎችም ባሰኛቸው ጊዜ መጠቀም ይችሉ ዘንድ አንድ ልዩ ክፍልና የቤተ መጻህፍቱን ቁልፍ በማስረከብ ለሸይኹ ብቻ ሳይሆን ለሙስሊሙ ዐለም ባጠቃላይ ትልቅ ውለታን ጥለው አልፈዋል። ከዚህ በኋላ አልባኒይ ከሶላት ውጭ ከማለዳ እስከ ዒሻ በኋላ ቤተ መጻህፍቱን ቤታቸው አደረጉት። ጥናታቸውን አጠናክረው የቀጠሉት ሸይኹልአልባኒይ የኋላ ኋላ በሐዲሥ ጥናት መስክ ብቻ ከመቶ በላይ ኪታቦችን ለኡማው አበርክተዋል። በዘርፉ ከተሰማሩ ሌሎች ዐሊሞች ጋር ሲታዩ ሸይኹል አልባኒይ ጫፍ የደረሱ ነበሩ ማለት ይቻላል። እንዲያውም ዐሊሞች “የነኢብኑ ሐጀር አልዐስቀላኒን፣ ኢብኑ ከሢርንና የሌሎችንም ሙሐዲሦች ዘመን እንደ አዲስ አመጣው” ሲሉ አወድሰዋቸዋል። የተውሒድና የሱናን ባንዲራ ሶሪያ ምድር ላይ ቀላል ለማይባል ጊዜ ያውለበለቡት ሸይኹል አልባኒይ ከተቀናቃኞቻቸው ጋር በዐቂዳ፣ በኢቲባዕ (ረሱልን ﷺ በመከተል)፣ በመዝሀብ ጭፍን ተከታይነትና በቢድዐ ዙሪያ በርካታ ውይይቶችን አድርገዋል። በሂደቱም በመዝሀብ ጭፍን ተከታዮችና በሱፊያ ሸይኾች ቀስቃሽነት ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል። በተመሳሳይ ጊዜ ደማስቆ ውስጥ ከሚገኙ ስመ ጥር ዓሊሞች በአቋማቸው እንዲገፉ ያላሰለሰ ማበረታቻ ከጎናቸው ነበር። ትግላቸውን አጠናክረው የዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ጭምር የሚካፈሉበት ደርስ እንዲሁም ወደተለያዩ የሶሪያና የዮርዳኖስ ከተሞች እየተዘዋወሩ ወርሃዊ ደዕዋ ማድረግ ቀጠሉ። ኳታር፣ ግብጽ፣ ኩዌት፣ ዐረብ ኢማራት፣ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝና ስፔን በተለያዩ ጊዜያት ለደዕዋ ከተጓዙባቸው ሃገራት ውስጥ ናቸው። ስራዎቻቸው ለህትመት ከበቁ ስማቸው በሰፊው ከታወቀ በኋላ በዝነኛው የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ሆነው ተመርጠው ለሶስት ዓመታት አገልግለዋል። ከዚህ በኋላ ሱቃቸውን ለአንድ ወንድማቸው በመተው ሙሉ ለሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ጥንታዊው የ“አዟሂሪያ” መክተባ ተመለሱ። ኢማሙል አልባኒይ ምንም እንኳ ከፖለቲካ የራቁ ቢሆኑም በተለያዩ ጊዜያት መንግስት በዐይነ ቁራኛ ይከታተላቸው ነበር። ሁለት ጊዜም ለእስራት ተዳርገዋል። በሁለተኛ እስራታቸው ከታላላቅ ዐሊሞች ጋር የተገናኙ ሲሆን በእስራት ላይ እያሉም የሙንዚሪን “ሙኽተሶሩ ሶሒሕ ሙስሊም ‘ተሕቂቅ' አድርገዋል። ለሐቅ ባላቸው ፅኑ አቋምና ለለውጥ ባላቸው የማይታጠፍ ተጋድሎ የሚታወቁት ሸይኹል አልባኒይ ውጫዊ የአመለካከት ወረራዎችን ብቻ ሳይሆን የኢስላምን ውበት ያደበዘዙ ውስጣዊ ወረራዎችንም በመዋጋት ፋና ወጊ ነበሩ። አልባኒይ ለተስፊያና ተርቢያ ማለትም ኢስላምን ከቢድዐ፣ ከሺርኪያት፣ ከደካማ ማስረጃዎችና ሰርጎ-ገብ አመለካከቶች ማፅዳት እንዲሁም ትውልድን ቁርኣንና ሶሒሕ ሱና ላይ በተመሰረተው ንፁሁ ኢስላም ላይ ኮትኩቶ የማውጣት አካሄድ ልዩ ትኩረት ይሰጡ ነበር። ከግማሽ ክፍለ-ዘመን በላይ የተጓዙበትን ይህን አካሄዳቸውን በርካቶች እንዲያጤኑበትና እንዲሄዱበት ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል። ለኡማው አንድነት እጅግ የሚጨነቁት አልባኒይ ለአንድነት የሚደርገው ጥረት ፍሬ ያፈራ ዘንድ ግን ከባዶ የ”አንድ እንሁን” ጩኸት ባለፈ የግድ ወደ ቁርኣንና ሱና መመለስ እንደሚያስፈልግ በፅኑ ያሳስባሉ። እዚህ ላይ በአንድ ወቅት ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡትን መልስ ብናነሳ አይከፋም። ጥያቄ፡- “ትክክለኛ ነገር ካልያዝን ብለን ከምንበታተን በስህተት ላይ ሆነን ብንሰባሰብ ይሻላል። መክንያቱም ሐቅ ሁሉ ትክክል አይደለምና። እንዲሁም ባጢል (ውድቅ ነገር) ሁሉም ስህተት አይደለምና!” አልባኒይ፡- “ይሄ ምናባዊና ቅዠታዊ ንግግር ነው። በስህተት ላይ ከሆንን መሰባሰባችን ምንድን ነው ፋይዳው? ከፊላችን በስህተት ላይ ከፊላችን ደግሞ በሐቅ ላይ ከሆንን ብንለያይ ምንድን ነው ጉዳቱ? አሸናፊና የላቀው ጌታችን እንዲህ ይላል:- {ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ምን አለ?} ሸይኹል አልባኒይ በጠንካራ የሰለፊያ አቋማቸው የተነሳ ብዙ ሰቃይና እንግልት ደርሶባቸዋል። ለኢስላም ሲባል ከአልባኒያ የተጀመረው ስደት ደማስቆን መጨረሻው አላደረገም። በተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ከሶሪያ ወደ ዮርዳኖስ፣ ከዮርዳኖስ ዳግም ወደ ሶሪያ፣ ከዚያም ወደ ሊባኖስ፣ ከዚያም ወደ ዐረብ ኢማራት፣ በመጨረሻም ወደ ዮርዳኖስ ዐማን ተንከራተዋል።
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Photo unavailableShow in Telegram
ድቤ መደብደብ የለውም አደብ ~ ዱዓእ፣ ዚክር እና ሶለዋት ዒባዳዎች ናቸው። ስለዚህ ዋጋ እንዲኖራቸው፣ አላህ እንዲቀበለን በአደብ መፈፀም ይኖርብናል። ከነዚህ አደቦች ውስጥ 1ኛው ኢኽላስ ነው። ለይዩልኝና ይስሙልኝ፣ ለጉራ፣ ለእልህ፣ ለመዝናናት፣ ... ሳይሆን አላህን ብቻ በማሰብ መፈፀም። 2ኛው አደብ ከነብያችን ﷺ በተገኘው መልኩ መፈፀም ነው። ድምፅን ዝቅ ማድረግ ለኢኽላስ የቀረብ ነው። በመተናነስ መፈፀምም ሌላ ወሳኝ ነጥብ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:- { وَٱذۡكُر رَّبَّكَ فِی نَفۡسِكَ تَضَرُّعࣰا وَخِیفَةࣰ وَدُونَ ٱلۡجَهۡرِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡـَٔاصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡغَـٰفِلِینَ } ''ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በሆነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው። ከዘንጊዎቹም አትኹን።" [አልአዕራፍ፡ 205] በዱዓእ፣ በዚክር እና በሶላት ዐለ'ነቢ መጨፈር ከአደብ የወጣ ተግባር ነው። ስሜት ውስጥ ገብተው ከፍ ያለና ትርጉም የለሽ ወጣ ያለ ድምፅ የሚያሰሙም አሉ። ይህም ወሰን መተላለፍ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:- { ٱدۡعُوا۟ رَبَّكُمۡ تَضَرُّعࣰا وَخُفۡیَةًۚ إِنَّهُۥ لَا یُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِینَ } "ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት። እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።" [አልአዕራፍ፡ 55] በዚክርና በሶላት ዐለ'ነቢ ወቅት ማጨብጨብ፣ ፉጨት፣ ማናፋት፣ ማቃሰት፣... የሙሽሪኮች እንጂ የሙስሊሞች አደብ አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል:- { وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَیۡتِ إِلَّا مُكَاۤءࣰ وَتَصۡدِیَةࣰۚ } {በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አልአንፋል፡ 35] ስለዚህ እነዚህ ዒባዳዎች ልብንን ሰብሰብ አድርጎ፣ መልእክቱን እያስተዋሉ በኹሹዕ መፈፀም ይገባል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.