cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ጣፍጭ የፍቅር ወጎች ♥️

እንኳን ወደ ጣፋጭ የፍቅር ወጎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ🙏★ከንጋት እስከ ንጋት በአብሮነት ወደ 🅕🅘🅚🅘🅡👑★ እውነተኛ የፍቅር ታሪኮች መገኛ ነን 👇ይሄን 1ጊዜ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ👇

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
79 623
المشتركون
-9924 ساعات
-8507 أيام
-1 56230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
Binance Telegram ላይ የራሱን Mine app Launch አድርጎዋል ። ለመጀመር ➡️https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startapp=ref_1753715732&startApp=ref_1753715732
إظهار الكل...
👍 1👏 1
🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁   የታሪኩ ርዕስ 😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓       🌀 #Part 3⃣1⃣ ✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ የደሀ ልጅ ፍቅር  ከአሁን ቡሀላ ብደዉይ ..... የባለተቤትሽ ስልኩን ወይም አድራሻዉን አፈላልጌ እነግርልሻለሁ.......አልኳት... ......ሰአዳም እሺ ብላ ጊዜ ሳፈጅ ስልኩን ዘጋችው >>>>>>> ሳላስበው ነበር ይህን ሃሳብ የተናገርኳት እንዴት እንደዚህ እንዳልኳት ይገርመኛል...ከኔ አፍ ነዉ የወጣዉ ወይስ ሌላ ተናገር የሚል ሀይል ያለ ይመስለኛል፡፡   .   ሰአዳ ይሄን ከተናገርኳት ቡሀላ በዚያው ቀረች..መደዋወል አቆምን እሷም አደዉል እኔም አልደዉልም.......   የሚገርም ነገር ነዉ በሒደት ጓደኞቼ ሲነግሩኝ.. አንዱ እንዲህ አለኝ አንተ ዉጭ ሁነህ የፍቅር ግንኙነት እንዳላችሁ አላቅም  እኔ ሰአዳን ለማግባት ተስማምተን  ከከተማ ወጣ ብለን ከሰአዳ ጋር እየተዝናኑ የተነሱትን ፎቶ አሳየኝ፡፡ ፎቷቸዉን ስመለከት ገረመኝ...ደግሞ በሌላ ቀን ይባስ ብሎ አንዱ ሰይድ የሚባል ልጅ ስለፍቅር እንደሚያወሩና ከከተማ ወጣ እያሉ እየተገናኙ በፕሮግራም እንደሚያወሩ ነገረኝ፡፡     ያአላህ የኔ ጅልነት የሰአዳ አልታመን ባይነት አላህን ሳማርር የነበረው ሁሉ ከፊቴ መጣብኝ ምን ይባላል አስተግፊሩሏህ ብቻ ነው ፡፡ አቤት የኔ ሰው ማመን ስንቱን ወንድ ስለትዳር አውርታዋለች የኔን ጓደኛ ሳይቀር ልታገባው ጨርሳ እንደነበር ወላሂ ነገሩኝ፡፡     ሌሎች ሴቶች ቃላቸውን በፅናት ሲጠብቁ አባቶቻቸው እንገላለን ብለው ሴቶቹ አብረህ ግደለን ብለው ወላጆቻቸውን አሸንፈው ያሳመኑት ሁሉ ታሪካቸው ፊቴ ላይ መጣብኝ፡፡ ከዚያን ቀን በኋላ በሰአዳ ቤተሰቦች ላይ ያለኝ መጥፎ አመለካከት ተስተካከለ ጥፋተኛዋ ራሷ ሰአዳ መሆኗ ገባኝ ፡፡እኔን የምታስታውሰኝ ትዝ የምላት የማትፈልጋቸው ሰወች ሲጠይቋት ለመከላከል የምወደዉ ከድር አለኝ እያለች፡፡ የምትፈልጋቸው ብር ያለዉ ሰዉ ሲመጡ እሽ ፈቃደኛ ነኝ የምትል አይነት ሰው እንደሆነች ገባኝ፡፡ በጣም የሚገርመኝ እንደምትወደኝ የምታስመስለው ነገር እንባ ለማምጣት ስትሞክር እኔም አምኜ መሸወዴ ነገሩ ደግ የሆንኩ የራሴ ሞኝነት ነው፡፡ ከዚያ .እኔም በግል ዲፕሎማ ትምህርት ጀመርኩ ሶስት አመት ጨርሸ  በLevel 4 ተመረኩኝ፡፡       የሰአዳ ፍቅር ብዙ መዘዝ አምጥቶብኛል ስራ ጠልነት..የምግብ ፍላጎት መቀነስ ...የሰውነት ድርቀት  .....ከሰወች ጋር ተቃራኒ መሆን ....ገንዘብ ማባከን ሆነ ስራየ ...>>የሚገርመኝ እንደዚህ ተናግሪያት የሷን መጥፎ ጎን ሰምቼ ለራሱ ልረሳት አልቻልኩም.....ስራ መስራት አልቻልኩም   ሌላ ሴት ለማግባት የሰአዳ ፍቅር አልወጣልኝ አለ .......የሰአዳን ነገር  ለኔ የዱንያ የሞት ሞት ሆነብኝ፡፡        ........በሰአዳ የተነሳ ማንንም ሴት ማመን መቅረብ እፈራለሁ ሁሉም ሴቶች እንደ ሰአዳ ከዳተኛ ናቸዉ እያልኩ ሴት ሳስብ ሰአዳ ትዝ ትለኛለች....ለሴት ያለኝ አመለካከት ወረደ........ጨካኝ ሁን ጨካኝ ሁን ይለኛል ግን እንዴት ልጨክን ሴት ማለት እህት ናት እኔም እህት አለኝ....ሴት ማለት እናት ናት የእኔ እናቴ ለኔ ብላ ከልጅነት ጀምራ የከፈለችዉ መስዋትነት አይኔ ላይ ድቅን ያላል፡፡ ሰአዳ ከዳችኝ ብየ የሌላ ሴት ሂወት ማበላሸት በእህቴ በእናቴ የማልፈቅደዉን የማልወደዉን ለሌሎች ሴቶች ማሸከም የለቅሷቸዉ ምክንያት መሆን አልፈልግም፡፡ ግን የሚገርመኝ ነገር አለ የሰዉ ልጅ ለሀላል እንደዚህ ይደክማል፡፡ ለፍቅርም ይሁን ገንዘብ ለማግኘትም ይሁን ..ለማግባት ለትዳር እንደዚህ መሰቃየት ግን ለዚና ለወንጀል ቀላል የሆነ ዘመን ሰአዳን በጊዜዉ ዚና እንስራ ብንል በጣም ቀላሌ ነበር ግን አላህ የከለከለኝን ለመከልከል ይሄ ሁሉ ግፍ አለፈብኝ ..በሀላል ለመክበር ብር ለማግኘት በጣም የከበደ ግን አምታቶ ሸዉዶ ለመክበር ቀላል የሆነበት ዘመን ያሳዝናል፡፡ ምን ይታወቃል ሰአዳ በዚህ አይነት ሌሎች ጋር የፈጠረችው ነገር ካለ በእኔ ማሳበቧ አልቀረም ከኔ አልፌ ላገባት ባሏ ሙሉነቷን(ቢክራነቿን) አግኝቶት ይሆን ብየ ማሰብ ሁሉ ጀመርኩ ..ወይንስ እኔው ጅሉ ከድር ላይ ከድር ነው የወሰደዉ ብላ አሳባብኝ ይሆን አላህ ከሪም ...ህይወት ይቀጥላልና    ከሀራም ከምወድቅ ብየ በቤተሰብ የመጣችልኝን ፀባይተኛ የሆነች ልጅ ተዋወኩኝ የምትኖረው ዱባይ ነው ...... ተስማምተን ቀለል ባለ ድግስ ሳይበዛ ኒካህ አደረግን ፡፡    አሁን የአገባሆት ሚስቴ አልሀምዱሊላህ ፀባዋ  ለኔ በጣም አሪፍ ነው ስሜቴን ትረዳኛለች ....ያለዉን ሒወቴን የተወሰነም ቢሆን ታቃለች.... እኔም የምፈልገዉ የዉስጤን የምትረዳኝ ነዉ...... አቤት አላህ ሲክስ ለኔ ህይወት መሳካት የሷ ውበት ረገፈ ለኔ የማትሆነው የላትም     አስቡት አሁን እድሚየ 28 ደርሻለሁ መረጋጋት መጨነቅ ማልቀስ ከጀመርኩ ሰአዳን ከአጣሁ ጀምሬ ስምንት አመታት አሳለፍኩኝ፡፡      አንዳንድ የሰፈር ሴቶች ያልበላቸዉን የሚያኩ ወሬ ወሬ የሚላቸዉ ይሄ ደግሞ አድቦ አግብቶ አይኖር ..አንዷ ጋር እረግቶ  ልጅ አይወልድምና ገና በማግቢያው አግብቶ ፈታ ቤተሰብ አሰዳቢ ይሉኛል ..     .....ግን የኔን ስቃይ ምክንያት የሚያቀዉ እኔ እና አንድ አላህ ነን...ለሰዉ ወሬ አልጨነቅም ..ግን የአሁን ሰዉ ወሬ ከሚያወራ ቀርቦ ቢረዳ ወይም የሰዉ እንደዚህ መሆን ለሱ አይጠቅመዉ አይጎዳዉ ለምን በሰዉ ሒወት ወሬ ያላምጣሉ??? የአሁን ሰዉ ስራ ከሚሰራ ወሬ ቢያላምጥ ይቀለዋል፡፡ እኔ ግን ለእንደዚህ አይነት ወሬ አልጨነቅም የኔ ጭንቀቴ ሰአዳን እንዴት አድርጌ ልርሳት??? አሁን ያገባኋት ሚስቴ ለኔ ልዩ ነች ጸባዩዋ ታማኝነቷ  አሳቢነቷ በምንም ቃላት ልግለፅላችሁ አልችልም ከገንዘቧ ጀምሮ በሁሉም ነገር ለኔ ያልሆነችው ነገር የላትም ..እኔም የደስታ ቀን እየመጣልኝ እንደሆን ይሰማኛል      ትምህርቴን ስጨርስ ለምን አላዝናናህም አለችኝ?   እንዴት አልኳት? ? የቪዚት ቪዛ ልላክልህና ዱባይ መጥተህ ዘና በል አለችኝ እሽ አልኳት ዲፕሎማ ስይዝ ዱባይ ከተዝናናሁ ድግሪ ብይዝማ አትጠይቁኝ ለሶስት ወር ዱባይ ሄድኩኝ ከሚስቴ ጋር ተገናኝን ፡፡ዛሬ ሌላ መዝናኛ ቦታ ነገ የአለም አንደኛዉ ህንፃ ቡርጅ ከሊፋ ሂጃለሁ፡፡ ኧረ ምኑን ላውራው እልፍ ቢሉት ሌላ ይገኛል ደጋ ሚስኪኑ ሞቱን ይመኛል እንደተባለው ያን ሁሉ ጭንቀት አስረሳችኝ ሁለት ወር ሙሉ ዘና ስል ቆየሁ    መቸም ደሃ ሆኖ ልዝናና ብቻ ማለት ራስን መሸወድ እንዳይሆን ለምን ስራ አልሞክርም ብየ ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ ስራ ለመግባት ደላላወቹ ከ አንድ ሺህ እስከ ሶስት ሺህ ድርሃም ይጠይቃሉ እንደምንም የሆነ የልብስ ካምፓኒ ስራ አግኝቸ  ቻርጃ የሚባለው ቦታ ስራ ገባሁ ስራው በጣም ይከብዳል ግን የጉብኝት ቪዛው እስከሚቀየር ነው አቅማችሁን ለማየት ነው አሉን እንደምንም ብቃቴን አስመሰከርኩና የቪዚት ቪዛውን ወደ ሰራተኛ ቪዛ( ኢቃማ) ተቀየረልኝ ዱባይስ ምን ትመስላለችበቀጣዩ እናየዋለን part 3⃣2⃣ ይ....ቀ.....ጥ.......ላ........ል
إظهار الكل...
👍 89
إظهار الكل...
👍 13👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አላቹ ደስ አለን ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች በሙሉ 🎊🎊🎊🎊🎊 #MAJOR በዶላር ጭማሪ ምክንያት በአለም ላይ ተቀባይነቱ እጀግ በጣም እየጨመረ ነው። #Major በቀጣይ ሳምንት ወደ token convert እንደሚደረግ አሳወቀዋል ፤ Focus አድርጋችሁ ስሩ ያልጀመራችሁ፦👇👇👇 https://t.me/major/start?startapp=1753715732 https://t.me/major/start?startapp=1753715732
إظهار الكل...
🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁   የታሪኩ ርዕስ 😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓       🌀 #Part 3⃣0⃣ ✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ ............የደሀ ልጅ ፍቅር............. ስልኩን ሳነሳዉ ሁሌም በልቤ ያለች አግብታ ትዝታዋ ያለቀቀኝ ሰአዳ ናት የደወለችዉ ....... የማላቀዉ ደስታ ከየት እንደመጣ አላቅም በጣም ደስ አለኝ ....ከድሬ እንዴት ነህ ጠፋህ እኮ አለችኝ........ አለሁ አንቺ ነሽ የጠፋሽዉ አልኳት..... .....እኔማ አለሁ ከሳዉዲ እንደመጣህ ትደዉልልኛለህ ብየ ጠብቄህ ነበር .. ???ብላ ወቀሰችኝ...... እሷ ብሎ ወቃሽ እኔ ስንት ሆኜ ተሳቅይቼ ያልወቀስኩትን እሷ እንደቀልድ ትወቅሰኛለች..በሆዴ እየገረመኝ...እንደዚህ አልኳት >>>>>>>>>>  ለምን  ማረሚያ ቤት ታስሬ ብዙ ሰዉ የማቀዉ የማላቀዉ እየመጣ ሲጠይቀኝ አንቺ እኮ አልመጣሽም ብየ ወቀስኳት ...    ብዙ ነገር አወራን... የሚገርም ነዉ እንደበፊቱ ከማግባቷ በፊት እንደምናወራዉ ዳግም ተግባብተን ያለፈዉን ረስተን  ማውራት ጀመርን ፡፡  ግን ሰአዳ ባለትዳር ነች፡፡ ግን የምናወራዉ ወሬ እሷ ትዳር ላይ ያለች አይመስልም..በጣም ወጣ ያለ ወሬ እናወራ ነበር...      የፍቅር ወሬ ሁሉ እናወራለን    በስልክ ማዉራታችንን ተያይዘንዋል  አንድ ቀን እንደዚህ አለችኝ.....ከድሬ እስኪ ዱአ አድርግ አላህ በመካከላችን የሆነ ነገር ፈጥሮ እንዲያገናኝን ከአላህ ተስፋ አንቁረጥ  ትለኛለች ......ሰአዳ ካገባችም ቡሀላ እንደ አዲስ በተስፋ በነፍስ ስጋየ ተጫወተችብኝ፡፡ ልብሱን ያልጣለ እብድ ሆንኩኝ ........... አንድ ቀን እንገናኝ እና እናዉራ  ብላ ደወለችልኝ ........እኔም ላስብበት አልኳት....  እሷን በአካል መገናኝት ፈልጊያለሁ ግን በአካል ብንገናኝ  ዝሙት ከመስራት እና   እስከዛሬ ያጣሁትን በበቀል ከመጨረስ ዉጭ ልላ የሚፈጠር ነገር እንደማይኖር እርግጠኛ ነኝ እሷ ባትስማማም እኔ ግን በሃይል እንደማደርገው ውስጤይ ይነግረኛል    ...ሰአዳን እንኳን ዚና ልንሰራ  አንድ ቀን ስሚያት አላዉቅም  ..በአይን ፍቅር ብቻ እሷን ላለማጣት ብየ ስንት በርሀ ተሰቃየሁኝ ምን ይደረጋል አላህ ያለዉ ሆነ፡፡          ጠዋት አስፓልት ዳር ቆሜ ከሩቁ እያለፈች ደወለችልኝ .......ስልኩን አነሳሁት እንዴት ነኝ አምሮብኛል???አለችኝ .......አዎ አምሮብሻል አልኳት ............ብታየኝ ያው ነኝ ምንም አልተቀየርኩ ዉበቴ እንዳለ ነዉ አለችኝ    ውስጤ ኧረ ተይእንጂ አልቀረብሽም ገና ድንግል ነኝ ባትይኝ ይላል ....ለአፌ ከአንገት በላይ ልክ ነሽ ውበት ጨምረሻል አልኳት       .... ድሮ ፊቷን የማብስላት ትውስታው እየታወሰኝ ....አሁንም ደግሜ በውስጤ ደግሞ ከዚህ በኋላ በኮስሞቲክስ ለሚጠበቅ ውበት እላለሁ ........ ከድሬ ስንገናኝ ብዙ የምነግርህ ነገር አለኝ አለችኝ .... እኔም እሽ ነገ እንገናኝ?? አልኳት .....እሺ  አለችኝ ..........የምንገናኝበትን  ቦታ እኔ ነግርሻለህ አልኳት ....... እሺ አለች ስልኩን ዘጋነው ፡፡   እንደነገ ልንገናኝ ዛሬ ማታ መልሳ ደወለች፡፡ እንደ ደወለች ስልኩን አላነሳሁትም...  የምሰራዉ ስራ በጣም ቆጨኝ...በዚህ የማይጨበጥ ፍቅር ውስጥ ከጌታየ መስመር እየለቀኩ እንደሆነ ተሰማኝ ..... እንዴት ባለትዳር ሴት ጋር አወራለሁ ??? ብንገናኝስ ካላገባኋት ሸይጧንስ ቢያሳስተኝ ???  አላህ ይቅር ይበለኝ አልኩኝ      ከዛም  ልፈትናት እና የልቧን ትርታ ለማዳመጥ ፈልጌ እኔ መልሼ ደወልኩላት  ...    ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ..... ሰአዳ ትዳር እንዴት ነው ተመችቶሻል ??? አልኳት ........ አሪፍ ነው ተመችቶኛል...አለችኝ ሳይኮ የምታወራውን መከታተል ይዣለሁ ......... በጣም ግራ ገባኝ ቀጠልኩና ሰአዲ ባልሽን ትወጅዋለሽ ???አልኳት ............. እሷም አዎ እወደዋለሁ  አለችኝ ሳቅ እያለች ..... እኔንስ ትወጅኛለሽ አትወጂኝም  ???አልኳት መቼም አንዴ ደፋር ሁኜ የለ .....ሰአዳም መልስ ሳመልስ የፈተና ምርጫ ላይ መልስ የለም የተባለ ይመስል ..  ዝም አለች ...መልሽልኝ እንጂ እያልኩ ብጠይቃት ..ዝም አይነቅዝም የተባለ ይመስል ብዙ ስታወራኝ የነበረችዉ ሰአዲ ዝም አለች፡፡    ____ ከዛም በመቀጠል እንደዚህ አልኳት ሰአዳ ግን ለምን ልጅ አትወልጅም ???  ...እሷም. ..ሞክረን ነበር ግን አልሆነም አንዴ ተበላሸብን ግን አሁንም እየሞከርኩ ነው አለችኝ    እና እኔን እየተጫወትሽብኝ ማለት ነዉ ?? አልኳት እንዴት አለችኝ  >>>ሰአዳ እስኪ አንድ ነገር ንገሪኝ.በጣም አሳፋሪ ነሽ እኔስ በአንቺ የተሰቃየሁት የሆንኩትን እኔ እና አላህ ነን የምናቀዉ.....ባል አለሽ ግን ???በባልሽ ላይ እኔን ታወሪያለሽ ?? ባልሽን ባፈሪ የሚያይሽን የፈጠረሽን አላህን አፈሪም ??? >>>>>>>እኔ ከድር ቆልፈሽና አሽገሽ  ያስቀመጥሽኝ እቃ አይደለሁም ስትፈልጊ ከፍተሽ የምትጠቀሚብኝ<<<<<<<<<<< .አልኳት  .....መልስ አልመለሰችም ፀጥ አለች ቀጠልኩ...  አንች ማለት ጥቅም አባራሪ ለራስሽ ምቾት ብቻ የምትኖሪ የጥቅም ሰው ነሽ ......እኔም ሞቅ ሞቅ ተናገር ተናገር የሚል የሚገፋፋ ነገር እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ከዛም ጨመርኩላት >>>>>ከአሁን ቡሀላ እኔን ከፈለግሽ ከባልሽ ጣጣሽን ጨርሰሽ ነይ፡፡  ካልሆነ ግን አትደውይልኝ በራሴ ላይ የደረሰው የሀሳብ የሞራል ውድቀት ሳያንሰኝ ሌላ አትጨምሪልኝ፡፡ አሁን ለራሱ ያለሁበትን ሁኔታ መሸከም አልቻልኩም፡፡     እራሴን ላገግም እያልኩ..ሒወቴን ገና አሀዱ ብየ እጀምራለሁ ስል ከአንቺ ሀሳብ ለመገላገል ሒወት እንደ ህፃን ልጅ ዳዴ እየሄድኩ ነገ ከነገ ወዲያ እነሳለሁ እያልኩ ...የራሴ ሒወት ልጀምር ስል ደዉለሽ የማይሆን ተስፋ እየሰጠሽ ዳግም ሁለተኛ ሒወቴን እያበላሸሽብኝ ነዉ ፡፡....    አንቺን ላለማጣት ብየ በስደት ስንት በርሀ አቋርጬ በሒወት እና በሞት መካከል ሁኜ ፈተና በዝቶብኝ..ዛሬ ወይ ነገ ኢዝሯኤል ሒወቴን እስከሚወስደዉ ተመኝቼ ከአሉት በታች ከሞቱ በላይ ሁኜ ያንን ሁሉ ፍቅር ያሸንፋል ብየ የተጎዳሁ አሁን ድረስ ጠባሳዉ ያለቀቀኝ የፍቅር ጅል ነኝ፡፡  ለፍቅር መስዋት ይከፈላል ለእንዳንች አይነቱ ግን ያሳፍራል ይሄን የነገርኩሽንም መልሰሽ ትረሽዋለሽ አንች ማለት እንዲህ ነሽ።     እኔ እኮ ነገን አስቤ ጥሩ ቀን ይመጣል ብየ በአንቺ ፍቅር የተጎዳሁ የፍቅር ማዕበል የወሰደኝ....ወስዶ ያልመለሰኝ ከድር ነኝ አንች ግን እንደሞኝ ነው የምታስቢኝ የወደደ ሰው መልሶ የሚጠላ አይመስላቹም ከንግዲ በኋላ  ግን  የህይወቴ መጥፎ ሰው አንች ነሽ ፡፡መቼም ቢሆንከአንቺ ሌላ መጥፎ ሰዉ አያገኘኝም ............ከአሁን ቡሀላ ብትደዉይ ..... ለባልተቤትሽ ስልኩን ፈልጌ ወይም አድራሻዉን አፈላልጌ ለባልሽ እነግርልሻለሁ.......አልኳት ከድር ለባሏ ይናገር ይሆን ?? በሚቀጥለዉ ክፍል እናያዋለን #Part 3⃣1⃣ ይ........ቀ........ .......ጥ.......ላ........ል 👇👇Start👇👇 https://t.me/major/start?startapp=1753715732 https://t.me/major/start?startapp=1753715732
إظهار الكل...
👍 76👏 4
🧕:እሱ ደግሞ የኮምቦልቻ ልጅ ነዉ ስሙም ጀማል ይባላል...  ሀርቡ ሹፌር ነዉ የታሰረዉ ሰዉ በመኪና ገጭቶ ነዉ .........በወሬ በወሬ ሀርቡ ቆንጆ ልጅ አለች ለትዳር ጠይቂያት እንደ አንተ ስሙ ከድር የሆነ  ልጅ እንደምትወድ ነግራኝ እምቢ አለችኝ  እኔም እስኪ ይሄን ታሪክ ንገረኝ ጀማል እኔን ሊሆን ይችላል አልኩት .....,አንተ ሳዉዲ ነበርክ እንዴ ??? አለኝ ...........አዎ ሳዉዲ ነበርኩ መጥቼ ነዉ አልኩት ... .......ሰአዳ የምትባል ልጅ ታውቃለህ ???አለኝ . .........አወን አልኩት አንተን ነበር ማለት ነዉ እወደዋለሁ እጠብቀዋለሁ ስትል የነበረችዉ??? አለኝ .......እኔም እንዴት ???አልኩት ........ሹፌር ነኝ ሀርቡ ስደርስ እነ ሰአዳ ካፌ አላቸው.... እሷም ካሸሪ ናት ሳንቲም ትቀበላለች፡፡  ቆንጅየ እናም ስነስርአት ያላት ልጅ ነበረች ፡፡ እናም ባገባት የትዳር አጋሬ ብትሆን ብየ ተመኘሁ ወደድኳት ... ቀርብ ብየ ሰአዳን ሳወራት የምትወደው ልጅ  ከድር እንደሚባል እና ከ የማገባዉ እሱን ነዉ እጠብቀዋለሁ ሳውዲ እንደሚኖር ነግራኛለች አለኝ     ....... ይህን ሲነግረኝ በጣም ገረመኝ  በወሬ ወሬ እሱም ሰአዳን ተመኝቶ እምቢ እንዳለችዉ ነገረኝ....ወይ መገጣጠም አጃኢብ ነዉ   ፡.ብቻ የማረሚያ ቤት ህይወት ቢያወሩት አያልቅም እናም ብዙ ሳንቆይ ወደ ደሴ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የላክነው ይግባኝ ተወስኖ መጣ ......... ውሳኔውም ይሄ ወንጀል አመት ማሳሰር ስለማይችል በ 600 ብር ቅጣት ይቀየር እነሱም ይፈቱ ይላል፡፡       በጣም ደስ አለን በአጠቃላይ እስር ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ 40 ቀን ቆይተን ከእስር ቤት እኔ እና ሙሀመድ ወጣን፡፡ ከስር ቤት ስወጣ ከታሳሪዎቹ ጋር በጣም ተግባብተን ስለነበር ለመለያየት እስኪያቅተን ተሰናበትኳቸዉ፡፡     የሀርቡ ህዝብ የተወሰነ በእኔ ያለው ግምት ተስተካከለ ፡፡        ከእስር ቤት እንደወጣሁ  ስልኬ ጠራ... አዲስ ስልክ ቁጥር ነበር ........ስልኬን አንስቼ ሀሎዉ ስል የሰማሁትን ድመፅ ማመን አቃተኝ... እዉነት እዉነት አልመሰለኝም ልቤ ቀጥ አለ... ሁሌም በልቤ ያለች አግብታ ትዝታዋ ያለቀቀኝ ሰአዳ ናት የደወለችዉ ....... የማላቀዉ ደስታ ከየት እንደመጣ አላቅም በጣም ደስ አለኝ ....ከድሬ እንዴት ነህ ጠፋህ እኮ አለችኝ የምናፍቃት የምወዳት ሰአዲ........ ሰአዳ ለምን ይሆን የደወለችዉ አዲስ ነገር በሰአዳ እና ከድሬ መካከል ይኖር ይሆን? ...ሰአዳ ለምን ደወለች?????? በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን Part3⃣0⃣ ይ..........ቀ............ .......ጥ............ላ................ል  ......... 👇👇Start👇👇 https://t.me/major/start?startapp=1753715732 https://t.me/major/start?startapp=1753715732
إظهار الكل...
👍 63 1👏 1
🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁   የታሪኩ ርዕስ 😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓       🌀 #Part 2⃣9⃣ ✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ በIslamic university channal ............የደሀ ልጅ ፍቅር.............   ሳናስበው  ማረሚያ ቤት ገባን፡፡ ሰዉ ባልሰራዉ ወንጀል በፍትህ ችግር እስር ቤት ተወረወርን..... እስር ቤት የፍርደኛ አንድ አልጋና ፍራሽ ቤተሰብ አመጣልን  .....   እኛ የታሰርነዉ በሀይማኖት ኬዝ ስለሆነ ወህኒ ቤት ያሉት ታሳሪዎች ያከብሩናል ይወዱናል፡፡ በሃይማኖት የታሰረ እንደአሸባሪ ነው የሚታየው         አሸባሪ እና ከ 4 ሰው በላይ የገደለ እና እንደ ኤድስ በሽተኛ ያለ ሰው የሚታሰረው በአንድ ክፍል ውስጥ ነው በጣም ያስፈራል...ወደ እዛ ማታሰሪያ ክፍል ዉስጥ አስገቡን .....     የምናድረዉ በአንድ ላይ ነዉ....ፍራሻችንን  አነጠፍን..... አዲስ የገባንበት ክፍል ያሉት ታሳሪዎች.....አብሽሩ እንኳን እናተ እኛም አላህ ባልፈቀደዉ  ወንጀል ሰርተን ገብተን ለምደነዋል፡፡ ......... ለሀይማኖትማ ብትሞቱስ ምነው??? ከናተ ጋር ሆነን በሀይማኖታችን ታስረን በነበር እያሉ ያፅናኑናል......... እናም እዚያ ክፍል ያለው ሁሉ ስለገባበት ስለታሰረበት ምክንያት ለአዲስ ገቢዎች ይነግራሉ....... ........ ከኔ ጎን ያለው ሰው እንዲህ አለኝ>>>>>>>> እኔ እዚህ ወህኒ ቤት የገባሁት ሁለት ሰው ገድየ ብዙዎቹን አቁስየ ነው አለኝ <<<<እኔም በሆዴ ሰዉ መግደል ብርቅ አይደለም... እኔም ባስጨናቂው ባህር እና ጭር ባለ በርሀ ስደት ሳዉዲ ለመግባት ስጓዝ ተርፌ የሞቱ ሬሳወች አፅሞች በብዛት  እያየሁ የተጓዝኩ ልጅ ነኝ እላለሁ ለብቻየ፡፡  አንዱ ደግሞ ቀጠል አደረገና ....እኔ ደግሞ የኤድስ በሽተኛ ነኝ እያለ ይስቃል ........ ብድግ አልኩኝ ከተኛሁበት እንደምንም ሌሎቹ አረጋጉኝ፡፡  ግን በሂደት ያ ሰው ጋር ተግባባን      ከተወሰኑ ቀናቶች በኋላ የይግባኝ ደብዳቤ  ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ደሴ ከተማ  ፅፈን ላክን፡፡ ...... ውሳኔውን ለመከታተል ከደሴ ከተማ እስከሚመጣ የተወሰኑ ቀናቶችን መጠበቅ ጀመርን፡፡መሃመድ አሚን በሃይለኛ ዱአ ያደርጋል ሌሊት ተኝቸ በመሀል ስባንን አይተኛም ዱአ ያደርጋል ይሰግዳል፡፡ አረፍ በል ተኛ ስለው ይሄ የሚታረፍበት ቦታ አይደለም አላህ በቶሎ ከዚህ ያውጣት እያለ ያለቅሳል ....... ማረሚያ ቤት ያስገርማል ራሱን የቻለ ሌላ ኢትዮጵያ  ነው የሚመስለው ስርዐቱ ከአንድ ለአንድ ጀምሮ እስከ አንድ ለአምስት ተደራጅቷል፡፡ ....... ጧት 12 ሰአት ከሆነ መተኛት አትችልም እዚያው ጊቢው ውስጥ ስራ ፍጠር ትባላለህ ሽመና የሚሰራ ቆሎ የሚሽጥ ሁሉ አለ፡፡  ታሳሪው ለምግብ ማብሰያ እንጨት መፍለጥ ግድ ነዉ... ይህን ማድረግ የማንችለው ብር እየከፈልን እናስፈልጣለን፡፡ ለአንድ እንጨት ዋጋው 2 ብር ነው እናም ከብዙ ሰወች ጋር እንተዋወቃለን     ከማረሳው የእስር ቤት ገጠመኝ  እዚያው ታራሚ ሁነዉ አትክልት የሚሸጡ አሉ ከሸዋሮቢት ቤተ ክርስቲያን የታሰሩ ሰው ናቸው ......አትክልት ቲማቲም ሽንኩርት ቃሪያ ይሸጣሉ ወጥ ስንሰራ መክተፊያም አብሮ አላቸው፡፡ እናም ለሙስሊም ሰው መስጠት አይፈልጉም በጣም ነው ዘና ነው የሚያደርጉኝ ......ለምን አትሰጡንም??? ስላቸው ........እናተ ስጋ አታጡም ይሉኛል፡፡ እንደምንም አባብየ ለምኜ ይሰጡኛል እከትፋለሁ     አንድ ቀን በምን ታስራችሁ ነው??? አልኳቸው  እነሱም የሃይማኖት ኬዝ ነው በናንተ በሙስሊሙ ብቻ አይደለም በእኛም በሀይማኖት ችግር አለ አሉኝ .......እንዴት ???አልኳቸው ........,መንግስት ትእዛዝ አምጥቶ ልክ እንደ ሀይማኖት አድርጋችሁ አስተምሩ ይለናል እናንተ ሙስሊሞች እምቢ ትላላችሁ ያስሯችሆል...... እኛ ደግሞ እሺ ብለን ስለምንቀበል አይነኩንም ......... ይሄው እኔም አልቀበልም ብየ አስረውኝ ነው አለኝ ፡፡ በጣም ይገርማል ፡፡     ሌላው ማረሚያ ቤት እያለሁ መቼም የማረሳቸዉ  በጣም የሚያስቁ ሽማግሌ ሰዉየ ነበሩ እድሜያቸው 80-90 የሚገመት ሽማግሌ ናቸዉ፡፡ በጣም ደስተኛና ጠንካራ ናቸው መሳቅ መጫወት ይወዳሉ ...... አንድ ቀን ፋዘር በምን ታስራችሁ ነው ???አልኳቸው .... ....አንድ ሚስት ነበረችኝ እርሷ ስትደክምብኝ ሌላ ሁለተኛ ድንግል ሴት አገባሁ፡፡ የመጀመሪያይቱ ሚስቴ ሁለተኛ አገባብኝ ብላ ከሰሰችኝ፡፡  ፍርድ ቤት ቁሜ ዳኛዋ ሴት ነበረች ለምን ሁለተኛ አገባህ ??? ብላ ዳኛዋ ጠየከችኝ..... ....እኔም ለዳኛዉ  እንዲህ አልኳት >>>>>>>እስኪ እሱ የምፅፊበት  እስክርቢቶ ካለቀ መፃፉን ካቆመ ምን ታደርጊዋለሽ ???አልኳት .......ዳኛዋም  እቀይረዋለሁ አለችኝ ........ እኔም እንደ አለቀዉ እስክርቢቶ የመጀመሪያዋ ሚስቴ ደከመች ሌላ አገባሁ አልኳት 😆😆አሉኝ የሚያስቁ ሰዉየ ......ከዚያስ??? አልኳቸዉ ...........ዳኛይቱ  በጣም ስቃ 6 አመት ፈረደችብኝ አሉኝ ፡፡ ይህንን ሲያወሩኝ ዘና ብለው ነው ጥርስ ጨርሰዋል አሳሳቃቸው ሳይቀር ያስቃል ፡፡     አንዴ ሌሊት ተኝተን  ይሄዉ ሰዉየ የደረጀ ደገፋዉን ሙዚቃን ያዜማሉ.....        የፍቅርሽን ተራራ ወጣሁት ተክዠ         በእጀ ምናምኑን በልቤ አንችን ይዠ፡፡ ይላሉ .....እኔም ተው አባት ሙዚቃ ሀራም ነው ስላቸው .. .......እሳቸዉም በሀገሬ ወጉ ምርቃን መሰል ስድብ ምናገባህ ዘረበዳ ውሀብያ ይሉኛል፡፡ ደግሞ አንዳንዴ ሲዘፍኑ        አየሁት አየሁት ሁሉንም አየሁት        አየሁት አየሁት ሁሉንም አየሁት        እንደ ሁለተኛ ሚስቴ የሚስማማኝ         የለም ያገኘሁት ሁሉንም አየሁት እያሉ ይዘፍኑና ብቻቸዉን ይስቃሉ ብቻ በጣም ነው ዘና የሚያደርጉኝ      ማታ ማታ ፊልም ለማየት ታሳሪው ሁሉ ሳንቲም ሲያዋጣ ቆመው ይሰበስባሉ....እኔም  ለምን አንቱ ትልቅ አይደለሁ እንዴ??? ፊልም ለምን ታያለሁ ???ስላቸው .....ለወህኒ ቤት ሀላፊዉ ይሄ አሸባሪ ነው ለፊልም አላዋጣም እያለ ነው ብለው ጮከው ይነግሩትና ከት ብለው በድዳቸው ይስቃሉ፡፡     እኔን የሚያስቀኝ አሳሳቃቸው ነው ፡፡ በባዶ ጥርሳቸዉ ሲስቁ እኔን ያስቁኛል..ይሄን ሽምግልና ይዘዉ ሁለተኛ ማግባታቸዉ በጣም ነዉ የሚገርመኝ፡፡   ብቻ የማረሚያ ቤት ታሪክ ቢወራ አያልቅም ..እኚህን ሽማግሌ ግን ከሁሉም አልረሳቸውም .........አብሶ ታማኝ እስረኛ አድርገዋቸው የማረሚያ ቤቱን እርሻና ከብቶች እንዲጠብቁ ሌላ ቦታ ወስደዋቸው የአገራቸው ሰው መሞቱን ሰምተው አገሬ ሄጀ ካልቀበርኩ ብለው ጋቢና ቀርቃሃቸውን ይዘው መናሃሪያ ሲደርሱ ፖሊሶች ይዘው የመለሷቸውን ነገር ሲያወሩ ያስቃሉ ለምን ሄድኩ ሲሏቸው ወዳጀንማ ሳልቀብር አልቀመጥም ያደረጉትን ያድርጉኝ ብየ ነው😆 ይሉና ይስቃሉ...      መቸም የማወራው ስለፍቅር መሆን ነበረበት ግን በእስርቤት  ያጋጠመኝ የህይወት ውጣ ውረድ ልንገራችሁ ብየ ነዉ..የሀርቡ ሰዉ ከድር አህባሽ ነዉ ሰላይ ነዉ ሲሉኝ የነበሩት ሁሉ እየመጡ ይጠይቁኛል...... አማንህ ወነጀልንህ ስምህን ያለስራህ አጠፋነዉ  አዉፍ በለን አሉኝ ......እኔም አብሽሩ አዉፍ ብያለሁ እላቸዋለሁ እየመጡ አጫዉተዉኝ ይሄዳሉ.....የሚዘይረኝ ሰዉ የሚጠይቀኝ በጣም ብዙ ነበር.....እኔ በባህሪያ ከማንም ጋር እግባባለሁ ፡፡    ደግሞ ከሌላ ልጅ ጋር ተዋወኩኝ የሀርቡ ልጅ መሆኔን አብሬ ስሜን ነገርኩት👇
إظهار الكل...
👍 24 3🤩 1
Major Star ሊስት የሚደረግበት ቀን ቀርቧል 🥶 በቅርቡ ከተጀመሩ ኤርድሮፖች መካከል አንዱ የሆነው ሜጀር በቅርብ ሳምንታት ሊስት እንደሚደረግ በስፋት እየተገለፀ ይገኛል 🔥🔥🔥 ላልጀነራቹ ለመጀመር 👇👇 https://t.me/major/start?startapp=1753715732 https://t.me/major/start?startapp=1753715732
إظهار الكل...
👍 2
🎊እንኳን ደስ ያላቹህ ደስ አለን 🎊 #Not Coin ያመለጣችሁ ሰዎች ይኸው  አዲስ ነገር ለእናንተ መጥቷል.. በብዙ እየተጠበቀ ያለ ነው አሁን ላይ ቴሌግራምም Verify አድርጎታል የቴሌግራም መስራች የሆነው #ዱሮቮስም እየተጫወተው ነው #Start ብላቹ አስጀምሩት። ሊንክ👇👇💸 https://t.me/major/start?startapp=1753715732 https://t.me/major/start?startapp=1753715732
إظهار الكل...
👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.