cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ https://t.me/lafto_qirat

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 610
المشتركون
+324 ساعات
+57 أيام
+6330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ማስታወሻ❗️ ባማረ አቀራረብ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ እየተሰጠ የሚገኘው የተፍሲር ደርስ #ነገም በአላህ ፍቃድ የሚቀጥል ይሆናል❗️ 🔖 🔖"ለዓይን ብርሃን እንደ ሚያስፈልገው ሁሉ ለልብም ቁርኣንና የቁርኣን እውቀት ያስፈልገዋል"።
إظهار الكل...
👍 2 2👌 1
የሽንት ቤት አጠቃቀም ስነ ስርኣት ~ ① እንዳይሰረቁ ወይም እንዳይጠፋ ካልሰጉ በስተቀር የአላህ ስም ያለበት ነገር ይዞ ሽንት ቤት ውስጥ አለመግባት። ② የሚፀዳዱት ሜዳ ላይ ከሆነ ከሰው እይታ ራቅ/ ሰወር ማለት። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጃህ: 1/ 60] ③ በሰው መተላለፊያ መንገድ ላይ ወይ አጠገብ፣ ሰዎች ከሚጠለሉበት ዛፍ ስር፣ ፍሬው ከሚበላ ዛፍ ስር፣ የፍራፍሬ ዛፍና አትክልቶች አጠገብ፣ ወራጅ ባልሆነ ውሃ ላይ፣ የውሃ ምንጭ ላይ፣ መቃብር ውስጥ አለመፀዳዳት። [ኢርዋኡል ገሊል: 1/100] [ሙስሊም: 269፣ 281] [ኢርዋእ: 1/102] ④ ንፋስ ወደሚነፍስበት አቅጣጫ ዙሮ አለመፀዳዳት። ⑤ የተሰነጠቀ መሬት ላይ ወይም ቀዳዳዎች ላይ አለመፀዳዳት። [አቡ ዳውድ: 29] ⑥ ውጭ ላይ የሚፀዳዱ ከሆነ ወደ መሬት ዝቅ እስከሚሉ ልብስን አለመሰብሰብ ወይም አለማውረድ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4652] ⑦ ውጭ ላይ በሚፀዳዱ ጊዜ ወደ ቂብላ አለመዞር፣ ጀርባንም ለቂብላ አለመስጠት። ሽንት ቤት ውስጥ ከሆነ ወይም ከፊት የሚጋርድ (ግድግዳና መሰል) ነገር ከኖረ ችግር የለውም። ይህንንም ቢሆን ከተቻለ መጠንቀቅ። [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም] [ኢርዋእ: ቁ· 61] ⑧ ሽንት ቤት ሲገቡ ግራ እግርን ማስቀደም። ⑨ ሽንት ቤት ሲገቡ "ቢስሚላህ። አላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹቡሢ ወልኸባኢሥ" ብሎ ከሸይጧን መጠበቂያ ዱዓ ማድረግ። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 3611] [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም] (10) በሚፀዳዱ ጊዜ ብልትን በቀኝ እጅ አለመንካት፣ በቀኝ እጅ አለመፀዳዳት። [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም] (11) በሚፀዳዱበት ጊዜ ያለ ምክንያት ከማውራት መቆጠብ። (12) ቢያንስ በሶስት ድንጋይ፣ ሶፍት፣ ወረቀትና መሰል ነገር መፀዳዳት። አንድም ቢሆን ሶስት የተለያዩ ጎኖች ወይም ገፆች ከኖሩትም በቂ ሊሆን ይችላል። ወይም በውሃ መጠቀም። አጥንት፣ ፋንዲያ፣ ምግብ ነክ ነገር እና ንፁህ ያልሆነ ነገር ለመፀዳጃነት አይውልም። [ሙስሊም፡ 262፣ 263፣ 271] (12) ከሽንት ቤት ሲወጡ ቀኝ እግርን አስቀድሞ መውጣት። (13) ከሽንት ቤት ሲወጡ "ጉፍራነክ" ማለት። [ሶሒሑል ጃሚዕ: 4707] = (ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 23/2010)
إظهار الكل...
👍 5👏 2
ብዙዎችን ለመቀየር ብዙዎች መሆን የለብህም፥ በዋጋ ከሁሉም የምታንሰው ትንሿ ጨው በዋጋ በሚበልጧት መኃል ገብታ ለሁሉም ለውጥ እና ጣዕምን እንደምትሰጥ ሁሉ በገባንበት ሁሉ የለውጥ እና የጣዕም ምክንያት ኢንሻሏህ እንሆናለህ፡፡ ከአንድ እስራ ሐሞት ይልቅ ጠብታ ማር ብዙ ንቦችን ትስባለች፥ ከጉልበት ብልሃት ከድፍረት ዕውቀት ይበልጣል። ✍ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
إظهار الكل...
👌 3
“አላህ ከአንተ ጋር ከሆነ የማንም ከአንተ ጋር አለመሆን አይጎዳህም አላህ ከአንተ ጋር ካልሆነ የሁሉም ከአንተ ጋር መሆን አይጠቅምህም” —————— ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ አደም
إظهار الكل...
9👍 3
💥 ልጆቻቸውን መድረሳ ለሚልኩ ወላጆች ልብ ውስጥ የሚገባ ምርጥ ምክር❗️ 🎙 በሸይኽ አሕመድ ሸይኽ አደም 📝 መስከረም 5 በነበረው የምርቃት ፕሮግራም ላይ የቀረበ 🕌 በላፍቶ ቢላል መስጂድ 🔗@lafto_qirat
إظهار الكل...
ምክር ለወላጆች.mp311.53 MB
👍 6
💥 ትንሽ ስለመውሊድ... 🎙 ኡስታዝ ሙሀመድ ሐሰን ማሜ 🏷 ከተፍሲር ደርስ ላይ ተቆርጦ የወጣ 📎 @lafto_qirat
إظهار الكل...
መውሊድ.mp311.00 MB
2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩነቱ ግልፅ ነው!!
إظهار الكل...
👍 10
"ሀቅ የጠፋች የሙዕሚን እቃ ናት ያገኛት ቦታ ይይዛታል!"
إظهار الكل...
👍 10
ድቤ መደብደብ የለውም አደብ ~ ዱዓእ፣ ዚክር እና ሶለዋት ዒባዳዎች ናቸው። ስለዚህ ዋጋ እንዲኖራቸው፣ አላህ እንዲቀበለን በአደብ መፈፀም ይኖርብናል። ከነዚህ አደቦች ውስጥ 1ኛው ኢኽላስ ነው። ለይዩልኝና ይስሙልኝ፣ ለጉራ፣ ለእልህ፣ ለመዝናናት፣ ... ሳይሆን አላህን ብቻ በማሰብ መፈፀም። 2ኛው አደብ ከነብያችን ﷺ በተገኘው መልኩ መፈፀም ነው። ድምፅን ዝቅ ማድረግ ለኢኽላስ የቀረብ ነው። በመተናነስ መፈፀምም ሌላ ወሳኝ ነጥብ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:- { وَٱذۡكُر رَّبَّكَ فِی نَفۡسِكَ تَضَرُّعࣰا وَخِیفَةࣰ وَدُونَ ٱلۡجَهۡرِ مِنَ ٱلۡقَوۡلِ بِٱلۡغُدُوِّ وَٱلۡـَٔاصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡغَـٰفِلِینَ } ''ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በሆነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው። ከዘንጊዎቹም አትኹን።" [አልአዕራፍ፡ 205] በዱዓእ፣ በዚክር እና በሶላት ዐለ'ነቢ መጨፈር ከአደብ የወጣ ተግባር ነው። ስሜት ውስጥ ገብተው ከፍ ያለና ትርጉም የለሽ ወጣ ያለ ድምፅ የሚያሰሙም አሉ። ይህም ወሰን መተላለፍ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:- { ٱدۡعُوا۟ رَبَّكُمۡ تَضَرُّعࣰا وَخُفۡیَةًۚ إِنَّهُۥ لَا یُحِبُّ ٱلۡمُعۡتَدِینَ } "ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት። እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።" [አልአዕራፍ፡ 55] በዚክርና በሶላት ዐለ'ነቢ ወቅት ማጨብጨብ፣ ፉጨት፣ ማናፋት፣ ማቃሰት፣... የሙሽሪኮች እንጂ የሙስሊሞች አደብ አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል:- { وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَیۡتِ إِلَّا مُكَاۤءࣰ وَتَصۡدِیَةࣰۚ فَذُوقُوا۟ ٱلۡعَذَابَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ } {በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አልአንፋል፡ 35] ስለዚህ እነዚህ ዒባዳዎች ልብንን ሰብሰብ አድርጎ፣ መልእክቱን እያስተዋሉ በኹሹዕ መፈፀም ይገባል። = ©ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.