cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት

ይህ ቻናል የምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባዔ ቤት በቤተ ከርስቲያን ዙሪያ መወያያ ገጽ ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
5 289
المشتركون
+124 ساعات
+597 أيام
+2430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

    "ትምህርት የማያልቅ ምርት ነው" ልጅን አለማስተማር ትልቅ የሕይወት ዕዳ ነው። በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ሕፃናት ትምህርት ካቆሙ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው።ይሄ ደግሞ ያልተማረ  ኋላ ጀርባ ሳያል የሚገዣ ዜጋ እንዲኖር  ብሎ ሥርዓቱ የፈጠረው አእምሮን የማቀንጨር ሥርዓታዊ ፕሮጀክት ነው። ስለሆነም የትምህርት በሮች ከተዘጉብን የማይዘጉ የአብነት በሮችን መክፈት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው። የማያነቡ የማይጽፉ ዜጎች እንዳይኖሩ የኔታዎቻችን እንደ ጥንቱ እንደ ጧቱ መፍትሄ ሊሆኑን ይገባል። ልጅን ወደ የኔታዎች ሰዶ አለማስተማር ደግሞ ወንጀል ሁኖ በማኅበረ ሰቡ ዘንድ መቀስቀስ አለበት። በእጃቸው ያለውን ትምህርት ቤት ከዘጉብን በእጃችን ያለውን ነባር አማራጭ እንጠቀም። የትውልድ ጉዳይ ያገባኛል የምትሉ ሁሉ ልጆቻችሁን የጎረቤት ልጆችን መላው ለትምህርት የደረሱ ልጆችን ሴት ወንድ ሳትሉ ወደ አብነት እንዲገቡ አነሣሡ። የነገ ሀገር፣የነገ  ሃይማኖት በተሠሩ አእምሮዎች ውስጥ ትገኛለች። የዘራነውን የምናጭደው የጨድነውን የምናመርተው ዘሬ ነው። ያልዘራነው ማጨድ ያላጨድነውን መሰብሰብ ግን ጉም አፋሽነት ዖፍ ነዳሽነት ነው። ሁሉም አልፎ ዛሬ ታሪክ መሆኑ ላይቀር ነገር መርሳት የለብንም።ነገ ደግሞ አሁን ያሉን ሕፃናት እና የሚተኩት ትውልዶች ናቸው። የሰው ያለሽ ከማለት በአብነት ትምህርት ቤቶቻችን በኩል  የተማረ ሰው እንሥራ። በምድር ላይ የነገ ተረካቢዎችን ከማፍራት የተሻለ ምንም ትሩፋት የለም።          ነገ ይታያችኋል ወይ??? ያለ ትምህርት ነገ ምንድን ነው? ነገ የማን ነው? በደንብ እናስብ በደንብ በቅንነት እንነት እንሥራ። ትናንት የዛሬ ውጤት ነው።ዛሬ ደግሞ የነገ ምርት ነው።ስለ ነገ መጨነቅ ቅዱስ ሀልዮ ነው። ሁሉም ሕጻናት ወደ አብነት ይሂዱና ነገን እንሣልባቸው።አለማስተማር ግን የአስተሳስብ ዕዳ መሆን አለበት። በሁሉም አካባቢዎች አብነት መማር ዕሴት ባህል  እስኪሆን  እንሥራ።የሰላም ዘመን  እስኪመጣ እጃችን ላይ ባለን እንትጋ።
إظهار الكل...
👍 18 14
....“በአባ ቢሾይ ገዳም ከአባቶች መነኰሳት ጋር ተገናኘሁ። በዚያም የቦታውን መንፈሳዊነትም ሆነ የእንግዳ ተቀባይነታቸውን ነገር፣ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተግባራቸውንና ትምህርታቸውን ተመለከትሁ፤ ሆኖም ግን ካየሁት ሁሉ አንዱንም እንኳ እንደሚገባ አድርጌ አሟልቼ ልገልጸው አልችልም። ሆኖም የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት በታሪካችን ውስጥ የነበረውን ሚና መዘንጋት ለእያንዳንዱ ዐረብ ታላቅ ኪሳራ የመሆኑ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ለራሴ ተረድቻለሁ። በእ*ስልምና ሃይማኖት ውስጥ ምንኲስናና ገዳማዊ ሕይወት የሚባል ነገር አለመኖሩን ማሰብ ውስጥን የሚረብሽና የሚያሳዝን ነገር ነው።” መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው።      ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም። ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!
إظهار الكل...
40👍 9🥰 4🔥 2
በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አንድ ጨዋነት የራቀው ሰው ሰደባቸው አሉ። በኋላ ግን ጸጽቶት እግራቸው ላይ ወድቆ “ይማሩኝ፣ አጥፍቻለሁ፣ አድጦኝ ነው” ሲላቸው፣ እርሳቸውም “ታዲያ ወደ ታች ያድጣል እንጂ ወደ ላይ ያድጣል እንዴ?” አሉት ይባላል።  ወደ ላይ የሚያድጣቸውን ብዙ ሰዎች እያየን ነው። ሰሞኑን ዘነበ ወላ የተባለ ግለሰብ፣ ሊነቅፈው ቀርቶ ሊረዳውና ሊያደንቀው እንኳ እጅግ የሚበዛበትን የምናኔ ሕይወት ለመንቀፍ ሲሞክር ሰምተናል (የተነገረው በሕንድኛ ወይም በታይ ቋንቋ አይደለም!)። ይህን የመሰሉ እናውቃለን ከሚሉ አላዋቂዎች ወይም ጭፍን ጥላቻ ካሳወራቸው ሰዎች በኦርቶዶክሳዊነት ላይ በተለያየ መንገድ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየበዙ መምጣታቸው ጉዳዩን እንደ ቀላል ለማለፍ የማይቻል ያደርገዋል። ዛሬ ካለው የተከማቸ ኦርቶዶክስ-ጠልነት ያደረሱን ከ20ኛው መ/ዓ መጀመሪያ ጀምሮ ኦርቶዶክስ ጠል በነበሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ይሰነዘሩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮችና ጽሑፎች መሆናቸውን ልብ ይሏል። ምናኔያዊ ሕይወት፣ ከትንሣኤ በኋላ የምናገኘውን እንደ መላእክት የመሆንን ሕይወት፣ በዚህ ዐለም ገንዘብ የማድረግ ሕይወት ነው። “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” እንዳለ ጌታችን። ማቴ. 22፡30 መላእክት በተፈጥሯቸው እንደማያገቡና እንደማይጋቡ ሁሉ፣ ከትንሣኤ በኋላ ደግሞ ለሰዎችም ማግባትና መጋባት እንደማይኖር ሁሉ፣ መላእክት ዛሬ የሚኖሩትን፣ የሰው ልጆች ደግሞ ከሞት በኋላ የሚያገኙትን ሕይወት መናንያን ገዳማውያን በአሁኑ ሕይወት ይኖሩታል። እንደዚሁም ምናኔያዊ ሕይወት አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ሕይወት ምን ይመስል እንደ ነበረ በመስታወት የሚያሳይ ነው፣ ጌታችን የሰጠውን ሕይወት በምልዓት የሚያሳይ ነው። ምናኔያዊ ሕይወት በክርስትና ውስጥ ያለውን እጅግ የገዘፈና ዘርፈ-ብዙ የሆነ ነገረ-ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ለጊዜው ብናቆየው እንኳ፣ ክርስቲያናዊ ገዳማት ለሰው ልጆች ያበረከቷቸው ኢኮኖሚያዊ፣ እውቀታዊና ታሪካዊ ጠቀሜታዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ጥቂቶቹን እንኳ ብናስታውስ፤ ዩኒቨርሲቲዎችና አዳሪ ት/ቤቶች በዋናነት የተቀዱት ከገዳማት ነው። የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሲመረቁ የሚለብሱት ጋዋንና የሚደፉት ቆብ የገዳማትን ቀሚስና ሞጣህት እንዲሁም ቆብ የሚመስለው በአጋጣሚ አይደለም። በአውሮፓ የውኃ ኃይልን ለወፍጮና ለቆዳ ሥራ መጠቀምንና ማዕድናትን ማውጣትንና መጠቀምን በስፋት ያስተዋወቁት ገዳማውያን ናቸው። የአውሮፓን የእርሻ መሬት፣ ሥነ ጥበብና እውቀት ከጥፋት በመጠበቅና በማበልጸግ ረገድ ገዳማት የተጫወቱት ሚና ምትክ አልባ ነው። አንዳንድ ገዳማት በየዓመቱ የአበምኔቶች መደበኛ ስብሰባ ስለነበራቸው፣ የደረሱባቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ እውቀቶችና ልምዶች ይለዋወጡ ስለነበር በዚህ መንገድ ሥልጣኔ በመላው አውሮፓ እንዲስፋፋ የራሳቸውን ታላቅ ሚና ተጫውተዋል። ከክርስትና በፊት የጉልበት ሥራ መልካም ክብርና ስም አልነበረውም። በግሪኮች ትምህርት መሠረት የጉልበት ሥራ የዝቅተኞቹ ኅብረተሰብ ክፍል (የድሀውና የባሪያዎች) ሥራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። በሮማውያን ዘንድም ለሥራ የነበረው መንፈስ ተመሳሳይ ነበር። ለጉልበት ሥራ በተለይም ለግብርና ከፍ ያለ ቦታና ከበሬታ የሰጡት ገዳማት ናቸው። ከዚህም ጋር ገዳማት ለድሆች፣ ለስደተኞች፣ ለወላጅ አልባ ልጆች፣ ለሕሙማንና ለችግረኞች መጠጊያዎች በመሆን አገለግልዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ4ኛው መ/ዓ የነበረው ቅዱስ ባስልዮስ የመሠረታቸው ገዳማት ሐኪም ቤቶች፣ የድሆች መመገቢያዎችና የችግረኞች መርጃ ማዕከሎችም ነበሩ። የዘመናዊ ሆስፒታል ጽንሰ-ሐሳብ መሠረቱ ክርስቲያናዊ ገዳማት ናቸው። እንደዚሁም ገዳማት የሥነ ጽሑፍና የትምህርት ማዕከላት ነበሩ። ታላላቅ ቤተ መጻሕፍት የነበራቸው ብዙ ገዳማት ነበሩ። ብዙ መጻሕፍት ከእኛ እንዲደርሱ ያደረጉት መጻሕፍትን የሚሰበስቡና ባለሙያዎችን መድበው በእጅ የሚያስገለብጡ ገዳማት ናቸው። ብዙዎቹ መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ከጥፋት ተርፈው ከዛሬ የደረሱት በገዳማት ተደብቀውና ተጠብቀው ስለኖሩ ነው። ግሪኮች በኦቶማን ቱርክ በተገዙባቸው ወደ 300 የሚደርሱ ዘመናት ውስጥ እምነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና ሥነ ጽሑፋቸውን ሕያው አድርገው የጠበቁት በገዳማት ዋና ማዕከልነት ነበር። ገዳማቱ ለካህናት ብቻ ሳይሆን በቱርኮች ግዛት ሥር ለነበሩ መላው ግሪካውያን ስውር ት/ቤቶች ነበሩ። በአገራችንና በሌሎች አገራትም ብዙ ተመሳሳይ ታሪኮች አሉ። ነጻነትን ለሚወዱና ባርነትን ለሚጸየፉ ሰዎች ሁሉ እነዚህ ትርጉማቸው ጥልቅ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ገዳማትን ትቁር ጥምድ የሚያደርጓቸውም ለዚህ ነው። መናንያን አባቶችና እናቶች ለሰው ልጅ ሁሉ ምሕረትን ከእግዚአብሔር የሚለምኑ ናቸው። በአስቄጥስ ገዳም ስለ ነበረ አባ ኢሳይያስ ስለ ተባለ አባት በመጽሐፈ ገነት እንዲህ ተብሎ እናገኛለን፡- “በዋዕየ ፀሐይ ላይ ራቁቱን ቁሞ ስለ መላው ዐለም ሲጸልይ ሳለ ከመነኰሳት አንዱ እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማ፡- ‘ከእርሱ ጸሎት የተነሣ ለዐለሙ ሁሉ ምሕረት አድርጌያለሁና ሂድና ለአባ ኢሳይያስ ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብስ ስጠው።’” ገዳማውያን መናንያን ሌላውን የሚዘርፉና የሚያጠፉ ሳይሆኑ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምኑ ናቸው፣ ሰውን የሚያሳድዱ ሳይሆኑ የተሰደዱትን የሚቀበሉ ናቸው። እንኳንስ የሰው ልጅ እንስሳትና አራዊት እንኳ አዳኞች ሲያሳድዷቸው ሸሽተው የሚጠጉባቸው ናቸው። የፍርሃትና የአጎብዳጅነት መንፈስ ያይደለ የእውነትና የጥብዓት መንፈስ ያለው ሁሉ ይህን ይረዳል።    ምንም እንኳ ምናኔያዊ ሕይወት ዓላማው በዚህ ዐለም ሀብት መበልጸግ ባይሆንም፣ በኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ረገድም ቢሆን ገዳማት በየዘመናቱ የነበራቸው ሚና ቀላል አልነበረም። ለአብነት ያህል በዘመናችን የግብፅን የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶች በከፍተኛ ድርሻ የሚሸፍኑት ኦርቶዶክሳውያን ገዳማት ናቸው። የአስቄጥስ ገዳም ለግብፅ የአየርና የዐፈር ጠባይ ተስማሚ የእህልና የአትክልት ዝርያዎችን በማምረት የአገሪቱን የምግብ አቅርቦት ችግር በመፍታት ረገድ የተጫወተው ሚና ታላቅ ነው። በተለይም ደግሞ የአስቄጥስ ገዳም መነኰሳት በሳይንሳዊ ምርምር በግብፅ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ያመረቱት “ፎደር ቢት” (fodder beet) የተሰኘ የስኳር ድንች ዓይነት አዲስ ምርት በእጅጉ ተመስግነውበታል። የአሰቄጥስ ገዳም መነኰሳት በዚህ ረገድ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ሙስሊሙ መሪ አንዋር ሳዳት ከታላቅ ምስጋና ጋር ብዙ ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ሌሎቹ የግብፅ ገዳማትም ለበረሃው ተስማሚ የሆኑ የዕፅዋትና አዝዕርት ዓይነቶችን በሳይንሳዊ ምርምር በመፈለግ ረገድ ከፍተኛ ሥራ እየሠሩ ናቸው። ወደ ግብጽ አባ ቢሾይ ገዳም ተጉዞ የነበረ አህመድ ኤል-ጋማል የተባለ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ጋዜጠኛ November 21, 1988 ላይ በወጣ “Khaleeg” በተባለ ጋዜጣ ላይ “A visit to the Depth of the Desert” በሚል ርዕስ እንዲህ ጽፎ ነበር፡-
إظهار الكل...
👍 7 7
🌿🌿🌿🌿🌿ዕቅድህ ምንድነው? #በዬኔታ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ባለፈው ዓመት መጨረሻ ለዚህ ዓመት ልትሠራው ያቀድኸውን ስንቱን ሠራህ ያቀድኸውን ለመፈጸም ትቸገራለህ? ያቀድኸውን ትተህ ያላቀድከውን አድርገህ ታውቃለህ? ዕቅድ ወደ ራዕይህ ፍጻሜ ለመድረስ የምትሳፈርበት መርከብ ነው። በሚገባ ካልሄደልህ የራእይህን ፍጻሜውን አታየውም ማለት ነው። የሚመጣውም ዓመት ያቀድኸው እንዲሳካ ራዕይህን መርምረው። የት መድረስ ነው ምትፈልገውን ምን ሲኖርህ ነው ዕቅዴ ተሳካ የምትለው? 🌿🌿🌿🌿 እያንዳንዱ ዓመታት ቢያሻህ መልአክ ካልፈለግህም ሰይጣን መሆን የምትችልባቸውን ዕድሎች የያዙ ናቸው። ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ዲያብሎስ የተሻረበት ቀኑ አንድ ነው። ይሁዳ ገሀነም የወረደበት ማትያስ በይሁዳ ፋንታ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ከተቀበሉ ሐዋርያት እያንዳንዱ የሆነበት ቀንም አንድ ነው። አየኽ ወንድሜ በዚህ ዓመት ስንቶቹ በገነት ካሉ ነፍሳት ጋር ተቀላቀሉ ስንቶቹ ደሞ ከገነት ተባረሩ ብለን ብንመረምር ያልጠበቅነውን ውጤት እናገኛለን :: 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ሰው ማንኛውንም ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ዕቅድ ሲያቅድ ከተፈጠረለት ዓላማ አንጻር ማቀድ ይገባዋል ። እግዚአብሔር አንተን ሲፈጥርህ ዓላማው መንግሥቱን ወርስህ ቅድስናውን ተካፍለህ ለዘለዓለም ሕያው ሁነህ እንድትኖር ነው። ያንተም ዕቅድ ከዚህ የራቀ ሊሆን አይገባውም ። ስታቅድ አስቀድመህ እግዚአብሔር ላንተ ያለውን ዕቅድ ማወቅ ይገባሃል። ክርስቲያን ሁነህ እንደ አሕዛብ እንዳታቅድ ተጠንቀቅ። ቤተክርስቲያን ሰውን ለዘለዓለም ሕይወት ለማብቃት ያቀደችውን ዕቅድ ሳታውቅ ታቅድና አንተና ቤተ ክርስቲያን አብራችሁ ሳትሠሩ ዓመቱ ያልፍባችኋል። ተቋማትና ሠራተኞቻቸው በሥራ ሚገናኙት ዕቅዳቸው ከተገናኘ አይደል? አንተና ቤተክርስቲያንም በሥራ ምትገናኙት ዕቅድህ ከቤተከርስቲያን ጋር አንድ ከሆነ ነው። ሕይወት እንዲህ ናት እና ሌሎችም 📝ሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
إظهار الكل...
👍 31 22
ዘመን አንተ ነህ (ዘመንሰ ለሊከ ) ዛሬ የእድሜያችን አንዱ ቀን ነው ፡፡ ዓመቱ ደግሞ ከእድሜያችን አንዱ ዓመት ነው፡፡ ማንም የሚጓዘው ወደ  እድሜ መዳረሻው ነው፡፡ ያለ ዓመት በዘለዓለማዊነት ለመኖር በአሁን መሥራት ግድ ነው፡፡ አሁን ራሱ እየኖርበት ያለው ሰዓት ነው፡፡ትናንት ታሪክ፣ አሁን ኑሮ፣ ነገ ተስፋ ናቸው፡፡ የአሁን  የመኖር ሁኔታ ለነገው ዋዜማ ነው ዋዜማውም አይነታ ይሆናል  የዘመን አይነታውም ዋዜማ ይሆናል ይህም ያልፋል ያማልፈው ዘመነ እግዚአብሔር ነው፡፡ አሁን የሚለወጠው ሰው ሲለወጥ ነው ያለዚያ ግን የዘመን ቁጥር ነው፡፡    የኛ ቤተ ክርስቲያን በአምስት ነገሮች ትገለጣለች።፦ ልጆቿንም ትመራለች፦               በሐዋርያዊ ትውፊት               በኦርቶዶክሳዊ አረዳድ               በኅብረታዊ ትርጉም               በመዳን ትምህርት መለኪያ               በተስፋ ነጽሮት መጻሕፍትን እና የመጻሕፍት የሆነውን ሁሉ እንዲህ በነዚህ ትረዳዋለች። የሌላ የሆነውን ደግሞ በዚህ አንጥራ ትለያለች ስትሻም ታወግዛለች። በዚህ መርምራም ትቀበላለች፡፡ ከዚህ የተነሣ ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ሰዉ ሁሉ  የእምነቱ መለኪያ  ማጥሪያ ወንፊት ሊኖረው ይገባል።   ያለፈው እና የሚመጣው ዘመን ትይዪ ናቸው፡፡    ቤተ ክርስቲያናችን የሚመጣው ዘመን ቅዱስ ነው ያለፈው ዘመን  ግን ርኩሥ ነው  ብላ አታስተምርም። ምክንያቱም የተኖረበትን ዘመን እንጂ  ያልተኖረበትን  ዘመን  በሰንሰለታዊ ቅብብሎሽ  በሕይወት ፈተና ተፈትና ገና ስላልተቀበለችው ነው።አዝማነ መንግሥተሰማያትን ግን በተስፋ ቅድስና ደጅ ትጸናለች፡፡ ስለሆነም ሁሌም የቀደመው ታሪክ ክፉውም ሆነ በጎው መምህራችን ነው።    ትናንት እና አሁን  ለኛ ምክርም ተግሣጽም ነው ዕውቀት እና መረዳት መረዳት እና እምነት እምነት እና ሥራ ሥራ እና ተስፋ፦  ዘመንን ያለፈ ዘመነኛ ያደርጋል፡፡  " ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።" 1ኛ ጴጥ 5፥13 ከትናንት የማይማር ትናንት ብቻ ነው፡፡ ትናንት መሠረት፣ ዛሬ ግድግዳ፣ ነገ ጣሪያ ነው፡፡ @ ምሥራቀ ፀሐይ አራቱ ጉባኤያት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት
إظهار الكل...
👍 24 12🥰 4😁 1
13
#ዐዲሱን ሰው ልበሱ:: ኤፌ፡4:24፡፡ #አዲስ ዓመት ሲባል ዘመኑ ሁሌም በየዓመቱ ዑደቱን የሚጀምርበት እንጂ ከነበረው የተለየ ሰኣት፥ጊዜ፥እለት፥ወርኅ፥ ዓመት፣ዘመን፥መጋቢ፣የሚመጣ አይደለም፡፡ #ነገር ግን በየዓመቱ የሚመግቡ አራቱ ወንጌላውያን ስለሚቀያየሩ፥ዘመኑም ቁጥሩ ስለሚጨምር፥የአራቱ ምግብና ከዋክብት፥የአራቱ፥የመጸው፥የክረምት፥የጸደይ፥የሐጋይ ምግብና ስለሚለዋወጥ ካልሆነ በስተቀር ዘመኑ ያው የከረመው ዘመን ቁጥር መጨመር ነው፡፡ #ለክርስትና አዲስ ዘመን ምኑ ነው???? #ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን፦ #በኦሪት ያረጀ ሕዋሳችንን በሐዲስ ኪዳን በወንጌል ማደስ ነው!!! #በኃጢአት ያረጀ ሰውነታችንን ሰውን በምታድስ ንስሓ ማጠብ!!! #በቂም፥በበቀል የጠቆረ ሰውነታችንን በንጽሕና ማደስ!!! #በድንቆርና የተያዘ ሰውነታችንን፡በአዲስ አእምሮ ማዘመን!!! #ምድራዊ ተስፋን የያዘ ሰውነትን በሰማያዊ ተስፋ መንግሥተ ሰማያት ማደስ ማኖር ነው!!! #በአጋንንት ሥራ ያረጀ ሰውነታችንን በተሐድሶ ጸንቶ የሚኖር ክርስቶስን ማውሐድ ነው፡፡ #ለክርስትና ሁሌም ሐዲስ ዘመኑ በሐዲስ ሕግ በወንጌል ጸንቶ መኖር ነው፡፡ "ወብሂሎ በእንተ ሐዲስ ትእዛዝ አብለየታ ለቀዳሚት።ወዘሰ ይበሊ ወይረሥእ ቅሩብ ውእቱ ለሙስና" ዕብ: ፰:፲፫:፡ "ዐዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቷል::አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቧል" ዕብ:8:13፡፡ #ስለዚህ ለክርስቲያን ሁሌም አዲስ #ዘመኑ #ሐዲሲቷ ሕግ ወንጌል ናት!!! #ለክርስቲያን አዲስ #ዘመኑ አዲስ ሕግ #ሥጋ ወደሙ ነው!!! #ለክርስቲያን አዲስ #ዘመኑ አዲስ ሕግ ልጅነት ናት!!! #ለክርስቲያን አዲስ ዘመኑ አዲስ ሕግ #ንስሓ ናት!!! #ለክርስቲያን አዲስ #ዘመኑ በክርስትናዊ ሕይወት መኖር ነው!!! # ለክርስቲያን አዲስ #ዘመኑ አዲስ ሰው ክርስቶስን መልበስ ነው!!! #ለክርስቲያን አዲስ #ዘመኑ አዲሲቷን መንግሥተ ሰማያት በሐዲስ ተሰፋ መውረስ ነው!!! #ለክርስቲያን ሁሌም አዲስ #ዘመኑ ምድራዊውን ትቶ ሰማያዊውን ማሰብ ነው!!! #አዲስ ዘመን የሚለወጥለት በእርጅና የኖረ ሰው ካለ ነው!!! #ክርስትና ሁሌም አዲስ ዘመን ነው፡፡ለክርስትና ብሉይ ዘመን የለውም፡፡ብሉይ ዘመኑ አልፎለታል፡፡ #ብሉይ ዘመን 5500 የነበረ ዘመነ ኦሪት ነው፡!!! #አዲስ ዘመን አዲሲቷን መንግሥት የምታወርስ ዘመነ ወንጌል ናት!!! #ክርስትና ሁሌም አዲስ ዘመን ነው፡፡ #እንኳን ለአዲስ ዘመን ዘመነ ወንጌል አደረሳችሁ!!! © ጌዴዎን ዘለዓለም::
إظهار الكل...
👍 8 8👏 5
Photo unavailableShow in Telegram
10
ኢትዮጵያዊው መልከጼዴቅ መልከጼዴቅ ማለት ንጉሠ ጽድቅ፣ ንጉሠ ሰላም ማለት ነው፡፡ እንደ ትርጓሜ ወንጌል ሐተታ ትውልዱ፣ ነገዱ ከነገደ ካም ነው፡፡ ስንክሳር፣ ገድለ አዳም፣ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ፣ መጽሐፈ ቀሌምንጦ ከነገደ ሴም ነው ይላሉ፡፡ ስለ ሁለት ምክንያት ይሆናል፦ 1ኛ አንድ ሰው ከአንድ ነገድ ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት ከሁለትና ከዚያም በላይ ከሆነ ነገድ ይወለዳልና፡፡ 2ኛ የወንድምን ልጅ ልጅ ብሎ መጥራት የተለመደ ስለሆነ ነው፡፡ አባቱ ቃይናን፣ እናቱ ባረካ ይባላሉ፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍ አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፤ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘለዓለም ካህን ሆኖ ይኖራል ይለዋል። ዕብ 7፥3 ስለ ዐራት ነገር እናት፣ አባት የለውም ይላል፡፡ 1ኛ የዕብራ ውያን አንድምታ እናት፣ አባቱ በዘሌዋውያን ስላልተጻፉ ነው ይላል፡፡ 2ኛ ዮሐንስ መደብር ከአብርሃም ነገድ ስላልሆነ ነው ይላል፡፡ 3ኛ ከቃለ መምህራን እንደ ሰማሁት (መ/ር ገብረ መድኅን እንደሚሉት) በምናኔ ሕግ ለመናኝ እናት፣ አባት የለውምና፤ አይሁድም በብሕትውና ይኖር ስለነበር እናት፣ አባት የሌለው ሰው ከዚህ አለ ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ልማድ እናት፣ አባት የለውም አለ፡፡ ዐራተኛው ምሥጢር ነው፡፡ እናት፣ አባት እንደሌለው ምሳሌው ለሚሆን ለወልድም በሰማይ እናት፣ በምድር አባት የለውምና፡፡ ለሕይወቱ ፍጻሜ እንደሌለው ወልድም በዚህ ጊዜ ተገኘ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋል አይባልምና፡፡ በጥቅሉ በክህነቱ፣ በመሥዋዕቱ፣ በሕይወቱ ሁሉ ምሳሌው ነው፡፡ በቤት ነገድ የምስርና የኑብያ ነገድ ከሚሆን ከሲዱ የተወለደ ነው፡፡ ሲዱ ሳይዳን አቅንቶ በስሙ አስጠርቷል፡፡ አሕዛባዊ ነው፡፡ የመልከጼዴቅ አባትም ጣዖታዊ ነው፡፡ መልከጼዴቅን ካም በ15 ዓመቱ ወደ ቀራንዮ በወሰደው ጊዜ ዐለቱ ተሰንጥቆ አጽመ አበውን ተቀብሎታል፡፡ በዚያ ላይ 12 ድንጋይ ጸፍጽፎ መሠዊያ ሠርቶ በኅብስትና በወይን ሲያስታኵት ይኖር ነበር፡፡ አብርሃም ለአምስቱ ነገሥተ ሰዶም ረድቶ ዐራቱን ነገሥተ ኮሎዶጎሞር ድል ነሥቶ ሲመለስ ሂዶ በተገናኘው ጊዜ ኅብስተ አኰቴት፣ ጽውዐ በረከት ይዞ ተቀብሎታል፡፡ ዘፍ 14፥1 ኑሮው በብሕትውና ሥርዐት ጥፍሩን ሳይቆርጥ፣ ጸጉሩን ሳይላጭ፣ የላመ የጣመ ሳይቀምስ፣ ከዋሻው ሳይወጣ፣ ዳባ ለብሶ፣ የቁርበት ቅናት ታጥቆ ነው፡፡ የተጣላ ሲመጣ ያስታርቃል፤ በዚህ ንጉሠ ሰላም ተብሏል፡፡ ይፈርድላቸውም ስለነበር ንጉሠ ጽድቅ ተብሏል፡፡ ኢየሩሳሌምን የመሠረተ እርሱ ነው፡፡ እርሱ ስለኖረባት ሳሌም ተብላለች፤ ሰላም ማለት ነው፡፡ ዮሐንስ መደብር 113 ዓመት ነግሦ ሞተ ይላል፡፡ መልከጼዴቅ በብሔረ ሕያዋን ካሉ ቅዱሳን አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ዓለም የተለየውን ሁሉ ሞተ፣ ዐረፈ ማለት በመጽሐፍ የተለመደ አነጋገር ስለሆነ ነው እንጅ የሥጋ ሞት አልሞተም፡፡ በምጽአት ከነኤልያስ፣ ከነሄኖክ ጋር መጥቶ መስክሮ ይሞታል፡፡ አንዳንዶቹ መልከጼዴቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎም በጣና አካባቢ ይኖር እንደነበር ይጽፋሉ፡፡ ከዚህም አልፈው አግብቶ ይኖር እንደነበር፣ 3 ልጆችን እንደ ወለደ፣ ኢትኤል የሚባለው ልጁም የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደ ነበር ይናገራሉ፡፡ መልከጼዴቅ ኢትዮጵያ መጥቶ የኖረበት ታሪክ የለውም፡፡ ኢትዮጵየያዊ የተባለበት ምክንየያት ከነገደ ካም ስለሆነ ነው፡፡ እንዲሁም ኑብያ ጥንቱን የኢትዮጵያ ግዛት ስለነበረች ነው፡፡ ጥንተ ነገዱ ከኑብያና ከግብጽ ነውና፡፡ ንጹሕና ድንግልም ነው፡፡ አላገባም፤ ልጅም የለውም፡፡ ጳጒሜን 3 ቀን መታሰቢያው ነው፡፡ በረከቱ ይደርብን፡፡
إظهار الكل...
👍 21
ሌሎቻችንም እንሳተፍ!
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.