cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

MESINA SDA CHURCH

👉Revelation 1 (KJV) 3: Blessed is he that readeth, and they that hear the words of this prophecy, and keep those things which are written therein: for the time is at hand. Comment 👇👇👇 @GospelMinistryBot @erdac

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
633
المشتركون
-124 ساعات
-27 أيام
+6530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖 26ኛ ትምህርት ✒ ስለ ሰንበት 1. የእግዚአብሔር ሕግ ከሣምንቱ የትኛው ቀን ሰንበት እንደሆነ ይነግረናል? መልስ ፡—ሰባተኛው ቀን፡፡ «የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።›› ዘፀአት 20፡8-10 2. ሰንበት ስለ ማን ተፈጠረ? መልስ ፡—ሰንበት ስለ ሰው ሆነ። ‹‹ደግሞ፡፡ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤›› ማር. 2፡27 3. ሰንበት የተፈጠረው መቼ በማንስ ነው? መልስ ፡—በፍጥረት መጨረሻና በሳምንቱ መጨረሻ በእግዚአብሔር ተፈጠረ። ‹‹ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ። እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ፡፡ እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።›› ዘፍ. 2፡1-3 4. እግዚአብሔር ይህን ቀን እንዴት ያለ ቀን አደረገዉ? መልስ ፡- የተባረከና ቅዱስ ቀን አደረገዉ። ‹‹እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።›› ዘθ.20:11። 5. እግዚአብሔር ሰንበትን ምን ብሎ ጠራው? መልስ :- የተቀደሰ ቀኔ ብሎ ጠራው፡፡ «ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ _ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው…።»ኢሳ. 58፡13። 6. ክርስቶስ ስለ ሰንበት አጠባበቅ ምን ምሳሌ ሰጠ? መልስ ፡—በሰንበት ቀን ፀሎት ቤት ተገኝተን እንድንፀልይና ቃሉን እንድናዳምጥ። «ወዳደገበቱም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።››ሉቃ. 4፡16 7. ጳውሎስ ልማዱ በሰንበት ቀን ምን ነበር? መልስ ፡—ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ የእግዚአብሔርን ቃል ማሰማት። ሀ. ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ገባ፥ ሦስት ሰንበትም ያህል ከእነርሱ ጋር ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ይነጋገር ነበር፤››ሐዋ.17:2 ለ. በወጡም ጊዜ ይህን ነገር በሚመጣው ሰንበት ይነግሩአቸው ዘንድ ለመኑአቸው። ዮሐ. 13፡42። ሐ. በሁለተኛውም ሰንበት ከጥቂቶቹ በቀር የከተማው ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰሙ ዘንድ ተሰበሰቡ።» ሐዋ.13፡44 8. በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል ሰንበት ምንድን ነው? መልስ ፡- ምልክት ‹‹ሰንበታቴንም ቀድሱ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ።›› ሕዝ.20:20። ➡ 27ኛ ትምህርት ይቀጥላል... @MesayD
إظهار الكل...
📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖 25ኛ ትምህርት ➡ አሥርቱን ትእዛዛት ያለ ስህተት በቃልዎ ያጥኑ (ዘፀአት 20:3-17) 1. ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። ዘፀ. 20፡3 2. በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። ዘፀ. 20፡4-6 3. የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።ዘፀ. 20፡7። 4. የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም። ዘፀ. 20:8-11 5. አባትህንና እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም። ዘፀ. 20፡12 6. አትግደል፡፡ ዘፀ. 20:13 7. አታመንዝር። ዘፀ. 20:14 8. አትስረቅ። ዘፀ. 20:15 9. በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር። 10. የባልንጀራህን ቤት አትመኝ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ፡፡ ዘፀ.20፡16-17። ➡ 26ኛ ትምህርት ይቀጥላል... @MesayD
إظهار الكل...
📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖 24ኛ ትምህርት የእግዚአብሔር ሕግ 1. እግዚአብሔር ስለ ሕግ ምን ይላል? መልስ:- የእግዚአብሔር ሕጉ ለዘለዓለም የፀናና የታመነ ነው ይላል። ሀ. «የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ነፍስን ይመልሳል የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።» መዝ. 19:7-8 ለ. «የእጆቹ ሥራ እውነትና ፍርድ ነው ትእዛዙም ሁሉ የታመነ ነው፥ ለዘላለምም የጸና ነው፥ በእውነትና በቅንም የተሠራ ነው፡፡›› መዝ.111፡7-8 2. የሰው ሁለንተናው ምንድን ነው? መልስ ፡—እግዚአብሔርን መፍራትና ትዕዛዙን መጠበቅ ነው፡፡ ‹‹የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ፡፡›› መክ. 12፡13። 3. የሱስ ሕጉን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ ምን አለ? መልስ ፡ ትዕዛዛትን ጠብቅ አለ፡፡ «አነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው።እርሱም፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው፡፡ ማቴ. 19:16-17 4. ከእግዚአብሔር ሕግጋት ስንቱን መጠበቅ ያስፈልጋል? መልስ :—ሁሉንም። ‹‹ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ አታመንዝር ያለው ደግሞ፡፡ አትግደል ብሎአልና፤ባታመነዝርም፥ ነገር ግን ብትገድል፥ ሕግን ተላላፊ ሆነሃል።›› ያዕ. 2፡10-11 5. ትእዛዙን አውቃለሁ የሚል የማይጠብቅም ምን ይባላል? መልስ ፡—ውሸታም ይባላል፡፡ «አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።›› 1ዮሐ. 2፡4 6. ዳዊት እግዚአብሔርን ደስ የሚለው ምንድነው ይላል? መልስ ፡—በርሱ አምኖ ሕጉን ሲጠብቅ ። ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።›› መዝ. 1፡1-2። 7. ኃይማኖት ሕግን ምን አታደርግም? መልስ ፦ አትሽርም። «እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።›› ሮሜ 3፡31 8. በመጨረሻ ዘመን የእግዚአብሔር ወገኖች በምን ይታወቃሉ? መልስ :- የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቃቸው። «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው።›› ራእ. 14፡12። ➡ 25ኛ ትምህርት ይቀጥላል... @MesayD
إظهار الكل...
📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖 23ኛ ትምህርት ✒ የሚከተሉትን ጥቅሶች በቃልዎ ያጥኑ 1. ሰው ኃጢአቱ ይቅር እንዲባልለት ምን ሊያደርግ ያስፈልገዋል? መልስ :- ንሰሐ መግባት፡፡ «እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም›› (ሐዋ.3፡19።) 2. ሰው ኃጢአቱን ከተናዘዘ በኋላ ምን ማድረግ ያስፈልገዋል? መልስ ፡—ኃጢአትን መተው፡፡ «ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።›› ምሳሌ 28፡13። 3. ኃጢአታችንን ብንናዘዝ እግዚአብሔር ምን ያደርግልናል? መልስ ፡—ይቅር ይለናል፡፡ «በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡›› (1ኛ ዮሐ. 1፡9።) 4. መንግሥተ ሰማይ ለመግባት ምን ያስፈልጋል? መልስ ፡- ከክፉ መንገድ መመለስ። «እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም›› (ማቴ. 18:3።) 5. የሱስ ይህንን መለወጥ እንደምን አድርጎ ይገልጸዋል? መልስ ፡—እንደገና በመወለድ፡፡ «ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ። ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።» (ዮሐ. 3፡ 5-8) 6. ሰው እንደገና መወለዱን በምን ያሳያል? መልስ ፡—ኃጢአቱን በማሸነፍ እና በመተው። ሀ. ‹ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።(1ዮሐ 5፡4።) ለ. «ስለዚህ የዲያቢሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።» (ዮሐ 3፡9።) 7. ንሰሐ ከገባን በኋላ ቀጥሎ ያለው እርምጃ ምንድነው? መልስ ፡- መጠመቅ። ‹‹ጴጥሮስም፦ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።» ሐዋ. 2፡38። 8. ከጥምቀት በኋላ እንደምን ያለ ኑሮ ልንኖር ይገባል? መልስ ፡- በአዲስ ሕይወት ልንኖር ይገባል። ሀ. ‹‹ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? ለ. እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።›› (ሮሜ 6፡3፣4።) 9. ጳውሎስ እንደምን ኖረ? መልስ ፡- በእግዚአብሔር ልጅ አምኖ ኖረ። ‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።›› ገላትያ 2፡20፡፡ 10. የሥጋ ምኞትን ሁሉ ምን ልናደርግ ይገባል? መልስ ፡—ልንተው ይገባል፡፡ «እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው። በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል። እናንተም ደግሞ ትኖሩባቸው በነበራችሁ ጊዜ፥ በፊት በእነዚህ ተመላለሳችሁ፡፡ አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ። እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥ የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።›› (ቆላ. 3፡5-10) 11. ስንት ጊዜ ልንጸልይ ይገባናል? መልስ ፡—ሁልጊዜ። ሀ. ‹‹ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥» ሉቃ. 18፡1። ለ. ‹‹ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።›› 1ተሰ.5፡17። ሐ. «በማታና በጥዋት በቀትርም እናገራለሁ እጮኽማለሁ፥ ቃሌንም ይሰማኛል።›› መዝ. 55፡17። 12. ከጸሎት ጋር ምን ሊኖረን ይገባል? መልስ ፡—እምነት፡፡ «ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው፡፡›› (ያዕ. 1:6-7) 13. የሱስ በምን ልንኖር ይገባል አለ? መልስ ፡ በእግዚአብሔር ቃል። «እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው›› (ማቴ 4:4።) 14. ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ምን ብሎ አስተማረው? መልስ ፡—የእግዚአብሔርን ቃል ኢንዲያጠና አስተማረው፡፡ ‹‹የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ፡፡» 2ጢሞ. 2:15። 15. የእግዚአብሔርን ቃል ከማጥናት ሌላ ምን ያስፈልጋል? መልስ ፡- ቃሉን አድራጊ መሆን። «ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል። ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል። ያዕ. 1፡22-25። ➡ 24ኛ ትምህርት ይቀጥላል... @MesayD
إظهار الكل...
👍 1
📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖 22ኛ ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት 1. የሱስ በምን ብቻ እንደምንድን ይናገራል? መልስ :- በእግዚአብሔር ቃል ብቻ። «እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው፡፡›› ማቴ. 4:4 2. ሰዎች ለምን ይስታሉ? መልስ ፡ መጽሐፍትን ስለማያነቡ። “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው:- መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ።›› ማቴ. 22፡29። 3. ሰው እንደምን አድርጎ ከኃጢአቱ ሊነጻ ይችላል? መልስ ፡ የእግዚአብሔርን ቃል በመጠበቅ፡፡ ሀ. «ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው። መዝ. 119፡9 ለ. «አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ፡፡›› መዝ.119:11 4. ለክርስቲያን አስተዳደግ ምን አስፈላጊ ነው? መልስ :- የቃሉ ወተት፡፡ «ጌታቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ። 1ጴጥ.2፡2። 5. ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ምን እንዲያደርግ መከረው? መልስ ፡—እራስህን ለእግዚአብሔር አፅንተህ ቁም አለው። «የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር _ ልታቀርብ ትጋ፡፡›› 2ጢሞ. 2:15። 6. የቤርያ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ጥቅስ እንደምን ፈለጉ? መልስ ፡—ዕለት ዕለት በመመርመር። «እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና።ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።›› ሐዋ. 17፡11። 7. ኢዮብ የእግዚአብሔርን ቃል እንደምን አድርጎ አከበረ? መልስ ፡—አብልጦ አከበረው። «ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።» ኢዮ. 23፡12። 8. የእግዚአብሔርን ቃል ከማጥናት በስተቀር ሌላ ምን ማድረግ አስፈላጊ ነው? መልስ ፡- እምነትን በተግባር መተርጎም። ሀ. "ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ያዕ.1:22። ለ. ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል፡፡› ያዕ.1:23-24 ሐ. ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል። ያዕ.1፤25። ➡ 23ኛ ትምህርት ይቀጥላል... @MesayD
إظهار الكل...
Hawella Tula SDA Church Mezemerane
إظهار الكل...
📖 መጽሐፍ ቅዱስ ይናገር 📖 21ኛ ትምህርት ✒ ጸሎት 1. ባለመዝሙሩ ዳዊት እግዚአብሔርን ምን ሰሚ ነህ ይለዋል? መልስ ፡—ፀሎትን ሰሚ። «ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ እንተ ይመጣል።,, መዝ. 65፡2 2. የሱስ ፀሎትን በተመለከተ ምን ምክር ሰጠ? መልስ :- ተግታችሁ ጸልዩ። ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።›› ማቴ. 26፡41። 3. ምን ጊዜ ልንጸልይ ይገባል? መልስ :—ሁልጊዜ ልንጸልይ ይገባል። ‹‹ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥›› ሉቃ. 18፡1 4. ስንፀለይ ማን ይረዳናል? መልስ ፡ መንፈስ ቅዱስ። «እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል›› ሮሜ 8፡26። 5. በማን ስም ልንጸልይ ይገባናል? መልስ : በየሱስ ስም። እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።» ዮሐ. 14፡13። 6. ጸሎታችን እንዳይሰማ የሚከለክለው ምንድን ነው? መልስ ፡—ክፋት። ሀ. ‹‹በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።›› መዝ. 66:18: ለ. «ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ጸሎቱ አስጸያፊ ናት፡፡›› ምሳሌ 28፡9። 7. የሱስ ስለ ምስጢር ጸሎት ምን ይላል? መልስ :- በስውር ፀልይ «አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።›› ማቴ. 6፡6 8. ከጸሎት ጋር ምን ሊኖረን ይገባል? መልስ ፡—ኃይማኖትና እምነት፡፡ ሀ. ‹‹ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።›› ማር. 11፡24። ለ. «ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። (ያዕ. 1፡6-8።) ➡ 22ኛ ትምህርት ይቀጥላል... @MesayD
إظهار الكل...
👍 1
SSL2024q3-11en.pdf1.57 KB
3
Happy Sabbath brethren
إظهار الكل...
1
إظهار الكل...
Lesson 11, 3rd Quarter 2024 - Taken and Tried by Advanced Sabbath School

Memory Text: “And he said, Abba, Father, all things are possible unto thee; take away this cup from me: nevertheless not what I will, but what thou wilt.” - Mark 14:36 KJV  “Christ was standing at the point of transition between two economies and their two great festivals. He, the spotless Lamb of God, was about to present Himself as a sin offering, that He would thus bring to an end the system of types and ceremonies that for four thousand years had pointed to His death. As He ate the Passover with His disciples, He instituted in its place the service that was to be the memorial of His great sacrifice. The national festival of the Jews was to pass away forever. The service which Christ established was to be observed by His followers in all lands and through all ages.” The Desire of Ages, page 65.2 “Through the teachings of the sacrificial service, Christ was to be uplifted before all nations, and all who would look to Him should live. Christ was the foundation of the Jewish economy. The whole system of types…

1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.