cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የልደታ ሙስሊም ሴቶች ጀመአ

قال رسول الله (صلي الله عليه وسلم) ،"الدين النصيحة" ، قلنا :لمن؟، قال،"لله ولكتابه ولرسوله ولأءمة المسلمين وعامتهم" رواه مسلم

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
257
المشتركون
+324 ساعات
+27 أيام
+1530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ትምህርት ቅንጦት አይደለም ~ ያ ኡመተል ኢስላም! ልጆችህን ትምህርት አስተምር። ካልሆነ ግን በገዛ ምድርህ ባይተዋር ትሆናለህ። ካልሆነ ግን ሌላው በተቋም እና በመዋቅር ሲዋጋህ አንተ በለቅሶ ነው የምትከላከለው። ካልሆነ ግን በገዛ ቀየህ ላይ "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" ይተረትብሃል። ካልሆነ ግን ግብር የምትከፍልበት ተቋም የምትወገርበት ዱላ ይሆናል። ካልሆነ ግን ለሚደርስብህ መገለልና መድሎ ምላሽህ ለቅሶ ብቻ ይሆናል። ካልሆነ ግን መብትህን የምታገኘው ሌሎች ሰፍረው ለክተው በሚሰጡህ መጠን ብቻ ይሆናል። አለመማር አንድምታው ብዙ ነው። አላስተምርም ካልክ ሚሽነሪ ገብቶ ልጆችህን በትምህርትና በጤና አገልግሎት ስም ይወስድልሃል። እነ ላጲሶ የሚሸነሪ ሰለባዎች ናቸው። አላስተምርም ካልክ ሴረኛ ፖሊሲዎችና ደንቦች እየተረቀቁ ከንግዱ ሴክተር ሳይቀር በካልቾ ትባረራለህ። አላስተምርም ካልክ ታሪክህን እያወላገደ፣ እምነትህን እያንጋደደ ለሚያጠለሽ አካል ቦታውን ትለቃለህ። አለመማር በጤናው፣ በፀጥታው፣ በአስተዳደሩ፣ ... ሴክተር የሚኖረው ክፍተት ከምናስበው በጣም የራቀ ነው። በዚህ ዘመን በስልኩ የተላከለትን መልእክት የማያነብ፣ የሰፈሩ አጥር ላይ የተለጠፈን ማሳሰቢያ የማያውቅ፣ ባንክ ቤት ገብቶ ስሙን መፃፍ አቅቶት ሰው የሚጠብቅ ወጣት ማፍራት እጅግ አደገኛ ነገር ነው። አስተምር ልጆችህን። በትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ችግሮችን ልጆችህን በማራቅ አትፈታቸውም። እያስተማርክ ታገል። ጎን በጎን ክፍተቶችን በራስህ በቤትህ ወይም ተደራጅተህ ሙላ። ብታስተምር ይሻልሃል! = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም ፊትን ለወንድ መግለጥ ~ አንዳንዴ ፊታቸውን ከባዳ ወንዶች የሚሸፍኑ እህቶቻችን እንዲገልጡ የሚገፋ ጫና ይገጥማቸዋል። ለምሳሌ ጥጋበኛ እጅ ላይ ወድቀው ካልገለጡ ለከባድ ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ። በመሰል ሁኔታዎች ላይ መግለጥ ይችላሉ? ወይስ ችግሩ የፈለገ ቢከፋ እምቢ ማለት አለባቸው? አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም የማይፈቀድ ነገር ይፈቀዳል። الضرورات تبيح المحظورات የሚለው የፊቅህ መርህ ጠንካራ መነሻ ያለውና የታወቀ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦ { لَا یُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ } አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም።" [አልበቀረህ: 286] በአስገዳጅ ሁኔታ ህይወትን ለማትረፍ በክት መብላት ይቻላል። ተጨባጭ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ የክህደት ንግግር በመናገርም ራስን ማትረፍ ይቻላል። { مَن كَ.فَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ إِیمَـٰنِهِۦۤ إِلَّا مَنۡ أُكۡرِهَ وَقَلۡبُهُۥ مُطۡمَىِٕنُّۢ بِٱلۡإِیمَـٰنِ } "ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ሁኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር።" [አነሕል: 106] ሌሎችም ጉዳዮች እንዲሁ ይታያሉ። የሙስሊሟ ለባዳ ወንዶች ፊቷን መግለጥም በዚሁ አግባብ የሚታይ ይሆናል። ይህንን መርህ በመንተራስ አስገዳጅ ጉዳይ ሲገጥም ጊዜ ሴት ልጅ ፊቷን መግለጥ እንደምትችል ዓሊሞች ይገልፃሉ። በዚህ ላይ በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል:- 1ኛ፦ በማጨት ጊዜ :- ይሄ ሐዲሦች የመጡበት እንዲሁም ኢጅማዕ ያለበት በመሆኑ ለብዙ ሰውም የሚሰወር ስላልመሰለኝ ለማሳጠር ያክል በዚሁ ልለፈው። 2ኛ፦ ለህክምና፦ ጉዳቱ ያለበት ክፍል ፊትም ሆነ ሌላ ክፍል መግለጥ ይቻላል። ከተቻለ ባል ወይም ሌላ መሕረም (ቅርብ ቤተሰብ) አብሮ መኖር አለበት። ባይሆን ሴት ሃኪም ካለ ወደ ወንድ፣ ሙስሊም ካለ ወደ ሌላ መሄድ አይገባም ይላሉ ዓሊሞች። ለህክምና በሚያስፈልገው መጠን ሃኪሙ አካሏን መመልከት ይችላል ይላሉ ኢብኑ ቁዳማ። [አልሙግኒ፡ 7/459] በነገራችን ላይ ጦር ሜዳ ላይ ሴቶች ሶሐቢያት ወንዶችን ያክሙ ነበር። ኡሙ ዐጢያህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦ غَزَوْتُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَبْعَ غَزَوَاتٍ أَخْلُفُهُمْ فِي رِحَالِهِمْ، فَأَصْنَعُ لَهُمُ الطَّعَامَ، وَأُدَاوِي الْجَرْحَى وَأَقُومُ عَلَى الْمَرْضَى "ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ሰባት ዘመቻዎችን ዘምቻለሁ። እቃዎቻቸውን እጠብቅ፣ ምግባቸውን አዘጋጅ፣ ቁስለኞችን አክም እንዲሁም ህመምተኞችን እንከባከብ ነበር።" [ሙስሊም፡ 1812] የቡኻሪን باب هل يداوي الرجل المرأة، والمرأة الرجل እንዲሁም ዘርዘር ያለ ነገር የፈለገ ፈትሑል ባሪን መመልከትም ይቻላል። 3ኛ፦ ችሎት ላይ፦ በፍርድ ችሎት ላይ ፍርድ ለመስጠት ዳኛው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ፊቷን ይመለከታል። ካልሆነ ሐቅን ማስከበር አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል። ምስክር ሆና ስትቀርብ ወይም በሷ ላይ ምስክርነት ለመስጠትም እንዲሁ መገለጥ ግዴታ ሊሆን ይቻላል። ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ይላሉ፦ وللشاهد النظر إلى وجه المشهود عليها لتكون الشهادة واقعة على عينها، قال أحمد: لا يشهد على امرأة إلا أن يكون قد عرفها بعينها "መስካሪ ሰው ምስክርነቱ ቦታው ላይ ያረፈ ይሆን ዘንድ የሚመሰከርባትን ሴት ሊመለከት ይችላል። (ኢማሙ) አሕመድ 'በትክክል ለይቶ እስካላወቃት ድረስ አንዲት ሴት ላይ አይመሰክርም' ብለዋል።" [አልሙግኒ፡ 7/459] ይሄ የሳቸው ሃሳብ ብቻ አይደለም። ሌሎችም "ኒቃብ በለበሰች ሴት ላይ ፊቷን ሳትገለጥ መመስከር አይቻልም" ይላሉ። [አሸርሑል ከቢር፣ ደርዲር፡ 4194] 4ኛ፦ በግብይት ላይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሻጭ ወንድ ገዢዋን ሴት ሊመለከት እንደሚችል ዑለማኦች ይገልፃሉ። [አልሙግኒ፡ 7/459] ያለበለዚያ በግብይቱ ላይ ለተፈጠረ ክፍተት ማስተካከያ ለማድረግ ሊቸገር ይችላል። ለምሳሌ እቃ ሽጦላት ፊቷን ካላየ ኋላ ላይ እቃው ችግር ኖሮበት መመለስ ቢያስፈልግ በትክክል እሷ መሆኗን መለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። 5ኛ፦ አስገዳጅ ህግ ባለበት ሁኔታ፦ በአንዳንድ ሃገራት ህግ ወይም ኤርፖርት አካባቢ ወይም ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመም ፊቷን መግለጥ ትችላለች። ለምሳሌ በመጥፎ ሰዎች እጅ ላይ ወድቃ ራሷን አደጋ ላይ ከምትጥል ፊቷን በመግለጥ ራሷን ማትረፍ ትችላለች። "አስገዳጅ ሁኔታዎች የተከለከለን ነገር ያስፈቅዳሉ።" ስለዚህ ማንነቷን ለመለየት የሚጠይቅ አስገዳጅ ሁኔታ ቢገጥም ወይም ሌላ ተጨባጭ ምክንያት ከኖረ ፊቷን መግለጥ ትችላለች ማለት ነው። ይሄ እንግዲህ ከዑለማኦች አቋም ውስጥ ለደረሰች ሴት ልጅ ፊትን መሸፈን ግዴታ ነው የሚለውን ስንወስድ ነው። የሆነ ሆኖ ጫን ያለ ሁኔታ ካልገጠማት በስተቀር ለትንሽ ለትልቁ እጅ ልትሰጥ አይገባም። ፍተሻና መሰል ቦታዎች ላይ ሴቶችን መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ ካለ ወይም ደግሞ ጉዳዩ አንገብጋቢ ካልሆነ ባዳ ለሆኑ ወንዶች ፊትን መግለጥ አይገባም። አስገዳጅ ችግር ሲገጥም ደግሞ ጉዳዩን በችግሩ መጠን ብቻ ማስተናገድ ይገባል። "አስገዳጅ ሁኔታዎች በልካቸው ነው የሚስተናገዱት።" እንጂ ችግሩን ማመሀኛ አድርጎ አጉል መዘናጋት ውስጥ መግባት አይገባም። ወላሁ አዕለም! በነጥቡ ላይ ሃሳብ ያለው ሰው ማካፈል ይችላል። = (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 01/2017) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

إظهار الكل...
🎞የኢብኑ አባስ መርከዝ " ዶክመንተሪ"

መስከረም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥር እና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ "ተቅዊም" تَّقْوِيم ማለት "የዘመን አቆጣጠር" ማለት ሲሆን ተቅዊም በሁለት ዐበይት ክፍል ይከፈላል፥ አንደኛው "ተቅዊሙ አሽ-ሸምሢያህ" تَّقْوِيم الشَمْسِيَّة ሲሆን ተቅዊሙ አሽ-ሸምሢያህ 365 ቀናት የያዘ የፀሐይ አቆጣጠር”solar calender” ነው። ሁለተኛው ደግሞ "ተቅዊሙል ቀመርያህ" تَّقْوِيم القَمَرِيَّة ሲሆን ተቅዊሙል ቀመርያ 354 ቀናትን የያዘ የጨረቃ አቆጣጠር”lunar calender” ነው። አምላካችን አሏህ ፀሐይ እና ጨረቃ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ማወቂያ እና መስፈሪያዎችን እንዳደረገ ተናግሯል፦ 10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥር እና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ በጨረቃ አቆጣጠር አዲስ ጨረቃ ሲታይ አዲሱ ወር ሙሐረም የወሮች መባቻ(መጀመሪያ) ሆኖ ይጀምራል፥ "ሙሐረም" مُحَرَّم የሚለው ቃል "ሐረመ" حَرَّمَ ማለትም "ቀደሰ" "አከበረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የተቀደሰ" "የተከበረ" ማለት ነው። ሙሐረም ክብር ያለው የአሏህ ወር ነው፦ ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8 ሐዲስ 59 አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ብለዋል፡- ”ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአሏህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ صِيَامِ شَهْرِ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّم ሙሐረም "የአሏህ ወር" የተባለበት አሏህ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አንድ ተብሎ ወር የተጀመረበት ወር ስለሆነ ነው። “ወር” የሚለው ቃል በነጠላ “ሸህር” شَهْر ሲሆን በነጠላ ቁጥር በቁርኣን 12 ውስጥ ጊዜ ተጠቅሷል፥ የሚያጅበው የወሮች ቁጥር አሏህ ዘንድ በአሏህ መጽሐፍ አሥራ ሁለት ወር ነው፦ 9፥36 የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ አሏህ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ሲሆን አሏህ ሰማያትን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጥሯል፦ 50፥38 ሰማያትን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ በግሪክ ኮይኔ "ሄክሳ" ἑξα ወይም "ሔክስ" ἕξ ማለት "ስድስት" ማለት ሲሆን "ሔሜራ" ἡμέρᾱ ወይም "ሄሜሮስ" ἥμερος ደግሞ "ቀን" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "አክሲማሮስ" ማለት "ስድስት ቀናት" ማለት ሲሆን አክሲማሮስ ስለ ስድስት ቀናት አፈጣጠር የሚያወራው ትምህርት ነው። በ4ኛው ክፍለ-ዘመን ከ 367-403 ድኅረ-ልደት የቆጵሮስ ኤጲጵ ቆጶስ የነበረው ኤጲፋንዮስ ያዘጋጀው መጽሐፍ እራሱ አክሲማሮስ ይባላል። ከ 180 እስከ 222 ድኅረ ልደት ድረስ ለ 42 ዓመታት የአሌክሳንድርያ ፓትርያርክ የነበረው ድሜጥሮስ የቀመረው የዘመን ቀመር “አቡሻኽር” ወይም “ባሕረ-ሐሳብ” ሲባል በዚህ የዘመን ቀመር ላይ ስለ “አዕዋዳት” ይናገራል፥ “አዕዋድ” ማለት “ዖደ” ማለትም “ዞረ” ከሚል የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን “ዙረት” ማለት ሲሆን በየጊዜው እየዞረ የሚመጣ ማለት ነው። የፀሐይ አቆጣጠር የሚዞረው 365 ቀናት የያዘው ሲሆን የጨረቃ አቆጣጠር የሚዞረው ደግሞ 354 ቀናት የያዘው ነው፥ የጨረቃ አቆጣጠር 11 ቀናት በመዘግየት ከፀሐይ አቆጣጠር ሲዘገይ "ሙሐረም" ወደ ኃላ ሲሆን ከፊት ለፊቱ ያለው ስሌት "መስከረም" ይሆናል። በአይሁድ የመጀመሪያው ወር ኒሳን ማለትም አቢብ ወር ሲሆን ከዚያ ሰባተኛው ወር ቲሽሬ ነው፦ ዘጸአት 12፥2 ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ከኒሳን ወር ሰባት ወር ስንቆጥር "ቲሽሬ" የሚባለው ወር መስከረም ነው፥ "ቲሽሬ" תִּשְׁרִי‎ ማለት "መጀመርያ" ማለት ነው። አይሁዳውያን ይህንን ወር "ሮሽ ሀ ሸናህ" רֹאשׁ הַשָּׁנָה ማለትም "የዓመቱ ርእስ፣ ጅማሮ፣ ራስ፣ አውራ" በማለት አዲስ ዓመት ይጀምራሉ። "ቲሽሬ" ወይም "ሮሽ ሀ ሸናህ" በፀሐይ አቆጣጠር "መስከረም" እና በጨረቃ አቆጣጠር "ሙሐረም" መሆኑን ፍንትው እና ቁልጭ አርጎ ያሳያል።
إظهار الكل...
"መስከረም" የሚለው ቃል "መዝከር" እና "ዓም" ከሚል ሁለት የግዕዝ ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "የዓመቱ መታሰቢያ" ማለት ነው። ይህ የአይሁዳውያን ሰባተኛ ወር "ኤታኒም" ተብሏል፦ 1 ነገሥት 8፥2 የእስራኤልም ሰዎች ኤታኒም በሚባል በሰባተኛው ወር በበዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ተከማቹ። וַיִּקָּ֨הֲל֜וּ אֶל־הַמֶּ֤לֶךְ שְׁלֹמֹה֙ כָּל־אִ֣ישׁ יִשְׂרָאֵ֔ל בְּיֶ֥רַח הָאֵֽתָנִ֖ים בֶּחָ֑ג ה֖וּא הַחֹ֥דֶשׁ הַשְּׁבִיעִֽי׃ "ኤታኒም" אֵיתָנִים ማለት "ጥንት" "መሠረት" ማለት ሲሆን ከአደም እስከ ሙሣ ድረስ ሲገለገሉበት የነበረ የወር መጀመሪያ እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገፅ 248-249 ላይ ገልጸዋል። በፀሐይ አቆጣጠር የወሩ መጀመሪያ መስከረም ስለሆነ በጽባሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" ሆነ በመለካውያን ኦርቶዶክስ"Estern Orthodox" ዘንድ መስከረም የመጀመሪያው ወር ነው። መስከረምን የመጀመሪያ ወር አርጎ የሚቆጥር የዘመን አቆጣጠር የባዛንታይን የዘመን አቆጣጠር"Byzantine calendar" ይባላል፥ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ከ 691-1728 ድኅረ ልደት የባዛንታይን የዘመን አቆጣጠር ትጠቀም ነበር። ጥር ላይ የሚጀምረው የግርጎሮሳውያን የዘመን አቆጣጠር "ጃንዋሪይ" ግን ባለ ሁለት ፊት ያለው የበሮች እና የመጀመሪያዎች አምላክ ከሚባለው "ጃኑስ" ከተባለው ጣዖት የመጣ ሲሆን የሮማ ካቶሊክ ደግሞ ከጣዖታውያኑ ቀይጦ ያመጣው ሰርጎ ገብ ነው። ምን አለፋችሁ መስከረምን የመጀመሪያ ወር መሠረት ተደርጎ የጨረቃ አቆጣጠር ብታሰሉት የሙሥሊሞች የመጀመሪያ ወር ሙሐረምን ታገኛላችሁ። ባይብል ደግሞ የጨረቃ አቆጣጠርን ዕውቅና ይሰጣል፦ መዝሙረ ዳዊት 104፥19 ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ። መጽሐፈ ሲራክ 43÷6 ጨረቃም ለሁሉም የዘመን መለኪያ ናት። በሰማይ ጠፈር ላይ ያሉት ትልቁ ብርሃን ጸሐይ እና ትንሹ ብርሃን ጨረቃ ለምልክቶች፣ ለዘመኖች፣ ለዕለታት እና ለዓመታት ምልክት እንደሆኑ ዘፍጥረት ይናገራል፦ ዘፍጥረት 1፥14 እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ ዘፍጥረት 1፥16 እግዚአብሔርም ”ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን አደረገ። በፀሐይ አቆጣጠር አንድ ወር 30 ቀን ብቻ ሳይሆን 28 29 30 31 ይውላል፥ ይህ የፀሐይም የጨረቃም ልዩነት ነው። በፀሐይ አቆጣጠር፦ 1. ሰባት ወራት ጥር፣ መጋቢት፣ ግንቦት፣ ሐምሌ፣ ነሐሴ፣ ጥቅምት እና ታህሳስ 31 ቀናት የያዙ ናቸው። ብዜቱ 31×7= 217 ቀናት ይሆናሉ። 2. አራት ወራት ሚያዚያ፣ ሰኔ፣ መስከረም እና ህዳር 30 ቀናት የያዙ ናቸው። ብዜቱ 30×4= 120 ቀናት ይሆናሉ። 3. አንዱ ወር የካቲት 28 ቀናት የያዘ ነው። በጥቅሉ 217፥120+28= 365 ይሆናል። የኢትዮጵያ ልክ እንደ አይሁድ 1 ወር 30 ቀን ብቻ ነው። የማሶሬቲክ አይሁዳውያን 1 ወር 30 ቀን ይሆንና 12 ወር ብቻ ስለሆነ 360 ቀን ብቻ ነው። 354 ወይም 365 አይቀበሉም። የኢትዮጵያ ከፀሐዩ ጋር ለማመሳሰል 1 ወር 30 ቀን ብቻ ይጠቀሙና 360 ቀን ያመጡታል፥ 5 ቀኗን 13 ወር በማድረግ ከግሪክ ጳጉሜ ብለው ወስደዋል።13ኛ ወር የሚባለው ሰው ሠራሽ እንጂ መለኮታዊ ቅሪት የለውም፥ "ጳጉሜ" የሚለው ቃል "ኤፓጎሜኖን" ἐπᾰγομένων ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ “ተጨማሪ” ወይም “የተጨመረ” ማለት ነው። ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ ከፓጋን ግሪክ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው፥ ይህ ሰርጎ ገብ እንጂ መልኮታዊ ቅሪት ያለው አይደለም። ሆነም ቀረ በፀሐይ አቆጣጠር መስከረም እና በጨረቃ አቆጣጠር ሙሐረም የወር መጀመሪያ እና የዓመት መለወጫ ነው፥ ቅሉ ግን መስከረም ሆነ ሙሐረምን ጠብቆ "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት እና በዓል አርጎ መያዝ መለኮታዊ ማስረጃ የሌለው ሰው ሠራሽ በዓል ነውና ጥንቃቄ እናድርግ! ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ @copied
إظهار الكل...
📢 ልዩ የቁርኣን ሒፍዝ ምርቃትና የደዕዋ ፕሮግራም 🔅ዛዱል-መዓድ የቁርኣንና የተርቢያ ማዕከል ለ1 ዓመት በቀን ሙሉ የተመላላሽ ፕሮግራም ቁርኣንን እየሐፈዙና ተያያዥ የሸሪዓህ ዕውቀቶችን እየቀስሙ የቆዩ ታዳጊ ወንዶችና ሴቶችን፤ እንዲሁም የዘንድሮ የክረምት ኮርስ ላይ የተሳተፉ ተማሪዎችን የፊታችን እሁድ ረቢዓል - አወል 5/1446 ዓ.ሂ ወይም (ጳጉሜ!) 3/ 2016 ዓ.ል ያስመርቃል። 🔅በዕለቱ ለሴቶችም ለወንዶችም የተዘጋጁ የተለያዩ አስተማሪ የመድረክ ዝግጅቶችና በተለያዩ መሻይኾች የሚቀርቡ ምክርና ሙሓደራዎች ይኖራሉ። 🔅ቦታ:- ፉሪ በድር መስጂድሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ @ዛዱል መዓድ 🔸🔹🔸🔹🔸🔹 🌐https://telegram.me/ahmedadem ~ https://www.facebook.com/yenegew/ ~~~~ 📶  http://www.youtube.com/c/ZadulMaad 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ
إظهار الكل...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

إظهار الكل...
ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች

የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ደርሶች 1) ሹሩጡ ሶላት 2) ሪያዱ ሷሊሒን 3) ኪታቡ ተውሒድ 4) ኪታቡ ተውሒድ 5) ሒስኑል ሙስሊም 6) ላሚየቱ ብኒ ተይሚያ 7) አልአርበዑነ ነወዊያህ 8) አልቀዋዒዱል አርበዕ 9) ሓኢየቱ ብኒ አቢ ዳውድ 10) ዶላሉ ጀመዐቲል አሕባሽ 11) ሸርሑ ሱንና ሊል በርበሃሪ

00:36
Video unavailableShow in Telegram
የማትፈልገውን ወንድ በመዳር አንድትን ሴት ማስገደድ ከታላላቅ ወንጀሎች መካከል ነው ይሉናል ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን አላህ ይዘንላቸውና። አንተ ይህን የምታደርግ አባት ሆይ! አንድ ሰው የማትፈልጋትን ሴት እንድታገባ ቢያደርግህ፤ ይህ ላንተ በደል አይደለም ወይ? ታዲያ ለምን በልጅህ ላይ በደል ትፈፅማለህ? አንተ ለዕውቅና፣ ሃብት ለማግኘት፣ ሃብታም ስለሆነ በዛውም ችግርህን ይቀርፍልኛል ብለህ በማሰብ፣ ቢዝነስ ያስጀምረኛል በማለት፣ ባለስልጣን ከሆነ ስልጣን ይሰጠኛል በማለት፣ የቅርብ ጓደኛህ ስለሆነ በሼም፣ ይቅር ብለው መቀያየም ይመጣል በማለት… ወዘተ ለአንተ ዱንያዊ ፍላጎት በማሰብ ልጅህን ለምን ትሸጣታለህ? አላህን አትፈራውም? ጭራሽ ያልፈለገችው በዲናዊ ጉዳይ ከሆነ ቀጥታ ጸብህ ከአላህ ጋር ነው። ለአንተ ጠፊ ዱናዊ ደስታ ብለህ የልጅህን የትዳር ህይዎት አታበላሺው፣ ገና ከወዲሁ በለጋ እድሜዋ አታኮላሻት። || t.me/MuradTadesse
إظهار الكل...
ocO21ZyEPuiqiAgiLBBzmAYcJIXUr2p5EcE9I.mp45.32 KB
ጓግተን የገባንበት ትዳር ለዱንያም ይሁን ለዲን አደጋ ሚሆንበት ሁኔታ ይኖራል። 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ t.me/Darutewhide
إظهار الكل...
ትዳር!!!.mp31.86 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.