cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Fix All Computer Software and Hardware Solution

Welcome To Computer Software and Hardware solution Channel. It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer Software and Hardware solution By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው! JOIN @fixallcomputer Contact @kidan12 or @sefu2

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
187
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡ Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ 1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡ “Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡ 2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ: ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ ደረጃ # 2: አፕስ (Apps) ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“. 3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡. በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡ 4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ አንዳንዴ የቅርብ ጊዜየተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ: ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ ደረጃ # 2: አፕስ (Apps) ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ ደረጃ # 4: “Uninstall Updates” 5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡ 6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ ደረጃ # 2: አፕስ (Apps) ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ 7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡ 8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡ በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡ ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ። 🌹🌹🌷🌷🍄🍄⛄️⛄️⛄️⛄️🍄🍄🌷🌷🌹🌹 ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ። 🔍🔍🔍🔍🔍▬▬ Share ▬▬🔎🔎🔎🔎🔎
إظهار الكل...
ኦርጂናል እና ፌክ ሚሞሪ እንዴት መለየት ይቻላል ሚሞሪ ለመግዛት አስበዋል? ፨ ኦርጂናል ሚሞሪ ከፌኩ በምን ይለያል? ============================== 1ኛ. ኦርጂናል ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን ውስጥ በማስገባት ፎርማት(Format)ማድረግ ነው። ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም ችግር ይጨርሳል ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኢረር(Error) ቦክስ ያሳያቹና ይቋረጣል ============================== 2ኛ.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ ወይም በስልኮ ወደ ሚሞሪው ፍይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን ፊልም ወይም ሌላ ፍይል ወደ ገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 - 30 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ ነው ማለት የው 3ኛ.ሶስተኛው መንገድ ደሞ ስልካችን ውስጥ በማስገባት ይህን SD insight የተባለ አፕፕ(App) ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን አፑን ከዚህ ዳውንሎድ መድረግ ይችላሉ https://www.apkmirror.com/apk/humanlogic/sd-insight-2/ sd-insight-2-1-5-9-release/sd-insight-1-5-9-android-apk-download/ ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕፕ ስንከፍተው ስለ ሚሞሪው ምርት መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል ነው ማለት ነው ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የትአይነት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም መረጃ አያሳየንም ይህ ማለት ሚሞሪው የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው ስለዚህ የማይታወቅ ሚሞሪ ነው ማለት ነው። ▬▬ Share ▬▬▬▬ ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://t.me/fixallcomputer
إظهار الكل...
SD Insight APKs - APKMirror

SD Insight APKs - APKMirror Free and safe Android APK downloads

ካሜራ ከመግዛት በፊት ማየት ያለብን ነጥቦች # አፔቸር (aperture) በኦፕቲክስ አፔቸር (optics aperture)ማለት ብርሃን የሚጓዝበት ቀዳዳ ወይም ፎቶ ሌንስ ቀዳዳ ሲሆን ቀዳዳው በተለያየ መጠን ብርሃን ማስገባት የሚችል ብቃት አለው። የብርሃን ምጣኔው የሚቆጣጠረው አፈሙዝ ስፋት ሲኖረው ለፎቶ በሚመጥን የብርሃን ምጣኔ በመፍቀድ የፎቶውን የብርሃን ተጋላጭነት (exposure) ይቆጣጠራል። አፔቸር የሚለካው በኤፍስቶፕ(f/stops) ሲሆን ከ 1.4 እስክ 16 ድረስ ነው። ኤፍስቶፕ ባነሰ ቁጥር ፎቶው ድምቀት ይኖርዋል በተቃራኒው ቁጥሩ በጨመረ ግዜ የፎቶው ድምቀት ወይም ብርሃን መጠን ይቀንሳል። # ISO አፔቸር በካሜራችን ውሰጥ የሚገባውን የብርሃን መጠን መቆጣጠሪያ ሲሆን አይሶ ደግሞ የፎቶውን መጨለም እና መብራት ይቆጣጠራል። ይህ ማለት የካሜራው ሴንሰር ምንያህል ብርሀን ማስቀመጥ ይችላል ማለት ነው። የአይሶ ቁጥር በጨመረ ቁጥር የፎቶ ግራፉ ድምቀት እየጨመረ ይመጣል በተቃራኒው የአይሶ ቁጥር ሲያንስ ፎቶግራፉ የመጨለም ባህሪ ያሳያል። በዚህ ምክንያት አይሶ ለማታ ፎቶዎች ወይም በቂብርሃን በሌለበት ወቅት ጥሩ ፎቶግራፍ እድናነሳ ይረዳል። አሁን ያሉት ካሜራዎች ISO ሃይላቸው ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በትንሽ ብርሀን ማለትም በትንሽ የሻማ ብርሀን ከፍተኛ የፎቶግራፍ ጥራት ማንሳት ተችሏል። ትንሽ ISO ማለት ሴንሰሩ ትንሽ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ሲሆን ትልቅ ISO ማለት ሴንሰሩ ትልቅ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ነው ። አሁን ያሉ ካሜራዎች ከ100 እስከ 3000 በላይ ISO መጠን አላቸው። # ካሜራ ሸተር (Camera Shutter) በያንዳንዱ ካሜራዎች ውስጥ የተለያዩ ክፍሎች ሲኖር ከዛ ውስጥ አንዱ ሌንስ ይባላል። ሌንስ (መስታያት ካሜራ) ካሜራ ውስጥ ያለ አካል ሲሆን ብርሃንን በማተኮር ወይም የመበተን ስራን ይሰራል። ሸተር ካሜራ ውስጥ የሚገኘ ሲሆን በካሜራ ሴንሰሩ ፊትለፊት የሚገኝ መጋረጃ መሰል ነው። ይህ መጋረጃው ካሜራው ፎቶ ሲያነሳ ይከፈታል። ካሜራው ፎቶ በሚያነሳበት ግዜ ሸተሩ በደንብ በመከፈት የተቻለውን የብርሀን መጠን በማስገባት ካሜራ ሴንሰር በማሳረፍ ፎቶ ለመፍጠር በቂ ብርሃን ካገኘ በሁሃላ ሸተሩ ይዘጋል።ሸተር ስፖድ ማለት የካሜራው ሸተር የሚከፍት የግዜ ርዝመት ማለት ነው። ይህ ማለት የካሜራ ሴንሰሩ በምን ያህል ግዜ ውስጥ የካሜራ ሴንሰር ለብርሃን ይጋለጣል ማለት ነው። ወይም ካሜራው ፎቶ ለማንሳት የሚወስድበት ግዜ ማለት ነው። ረዥም ሸተር ስፒድ በምንጠቀምበት ግዜ ሴንሰሩ ለከፍተኛ ብርሃን ይጋለጣል በዚህ ግዜ ፎቶው ደብዛዛ ይሆናል። ረዥም ሸተር ስፒድ ባለግዜ ተንቀሳቃሽ ነገሮች በፎቶ ላይ ደብዛዛ ይሆናሉ።ብዙ ግዜ በመኪና ማስታወቂያ ለይ የመኪናው ፍጥነት እዳለው ለማስመሰል እንጠቀማለን። አጭር ሸተር ስፒድ ተጠቀምን ማለት ደግሞ ሴንሰሩ ለተወሰነ ግዜ ብቻ ለብርሃን ተጋለጠ ማለት ሲሆን ይህ ማለት ቅዝፈታዊ ፎቶዎች ማንሳት ይቻላል። ሸተር ስፒድ ትንሽ ከሆነ የፎቶግራፍ የመደብዘዝ ሁኔታ ይቀንሳል። ለምሳሌ በፍጥነት የሚያለፍ እቃን በ1/30 ሰከንድ እና በ1/200 ሰከንድ ፎቶ ብናነሳ 1/30 ሰከንድ ፎቶግራፍ ደብዘዝ ያለ ሲሆን 1/200 ሰከንድ ደግሞ ቀጥያለ ወይም ያልደበዘዘ ፎቶ ይወጣወል። # ሜጋፒክስል ሜጋፒክስል ማለት የሚሊዮን ፒክስል ጥርቅም ነው። ፒክስል ደግሞ የዲጂታል ምስል የሚገኘ አካል ሲሆን የምስሉ አነስተኛ መለኪያ ነው። ፒክስልን እንደ ነጥም ማሰብ ይቻላል። ነጥብ ተሰብስበው መስመር እንደሚሰሩ ሁሉ ፒክስል ተሰባስቦ ደግሞ ምስል ይሰራሉ ግን እደ ነጥብ አይቆጠሩም ማለት አደለም። የሜጋፒክስሉ ቁጥር ብዛት የአንድ ምስል ልቀት(resolutions) ይወስናል እና ተጨማሪ ሜጋፒክስሎች ያለው ዲጂታል ምስል ተጨማሪ ልቀት አለው ማለት ነው።በዲጂታል ፎቶግራፍ ላይ ከፍተኛ ልቀት መኖሩ ጠቃሚ ነው። ይህም ካሜራ የበለጠ ምስሎችን ለመፍጠር ብዙ ፒክሴሎችን እንደሚጠቀም ይህም የበለጠ ትክክለኛ ምስል ለመፍጠር ይረዳል። የካሜራ ሴንሰሮች ፒክስል ተብለው የሚጠሩ ብርሃን ተቀባዮች በውስጡ ይዞል።እያንዳንዳቸው እነዚህ ተቀባይም የብርሃኑን በመለካት ይመዘግባሉ። አንድ ሴንሰር እነዚህን አይነት ተቀባዮች በሚሊየን አይነት ይኖሩታል። ስለዚህ ሚሊየን ተቀባዮች ሜጋ ፒክስል ተብለው ይጠራሉ። ብዙ ፒክስል አለ ማለት የፎቶግራፍ ጥራት ይጨምረዋል ማለት ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ገበያ ላይ ያሉ ስልኮች እስከ 25 ሜጋፒክስል ድረስ ሲኖሩ የሳምሰንግ እና አይፎን ስልኮች ለምን ከ13 ሜጋፒክስል ሆነው እንዴት በጥራት ይበልጣሉ? ይህነን ለመመለስ ከላያ የተጻፉትን የካሜራ ባህራት ማየት ትሩ ነው። በነዚህ ስልኮች በላቀ መልኩ ይተገበራሉ በተጨማሪም የፎቶግራፍ ጥራቱ በሜጋፒክስሉ ብቻ ሳይሆን በሴንሰሩ የቁመት መጠን ይወሰናል። ለምሳሌ ካሜራው 30 ሜጋፒክስል ሆኖ ፒክስል ሴንሰሩ ትንሽ ከሆነ የ20 ሜጋፒክስሉ ትልቅ ሴንሰር ያለው የላቀ ጥራት አለው ማለት ነው። ስለዚህ ስልክ ወይም ካሜራ በምንገዛበት ግዜ ሜጋፒክስሉ ለይ ብቻ ትኩረት አለማረግ ተገቢ ነው። ለሌሎችም እንዲደርስ #ሼር አድርጉት ▬▬ Share ▬▬▬▬ ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። here it is https://t.me/Information_Science_Technology በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ Share ..
إظهار الكل...
Information Science and Technology

Information science is a field primarily concerned with the analysis, collection, classification, manipulation, storage, retrieval, movement, dissemination, and transfer of information.

የ3ጂ/ 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ፍጆታን ለመቆጣጠር ወይንም ለመቀነስ 12 ጠቃሚ ምክሮች! በተለይ ቁጥር 3. በጣም ጠቃሚ ነው.. የኢንተርኔት አጠቃቀምን መመጠን የተለያዩ መተግበሪያዎች/ Applications/ ሙሉ በሙሉ ስራላይ በሚሆኑበት ጊዜ የተለያየ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ.. ለምሳሌ:- ቪዲዮ የሚያጫውቱ እንደ ዩቲዩብ/youtube/ እና ፌስ ቡክ/facebook/ ያሉ መተግበሪያዎች ከሌሎች መተግበሪያዎች ይልቅ ከፍተኛ መጠን ያለው ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡ በመሆኑም ስልክዎ ላይ ጭነው የሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች የሚጠቀሙትን የኢንተርኔት መጠን ለመቆጣጠር የሚከተለውን ቅደም ተከተል መተግበር ይችላሉ፡ ከተቻለ ሁልጊዜም ለወይፋይ ቅድሚያ ይስጡ ካልሆነ ግን የሚከተሉትን መላዎች ይጠቀሙ 1.ሴቲንግ /Setting/ ውስጥ Data usageን ይመርጣሉ > mobile data ውስጥ > data usage cycle የሚለው ላይ > ቀስቶቹን በማንቀሳቀስ ምን ያህል መጠን ያለው ኢንተርኔት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠቀም እንደሚፈልጉ መመጠን ይችላሉ፡፡ 2. በራስ መር ማዘመንን /Update/ ማጥፋት ስልክዎ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮች ወይም መተግበሪያዎች እንዲዘምኑ /Update/ ካልፈቀዱ በስተቀር በራሳቸው ጊዜ ያለርስዎ ፈቃድ እንዳይዘምኑ በማድረግ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ 3. ቪዲዮ ሙዚቃ እና ጌም በቀጥታ ከኢንተርኔት ላይ መመልከት/መጫወት ከፍተኛ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎችን በቀጥታ ሲመለከቱ ወይም ሲያወርዱ በተለይ ደግሞ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ቪዲዮዎች እናሙዚቃዎች ከሆኑ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡በአንዳንድ አጋጣሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ እና ሙዚቃን መምረጥ በጥራት ዝቅተኛ ከሆነ ተመሳሳይ ይዘትካለው ቪዲዮ እና ሙዚቃ በሁለት እጥፍ የሚልቅ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡ለምሳሌ:-በሞባይልዎ ከዩቲዩብ (youtube)ቪዲዮ እና ሙዚቃን እየተመለከቱ ከሆነ ጥራቱን ዝቅ በማድረግየኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡ ይህንንለማድረግ 3.1. ስልክዎ ላይ የዩቲዩብ/youtube/ መተግበሪያን ይክፈቱ 3.2.ሜኑ የሚለው ውስጥ ጄነራል/General/ን ይምረጡ 3.3.High Quality on Mobile የሚለውን ያልተመረጠ /Un-tick/ በማድረግ የቪዲዮውን ጥራት ዝቅ ማድረግ ይችላሉ ያስተውሉ * ከፍተኛ ጥራት ያለው ሙዚቃ(ምስል የሌለው) በ(256kbps) የጥራት መጠን ሲጠቀሙ በሰዓት እስከ 100 ሜጋባይት የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ቪዲዮ በHD ጥራት ሲመለከቱ በሰዓት እስከ 1ጂቢ የኢንተርኔት ፍጆታ ይጠቀማሉ፡፡ ጌሞችን ከኢንተርኔት በቀጥታ እየተጠቀሙ ከሆነ በሰዓት ከ10 እስከ 80 ሜ.ባ ድረስ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡ 4. መተግበሪያዎች ማሳወቂያ/ Notification/ እንዳይልኩ ማድረግ እና ከጀርባ በኩል/Background/ ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ ማገድ ★አንዳንድ መተግበሪያዎች እየተጠቀሙባቸው ባይሆንም በውስጥ በኩል እርስዎ ሳያውቁ ኢንተርኔት ይጠቀማሉ ለምሳሌ:- የተሻለ የመተግበሪያው/Application/ ስሪት ሲኖር ራሳቸውን ያዘምናሉ። ስለዚህ መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ስለመተግበሪያው የተለያዩ ማሳወቂያዎች/ notifications/ እንዲደርስዎ ይፈልጉ እንደሆነ ሲጠየቁ መከልከል እንዲሁም አካባቢዎን ፈልጎ እንዲያገኝ ፈቃድ ሲጠየቁ ባለመፍቀድ የኢንተርኔት አጠቃቀምዎን መመጠን ይችላሉ፡፡ የጫኗቸውን መተግበሪያዎች ማዘመን /አፕዴት ማድረግም ሆነ መጠቀም ሲፈልጉ ብቻ ራስዎ ገብተው እንዲፈቅዱ አድርገው መጫን ይችላሉ ▬▬ Share ▬▬▬▬
إظهار الكل...
ስለ ስልክ ቫይረስ ምንያህል ያቃሉ What is Virus ?? #Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ ➲Spyware Virus ➲Malware Virus ➲Ransonware Virus ➲Adware Virus ➲Trojan Horse Virus ናቸው እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው ⓵ ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው ⓶ በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File) ለምሳሌ Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ ⓷ ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው ⓸ ስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል ይህ ማለት እኛ ስልኩን ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል ⓹ Software File ማጥፋት የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ => Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል. ስለ #ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናያለን እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን ⓵ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ ለምሳሌ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time #ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል ለምን ቢባል Fake የሆኑ #ድረገጾች ላይ #ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል ⓶ Bluetooth Email እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን በኋላ መዘጋቱን #Check Up ማድረግ ⓷ የስልካችንን #Software Update ማድረግ በሰአቱ እና በግዜ ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን #ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ #Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ #About Phone የሚል አለ እሱን እንዴ #Click እንላለን ከዛ Software Update የሚለውን #Click ማለት ⓸ ትክክለኛ እና #Original Antivirus መጠቀም ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File #Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት #Remove ማድረግ እነዚህን Original Antivirus ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ ➷➷➷➷➷➷ ➊ #Norton Antivirus ➋ #KasperskyAntiVirus ➌ #BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection ⓹ ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ #Email ለምሳሌ በ #G -mail ነው Email ለምሳሌ በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች #Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ #Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም ⓺ ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application # Update ማድረግ ለምን ቢባል አንዳንድ Applicationኖች ከ ቆይታ ብዛት የተነሳ ወደ ቫይረስ ይቀየራሉ ስለዚህ ሁሉኑም Application በየጊዜው Update ማድረግ አለብን ስልካችን ላይ ያሉ Applicationኖችን Update ለማድረግ መጀመሪያ ወደ PlayStore ላይ እንገባለን ከዛ (My APP) ዉስጥ እንገባለን ከዛ Update መሆን ያለበት Application ካለ እራሱ ይህን Application Update አድርግ ብሎ ይጠቁመናል ከዛ Update የሚለውን #Click ማድረግ ⓻ Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል (Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ? Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው #ቫይረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ስለዚህ ማንኛውንም Notification ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን ⓼ ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል Share This To Your Friends !!!!!
إظهار الكل...
የተወሰኑ ICT ታክኒካዊ ስያሜዎች እናሳውቃችሁ፡፡👏🙌 1. ጥቁር መዝገብ (Blacklist) - በገዳቢ የክልከላ ፖሊሰ የታገዱ ድረ ገጾች እና ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ዝርዝር ነው። 2. ብሉቱዝ (Bluetooth) -አልባ ከሞባይል እና ከባለመስመር ስልኮች በአጭር ርቀት ዳታ ለመላላክ የሚያስችል ገመድ የግንኙነት ደረጃ ነው። ቡሉቱዝ ዳታ ለመለዋወጥ አጭር ሞገዶችን ይጠቀማል 3. ቡቲንግ (Booting) - ኮምፒውተርን ሥራ ማስጀመር ወይም ማስነሳት ነው። 4. አቫስት (Avast) - ጸረ ቫይረስ መሣሪያ 5. መሠረታዊ የግብአት/ውጤት ሲስተምሶፍትዌር (Basic Input/Output System-BIOS) - የኮምፒውተር ሶፍትዌር የመጀመሪያው እና መሠረታዊው ደረጃ ነው። ባዮስ የኮምፒውተራችንን ሐርድዌር ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚረዱ የተለያዩ አማራጮችን ይሰጠናል፤ ኮምፒውተራችን ሲከፈት በይለፍ ቃል ብቻ እንዲገባ ማድረግ ከእነዚህ አንዱ ነው። 6. ሲክሊነር (CCleaner) - በነጻ የሚገኝ ሶፍትዌር ነው። በቅርብ በተጠቀምንባቸው ፕሮግራሞችና በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም አማካኝነት በሐርድ ዌራችን ላይ የተተዉ ጊዜያዊ ፋይሎችን ዱካ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያጸዳ ሶፍትዌር ነው። 7. ሲዲ በርነር (CD Burner) - በባዶ ሲዲዎች ላይ መረጃ ለመጻፍ የሚችል የኮምፒውተር ድራይቭ ነው። ዲቪዲ በርነር (DVD burners) በተመሳሳይ መንገድ በባዶ ዲቪዲዎች ላይ ይጽፋል። ሲዲ-አርደብሊው (CD-RW ) እና ዲቪዲ-አርደብሊው ድራይቮች (DVD-RW drives) ደግሞ በሲዲ/ ዲቪዲ ላይ የተጻፈውን አጥፍተው ከአንድ ጊዜ በላይ መልሰው መጻፍ ይችላሉ። 8. ሰርከምቬንሽን (Circumvention) - በኢንተርኔት አፈና የታገዱ ድረ ገጾችን እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ለማግኘት እገዳውን ማለፍ። 9. ክሌም ዊን (Clam Win) - ለዊንዶውስ የተሠራ የኤፍኦኤስኤስ ጸረ ቫይረስ 10. ኮቢያን ባክአፕ (Cobian Backup) - የኤፍኦኤስኤስ የመጠባበቂያ ማከማቻ መሣሪያ ነው። የቅርብ ጊዜዎቹ የኮቢያን አይነቶች ምንጫቸው የማይገለጽ ነገር ግን በነጻ የሚገኙ ናቸው፤ የቀድሞዎቹ ግን በኤፍኦኤስኤስ ብቻ የሚለቀቁ ነበሩ። 11. ኮሞዶ ፋየርዎል (Comodo Firewall) - ምንጩ (ውስጣዊ መዋቅሩ) ለምርመራ ክፍት የሆነ፣በነጻ የሚገኝ የፋየርዎል መሣሪያ ነው። 12. ኩኪ (Cookie) - የኢንተርኔት ማሰሻ (browser) በኮምፒውተር ላይ የሚተዋቸው የጎበኘነውን ድረ ገጽ እና ተያያዥ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ አነስተኛ ፋይል ነው። 13. ዲጂታል ፊርማ (Digital signature) - ኢንክሪፕሽንን በመጠቀም አንድ ፋይል ወይም መልእክት ከትክክለኛው ሰው የተላከ መሆኑን የማረጋገጫ መንገድ 14. የዶሜይን ስም (Domain name) - በቃላት የሚገለጽ የድረ ገጽ ወይም የኢንተርኔት አገልግሎት አድራሻ 15. ኢንክሪፕሽን (Encryption) - የተራቀቀ ሒሳባዊ ስሌትን በመጠቀም ኢንክሪፕት (encrypt) ማድረግ፤ ትክከለኛው መረጃ ማለትምያለው የይለፍ ቃል ወይም የኢንክሪፕሽን ቁልፍ (encryption key) ሰው ብቻ ኢንክሪፕት የተደረገውን መረጃ ዲክሪፕት ማድረግ/መክፈት (decrypted) እንዲችል የሚያደርግ 16. ኢንጂሜይል (Enigmail) - የታንደርበርድ የኢሜይል ፕሮግራም አጋዥ መሣሪያ (add-on) ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢንክሪፕት የተደረገ ወይም በዲጂታል ፊርማ የታተመ መልእክት ለመላክና ለመቀበል የሚያስችል 17. ኢሬዘር/መደምሰሻ (Eraser) - ከኮምፒውተር ወይም ከሌሎች ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማከማቻዎች ላይ የሚገኝ መረጃን በአስተማማኝ እና በዘላቂነት ከነጭራሹ ለማጥፋት (delete) የሚያከማይክሮሶፍት 18. ፋየርፎክስ (Firefox) - የታወቀ የኤፍኦኤስኤስ ማሰሻ (FOSS Web browser) ነው፤ ከማይክሮሶፍት ማሰሻ “ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” የተለየ አማራጭ ነው። 19. ፋየርዎል (Firewall) - ኮምፒውተርን አስተማማኝ ካልሆኑ የኢንተርኔት እና የቤት ውስጥ መረቦች ግንኙነት የሚጠብቅ መሣሪያ ነው። 20. ነጻና ቀመሩ የሚታይ ሶፍትዌር- ኤፍኦኤስኤስ (Free and Open Source Software-FOSS) - ያለክፍያ በነጻ የሚገኙ እንዲሁም ተጠቃሚዎች የሶፍትዌሮቹን አሠራር እንዲመረምሩ፣ እንዲፈትሹ፣ እንዲያሻሽሉና ለሌሎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅዱ ሶፍትዌሮች ምድብ 21. ፍሪዌር (Freeware) - በነጻ የሚገኙ፣ ነገር ግን ተጠቃሚዎች መሠረታዊ የፈጠራ አወቃቀሩን (source code) እንዳያገኙ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ክልከላዎችን የሚያደርጉ ሶፍትዌሮች 22. ጂኤንዩ/ሊኑክስ (GNU/Linux) - የኤፍኦኤስኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ነው፤ ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ አማራጭ ሲስተም ነው። 23.ጂፒኤስ (Global Positioning System - GPያደረገ በስፔስ/ምህዋር ላይ መሠረት ያደረገ በሳተላይት በመታገዝ ቦታንና ጊዜን ለመለየት የሚያስችል፤ በማንኛውም የአየር ሁኔታ፣ በየትኛውም የምድራችን ወይም በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች የሚሠራ፤ ከሞላ ጎደል በምንም ነገር የማያደናቀፍ ከሰማይ ከፍታ ለመመልከት የሚያስችል የሳተላይት መመልከቻ ነው። 24. #ሐከር/ሰባሪ (Hacker) - በዚህ አገባቡ፣ ከርቀት ኮምፒውተራችንን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ወይም ስሱ መረጃዎቻችንን ለመስረቅአይፒ የሚሞክር ወንጀለኛ 25. የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አድራሻ-( አድራሻ) (Internet Protocol address -IP address) - ማንኛውምሰጪ ኮምፒውተር ከኢንተርኔት ጋራ ሲገናኝ የሚሰጠው ልዩ መለያ 26. ኢንተርኔት አገልግሎት (አይኤስፒ) (Internet Service Provider-ISP) - የኢንተወይም ግንኙነት መስመር አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ ወይም ድርጅት። የብዙ አገሮች መንግሥታት ኢንተርኔትን በጣም ይቆጣጠራሉ፤ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች (አይኤስፒ) በመጠቀምም የኢንተርኔትአሶሲዬሽን ክልከላ፣ ስለላ እና እገዳ ያደርጋሉ። 27. ኢንፍራሬድ ዳታ (Infrared Data Association) (ኢርዳ/IrDAአልባ በአጭር ርቀት የኢንፍራሬድ ስፔክተረም ጨረሮችን በመጠቀም መረጃ/ዳታ ለመለዋወጥ የሚያስችል ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ ነው። በዘመናዊ መገልገያዎች ውስጥ ኢርዳ/IrDA በብሉቱዝ ተተክቷል። 28. ጃቫ አፕሊኬሽንስ (Java Applications) (አፕልትስ/Applets) - በብዙ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሠሩ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ በድረ ገጾች ውስጥ የተሻሻሉ አገልግሎቶችን (functionalities) ለመስጠት ጥቅም ላይ ይውላሉ። 29. ኪይሎገር (Keylogger) - ለስለላ ተግባር የሚውል የስፓይዌር አይነት ነው፤ በኮምፒውተሩ የመተየቢያ ገበታ (keyboard) ላይ የነካናቸውን/ የተጫንናቸውን ቁልፎች/ፊደሎች በሙሉ መዝግቦ ለሦስተኛ ወገን ይልካል። ኪይሎገሮች የኢሜይሎችን እና የይለፍ ቃሎችን ለመስረቅ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ። 30. ኪፓስ (KeePass) - የአስተማማኝ የይለፍ ቃል ማከማቻ (database) ፍሪዌር ነው። Share... https://t.me/fixallcomputer
إظهار الكل...
Fix All Computer Software and Hardware Solution

Welcome To Computer Software and Hardware solution Channel. It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer Software and Hardware solution By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው! JOIN @fixallcomputer Contact @kidan12 or @sefu2

😁 የቴክኖሎጂ እውነታዎች 🔰 ዛሬ ከ3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች Internet ይጠቀማሉ ይህም ከዓለም ህዝብ 40 በመቶው ነው። 🔰 በየ57 ደቂቃው ከ570 በላይ አዳዲስ Websites ይፈጠራሉ። 🔰 በየቀኑ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ Google Search ይደረጋል። 🔰 በ2020 ቪዲዮ ከሁሉም ከInternet ትራፊክ 80% ያህሉን ይይዛል። 🔰 40,000 የTwitter ትዊቶች በደቂቃ ይላካሉ በቀን 500 ሚሊዮን ትዊቶች ማለት ነው። 🔰 በAmerica ከሚደረጉ ከ7 ፍቺዎች መካከል ለአንዱ ፌስቡክ ተጠያቂ ነው። 🔰 በ2020 ከ8.2 ቢሊዮን በላይ መረጃዎች ተሰርቀዋል ወይም Hack ተደርገዋል። 🔰 የመጀመሪያው ኮምፒዩተር ወደ 2.5 ሜትር የሚጠጋ ቁመት ያለው ሲሆን ክብደቱ ወደ 30,000 ኪ.ግ. ይመዝናል። 🔰 NASA ውስጥ የInternet ፍጥነት በሰከንድ 90GB ነው። 🔰 በዓለም ትልቁ ሃርድ ድራይቭ 60TB SSD ነው። 🔰 Bluetooth ኖርዌይን እና ዴንማርክን አንድ ባደረገው ሃራልድ ብሉቱዝ በተባለ ንጉስ ተሰየመ ነው። 🔰 የጉግል መሥራቾች እ.ኤ.አ. በ1999 ጉግል ን በ1 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ፈቃደኞች ቢሆኑም Excite ግን አልተቀበላቸውም። ጉግል አሁን 527 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው። Share This For Your Friends!!! https://t.me/fixallcomputer
إظهار الكل...
Fix All Computer Software and Hardware Solution

Welcome To Computer Software and Hardware solution Channel. It Gives You Some Hints To Repair(Improve Performance Of) Your Computer Software and Hardware solution By Yourself. ለጠጋኞችም የሚጠቅም ምርጥ ቻናል ነው! JOIN @fixallcomputer Contact @kidan12 or @sefu2

ኮምፒውተር ላይ ልታውቋቸው ግድ ነው ያልናቸውን አቋራጭ የኪቦርድ መንገዶችን (Shortcuts) እናሳውቃችሁ። Ctrl+C እና Ctrl+X Ctrl+C የመርጥነውን ጽሁፍ ወይንም ፎልደር ይሁን ፋይል ኮፒ ለማድረግ ይረዳናል። አይ ድግግሞሽ አልፈልግም ቆርጬ (Cut) ነው መውሰድ የምፈልገው ካልን ደሞ Ctrl+Xን መንካት ነው። ከት ካደረግንበት ቦታ ፋይሉን ወይም ጽሁፉን ያጠፋዋል። ለአፕል ኮምፑተር ተጠቃሚዎች Ctrlን በcommand(cmd) በመተካት መጠቀም ይችላሉ። Ctrl+V ይህ አቋራጭ የሚጠቅመን ከላይ ኮፒ ወይም ከት ያደርግነውን በምፈልገው ቦታ ላይ ለማቀመጥ ነው። የንምፈልገው ቦታ ላይ ሄደን Ctrl+V ስንነካ ፋይሉን ያስቀምጥልናል። ለአፕል ተጥቃሚዎች Cmd+Vን መጠቀም ይችላሉ Ctrl+F Ctrl+F በመካት የመፈለጊያ ሳጥን (Search) መክፈት እንችላለን። የህም የፈለግነዉን ጽሁፍ(text) እና ፋይል ለማግኘት ይረዳናል። ለአፕል ተጠቃዎች Cmd+F በመንካት መጠቀም ይችላሉ። Alt+Tab Alt+Tab መጫን በተከፈቱ ፕሮግራሞች መሃል እንደፈለግን እንድቀያይር ያደርገናል። ለምሳሌ በብራውዘር ኢንተርኔት እየተጠቀምን ከነበር እና ወደ መፈትነው ወርድ ፋይል መሄድ ብንፈልግ Alt+Tab በመንካት መለወጥ እንችላለን። ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Tab ተጥቀሙ። Ctrl+Backspace እና Ctrl+Left ወይም Right arrow Backspace የጽሁፍ ፋይል ላይ አንድ ፊደልን ወይም ምልክትን ለማጥፋት ይጠቅምናል። ነገር ግን Ctrl+Backspace ሁሉንም ነገር አንድ ሳያስቀር ያጠፋልናል። Ctrlን ተጭነን የግራ(left) እና ቀኝ(Right) ቀስቶችን ስንነካ እንደ ከርሰር ተጥቅመን የምንፈሊገዉን ተከታታይ ፋይል ወይም ጽሁፍ በጅምላ እንድንመርጥ ይረዳናል። Ctrl+S ዶክመንቶች ላይ እየሰራን የሰራበውን ቶሎ ሴቭ ማድረግ ቢያስፈልህልገን የምንጠቀመው Ctrl+S ነው። በተለይ እንደኛ አገር ላሉ የመብራት ችግር ላለባቨው አገሮች ዶችመታቭን ሴቭ ሳናደርግ እንዳይጠፋ ፍቱን መፍትሄ ነው። ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+S ተጠቀሙ። Ctrl+Home እና Ctrl+End Ctrl+Home ከርሳችንን ወደ ዶክመንታችም መጅውመሪያ ይመልሰዋል። በተቃራኒው Ctrl+End ደሞ ከርሰራችንን ወደ. ዶክመንታችን መጨረሻ ይወስዋል። Ctrl+P ፒሪንት ማድረግ የምንፈልገው ፋይል ወንም ዶቹመንት ካለ Ctrl+P ስንነካ የፕሪንትን መስኮት በመክፈት የፕሪንት አማራጮችን ያሳየናል። ለአፕል ተጠቃሚዎች cmd+Pን ተጠቀሙ። PageUp ፣ Spacebar እና Pagedown ከስሙ መገመት እንደሚቻለው PageUp እና Pagedown ዶክመንታችን ላይ ወደ ቀጣይ ገጽ ወንም ወደ ቀድሞ ገጽ ለመሄድ ይጠቅመናል። የኢንተርኔት ብራውዘር በመጠቀምበት ሰአት ደሞ Spacebar ወይም Shift+Spacebar አንድ ገጽ ለመዝለል ያስችለናል።
إظهار الكل...
በኮምፒውተራችን አዲስ ዊንዶው ምርት ከጫንን በኋላ ደህንነቱን እንዴት አስተማማኝ እናደርጋለን? አዲስ ዊንዶውስ ምርቶችን /Windows/ (7፣ 8፣10) ወይም ሌላ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከጫንን በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግና ለማሻሻል ከዚህ በታች የተቀመጡትን የደህንነት እርምጃዎች መተግበር ይመከራል፡፡ #1. የዊንዶው ስርዓትን ማዘመን/up to date/ የቅርብ ጊዜ የደህንነት ማዘመኛዎች እና መጠገኛዎችን /updates and patches/ መጫን፡፡ #2. ሶፍትዌሮችን ማዘመን /Update software/ ፕሮግራሞች እና መተግበሪያዎች ሁሉም ዓይነት የቅርብ ጊዜ ማዘመኛዎች እና የደህንነት መጠገኛዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የታወቁ ሶፍትዌሮች እንደ ጃቫ ፣ አዶቤ ፍላሽ ፣ አዶቤ ሾክዌቭ ፣ አዶቤ አክሮባት ሪደር የመሳሰሉት ጊዜ ያለፈባቸው ከሆኑ በአጥፊ ተልእኮ ላይ የተሰማሩ ተዋንያን ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎች በቀላሉ ለመድረስ ያስችላቸዋል። #3. መልሶ ማግኛ ስርዓት መፍጠር/Create a restore point/ ለዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች(OS) የደህንነት ማዘመኛዎች ከተጫነ ቀጣዩ እርምጃ በዊንዶውስ ውስጥ ወደ ነበረበት የመመለሻ ቦታ መፍጠር ነው። በኮምፒተር ላይ ችግርን ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም ስርዓቱ ላይ ማንኛቸውም ለውጦች ከማድረግዎ በፊት የመልሶ ማግኛ አማራጭን ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል። #4. ፀረ-ቫይረስ መጫን Install antivirus product - አስተማማኝ የደህንነት መፍትሔ የሚሰጥ ማለትም ሪልታይም ቅኝት ፣ ራስ-ሰር ዝመና (Automatic update) እና ፋየርዎል ማካተት አለበት #5. ለባለብዙ ደረጃ የጥቃት መከላከያ ንቁ የደህንነት መፍትሄን መጫን/Install a proactive security solution for multi-layered protection #6. የምትክ ስርዓት መፍጠር /Back up your system/ #7. መደበኛ አካውንት መጠቀም/ Use a standard user account/ #8. የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥርዎን ንቁ ማድረግ/Keep your User Account Control enabled/ - የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥር በኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያልተፈቀዱ ለውጦችን እንዳይኖሩ ያግዛል። Contact @fixallcomputer 0936585912/0904904909 Join👇 @kidan12 @sefu2
إظهار الكل...
ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection) ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን (Remote Desktop Connection) ማለት በአንድ አይነት ኔትወርክ ላይ የሆኑ ኮምፒውተርችን ወይም በኢንተርኔት የተያያዙ ኮምፒውተሮችን ከርቀት ሆኖ ከአንድ ኮምፒውተር ላይ ለመቆጣጠር የምንጠቀምበት የዊንዶ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ የምናገኘው ፕሮግራም ሲሆን ባለገመድና ገመድ አልባ ኔትወርክ ላይ እንጠቀምበታለን:: አንድ ሲስተም አድሚኒስትሬተር ሪሞትሊ ሆኖ ሌላ ኮምፒውተር ላይ በሪሞት ዴስክቶፕ በመግባት(በመጠቀም) ፋይሎችን ማዘዋወር፣ ዳውንሎድ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮች ሲበላሹ ማስተካከል፣ ኢንስቶል(መጫን)ና ሶፍትዌሮችን ማጥፋት ይችላል፡፡ፕሮግራሙን ለመጠቀም በኔትወርኩ ውስጥ ያሉ ኮምፒውተሮች መከፈት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ኔትወርክ ኮኔክሽን(ግንኙነት) መኖር አለበት በተጨማሪ ሪሞት ዴስክቶፕ ፕሮግራም በእያንዳንዱ ኮምፒውተር ላይ መከፈትና ኔትወርክ አክሰስ መፈቀድ ይኖርበታል ይሄን ለማድረግ የአድሚኒስትሬተር አካውንት ተጠቃሚ መሆን ይኖርበታል ሪሞት ዴስክቶፕ ለመክፈት የምንከተለው ሂደት 1. ማይኮምፒውተር ላይ ራይት ክሊክ ፕሮፐርቲ 2. ሪሞት ዴስክቶፕ (Remote Desktop) ታብ 3. Allows users to connect remotely to this computer የሚለውን ሳጥን እንምረጥ 4. ሪሞትሊ ይህን ኮምፒውተር የሚጠቀሙትን ዩዘሮች(ተጠቃሚዎች) ሴሌክት ሪሞት ዩዘር የሚለውን ቁልፍ በመጫን በኔትወርካችን ውስጥ ያሉ ዩዘሮችን እንምረጥ 5. ኦኬ ማስታወሻ ሪሞት ዩዘር ተጠቃሚዎችን መምረጥ የግድ አስፈላጊ አይደለም በፈላጎታችን ለሴኩሪቲ የምነመርጠው ነው ሪሞት ዴስክቶፕ ለመጠቀም የምንከተለው ሂደት(ስቴፕ) 1. ስታርት - ራን 2. በራን ሳጥን ላይ mstsc ብለን ኦኬ ወይም 1. ስታርት 2. ኦል ፕሮግራምስ 3. አክሰሰሪስ 4. ኮምኒኬሽን 5. ሪሞት ዴስክቶፕ ኮኔክሽን 🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥🖥 👉👉Click the Start Window 💻👉Type in and enter remote settings into the Cortana search box 💻👉Select Allow Remote PC access to your computer 👉👉Click the Remote tab on the System Properties window 👉👉Click Allow remote desktop connection Manager to this computer 👉👉Make sure the box beside Network Level Authentication is checked. This will ensure that you have a more secure remote access experience. 👉👉👉You can also download and install free remote access software online.  Join👇 @fixallcomputer ኮምፒውተርዎን ማሰራት ከፈለጉ 👉 ☏0904904909/☏0936585912 Contact @kidan12 or @sefu2 #share
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.