cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Heaven Army

የወንጌል ቃል ሙላት ያለው ፥ ልጅነቱና ተልዕኮውን የተረዳ፥ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ አማኝ ትውልድ  ማስነሳት!! ዩቱብ/ YouTube: https://www.youtube.com/@HeavenArmy-eo7fy?sub_confirmation=1

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 478
المشتركون
+224 ساعات
-137 أيام
-2730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
🎖️ ሄቨን አርሚ 📖የወንጌል ቃል ሙላት ያለው ፥ በመንፈስ ቅዱስ የታጠቀ ልጅነቱና ተልዕኮውን የተረዳ አማኝ ትውልድ ማስነሳት!! ♦️ይህን ሊንክ ለሌሎች በማጋራት ወዳጆቻችሁን ይጋብዙ። 🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀              ይቀላቀሉን                  🔻🔻          @heavenarmyy          @heavenarmyy          @heavenarmyy                  🔺🔺                   Join
إظهار الكل...
👍 2
Announcement
ሰላም የተወደዳችሁ!! 📌በ2017 የቴሌግራም አገልግሎት ፕሮግራማችን ላይ ማሻሻያ አድርገናል። የማቴዎስ ወንጌል ጥናታችን ሳይቋረጥ የሚቀጥል ሲሆን የላይቭ አገልግሎታችን ግን ረቡዕ ፣ ቅዳሜ(ጸሎት) እና እሁድ ብቻ የሚሆን ሲሆን በመካከል ባሉ ቀናትም የማቴዎስ ወንጌል ጥናቱ የሚቀጥል ይሆናል። 📌ስለዚህ ከዚህ በኋላ የላይቭ ጥናት የሚኖረን ቀን ረቡዕ እና እሁድ ብቻ ሲሆን ቅዳሜ ምሽት ደግሞ የጸሎት ጊዜ ይኖረናል። ሁሉም አገልግሎቶች ምሽት 4:00 ላይ የሚደረጉ ይሆናል። ሄቨን አርሚ
إظهار الكل...
የእግዚአብሔር መንግሥት
📌የማቴዎስ ወንጌል ጥናት 📎ከስር ያሉ ክፍሎችን በመጫን በአገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ የቀረበ ያለውን የማቴዎስ ወንጌል ጥናት የድምጽ ቅጂ ያገኛሉ!! ክፍል 01 || ክፍል 02 || ክፍል 03 || ክፍል 04 || ክፍል 05 || ክፍል 06 || ክፍል 07 || ክፍል 08 || ክፍል 09 || ክፍል 10 || ክፍል 11 || ክፍል 12 || ክፍል 13 || ክፍል 14 || ክፍል 15 || ክፈል 16 || ክፍል 17 || ክፍል 18 || ክፍል 19 || ክፍል 20 || ክፍል 21 || ክፍል 22 በላይቭ አገልግሎቱ ለመካፈል ከማክሰኞ እስከ እሁድ ባሉ ቀናት ሁሉ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በቻነላችን መከታተል ትችላላችሁ። ሄቨን አርሚ 🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀              ይቀላቀሉን                  🔻🔻          @heavenarmyy          @heavenarmyy          @heavenarmyy                  🔺🔺                   Join
إظهار الكل...
🔥ሌላ ሰው🔥 📖“የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።” — 1ኛ ሳሙኤል 10፥6 📌ሳኦል ሳሙኤልን ስያገኘው ስለነበረው ማንነት መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረን ነገር ቢኖር ቁንጅና ፥ ቁመቱ እናም የቂስ ልጅ መሆኑ ብቻ ነበር። ይህን ወጣት የሚገልጽ ምንም ሌላ ነገር የለውም። ይሄ ደግሞ ብቻውን ለምንም የማይጠቅም የህይወት መገለጫ ነው። ምክንያቱም ውበት ከንቱ ነው። ሳኦል ማነው? መልሱ ይሄው ነው። በቃ አለቀ። 📌ለራሱ እንኳን ምን በህይቱ የታካሄደ እንዳለ የማያውቅ። ለሱ አጋጣሚ በሚመስል መንገድ እግዚአብሔር የመራው ሰው ነው። አሁን ደግሞ ንጉን ያስፈልጋል። የእስራኤል ህዝብ ጸሎቱ ተሰምቶለታል። እና ለንጉስነት እና እግዚአብሔር የኔ ያለውን ምርጥ ህዝብ ለመምራት መልክ እና ቁመት ብቻ ምን ይበጃል? ከንቱ ነው። 📌ስለዚህ ከዚህ የተለየ ማንነት መጎናጸፍ አለበት። ጠቢብ መሆን ፣ ብርቱ እና ጀግና መሆን ፥ ተናግሮ መሰማት እና ሞገስ ማግኘት የመሳሰሉ ነገሮች የግድ ያስፈልገዋል። ከየት ያምጣው? ሳሙኤል አለው። መንፈስ ቅዱስ በኋይል ሲወርድብህ ሌላ ሰው ትሆናለህ!!!! ከዛ በኋላ መገለጫህ መልክና ቁመና አይሆንም። 📌ይህ ማንነት የራሱ ሳይሆን የወረደበት ቅዱስ መንፈስ ያጎናጸፈው ነው። ሄሌሉያ!! ክርስትናም ይሄ ነው። ከራሳችን ከማይበጅ መልክ ወጥተን በመለኮት ባህርይ ተካፋይ የምንሆነው ፤ እንደማንኛውም ሰው ሳይሆን አዲስ ፍጥረት ሆነን በአለም የማይመረመር መንፈሳዊ ማንነት የምንጎናጸፈው በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት ነው። ይህ ቅዱስ አምላክ የሆነው መንፈስ የወረደው ጉባኤ ለማሞቅ ሳይሆን ከአዳም መልክ ወደ ልጁ መልክ ለውጦን ሌላ ሰው ልያረገን ነው። የተሻሻለ አሮጌ ሰው አይደለም። ሌላ አዲስ ፍጥረት። ይህ በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ርስት ነው። አሜን!! ጸሎትእግዚአብሔር አባት ሆይ በክርስቶስ ስራ በኩል ቅዱስ መንፈስህን ስላፈሰስክልን አመሰግናለሁ። ይህ መንፈስ ሊቀድሰኝ እንደመጣ አውቃለሁ። የሚቀድሰኝም ከአለም የተለየ መልክ በማጎናጸፍ ነው። ይህ በህይወቴ እለት እለት እንዲሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ስም በቅዱስ መንፈስህ ሙላኝ። አሜን!! ሄቨን አርሚ 🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀              ይቀላቀሉን                  🔻🔻          @heavenarmyy          @heavenarmyy          @heavenarmyy                  🔺🔺                   Join
إظهار الكل...
👍 4🥰 1🙏 1
የእግዚአብሔር መንግስት
📖የማቴዎስ ወንጌል ክፍል 22 ማቴ 5:8 የተራራው ስብከት 6 አገልጋይ ሄኖክ አክሊሉ ሄቨን አርሚ 🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀              ይቀላቀሉን                  🔻🔻          @heavenarmyy          @heavenarmyy          @heavenarmyy                  🔺🔺                   Join
إظهار الكل...
record.ogg9.91 MB
🔥 1
📌ምስጋና ነው ያለኝ ♦️የሐዋሳ ህይወት ብርሃን "ለ"መዘምራን ♦️በዚህ ዝማሬ ጌታን አመስግኑት። ሄቨን አርሚ 🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀             ይቀላቀሉን                  🔻🔻          @heavenarmyy          @heavenarmyy          @heavenarmyy                                   🔺🔺                   Join
إظهار الكل...
ምስጋና_ነው_New_Protestant_Mezmur_ሀዋሳ_የሕይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያን_ለ_መዘምራ.m4a5.62 MB
2
እንኳን እግዚአብሔር ረድቷችሁ ለአዲስ አመት ደረሳችሁ። ብሩህ እና የተባረከ አመት ይሁንላችሁ!! 🌼🌼🌼🌼 ሄቨን አርሚ
إظهار الكل...
🛑የላይቭ ሰዓታችን ደረሰ!! ሊንክ: https://t.me/heavenarmyy?livestream=e4e4b7a76394d69439
إظهار الكل...
Heaven Army

ሄቨን አርሚ የመጨረሻው ዘመን አማኞችን ለክርስቶስ ምጸአት እና ለሚያዘጋጃቸውም ሪቫይቫል ለማንቃት ይተጋል። ዩቱብ/ YouTube:

https://www.youtube.com/@HeavenArmy-eo7fy?sub_confirmation=1

📌በሙሉ ልብ መፈለግ
“እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።”   — ኤርምያስ 29፥13
📖ቀስ በቀስ እግዚአብሔር የራሴ ያለው ምርጥ ህዝብ እያፈገፈገ ነበር። በዛ ላይ ክፉ ነገስታት እየተፈራረቁ ከእግዚአብሔር ሀሳብ ይሰርቋቸው ነበር። እና ህዝቡ በሁለት እግሩ ሁለት አለም ረገጠ። የበዓል መስዋዕት እና የእግዚአብሔርን መስዋዕት አንድ ላይ በላ። ለሁለቱም ሰዋ። 📖እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን እንፈልጋለን ይላሉ። ነገር ግን የበዓልን ጣኦት ከማምለክ አይመለሱም ። ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር ክብር ከእነርሱ ራቀ ፤ ለባቢሎን ምርኮም ታልፈው ተሰጡ። የዚህ ምርኮ አላማ ምን እንደሆነ እግዚአብሔር በኤርሚያስ በኩል ለተማረኩ አይሁድ እንዲህ ይላቸዋል።
“ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።” — ኤርምያስ 29፥11
📖ይህ የሰላም ሐሳብ ምንድ ነው? ...ከዚህ በፊት በሙሉ ልብ ስላልፈለጋችሁኝ ክብሬ ከናንተ ርቆ ነበር። አሁን ግን ትሁት አደርጋችሁና መልሳችሁ በሙሉ ልብ ልትፈልጉኝ ትጀምራላችሁ። ያን ጊዜ እኔም እገኛለሁ። 📖እግዚአብሔር ያልተገኘላቸው በሙሉ ልብ ስላልፈለጉ ነበር። እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ። ደግሞም በዓልን ይፈልጋሉ። የበዓል ጣኦትን ለምን አመለኩ? በዓል የብልጽግና ወይም የልምላሜ አምላክ ብለው ባቢሎናዊያን በኩር ሰው ከነነፍሱ አቃጥለው እየሰው የሚያመልኩት ጣኦት ነው።... ያው አጋንንት ማለት ነው። እነዚህን ሰዎች ወደዚህ የመራቸው የአለም ወይም የገንዘብ ፍቅር እንጂ ሌላ ከይደለም። 📖እግዚአብሔር ለናንተ ያለኝ ሀሳብ ታላቅ ነው ሲላቸው ያ ታላቅ ወይም ውብ የሆነ ፍጻሜ ያለው ሀሳቡ ምንድ ነው? በህዝቡ መካከል መገኘት። ክብሩን በመካከላቸው ማኖር። ይህ እንዲመጣ የፈለጉት ከንቱ እንደሆነ ፥ የተመኩት ከንቱ እንደሆነ እስኪገባቸው እና ተመልሰው እግዚአብሔርን እስኪፈልጉ ድረስ ሰባ አመት ተዋቸው። ልባቸውን ከትዕቢታቸው በመከራ ፈትኖ ልያጠራ ፈልጎ ነበርና። 📖ከዛ በኋላ እግዚአብሔር እገኛለሁ አለ። የክብሩ መገኘት ምን ይጠይቃል? ጸሎት ብቻ በቂ አይደለም!! በሙሉ ልብ እግዚአብሔርን መፈለግ። እግዚአብሔርን መፈለግ ማለት መጸለይ ማለት አይደለም። መጸለይ ፍለጋችንን የምንገልጥበት ቋንቋ ነው። መፈለግ ማለት ቅድሚያ መስጠት፥ መታዘዝ ፥ ማስበለጥ እና ዋና አላማ እና ግብ ማድረግን የያዘ ነው። ያኔ ብቻ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል። ያን ጊዜ አሳሳቢ የሚሆን ምንም ነገር የለም። እርሱ ሁሉ ይሆነናል። 🤲 እግዚአብሔርም በምድራችን ቤተክርስቲያን ክብሩን ትተን ሌላ ፍለጋ ከሄድንበት ይመልሰን። መመለሱ የሚጠይቀውን ሁሉ አስከፍሎ እሱ እና እሱን ብቻ ወደ ምንፈልግበት ፍቅር ይመልሰን። ሄቨን አርሚ 🍀sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ🍀              ይቀላቀሉን                  🔻🔻          @heavenarmyy          @heavenarmyy          @heavenarmyy                  🔺🔺                   Join
إظهار الكل...
ሰላም የተወደዳችሁ!! በግሩፓችን ላይ ስለ ቆይታችሁ አሁንም መጻፍ ትችላላችሁ። በኮነክሽን ምክንያት የላይቭ አገልግሎቱ ወደ ነገ የተዘዋወረ ሲሆን እናንተ ግን በጽሑፍ ግሩፑ ላይ ማውራት እንደምትችሉ ልንገልጽ እንወዳለን። https://t.me/HeavenArmyBonga ሄቨን አርሚ
إظهار الكل...
👍 3
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.