cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Spiritual beauty

በዚህ channel ለማስተማር እና ለማነሳሳት የሚረዱ አጫጭር ክርስቲያናዊ ታሪኮችን፣ ትንቢታዊ እና መንፈሣዊ መፅሐፍቶችን፣ የተለያዩ መዝሙሮችን ያገኙበታል ::

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
202
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የሰይጣን ቀንበር ሰባኪው «ዛሬም እግዚአብሔር «ወደ እኔ ኑ» የሚለው ቃሉ አልታጠፈም። ለደካሞችና ሸክም ለበዛባቸው ሸክማቸውን ሊጋራ የፍቅር ጥሪውን አብዝቷል። በእርሱ አምነን ወደ መንግሥቱ ብንመጣ ሸክማችን ይወገዳል፤ ይህንን ጥሪ ባንቀበል ግን በሸክማችን ላይ ሌላ የማንችለው ሸክም ይጨመርብናል።» ለሚለው ስብከታቸው በዚህ ምሳሌ አድማጮቻቸውን አስገነዘቡ። «አንድ ተንኮለኛ አህያ ነበረች። ሁልጊዜ ባለቤቷ ጨው ጭኖባት ስትሄድ ወንዝ አካባቢ ስትደርስ ትተኛና ትንፈራገጣለች። በዚህ ጊዜ ውኃ ጭነቱ ውስጥ ይገባና ጨው ሟምቶ ትንሽ ሸክም ይቀልላታል። ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ይህንን በምታደርግበት ጊዜ ባለቤቷ ነቃባትና፤ ጨው የሚጭንባት የነበረችውን ይህችን ተንኮለኛ አህያ አሸዋ ጭኖ ያመላልስባት ጀመር። እርስዋም እንደለመደችው ጭነት ይቀልልኛል ብላ ወንዝ ዳር ሄዳ ውኃው ላይ ስትንፈራገጥ ውኃው ወደ አሸዋው ይገባና ከመቅለል ይልቅ በጣም ከብዶ ለመነሣት ያቅታትና በዚያው ትቀራለች።» አዎ፥ ቀላሉንና የሚጠቅመውን የእግዚአብሔርን ቀንበር አልሸከምም ካልን ሰይጣን የራሱን ቀንበር ያሸክመናልና እንመለስ፣ ለዚህም ደግሞ በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነው አምላክ በጸጋው ያግዘን። አሜን!🙏 «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና።» (ማቴ. 11፡28-29) https://t.me/spiritualbty
إظهار الكل...
2
ነፍሴን ለባለቤቱ ላስረክብ! ሰባኪው «ሕዝቡን የሚጠብቅ እግዚአብሔር ለሕዝቡ በነፍስም በሥጋም ዋስትና አለው። በዚህ ምድር ስንኖር በእርሱ ታምነን ልንወጣና ልንገባ ይገባል። እንዲህ ከሆነ እግዚአብሔር ከጠላታችን እጅ ይታደገናል፥ ከሞትም አፋፍ ቢሆን እንደ ፈቃዱ ያድነናል።» የሚለውን ትምህርት ለማስረዳት የሚከተለውን ምሳሌ ተጠቀሙ። አንድ ቀን ወንበዴዎች «ይህ በሰፈራችን ያለው አማኝ ሰውዬ ሁልጊዜ ደልቶትና ደስ ብሎት ጥሩ ለብሶ፥ ጥሩ በልቶ የሚኖረው ብዙ ሀብት ቢኖረው ነውና እንዝረፈው» ተባባሉ አንድ ቀንም አማኙ አምሽቶ ሲመጣ አሳቻ ቦታ አስቆሙትና «ያለህን አውጣ» ብለው ገንዘቡንና የለበሰውን ልብስ ሁሉ አስወለቁት! መጨረሻ ላይ ሊገድሉት ሲነሡ፥ «ክመግደላችሁ በፊት ነፍሴን ለባለቤቱ ላስረክብ፤ የጸሎት ጊዜ ስጡኝ!» ብሎ ተንበረከከና እጁን ወደ ላይ አድርጎ ሲጸልይ አዩትና ሰዎቹ «ይኽ ሰውዬ በእውነትም ባለቤት ሳይኖረው አይቀርም» አሉና ፈርተው በሩጫ ከአካባቢው ሮጠው ተሰወሩ። እርሱም በጨለማ ራቁቱን ወደ ቤቱ ሄደ። እግዚአብሔርም ከሞት አፋፍ አዳነው። «እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።» [11. (91):3] አዎ፥ በታላቁ እግዚአብሔር ከታመንንና በእርሱ ከተደገፍን እርሱ የነፍሳችንም የሥጋችንም ባለቤት ነው። ከሞትም የሚያድን ጌታ እርሱ ብቻ ነውና ሕይወታችንን ለእርሱ ሰጥተንና በእርሱም ታምነን እንድናልፍ እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን! https://t.me/spiritualbty
إظهار الكل...
👍 2
በእግዚአብሔር ስለመታመን ቋጥኙን ልቀቅ! ሰባኪው «ለሰው ልጆች ሁሉ አምነን እንድንድንበት የተሰጠን የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነውና በእርሱ ብቻ እንመን፤ ሌላ መመኪያና የሕይወት መደገፊያ አይኑረን፤ ለዘላለም አይሆንምና።» የሚለውን ትምህርቱን ለማስጨበጥ የሚከተለውን ምሳሌ ተጠቀመ። አንድ ሰው በሕልሙ ትልቅና ረጅም ገደል ውስጥ ገብቶ አየ። የገደሉ መሐል ላይ ሆኖ አንድ ቋጥኝ ይዟል። ሰውነቱ ሁሉ ውን ውን እያለ ከላይ ረጅሙን ገደል ወርዷል፤ ከበታች ሌላ ረጅም ገደል ይቀረዋል። መሀል ላይ ሆኖ «ጌታ ሆይ፥ አድነኝ፥ ጠፋሁ፥ እርዳኝ!» እያለ ሲጮህ እግዚአብሔር በገደሉ ጫፍ ላይ ብቅ ብሎ ይመስለዋል፥ «እንዳድንህ ትፈልጋለህ?» ይለዋል። «አዎን እፈልጋለሁ» ይላል። «እንግዲያውስ ቋጥኙን ልቀቅ» ሲለው ደነገጠና «እምቢ አለ»። እንዲያውም እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ «ከዚህ የተሻለ አሳብ ያለው ሌላ እግዚአብሔር አለ ወይ?» በኋላ ብንን ሲል በሕልሙ ነው። ወደ ጸሎት ክፍሉ ሄደና ሲጸልይ ከጌታ ጋር የሚያወዳድረው ሌላ የሚመካበት ነገር እንዳለው ገለጠለት። አጎቱ የታወቁ ሀብታም ናቸው፤ የነዳጅ ማደያ ዴፖ አላቸውና ወደ ጌታ ሲጸልይ «ጌታ ሆይ፥ ይህን ይህን ስጠኝ እምቢ ካልከኝ ግን ወደ አጎቴ እሄዳለሁ።» ይል ነበር። ዛሬ ግን ጌታ ከተናገረው በኋላ ግን ሲጸልይ «ጌታ ሆይ፥ ይህን አድርግልኝ፥ እምቢ ካልከኝ ግን ወደ ማን እሄዳለሁ?» ይል ጀመር። «ወደ ማን እንሄዳለን አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ» (ዮሐ. 6:68) አዎ ወገኖቼ፥ ከዘላለም ሞት ወደ ዘላለም ሕይወት የሚያሻግር ጌታ ብቻ ነውና ወደ እርሱ እንምጣ። ለእኛ የሚያስብልን ከእርሱም የተሻለ ሌላ አሳብ ያለው እግዚአብሔር የለምና ከእርሱ ውጭ የምንታመንበትን ሁሉ ትተን ጌታን ብቻ እንድንይዝ እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን! 👇👇ይቀላቀሉን ወዳጆን ይጋብዙ 👈         https://t.me/spiritualbty
إظهار الكل...
👍 1
ጌታ ሆይ፥ ቤታችን እንዳይጠፋህ! ሰባኪው «እግዚአብሔር በስሙ ታምነው የሚለምኑትን ሰዎች ጸሎት ይሰማል እንጂ በቤቱ ውስጥ ብዙ ዘመን ማስቆጠራቸውን፥ ብዙ ጊዜ ጾም ጸሎት መያዛቸውን፥ አስራትና መባ መክፈላቸውንና መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ገብተው ተምረው መመረቃቸውን እንደ ዋና ነገር አድርጎ አይመለከትም። እርሱ ጸሎትን ለመመለስ የሚመለከተው ዋና ነገር እምነትን ነው። ከልባቸው በእርሱ ላይ ታምነው የሚጸልዩትን ሰዎች ጸሎት በእውነት ይሰማል» ለሚለው ስብከታቸው የሚከተለውን ምሳሌ ተጠቀሙ። አንድ አገር ውስጥ ያሉ ሚስዮናውያን ባልና ሚስት አንዲት ምስኪን ሴት ያገኙና «ክርስቶስ ከዘላለም ሞት ያድናል።» ብለው ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ይመሰክሩላታል። እርሷም ይህንን አምና በእውነት ሕይወቷን ለጌታ ትሰጣለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሳምንት በኋላ የምትወደው አንድ ልጇ በጠና ይታመማል። ወደ ሚሲዮናውያኖቹ ትሄድና ባለፈው ስትነግሩኝ ኢየሱስ ያድናል ብላችሁኝ ነበር፥ እኔም አምኜአለሁ፥ ያድናልና ልጄን ሳይሞት ጌታ እንዲያድነው ጸልዩልኝ» ትላለች። እነርሱም «ጌታ የሚያየው እምነትሽን እንጂ አዲስነትሽን አይደለምና አንቺው ጸልዪ ይሰማሻል» ይሏታል። እርሷም «እኔ አዲስ አማኝ ነኝ ጸሎት አልችልም» ትላለች። እነርሱም «አንቺ ጸልዪ ይሰማሻል» ይሏታል። እርሷም «አዲስ አማኝ ስለሆንኩ ጸሎት አልችልም» ትላለች። እነርሱም «ጌታ የሚያየው እምነትሽን እንጂ አዲስነትሽን አይደለምና ጸልዪ» ይሏታል። በዚህ ጊዜ እጇን አንሥታ ዓይኗን ጨፍና ከእነርሱ ጋር እንዲህ በማለት አብራ ጸለየች፥ «ጌታ ሆይ፥ አንተ አዳኝ እንደሆንክ አምናለሁና ልጄን ፈውስልኝ፤ ቤታችንም እንዳይጠፋህ ልንገርህ ከዚህ ካለንበት በስተቀኝ በኩል ባለው መንገድ ቀጥታ ትሄድና ወደ ግራ ትታጠፋለህ፥ ታጥፈህም የምታገኘውን የእንጨት በር አልፈህ ገርበብ ያለውን የቤታችንን በር ቀስ ብለህ ልጄን ሳታስደነግጥ ገብተህ ፈውስልኝ፥ አሜን።» ብላ ጨርሳ ወደ ቤቷ ስትሄድ ልጇ ሮጦ እማዬ ብሎ ተቀበላት። “ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፡- አንተ ልጅ፥ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው።» (ማር. 2፡5) አዎን ጌታ እምነትን ያያል። ወገኖቼ ሆይ፥ ጌታ ሲያየው የሚያስደስተውን እምነት አምላክ ይስጠን። አሜን🙏 👇👇ይቀላቀሉን ወዳጆን ይጋብዙ 👈 https://t.me/spiritualbty
إظهار الكل...
1
የራብ አድማ ሰባኪው በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ሰዎች ሁሉ ስለ ጾም ጸሎት ሲያስተምሩ «በእግዚአብሔር ፊት መጾምና መጸለይ የተገባ ነው። ይህ የሚሰማልን ግን ከቂምና ከቁርሾ ርቀን በልብ ንጽሕናና በቅንነት ሲሆን ነው። በተቃራኒው ግን ወደ ጌታ ብንቀርብ ጾም ሳይሆን የራብ አድማ ነው።» ለሚለው ትምህርታቸው የሚከተለውን ምሳሌ ተጠቀሙ። በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ የጸሎት አገልጋዮች እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲያሳድግ፥ አገራችንን እንዲባርክ፥ በሽታን ከምድራችን ላይ እንዲያጠፋልን፥ ለአንድ ሳምንት የጾም ጸሎት ቀን ይኑረን ብለው ጾም ጸሎት አደረጉ። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በኅብረት በፕሮግራማችን ፍጻሜ ላይ ማዕድ አብረን እንቁረስ በማለት ሁሉም በአንድ ላይ ምግብ ለመብላት ተሰበሰቡ። በዚህ ጊዜ ሁሉም ሁለት ሁለት ሆነው እየበሉ ሳለ ሁለት ወንድሞች ብቻ ከመካከላቸው አይበሉም። አስተናጋጃቸውም «ምን ነው ተጸልዮአል እኮ ለምን አትበሉም?» ቢላቸው እንዲህ አሉት። እኛ እኮ አብረን አንበላም፥ ምክንያቱም ከተኮራረፍንና ከተጣላን ሁለት ወር አልፎናል።» ብለው መለሱለት። «እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን. . .?» (ኢሳ. 58: 5)። ቅዱሳን፥ እርስ በርሳችን ይቅር ሳንባባል በጥልና በኩርፊያ ወደ ጻድቁ አምላክ ፊት በጾም በጸሎት መቅረብ የባሰ ፍርድ ያመጣልና እርስ በርሳችን ይቅር ተባብለንና ተቀባብለን ከእግዚአብሔር ጋር እንድንኖር ፈጣሪ ይርዳን። አሜን! 👇👇ይቀላቀሉን ወዳጆን ይጋብዙ 👇👈 https://t.me/spiritualbty
إظهار الكل...
1
የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዋሳ ይሁን! ሰባኪው «እኛ ሰዎች በዚህ ምድር ስንኖር እኔነት ሊያጠቃን አይገባም። «ከእኔ ይልቅ ለባልንጀራዬ» የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ ሊኖረን ይገባል እንጂ ሁልጊዜ ነፍስ እንዳላወቀ ሕፃን ልጅ ሁሉንም ነገር ለእኔ ለእኔ እያልን የራሳችንን ጥቅም ብቻ ማሳደድ የለብንም። ይህ እግዚአብሔርን ያሳዝነዋልና» ለሚለው ትምህርታቸው ይህንን ምሳሌ ተናገሩ። «ታሪኩ የተፈጸመው አዋሳ ነው። እናትና ልጅ አብረው ተንበርክከው ቤታቸው እየጸለዩ ሳለ ልጁ የሚጸልየው ጸሎት እናቲቱን አስገረማቸውና የራሳቸውን ጸሎት መጸለይ አቁመው እንደተንበረከኩ የልጃቸውን መስማት ጀመሩ። እየደጋገመ በተመስጦ ሆኖ ልጃቸው እንዲህ እያለ ይጸልያል። «ጌታ ሆይ፥ እለምንሃለሁ፤ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዋሳ ይሁን!» መጨረሻ ላይ ጸሎታቸውን ሲጨርሱ እናት ስለ ገረማቸው ጠየቁት። «የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዋሳ ይሁን እያልክ የጸለይከው ለምንድን ነው? አዲስ አበባ እንደሆነ አላወቅክም ወይ?» ቢሉት፥ «ትናንትና የ ስድስተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ላይ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ማን ነው ተብዬ ተጠይቄ አዋሳ ነው ብዬ ስለመለስኩ ራይት እንዳገኝ ነው» አላቸው። “እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥» (ፊልጵ. 2፡4)። ወገኖቼ፥ ሁልጊዜ የራሳችንን ብቻ አንመልከት። የራሳችንን ጥቅም ብቻ ከፈለግን በእውነት ላይ እንስታለን። በቀሪው ዘመናችን ከእኛ ይልቅ የሌሎችን ጥቅም እንድናስቀድም አምላክ ይርዳን። አሜን!
إظهار الكل...
3
የትንሹ ልጅ ጸሎት ሰባኪው «የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ በማጥናትና በማወቅ እንዲሁም በመኖር ከወተት ወደ አጥንት እየበሰልንና እያደግን ልንመላለስ፥ ጌታንም ደስ እያሰኘን ልናድግና የበለጠ ለማወቅ እንጓጓ እንጂ በትንሹ በቃሉ እውቀት ብቻ ካቆምን ምናልባት ልንስት እንችላለን።» የሚለውን ጤናማና አስፈላጊ ትምህርት ለማስረዳት ቀጣዩን ምሳሌ ተጠቀሙ። «አንድ ትንሽ ልጅ ሁልጊዜ በቤቱ ሲኖር የሚጸልየው ለምግብ ብቻ ነው፥ ማለትም ምግብ ሲቀርብ፥ ሁልጊዜ እንዲጸልይ የሚጋበዘውም እርሱ ነው። እርሱም በትንሽ አንደበቱ «ጌታ ሆይ፥ ይህንን ምግብ ስለ ሰጠኸን እናመሰግንሃለን። ላጡትና ለተቸገሩትም የሚበሉትን ምግብ እንድትሰጣቸው እንለምንሃለን።» ብሎ ይጸልያል። ታዲያ አንድ ቀን እናቱ በጠና ታመሙና እርሱም እንዲጸልይ አባቱ ጋበዙት። እርሱም በኮልታፋ አንደበቱ የተለማመደውን ከዚህም የተለየ ሌላ ጸሎት የሌለ የመሰለውን ጸሎት እንዲህ ሲል ጸለየ! «ጌታ ሆይ፥ ይህንን በሽታ ስለ ሰጠኸን እናመሰግንሃለን፥ ላጡትና ለተቸገሩትም እንደ ቸርነትህ እንድትሰጣቸው እንለምንሃለን።» ብሎ አረፈው። አዎ ወገኖቼ ሆይ፥ ዛሬም እኛ በቃሉ ላይ ካለን እውቀት በተጨማሪ የበለጠ ለማወቅ ባለመጣራችን የዱሮዋን ብቻ ይዘን አዲስ ነገር በሕይወታችን ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አንሆንም፤ ከዚህ የተነሣ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ስንጣላ እንገኛለን። ከእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ጌታ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን በጸጋው ይጠብቅ። አሜን!
إظهار الكل...
2👍 1
ወይ ውረድ፥ ወይ ፍረድ ሰባኪው «በራሳችን ለራሳችን ምንም ማድረግ ስለማንችል መጨነቅ የለብንም። ነገሮች ሁሉ ከአቅማችን በላይ የሆኑት ለእኛ ለሰው ልጆች እንጂ ለእግዚአብሔር አምላክ አይደለምና ጭንቀታችንን ወደ እርሱ እንደ ቃሉ እናምጣ፥ ለጌታ የሚሳነው ነገር የለምና።» የሚለውን ስብከታቸውን ለማስጨበጥ የሚከተለውን ምሳሌ ተጠቀሙ። «አንድ በጣም የሚያስጨንቁና የሚያስቸግሩ ባላባት ነበሩ። በትንሽ በትልቁ ከሥራቸው ያሉትን ጭፍሮች ያርበደብዱ ነበር። አንድ ቀንም እንደ ልማዳቸው በሰው ዘንድ ማድረግ የማይቻል ትእዛዝ እንዲህ ሲሉ ለጭሰኛው ሰጡ፥ «በሦስት ቀን ውስጥ ከፊትና ከኋላ ራስ ያለው በቅሎ እፈልጋለሁና እንድታመጣልኝ!» ጭሰኛውም እሺ ብሎ ከየት እንደሚያገኝ ግራ ገብቶት ወደ ቤቱ ሄደና ጭንቀቱን ለባለቤቱ ነገራት። እርሷ እንዲህ ብላ አጽናናችው «አይዞህ፥ ለዚህ ጥያቄ ወይ ባዝራችን ትወልዳለች፥ ወይ እግዚአብሔር ይፈርዳል።» አለችውና አብራው በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ፈጣሪ «ወይ ውረድ፥ ወይ ፍረድ» የሚለውን ጸሎታቸውን ቀጠሉ። በሁለተኛው ቀን ባላባቱ ከፈረስ ወድቆ እንደ ሞተ ሲሰሙ፥ «ባላባቱ ሞተ አትበሉን እግዚአብሔር ፈረደ በሉን እንጂ» ብለው ተናገሩ። «እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።» (1ኛ ጴጥ. 5፡7)። ቅዱሳን፥ ምን ይሆን ከአቅማችን በላይ ሆኖ ያስጨነቀን ነገርና አልገፋ ያለን ተራራ፤ እግዚአብሔር አምላካችን እውነተኛ ፈራጅ ነና ወደ እርሱ በእምነት እናቅርበው። እርሱ በቅን ይፈርድልናል። ይህንንም ሁልጊዜ ማድረግ እንድንችል ጌታ በጸጋው ይደግፈን። አሜን!
إظهار الكل...
👍 3
የድሀው ሰው ጸሎት ሰባኪው «እግዚአብሔር የሰጠንን ንብረት እግዚአብሔር ራሱ በቃ ብሎ እስከሚቀይረው ወይም እስከሚያሳድግልን ድረስ ያለማንጎራጎር ደስ በመሰኘትና ኑሮዬ ይበቃኛል በማለት መኖር አለብን እንጂ ወደፊት ማጉረምረም የለብንም። የሚያስፈልገንን እግዚአብሔር ሰጥቶናል፥ ይሰጠናልም።» የሚለውን ትምህርታቸውን በምሳሌ አስረግጠው እንደሚከተለው አስተማሩ። አንድ ሀብታምና አንድ ድሀ እንዲህ ብለው ጸሎት አደረጉ። ሀብታሙ «ጌታ ሆይ፥ ይህቺ ቮልስዋገን መኪና በጣም ከማርጀቷ የተነሣ ሰዎች ለሠርግና ለተለያዩ ፕሮግራሞች አብሬአቸው እንድሆን አይጋብዙኝምና እባክህን አዲስ ማርቼዲስ መኪና እንድትለውጥልኝ እለምንሃለሁ» አሉ። ድሀው ደግሞ «ጌታ ሆይ፥ ዛሬ እራቴን የምበላው ዳቦ የለኝምና እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ።» አሉ። በዚህ ጊዜ የድሀውን ሰው ጸሎት ሀብታሙ ሰሙና «አንተ አሁን ከእኔ ጋር እኩል ቆመህ የዳቦ ጸሎት ታደርጋለህ፥ ይህንን ትንሽ ጸሎትስ እኔ እመልሰዋለሁ።» አሉና ሁለት ብር አውጥተው ሰጡት። ድሀውም «ጌታዬ፥ ከእርስዎ ጸሎት ይልቅ የእኔ ቀድሞ ተሰምቷልና አመሰግናለሁ» ብሎ ሄደ። «አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።» (ፊልጵ. 4፡19)። አዎ ወገኖቼ ሆይ፥ እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ሰጥቶናል፥ ከዚህ በበለጠ ደግሞ እባርክሃለሁ ብሎ ራሱ በሰጠን ነገር ላይ ረክተንና ተደስተን እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን! እስከሚነሣ ድረስ እርሱ ያለማንጎራጎር እንድንኖር
إظهار الكل...
2
ስለ ጸሎት ለእናቴም ደህና አማች ስጣት ሰባኪው በአንድ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ መልእክት ሲያቀርቡ፥ «እኛን የሰው ልጆች ሁሉ እግዚአብሔር በምድር ላይ ያስቀመጠን እንደ ቃሉ ሁልጊዜ እርሱን እንድናመሰግን እንጂ ስለ ራሳችን እንድንለምን ብቻ አይደለም» በማለት የሚከተለውን ምሳሌ በመጠቀም፥ ሁል ጊዜ አመስጋኞች እንጂ መጸለይ ከጀመርንበት ጊዜ አንሥቶ እስከ መጨረሻ ያለው ጊዜ ሁሉ በልመና ብቻ የተሞላ መሆን የለበትም ሲሉ አስረግጠው ተናገሩ። አንዲት ወጣት ልጃገረድ በጌታ ፊት ሆና የጸሎት ፕሮግራሟን ስትመረምረው ከምስጋና ይልቅ ስለ ራሷ በልመና ብቻ የተሞላ እንደሆነ ተረዳችና ለራሷ እንዲህ ስትል ወሰነች። «ከዚህ በኋላ የጸሎት ጊዜዬን ምስጋና ብቻ ነው የማደርገው እንጂ ስለ ራሴ አንድም አልለምንም» በማለት ጸሎቷን ጀመረች፤ እንዲህ እያለች፥ «ጌታ ሆይ፥ ስለ ቤተሰቦቼ አመሰግንሃለሁ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያኔ አመሰግንሃለሁ፥ ስለ አገሬና መሪዎቹ አመሰግንሃለሁ።» እንዲህ እንዲህ እያለች ቀጠለችና ድንገት ሳታስበው «በል እንግዲህ ጌታ ሆይ፥ ለእናቴም ጥሩ አማች ስጣት» ብላ ስለ ራሷ ለመነች። ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸከም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ። (ገላ. 6፡2)። አዎ ምንም ስለ ራሳችን መጸለይ (መለመን) መልካም ቢሆንም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ ራሳችን በልመና ብቻ ተሞልተን ስለ ሌሎች መጸለይንና ማመስገንን እንዳንረሳ። ድል የሚገኘው በልመና ሳይሆን በምስጋና ነውና ይህን እንድናደርግ እግዚአብሔር በጸጋው ይደግፈን። አሜን!
إظهار الكل...
👍 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.