cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethio ልብወለድ store ™

☞For idea and promotion 👉 @ethiolearning_AD ☞በየቀኑ ተከታታይ ልብወለድ ይለቀቃል ☞ ዘና ፈታ ማለት ከፈለጉ ☞ ልብወለድ ☞ ታሪክ ☞ የድሮና አዳዲስ መፅሐፍቶችን ተወዳጅ ልብወለድይለቀቃል join request ያድርጉ ገባ ..ገባ በሉ ...... 👇👇👇👇👇👇::

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 872
المشتركون
-324 ساعات
-187 أيام
-1130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Repost from Crypto Learning™
Photo unavailableShow in Telegram
Binance Telegram ላይ የራሱን Mine app Launch አድርጎዋል ። Note : Backed By Binance ለመጀመር 👇👇👇 https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_1954465518&startapp=ref_1954465518&utm_medium=web_share_copy
إظهار الكل...
👍 2
‍ 🌺 ምኞቴ🌺 እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛             ▬▬▬❁ክፍል አስራ አንድ▬▬▬ ..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት ረድኤትም ..... "ኤዲዬ አንቺምኮ አምሮብሻል ምን ተገኝቶ ነዉ?" ....."እኔማ የዉበቴም የድምቀቴም ምክንያት ባሌ ነዉ፡፡......" ብላ ስለ ቁርሱ፤ ስለ ወረቀቱ ምንም ሳታስቀር ለረዲ ነገረቻት፡፡ ኤዲና ረድኤት በደንብ ተግባብተዋል፡፡ ብዙ ሚስጥሮችን አብረዉ እየተጋሩ ነዉ፡፡ ረዲ ለኤዲ 'ባልሽን ልቀማሽ ነዉ ተዘጋጂ!" የሚለዉ ሲቀር፡፡ .....ኤዲም "አንቺስ የዚህ ዉበት ምንጭ ማን ይሆን ረዲ?" አለቻት፡፡ ባልሽ ቢኒያም ነዉ አትላት ነገር... እ እ እያለች ስትደናገጥ የረድኤት አባት ከቤት ዉስጥ ወጡና "እንዴት አደርሽ ኤደን" ብለዉ ጨዋታቸዉን አቋረጧቸዉ፡፡ ...... "ደህና አደሩ አባባ" ብላ መለሰችላቸዉ፡፡ አባባ  ትንሽ ቀለድለድ ካደረጉ ቡኃላ ... "ኤዲ" አሏት፡፡ ..."አቤት አባባ" አለቻችዉ፡፡ ..."ኧረ እቺን ጓደኛሽን ምከሪያት እስኪ" ..."ማንን? ረድኤትን?" ስትላቸዉ ..."መቼም በለጡን ምከሪያት አልልሽ የኔ ልጅ" ሲሉ ሁሉም ተሳሳቁ፡፡ አባባ ቀልዳቸዉና ምራቸዉ አያስታዉቅም፡፡ ቁም ነገር እያወሩ በመሃል ይቀልዳሉ፡፡ በቀልዱም መሃል ያመራሉ፡፡ ሁሌም ፀባያቸዉ እንዲህ ነዉ፡፡ ቀጠል አደረጉና.... ..."ባል እየተንጋጋ ይመጣል እሷ ግን አሻፈረኝ አለች፡፡ ሁሌም ልማር ነዉ የምትለዉ፡፡ አግብቶስ ትምህርት የከለከላል እንዴ የኔ ልጅ?" ብለዉ ጠየቋት ኤዲን፡፡ ረድኤት አንዴ ኤዲን፤ አንዴ አባቷን እያየች የሚሉትን ትሰማለች፡፡ ..."አይ አይከለከልም፡፡ እንደዉም ሴት ልጅ በጊዜ ስታገባ ነዉ ጥሩዉ" አለቻቸዉ ..."ተባረኪ የኔ ልጅ" አሏት ደስ ብሏቸዉ "...እንደዉም እንደ ቢኒያም አይነት ባል ፈልጊማ ኤዲ፡፡ ሳልጠይቃት ነዉ የምድራት" ሲሉ ሁሉም ተሳሳቁ፡፡ ረዲ "እሱ እራሱ ቢኒ በመጣ"አለች በዉስጧ፡፡ ..... ጨዋታዉ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ እማማ በለጡም አራተኛ ተጨምረዉ ወሬዉን አድምቀዉታል፡፡ . ቢኒ በንግግሩ ኤዲን እንዳስደሰታት አዉቋል፡፡ ይበልጥ ወደ እሱ እንድትቀርብ ያደረገዉም ዘዴ ነዉ፡፡ ከኤዲ ጋር በተነጋገሩት መሰረት ሁለተኛ ማግባት እንዳለበት ወስነዋል፡፡ ሌላ ሴት ፍለጋ መኳተን አልፈለገም፡፡ እዚሁ እፊቱ በሱ ፍቅር የተራበችዉን ረድኤትን ሊያገባት ነዉ፡፡"ግን... በምን መልኩ? አባቷስ እሺ ብለዉ ይድሩልኝ ይሆን?" እያ ያስብ ጀመር፡፡... . ......"ረዲዬ..." አሏት እማማ በለጡ ልጃቸዉን ..."ወይዬ እማዬ...." ቤት አብረዉ ቁጭ ብለዉ ነበር፡፡ አባባ ስለሌሉ ረድኤትን የሚያዋርባት ምቹ ጊዜ አግኝተዋል እማማ በለጡ፡፡ ... "አባትሽ ሁለት ሚስት እንደነበረዉ ታዉቂያለሽ?" ረድኤትም "ኧረ እማዬ አላዉቅም፡፡" አለች መልሱን ለማሳጠር ያክል፡፡ ምክንያቱም ወደ እሷ ቀስ እያሉ እንደሚመጡ አላጣችዉም፡፡ .... "ይሄዉልሽ የኔ ልጅ! አባትሽ መጀመሪያ ሌላ ሚስት ነበረችዉ..." "ካንቺ በፊት?" ብላ ሊቀጥሉት የነበረዉን ወሬ አቋረጠቻቸዉ፡፡ በዚያም ላይ ደንግጣለች፡፡ረድኤት እስካሁን ድረስ እናቷ የአባቷ ሁለተኛ ሚስት እንደነበረች አታዉቅምና፡፡ ...."አዎ ከኔ በፊት ሌላ ሚስት ነበረችዉ" ...."እና ምን ሆነች ማሚ? ፈቷት ነዉ ወይስ...?" ...."አይ አልፈታትም ነበር፡፡ ሙታ ነዉ ፈጣሪ ነብሷን ይማራትና" አሉ ...."እንዴት?... ለምን?... ማለቴ ...በምን ምክንያት ሞተች            ✎ ክፍል አስራ ሁለት ከ 150 Like በኋላ  ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
إظهار الكل...

👍 21 4
Photo unavailableShow in Telegram
የቅርብ ጊዜዎቹን የ crypto ዜና እና የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎች ለማወቅ ምርጫዎ👇👇 @crypto_learningx @crypto_learningx @crypto_learningx
إظهار الكل...
👍 3
‍ 🌺 ምኞቴ🌺 እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛             ▬▬▬❁ክፍል አስር▬▬▬ .... ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡ እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡ ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ.... "ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡ እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡✍... እማማ ሚረዱ፤ ኮሽታ ሰምተዉ የሚነቁ በአሁኑ አባባል አራዳ የሚባሉ ሴት ናቸዉ፡፡ እስከዛሬም ልጃቸዉን አላጤኗትም እንጂ ቅዠት ከመስማታቸዉ ቀድመዉ ያዉቁባት ነበር፡፡ ይሄዉ አሁን ደግሞ ስሙ ቢላቸዉ በራቸዉ ስር መጥቶ ቢኒያም ልጃቸዉን ረድኤትን እያዋራት ነዉ፡፡ ..... "ቢኒ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላዉቅም፡፡ ግን... ትቸዋለሁ፡፡ ምክንያቱም አንተን ላገኝህ አልችልም፡፡ ኤዲንም ላሳዝናት አልፈልግም፡፡" አለችዉ ረዲ ቢኒም....."ረዲ እሱን ላወራሽ አልነበረም፡፡ በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር አመጣጤ! በይ ደህና ዋይ" ብሏት መልሷን ሳይሰማ ጥሏት ሄደ፡፡ ረድኤት በህይወቷ እንደዚች ሰዓት የተደሰተችበት ቀን የለም፡፡ ደስታ ቢገል ኑሮ ቢኒ "በጣም እንዳማረብሽ ልነግርሽ ነበር አመጣጤ" ካላት በኃላ ትንፋሿ ፀጥ ብሎ ትሞት ነበር፡፡ ከበር እስከሚወጣ በአይኗ ከሸኘችዉ ቡኃላ ከተቀመጠችበት ተነስታ መስተዋት ፍለጋ እየሮጠች ስገባ እናቷ የመስኮቱን መስተዋት ከፍተዉ እንደማፅዳት እያደረጉ ነበር፡፡ ደነገጠች፡፡"እማዬ ስናወራ ሰምታን ይሆን እንዴ?" ብላ አሰበች፡፡ የእናቷ ነገር ደስታዋን እንዳያከስምባት ቶሎ ብላ ወደ መኝታ ክፍሏ መስተዋቱ ፊት ተገተረች፡፡ 'እዉነትም ቆንጆ ነኝ!" ስትል ለራሷ አሰበች፡፡ረዲን በጣም ብዙ ወንዶች ግማሹ ለትዳር፣ ግማሹ ለአዳር፣ ሌላዉ ደግሞ ለፍቅር ጓደኝነት ሲጠይቋት አላማና ኢላማ ያላት ስነ-ስርዓት ያላት ልጅ ስለነበረች ሁሉንም ገፍታ አባራቸዋለች፡፡ ለቁጥር የሚያዳግቱ ብዙ ወንዶች ለዉበቷ ቋምጠዉላታል፤ በጣም ዉብ ነች፡፡ብዙ ሰዎች የቁንጅናዋን ልክ ለመናገር ቃላት ደርድረዋል፡፡ እሷ ... ግን ለጊዜያዊ ስሜት የምትረታ የዋዛ አልነበረችምና አሻፈረኝ ብላለች፡፡ የቢኒ አንዷ ቃል ግን ዉስጧ ገብቷል፡፡ ልትተወዉ የነበረችዉን ሴት እንደገና የልቧን ፍም ጭሮባታል፡፡ "ቢኒንማ አልተወዉም!!" የረዲኤት ዉሳኔ ነበር፡፡ ... ኤዲ ከእንቅልፏ እንደነቃች በባሏ እጅ የተከሸነዉን ጣፋጭ ቁርስ ማጣጣም ይዛለች፡፡ ቁርሷን በልታ ሳጨርስ ተኝታበት ወደነበረዉ አልጋ ዘወር ስትል ከትራሷ ስር ብጣሽ ወረቀት አየች፡፡ አነሳችዉና ስትገልጠዉ "የኔ ፍቅር አፈቅርሻለሁ፡፡ ፈጣሪ ይጠብቅሽ!" የሚል ፅሁፍ አነበበች፡፡ ደስታ ልቧን ፈነቀለዉ፡፡ ቢኒ እዉነትም ፍቅር ነዉ፡፡ ቁርስ ሰርቶ አካሏን ከመጠገኑም በላይ 'አፈቅርሻለሁ' ብሎ የመንፈስ ምግብ ሰጣት፡፡ ባዲስ ንጋት ከቁርስ ጋር ፍቅር መገባት፡፡ኤዲ አዳሯን እንቅልፍ ማጣቷን ሁሉ እረሳችዉ፡፡ በደስታ ተፍነከነከች፤ በሀሴት ጮቤ እረገጠች፡፡ በዚህ ልዩ ጧት፤ በዚህ ልዩ ቀን የጧቷን ፀሐይ ልትሻማ ከቤቷ ወጥታ ለፀሐይ ጀርባዋን ሰጥታ ቁጭ አለች፡፡ ...... ረድኤት ቆንጆ መባሏ ሳያንስ ሌላ ዉበት፤ ሌላ ድምቀት ተላብሳ፤ ንጋቷን በፍቅር አድሳ እሷም እንደ ኤዲ የፀሐይን ሙቀት ልትኮመኩም ወጣች፡፡ ከመዉጣቷ ኤዲን ስላየቻት ወደሷ ሄደች፡፡ ረድኤት ላይ ዉበት ጎልቷል፤ ኤዲ ላይ ደግሞ ደስታ ነግሷል፡፡ ሁለቱም ለጨለማ ድምቀት እንደሆነችዉ ጨረቃ ደምቀዋል፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጡ ቡኃላ ኤዲ፡ ረዲን... ..... "ዛሬ ወደየት ልትሄጂ ነዉ ባክሽ ተሽቀርቅረሻልሳ" አለቻት              ✎ ክፍል አስራ አንድ ከ 150 Like በኋላ  ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
إظهار الكل...
👍 25 6😁 2
Repost from Educational quiz™
Photo unavailableShow in Telegram
💰አብዛኛው ሰው አሁን ላይ በAirdrop በቀላሉ ብዙ ገንዘብ እያገኘ ነዉ✉️ ለምሳሌ በ notcoin እና dogs ብቻ ብዙ ልጆች ብዙ ሺ ብር ሰርተዋል::✔️ 😊So እናንተም online ስትገቡ task ብቻ በመስራት አሪፍ ገንዘብ መስራት ትችላላች✅በቅርቡ list በመሆን ወደ ገንዘብ ሚቀየሩ Airdrops ዉስጥ ከዚህ በታች ያሉትን ዛሬዉኑ መጀመር ትችላላችሁ1️⃣Blum ➡️ START 2️⃣Major ➡️ START 3️⃣Cats ➡️ START 4️⃣X empire ➡️ START 5️⃣Lost dogs➡️ START 📁🌐🟠🟠GOOD LUCK 🙂
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
2017 ራሳችሁን የምትቀይሩበት አመት ያድርግላችሁ እንላለን 🙌❤️ ምንም መጥቶ የእናንተን ህይወት አይቀይርም በደፈናውም ፈጣሪ አለልኝ ብቻ አትበሉ እሱ መንገዱን መርቷችኃል እናንተ ደግሞ የቻላሁትን አድርጉ ። መልካም አዲስ አመት በድጋሚ 🙏❤️
إظهار الكل...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
✅ይሄ ቴሌብር ላይ የመጣ አዲስ ጨዋታ ሲሆን ሁሉንም ፊደሎች ካገኛችሁ እስከ 100ሺ ብር ድረስ ማሸነፍ ትችላላችሁ። ✅ካሉት ውስጥ የማትፈልጉት ፊደል ካለ ለሰዎች መላክ ትችላላችሁ። ✅September 11 ያበቃል። ✅እድላችሁን ማስፋት የምትችሉበትን መንገድ ከታች እንለቃለን።
إظهار الكل...
👍 3
Repost from Crypto Learning™
Photo unavailableShow in Telegram
$CATIZN አስቀድሜ September 30 List እንደሚደረግ ከሳምንት በፊት አሳውቂያቹ ነበር አሁን ከ10 ቀናት አስቀድሞ September 20 በBYBIT Exchange ላይ LIST ይደረጋል። ካልጀመራቹት ሊጠናቀቅ 15 ቀናት ብቻ ነው የቀሩት ከወዲሁ Countdown ጀምረዋል https://t.me/catizenbot/gameapp?startapp=r_1312_15689603 https://t.me/catizenbot/gameapp?startapp=r_1312_15689603
إظهار الكل...
👍 1
✅ አዲስ Air drops ከ Dogs ጋር ተመሳሳይ ነው እንዳያመልጣችሁ 👇👇👇 https://t.me/money_dogs_bot/money_dogs?startapp=6Av7vc4b
إظهار الكل...
👍 5
‍ 🌺 ምኞቴ🌺 እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመልካም ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛             ▬▬▬❁ክፍል ዘጠኝ▬▬▬         ✍.... ኤዲ ለቢኒ ካላት ፍቅር  የተነሳ ስታከብረዉ ወደር የላትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ለሱ ንግግር ቦታ ትሰጣለች፡፡ በእያንዳንዷ ክንዋኔም ላይ የቢኒ ቃል ተቀዳሚ ነዉ፡፡ ... ሁለቱም በእኩል ቅጽበት "እ..." ሲሉ... ኤዲ ቀደም ብላ "ወይዬ ቢኒ ምን ልትለኝ ነበር?" አለችዉ፡፡ ቢኒም "ኤዲዬ የኔ ቆንጆ አንቺ ሁሌም እኔን ታስቀድሚያለሽ፡፡ "የኔ ፍቅር ታዉቃለሃ?" .....  "ምኑን ነዉ የማዉቀዉ ኤዲዬ?" .....  "እኔና አንተ ከተጋባን አራተኛ አመታችን ነዉ፡፡" .....  " እ... በፍቅር ክንፍ አድርገሽኝ ያበድኩልሽ ቀን! ያ ቀን እንዴት ይጠፋኛል ዉዴ!?" .....  "እሱ አይደለም ፍቅሬ" .....  "እና ምንድን ነዉ ....?" .....  "ከተጋባን ቆይተናል ግን እስካሁን...." ...  "ማሬ አታስጨንቂኛ ፕሊስ ንገሪኝ?" .....  "ቢኒ የኔ ዉድ...." ....  "ወይዬ ኤዲ የኔ ቆንጆ! ... ንገሪኛ!" .....  "ልጅ ልወልድልህ አልቻልኩም ቢኒ" ቢኒ በዉስጡ ያለዉን ስሜት ኤዲ አወጣችዉ፡፡ "ሁለታችንም አንድ አይነት ነገር ነበር የምናስበዉ ማለት ነዉ?" አለ በሆዱ፡፡ ትክክለኛ ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ነዉ የሚቀዱት ማለት ይሄኔ ነዉ፡፡ ቢኒ ኤዲን ሊጎዳት አልፈለገም.... ..... "ኤዲዬ ይሄኮ ታዲያ የፈጣሪ ዉሳኔ ነዉ፡፡ ፈጣሪ ባለ ጊዜ ትወልጂ ይሆናል፡፡" አላት፡፡ ..... " አዎ የኔ ፍቅር ፈጣሪ ካለ እወልድ ይሆናል፡፡ ግን ደግሞ አንተ ከኔ በይበልጥ ልጅ ማግኘት፤ ዘርህን መተካት ይኖርብሃልኮ ዉዴ!" ..... "እና ምን ላርግ ዉዴ? ልጅ ከመዉለድ በላይ አንቺ ለኔ እንደምታስፈልጊኝ ታዉቂያለሽ፡፡ ስለዚህ ማሬ...." ፡ ፡ ፡ ረዲኤት ስለ ቢኒ ስታብሰለስል ቆይታ ሲጨንቃት  ጋደም ባለችበት እንቅልፍ ሸለብ አድርጓታል፡፡ እማማ በለጡም የረዲ የሰሞኑን ቅብዥር አላምራቸዉ ቢል ወደ ረዲ የመኝታ ክፍል ገብተዉ ከጎኗ ቁጭ ከማለታቸዉ ነበር ... ረዲ እንደ ቅብዥር ነገር ጀምሯት "ቢኒ እወድሃለሁ" የምትለዉ፡፡ እማማ በለጡ በቆሙበት ደርቀዉ ቀሩ፡፡እስከዛሬ ልጃቸውን ምን እዲህ እንፈሚያደርጋት ገባቸው ቢኒ የኤዲ ባል...እንዴት?... እያሉ ብቻቸውን ያወሩ ጀመር፡፡ ምን ይበሉ? ሊቀሰቅሷት አቃታቸዉና እንደገና መለስ አሉ፡፡ "በአካል ባታገኘዉ እንኳ በህልሟ እስኪ የሷ ይሁን!" እያሉ ይመስላሉ፡፡ እማማ በለጡ በጣም ጥሩ ሴት ናቸዉ፡፡ ልጃቸዉ አንድ ከመሆኗ የተነሳ እንደ እናት ብቻ ሳይሆን እንደ እህትም፣ እንደ ጓደኛም ሆነዉ ነዉ ያሳደጓት፡፡ ረዲን ዛሬ ጫን ያለዉ ይዟት እንጂ አንድም ነገር ከእናቷ ደብቃ አታዉቅም፡፡ አሁን ግን ... የሰዉ ባል አፈቀርኩ ብትል እንኳን ለእናት ለጓደኛም ለመንገር ያሸማቅቃል፡፡ እማማ በለጡ ጉዳቸዉን ሰምተዉ በእጃቸዉ መዳፋ አገጫቸዉን ይዘዉ "ጉድ... ጉድ" እያሉ ከረዲኤት ክፍል ወጡ፡፡ እማማ በለጡ ከመዉጣታቸዉ ረዲኤት ብርግግ ብላ ስትነሳ ፊቷ በላብ ተዉጧል፡፡ በቅብዥሯ "እወድሃለሁ" ስትለዉ የነበረዉ ቢኒያም ከአጠገቧ የለም፡፡ የሞባይሏን ሰአት ስታይ ቢኒ ለስራ የሚወጣበት ሰዓት ደርሷል፡፡ በፍጥነት ተነሳችና ወደ መታጠቢያ ክፍል ሂዳ እጇ ላይ ዉሀ በማድረግ ፊቷት ውሃ ረጨት ረጨት አደረገች፡፡ በሷ ሃሳብ መታጠቧ ነበር፡፡ እየሮጠች ወጣችና በሯ ላይ ቁጭ ብላ እየተቁለጨለጨች የነ ቢኒን ቤት በር በር ታይ ጀመር፡፡ . ....ቢኒ፡ ኤዲ መረበሿን ሲያይ አብሯት እንኳ ባይዉል ቁርስ አብሯት ለመብላት ወስኖ ነበር ማርፈዱ፡፡ ኤዲ ግን... አዳሯን ሙሉ እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ስላደረች ንጋቱ ላይ ለብዙ ቀን እንቅልፍ ያልተኛች በሚመስል መልኩ ለሽሽሽ ብላለች፡፡ ቢኒም ቶሎ እንደማትነሳ ስለተረዳ ቁርሷን ከአጠገቧ አስቀምጦ በብጣሽ ወረቀት "የኔ ቆንጆ አፈቅርሻለሁ!፡፡ ፈጣሪ ይጠብቅሽ" የሚል ፅሁፍ አኑሮ ከመዉጣቱ... በሩ ፊት ለፊት ረዲኤትን አያት፡፡ ከግቢ የመዉጫዉን በር ተወና ወደ ረዲኤት ጠጋ ብሎ "ደህና አደርሽ " ሲላት ረዲኤት አላየችዉም ነበርና ከየት የመጣ የቢኒ ድምፅ ነዉ ብላ ዘወር ስትል በህልሟም በእዉኗም የምታስበዉ ቢኒ አጠገቧ ቁሞላታል፡፡ እንደመሽኮርመም እያደረጋት "ደህና አደርክ ቢኒ እንዴት አደርክ አለችዉ፡፡ ቢኒም "ትናንት ደዉዬልሽ ባትሪ ዘጋብሽ መሰለኝ..." ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ.... "ቢኒ ምን እንደምልህ አላዉቅም..... " እያለች ስታወራዉ፡፡ እማማ በለጡ የቤቱን መስኮት ገርበብ አድርገዉ ንግግራቸዉን እያዳመጡ ነበር፡፡            ✎ ክፍል አስር ከ 130 Like በኋላ  ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።         ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄
إظهار الكل...
👍 40 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.