cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Education

"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደህንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። " ቅዱስ ጎርጎርዮስ "ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ. 2:14

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
8 053
المشتركون
+2724 ساعات
+637 أيام
+98930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሰይጣን የኢዮብን ሀብት ሲያወድምበት ፣ ዐሥር ልጆቹን ሲገድልበት ፣ ጤናውን ሲወስድበት አንድ ነገር ግን አልነካበትም:: ሚስቱን:: ለምን? ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን?  ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?   https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ጠቢቡ "በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው" ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን? https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም:: https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር:: https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings "ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር:: አዎ ሚስት ሕይወት ናት:: እንደ ኢዮብ ሚስት ብትከፋም እንደ ምሳ. 31ዋ ሚስት መልካም ብትሆንም ሕይወት ናት:: ሕይወት ደስታም ኀዘንም አለበት::  "ሕይወት እንዲህ ናት" c'est la vie እንዲል ፈረንሳይ:: ራሱ ኢዮብም "በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?" ብሎአል:: ኢዮ. 7:1 አዳምም አለ :- "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት" "አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መስከረም 2016 ዓ.ም. ሕንድ ውቅያኖስ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
إظهار الكل...
📚ርዕስ:- ሕማማት 📝ደራሲ:- ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 📜ዘውግ፦ ሃይማኖታዊ 📖የገፅ ብዛት:- 460 📅ዓ.ም:- 2010 🔓Password:- @eotc_books_by_pdf ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ! ══════════════════ SHARE and JOIN🙏 👆👆👆JOIN👆👆👆 ══════════════════
إظهار الكل...
ሕማማት_በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ_@eotc_books_by_pdf.pdf42.31 MB
👍 10 2
📚ርዕስ፦አባቶችህን ዕወቅ 📝ደራሲ፦ዲ/ን አቤል ካሳሁን 📜ዘዉግ፦መንፈሳዊ 📖የገጽ ብዛት፦310 📅ዓ.ም፦2012 ማጋራት አይዘንጋ! https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
إظهار الكل...
አባቶችህን ዕወቅ.pdf39.34 MB
👍 13 6
+++ "አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው?" +++ በሕይወትህ ውስጥ በጣም የሚያስፈራህ ነገር ምንድር ነው? ተብለህ ብትጠየቅ ምን ትመልሳለህ? "ሞት" ልትል ትችላለህ። በእርግጥ ላልተዘጋጀን ኃጥአን የሞታችን ቀን መጠየቅን ወደሚወድ አምላክ የምንሄድበት ዕለት በመሆኑ እጅግ የሚያስፈራ ቀን ነው። ይሁን እንጂ ለሰው ከተስፋ ቢስነት በላይ የሚያስፈራው ነገር የለም። ሰው ተስፋውን ያጣ ቀን ሁሉ ነገሩን ያጣል። የሚያየው ሁሉ ትርጉም የለሽ ይሆንበታል። እሳቷ ፀሐይ ጥቁር ዐለት ትመስለዋለች፣ ጣፋጩ ይጎመዝዘዋል፣ የቀናው ይጎረብጠዋል። የመኖር ጉጉቱ ሁሉ ይጠፋል። ተስፋ ስትቆርጥ ሞት ወደ አንተ እስኪመጣ ድረስ አትጠብቅም። አንተ ወደ ሞት ትገሰግሳለህ። ታዲያ ለሰው ልጅ "ተስፋ ከመቁረጥ" በላይ ምን የሚያስፈራ ጠላት ሊኖረው ይችላል? በሰው ሕይወት ውስጥ "ተስፋ" ትልቅ ገፊ ኃይል ነው። ማናቸውንም የዕለት ሥራዎቻችንን የምናከናውነው ባለ ተስፋ ፍጥረት ስለሆንን ነው። ለዚህም ነው መዝሙረኛው "ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች" ሲል የሚዘምረው።(መዝ 16፥9) ደስታም ያለው በተስፋ ውስጥ ነው። ሰው በወደቀ ጊዜ አዝኖ የማይቀረው "እነሣለሁ" ብሎ ተስፋ ስለሚያደርግ ነው። በገጠመው ከባድ ኃዘን የማይሰበረው የተስፋን ምርኩዝ ስለሚይዝ ነው።  ይህ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሊደገፈው የሚገባ የማይሰበር የተስፋ ምርኩዝ ማን ነው? ይህ ሊጠፋ የሚጤሰውን የተስፋ ጥዋፍ እንደ አዲስ የሚያበራው፣ ተቀጥቅጦ የደቀቀውንም የተስፋ ሸንበቆ ጠግኖ ወደ ቀድሞ ማንነቱ የሚያድሰው ኃያል እርሱ ማን ነው? "መድኃኒታችን እግዚአብሔር ተስፋችን ኢየሱስ ክርስቶስ" አይደለምን!!! (1ኛ ጢሞ 1፥1) ክርስቲያኖች በራሳቸው ማስተዋል ወይም በሀብታቸው አይደገፉም። እንደ እነርሱ ተሰባሪ በሆነ ሰው ላይም ተስፋቸውን አያደርጉም። የክርስቲያን ተስፋው "የተስፋ አምላክ" ክርስቶስ ነው።(ሮሜ 15፥13) ክርስቶስን ለምን ተስፋ እናደርጋለን? "ሁሉ በእርሱ ስለሆነ፤ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ የሆነ" ስለሌለ፣ ኃይልና ችሎታ በእጁ ስለሆነ፣ ያጎበጠንን ሸክም አራግፎ ሊያሳርፈን "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሎ ስለ ጠራን፣ ወደ ጠራን አምላክ ቀና እንላለን።(ዮሐ 1፥3፣ 2ኛ ዜና 20፥6፣ ማቴ 11፥28) እርሱን ተስፋ ብናደርግ እንደ ሰው አይለወጥብንም። እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንም።(ኢሳ 46፥4) ነፍሱን እስኪሰጥ ስለወደደን፣ በብዙ ሕማም በእጁ መዳፍ ላይ ስለቀረጸን ፍቅሩ ቀዝቅዞ ጨርሶ ሊረሳን አይችልም።(ኢሳ 49፥16) በቸገረህ ጊዜ ብርና ወርቅ የለኝም ብለህ ተስፋ አትቁረጥ። "ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል"።(ኢዮ 22፥25) ስትታመምም "ማን ይረዳኛል?" አትበል። እግዚአብሔር በሕመም አልጋ ሳለህ ይረዳሃል። በበሽታህም ጊዜ አልጋህን እያነጠፈ ይንከባከብሃል።(መዝ 41፥3) እርሱ ካልተውከው አይተውህም፣ ካልሸሸኸው ከአንተ አይርቅም። ተስፋ ቆርጠህ ከሕይወትህ ካላስወጣኸው አንተን መፈለግ አይደክመውም። ሰይጣን በአንድ ኃጢአት ደጋግሞ በጣለህ ጊዜም ፈጥነህ ተስፋ አትቁረጥ። የፈጣሪህንም መሐሪነት አትጠራጠር። ለጠላትህም እንዲህ በቀላሉ እጅ አትስጥ። ስለዚህ ነገር በገነተ አበው (Paradise of fathers) የተጻፈን ታሪክ እስኪ  እናስታውስ። ሰይጣን በተመሳሳይ ኃጢአት  ብዙ ጊዜ እያሰነካከለ የሚጥለው አንድ መነኩሴ ነበር። ታዲያ ይህ መነኩሴ ሁል ጊዜ በአንድ ኃጢአት እየደጋገመ መውደቁ ቢያሳዝነውም፣ መልሶ ንስሐ እየገባ ፈጣሪውን "አውጣኝ" ብሎ መማጸን ግን አላቆመም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን መነኩሴው ቆሞ መዝሙረ ዳዊት ሲጸልይ ሳለ ድንገት ሰይጣን ወደ እርሱ መጣና:- "ፊቱ ቆመህ በእነዚህ ንጹሕ ባልሆኑ ከንፈሮችህ የእግዚአብሔርን ስም ስትጠራ አታፍርም?" አለው። ያም መነኩሴ "አንተ እኔን ጨክነህ ታሰናክላለህ። እኔ ደግሞ መሐሪውን አምላክ እንዲያዝንልኝ ሳላቋርጥ እለምነዋለሁ። እስኪ ከአንተ ጭካኔ እና ከአምላክ ምሕረት የቱ እንደሚበልጥ እናያለን።" ሲል መለሰለት። ሰይጣንም የመነኩሴውን ተስፋ አለመቁረጥ ባየ ጊዜ ከእርሱ ሸሽቶ ሄደ። የፈተና ማዕበል በሚበዛባት በዚህች ዓለም ስንኖር፣ ዐውሎና ወጀቡ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን መልሕቃችንን የምንጥልበት የተስፋ መሬታችን አምላካችን እግዚአብሔር ነው። "ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመ ቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ" "ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ አባቶቻችን አልነገሩንም። እኛም አልሰማንም፤ አላየንምም!" "አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?    ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።"                                               መዝ 39፥7 ዲያቆን አቤል ካሳሁን https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
إظهار الكل...
👍 22🥰 4🕊 3 1
+++ የይሁዳ እግሮች +++     ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመሥጠት ከአይሁድ ጋር የተስማማው ረቡዕ ዕለት ነበር፡፡ ይህን ስምምነት አድርጎ እንደጨረሰ ወደ ጌታና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ማኅበር ተመለሰ፡፡ ከረቡዕ ጀምሮ እስከ ሐሙስ ማታ ድረስም ከጌታ ፊት ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ አሳለፈ፡፡ ይህ በትክክል ይሁዳ ምን ዓይነት አስመሳይና ክፉ ሰው እንደነበረ ያሳያል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁኔታዎች አስፈርተውት ጌታውን ለሦስተኛ ጊዜ አላውቀውም ብሎ ከካደ በኋላ ጌታችን ለአንድ አፍታ ቀና ብሎ ስለተመለከተው ብቻ የጌታውን ፊት በድፍረት ለመመልከት አቅም አጥቶ መራራ ልቅሶን እያለቀሰ ከአጥር ውጪ ወጥቶ ነበር፡፡ ይሁዳ ግን አሳልፎ ሊሠጠው ከተስማማባት ሰዓት ጀምሮ ድምፁን አጥፍቶ ከጌታችን ጋር እንደ ወትሮው አብሮ ሲቀመጥ አንድ ጊዜ እንኳን አልተሸማቀቀም፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ልብ አድርጉ! በራሱ ሃሳብ አመንጪነት ፣ ራሱ ወደ አይሁድ ሸንጎ ሔዶ ፣ ብር ለመቀበል ተስፋ ተቀብሎ ከመጣ በኋላም የጌታችንን ዓይኑን እያየ ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› ብሎ ለመጠየቅም ድፍረት ነበረው! በዚያች ሰዓት እንደ ዳታንና አቤሮን መሬት ተሰንጥቃ ስላልዋጠችው ፣ ምላሱ ከጉሮሮው ጋር ስላልተጣበቀ ፣ በድፍረትና በመናቅ በእውነተኛው ጌታ ላይ የተናገሩት የሽንገላ ከንፈሮቹ ዲዳ ባለመሆናቸው የፈጣሪን ትዕግሥቱን እናደንቃለን፡፡ ሁሉን የሚያውቀው ጌታ ግን ይሁዳ ሊሸነግለው መሞከሩን ቢያውቅም ‹አንተ አስመሳይ!› ብሎ አላዋረደውም፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     የእግዚአብሔር ነቢይ ኤልሳዕ ሎሌው ግያዝ የማይገባውን ገንዘብ ከለምጹ ከነጻው ከሶርያዊው ንዕማን ተቀብሎ ቤቱ ወስዶ ከሸሸገ በኋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ከፊቱ መጥቶ ሲቆም ‹ግያዝ ሆይ ከወዴት መጣህ?› ብሎ ጠይቆት ነበረ፡፡ ግያዝም ‹‹እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሔድሁም›› አለ፡፡ ኤልሳዕም ፡- ‹‹ልቤ ከአንተ ጋር አልሔደምን?›› ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ይጣበቃል ብሎ ረግሞት እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ወጣ፡፡ (፪ነገሥ. ፭፥፳‐፳፯) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ሐዋርያው ጴጥሮስም ሐናንያና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስት ገንዘባቸውን ከቤታቸው ሸሽገው መንፈስ ቅዱስን ሊያታልሉና በማስመሰል በፊቱ ሊቆሙ ሲሞክሩ ‹እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሻችሁም› ብሎ በካህን ቃሉ ተናግሮ ተቀሥፈው እንዲሞቱ አድርጓቸዋል፡፡ (ሐዋ. ፭፥፩-፲) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     የነቢያትና የሐዋርያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኤልሳዕና ከጴጥሮስ በላይ የልብን የሚያውቅና መቅጣት የሚቻለው ነው፡፡ ሆኖም ከአይሁድ ጋር ሊሸጠው ተዋውሎ የመጣው ይሁዳ ዓይኑን በጨው አጥቦ  ‹አሳልፌ የምሠጥህ እኔ እሆንን?› እያለ ሲዘብትበት በታላቅ ትዕግሥት ዝም አለው፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን ሊያታልሉ የሞከሩ ሰዎች እንዲህ ከተቀጡ የነቢያትን አምላክ ሊያታልል የሞከረ ‹‹…እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?›› (ዕብ. ፲፥፳፱)    https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ከሁሉም ልብ የሚሰብረው ሐሙስ ምሽት የሆነው ነገር ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ›› የእግር ሹራብ በማይደረግበትና ክፍት ጫማ በሚደረግበት በዚያ ዘመን ቀኑን ሙሉ ሲጓዙ የዋሉበትን የሐዋርያቱን በአቧራ ያደፉ እግሮች ሊያጥብ ተነሣ፡፡ (ዮሐ.፲፫፥፬) በእስራኤል ባህል እግር ማጠብ የሎሌዎች ሥራ ቢሆንም የሰማይና የምድር ንጉሥ ግን በትሕትና እንደ ሎሌ ሆነ፡፡ (፩ሳሙ. ፳፭፥፵፩) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ጌታችን አጎንብሶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ ይሁዳም ሊታጠብ ተራውን ይጠብቅ ነበር፡፡ ጌታውን ሊሸጥ በተስማማበት ማግሥት ጌታችን አጎንብሶ እግሩን አጠበው፡፡ ‹‹ወኀፀበ እግረ ይሁዳ አስቆሮታዊ ዘያገብኦ›› ‹‹የሚያስይዘውን የአስቆሮቱ የይሁዳንም እግር አጠበ›› እንዲል (ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ከአንድ ቀን በፊት ክፋትን ለማሴር ወደ አይሁድ ካህናት ግቢ የሮጡትን የይሁዳን እግሮች ጌታችን አጎንብሶ አጠባቸው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሊያስይዘው ወደ አይሁድ የሚሮጥባቸውን እግሮች ፣ የሚይዙትን ወታደሮች እየመራ ወደ እርሱ የሚመለስባቸውን እግሮች አጠበለት፡፡ ምንም እንኳን በነገው ዕለት እግሮቹን እንዲቸነከር አሳልፎ የሠጠው መሆኑን ቢያውቅም ሰውን ወዳጁ ክርስቶስ ግን የአስቆሮቱ ይሁዳን ለመጨረሻ ጊዜ እግሩን አጥቦ ተሰናበተው፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     እንደ ነቢዩ ዳዊት ‹‹አቤቱ፥ ምሕረትህን እንዴት አበዛህ!›› ከማለት በቀር በምን አንደበት ልንናገር እንችላለን? (መዝ. ፴፮፥፯) ‹‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ›› ያለን ጌታ አሳልፎ የሚሠጠውን የይሁዳን እግር ሲያጥብ ከማየትስ በላይ በቂም በቀል ለሚቆስለው ልባችን ምን መድኃኒት ይኖር ይሆን? https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ይሁዳ ሆይ እስቲ አንድ ጊዜ ንገረን ፤ ጌታ አጎንብሶ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት አስቻለህ? ‹እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ› የሚሰገድለት አምላክ እግርህን ሲያጥብህ እንዴት ትንሽ እንኳን አልተሰማህም? አንተ እግሩን ልታጥበው እንኳን የማይገባህ ፈጣሪ እግርህን ሲያጥብህ እያየህ እንዴት ልብህ ደነደነ? መጥምቁ ዮሐንስ ‹የጫማውን ጠፍር ልፈታ አይገባኝም› ያለው ጌታ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት ልብህ በጸጸት አልተሰበረም? ረቡዕ አሳልፈህ ልትሠጠው ተስማምተህ መጥተህ ሐሙስ አጎንብሶ ሲያጥብህ እንዴት አልጨነቀህም? ከአይሁድ ጋር የተስማማኸው ነገር ‹ይቅርብኝ› ለማለት ጌታችን ከእግርህ በታች ዝቅ ብሎ ካጠበህ ሰዓት የተሻለ ማሰቢያ ጊዜ ከየት ይገኛል? በፍቅሩ ውስጥ ክፋትህ ፣ በትሕትናው ውስጥ ትዕቢትህ እንዴት አልታየህም? እንዴትስ እግሮችህን ሠጥተህ ያለ አሳብ ታጠብህ? https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings     ቅዱስ ጴጥሮስ እንኳን ‹‹ጌታ ሆይ አንተ [እንዴት] የእኔን እግር ታጥባለህ?› ብሎ ተጨንቆ ጠይቆ ነበር፡፡ ‹የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም›  ብሎ ተከላክሎም ነበር፡፡ ልበ ደንዳናው ይሁዳ ግን ዝም ብሎ እግሮቹን ሠጠ፡፡ የከዳውን ጌታ የቁልቁል እየተመለከተ ለአፍታ እንኳን ልቡ አልተመለሰም፡፡ ሐዋርያት ጌታ ባጠበው እግራቸው ለጊዜው ፈርተው ቢሮጡም በኋላ ግን በጸጸት ተመለሱበት፡፡ በአምላክ እጅ በታጠበ እግራቸው ያለመሰልቸት ዓለምን ዞረው ወንጌሉን አስተምረው እስከሞት ድረስ ታመኑ፡፡ በእግራቸውም እንደ ስማቸው ሐዋርያት (ተጓዦች) ሆኑበት፡፡ ይሁዳ ግን በአምላክ እጅ በታጠበው እግሩ ወደ አይሁድ ገስግሶ ጌታ ለሚያንገላታው ጦር መንገድ እየመራበት ተመለሰ፡፡
إظهار الكل...
👍 7
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ‹‹ኦ እግዚኦ ዘኢትደፈር ይሁዳ ደፈረከ›› ‹‹አቤቱ የማትደፈር አንተን ደፋር ይሁዳ ደፈረህ!››                (ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ ፩፥፳፩) ("ሕማማት" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
إظهار الكل...
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Education

"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደህንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። " ቅዱስ ጎርጎርዮስ "ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ. 2:14

5🥰 5👍 4
إظهار الكل...
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Education

Boost this channel to help it unlock additional features.

+ ለንስሓ የሚቀሰቅስ ዶሮ +          🐓🐓🐓🐓🐓 ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?     በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡      ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "ሕማማት" https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
إظهار الكل...
21👍 6❤‍🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከጠርሙሱ ስእሉን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም ይነሳ!!! *** በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም እና ስእል አድኖ ተጠቅሞ ለአሉታዊ የዓለማዊ ንግድ እየተጠቀመ የሚገኘውን BGI ስእሉን ከጠርሙሱ ያነሳ ዘንድ ካለፈው ወቅቶች የተሻለ ዘመቻ ተከፍቷል https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ይበል የሚያሰኝ ነው። በቀጣይም የጠቅላይ ቤተክህነት የህግ ክፍል የእዚህ ዘመቻ አካል በመሆን የሳይበር ዘመቻውን ወደ በጎ ፍሬ ያሳድጉታል የሚል ተስፋ አለኝ። https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings በእዚህ ጉዳይ ጣታችንን ወደ እኛ ስንቀስር ደግሞ ከBGI በላይ በሰማዕቱ ስም የተሳለቅነው እና ስእል አድኖው ላይ የቀለድን እኛው "የሰማዕቱ በረከት ይደርብን " የምንለው ልጆቹ ነን። https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ፋብሪካው ዓመታዊ ትርፉ እያካበተ እንዲሰፋ ያደረግነው እነማን ሆነን ነው ? የሰማዕቱን ጽዋውንም ቢራውንም በአንድ ምላሳችን የምንቀምሰው እነማን ሆንን እና ነው? https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings በቤታችን ለስርዓተ አምልኮ የምንጠቀመው ስእል አድኖን ከቢራ ጠርሙስ ላይ እየተመለከትን በዝምታ BGI የተባባሩ እጄታዎች የማን ሆነ እና ነው? ወዳጄ...እግር ካልተንቀሳቀሰ አይራመድም ። ቆመን አራምዱን ብለን መለመን አይቻልም። አለመጠጣት ሰማዕቱን ብቻ ሳይሆን እኛንም ያስከብራል። https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ይነሳ ስእሉ ከጠርሙሱ ከሚል ቃል በፊት ልባችን ከጠርሙስ ብናነሳው ሁሉም ነገር ይዘጋል። https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings Kune Demelash kassaye -Arba Minch
إظهار الكل...
👍 56💯 15 12🥰 4
+  አትክልተኛ መስሏት ነበር + መግደላዊት ማርያም በዕለተ እሑድ ገና ጨለማ ሳለ ወደ ጌታ መቃብር ልትሔድ ተነሣች፡፡ እርግጥ ነው በጨለማ መውጣት ያውም ለሴት ልጅ የሚያስፈራት ቢሆንም ለዚህች ቅድስት ግን ከክርስቶስ ሞት በላይ ሌላ ጨለማ ገዝፎ ሊታያት አልቻለም፡፡ የሕይወትዋ ብርሃን በመቃብር ውስጥ አድሮአልና ሌላ ብርሃን ነግቶ መንገድ እንዲያሳያት አልጠበቀችም፡፡ ለሰው ሁሉ የሚያበራውን መብራት ክርስቶስን ከመቃብር ዕንቅብ በታች ካኖሩት ሦስት ቀን መሆኑ እንጂ የቀንና ሌሊቱ ልዩነት አልታወቃትም፡፡ በእርግጥም ሰባት አጋንንት ከላይዋ ላይ አውጥቶላት የነበረችን ሴት የቱ ጨለማ የቱ ጋኔን ሊያስፈራት ይችላል? ‹‹ፍቅር ፍጹም ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል››ና ጨለማውን ሳትፈራ ይህች ሴት እስኪነጋ ልቆይ ሳትል ወደ ጌታችን መቃብር ገሰገሰች፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings እንደጠበቀችው ግን ጌታችንን በመቃብር አላገኘችውም፡፡ በዚያ የለም፡፡ በመቃብር አለመገኘቱ ለእርስዋም ሆነ ለደቀ መዛሙርቱ ተስፋ የሚያስቆርጥ ኀዘን ላይ የሚጥላቸው ነገር ሆነ እንጂ ‹‹እነሣለሁ›› ማለቱን እንዲያስታውሱ ምክንያት አልሆናቸውም፡፡ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን እንኳን ጲላጦስ ፊት ቀርበው ‹‹ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፡- ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን›› ብለው ነበር፡፡ (ማቴ. 27፡63) ሐዋርያቱና ማርያም መግደላዊት ግን መቃብሩ ባዶ ሆኖ ሲያዩ እንኳን ‹እነሣለሁ› እንዳለ ትዝ አላላቸውም፡፡ ስለዚህ የእምነት ጉድለታቸውም ደቀ መዛሙርቱን ‹‹እናንተ የማታስተውሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ›› ብሎ ፤ እርስዋን ደግሞ ‹‹አትንኪኝ›› ብሎ ገሠፆአቸዋል፡፡ (ሉቃ. 24፡25፣ ዮሐ. 20፡ 17) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings መግደላዊትዋ ጌታችንን በመቃብር ብታጣውም ‹በዚህ ከሌለማ ወደ ቤቴ ልሒድና ልረፍ› ከማለት ይልቅ በዚያው ቆማ ታለቅስ ጀመር፡፡ ከዚህ በኋላ በዕንባ በፈዘዙ ዓይኖችዋ ሁለት መላእክት ከመቃብሩ ግራና ቀኝ ሆነው ተቀምጠው አየች፡፡ ሳታስተውልም ‹‹ጌታዬን ወስደውታል›› አለቻቸው፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳብራራው) መላእክቱ ወደ ውጪ ሲያዩ ዓይናቸውን ተከትላ ዘወር ስትል ጌታችንን ቆሞ አየችው፡፡ ሆኖም አላወቀችውም፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ‹‹ኢየሱስም አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት፡፡ እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሏት ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› (ዮሐ. 20፡15) https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ይህንን ተከትሎ ጌታችን ስላለማመንዋ ገሥፆአት ማንነቱን ገለጸላት፡፡ በዚህም ይህች ቅድስት ትንሣኤውን ከሰበኩ የጽዮን ልጆች አንዲትዋ ሆነች፡፡ የእስራኤልን ነጻ መውጣት የሙሴ እኅት ማርያም በከበሮ እንዳበሠረች ማርያምም የሰው ልጅን ነጻ መውጣት ያለ ከበሮ አወጀች፡፡ እርስዋን ብቻም ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም ዓርብ ዕለት እያለቀሱ ደረት እየመቱ ሞቱን በዕንባ አጅበዋልና እሑድ ዕለት የትንሣኤው ዜና አብሣሪዎች ለመሆን አበቃቸው፡፡ ሴት ልጅን ‹‹ደስ ይበልሽ›› በማለት የተጀመረው የአምላክ የማዳን ሥራም ሴት ልጅ ራስዋ ለሌሎች ‹‹ደስ ይበላችሁ›› ባይ እንድትሆን በማድረግ ተጠናቀቀ፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ማርያም መግደላዊት  ‹‹የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበርና ፡- ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው›› የሚለው ንግግር እንዲሁ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ቃል የተናገረችው ሳታውቀው ቢሆንም ንግግርዋ ግን ከስኅተትነቱ ይልቅ ቅኔነቱ የሚበልጥ ንግግር ነው፡፡ ‹‹አትክልተኛ መስሏት ነበር›› የሚለው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው? አበው በትንቢተ ሕዝቅኤል 44ን ሲተረጉሙ ‹ከእውነት የሚሻል ስኅተት ከመግደል የሚሻል መሳት አለና›› ያሉት ይህንን ዓይነቱን ሳይሆን አይቀርም፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ለመግደላዊት ማርያም ክርስቶስ አትክልተኛ መስሏት ነበር፡፡ ወይ ግሩም! ክርስቶስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ ለሰዎች ‹ያልመሰላቸው› ምን ነገር አለ? እንደተወለደ ለአይሁድ ‹የዮሴፍ ልጅ መስሏቸው ነበር› ፣ ለሔሮድስ ደግሞ መንግሥቱን የሚቀናቀን ምድራዊ ንጉሥ መስሎት ነበር፡፡ ለኒቆዲሞስ ነቢይ መስሎት ነበር ፣ ለሳምራዊቷ ሴት ደግሞ መጀመሪያ ውኃ የሚለምን ተራ ሰው መሰላት ፣ በኋላ ደግሞ ነቢይ መስሎ ታይቷት ነበር፡፡ ክርስቶስ ለብዙዎ ያልመሰላቸው ምን አለ? ለግማሹ ኤልያስ ፣ ለአንዳንዱ ሙሴ ለሌላው ኢያሱ መሰለው፡፡ ለኤማሁስ ተጓዦች ‹መንገደኛ› ፣ ለሮም ወታደሮች ‹ወንጀለኛ› ፣ ለሔሮድስ መኳንንት ‹አስማተኛ› መስሏቸው ነበር፡፡ እኛ እርሱን እንድንመስል እርሱ እያንዳንዳችንን መስሎ ተሰደበ ተወቀሰ በመከራ ተሰቅሎ ሞተ፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመግደላዊት ማርያም ‹‹አትክልተኛ›› መሰላት፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings ማርያም ሆይ በአንድ በኩልስ ልክ ብለሻል፡፡ ያየሽው እርሱ አትክልተኛ ነው፡፡ በእውነትስ አትክልተኛ ካልሆነ ‹‹አዳም ሆይ ወዴት ነህ›› እያለ በገነት ዛፎች መካከል ምን አመላለሰው? አንቺ አልተሳሳትሽም ‹‹ወይንን ተከልሁ አላፈራም ፣ ለወይኔ ያላደረግሁት ምን አለ? በእኔና በወይኔ መካከል ፍረዱ›› ብሎ የጠራን እርሱ አይደለምን? ‹‹ዘር ዘሪ ሊዘራ ወጣ ፣ ዘር ዘሪው እኔ ነኝ ፤ አጫጆቹ መላእክት ናቸው›› ብሎ በምሳሌ ያስተማረ እርሱ አይደለምን? ከዚህ በላይ አትክልተኛ ከየት ሊመጣ? ‹የወይን ሥፍራን ነበረችው ቅጥርም ቀጠረላት› በተባለችዋ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁላችንን ከአብ ጋር ላንነቀል የተከለን ፣ የጎኑን ውኃ እያጠጣን ፣ በመስቀሉ እየኮተኮተ የሚያሳድገን ‹‹ጳውሎስ ሲተክል አጵሎስ ሲያጠጣ ጌታ ያሳድግ ነበረ›› የተባለለት አትክልተኛ እርሱ አይደለምን? ሦስት ዓመት ተመላልሶ ፍሬ እያጣብን አዘነ እንጂ ፣ እሾኽና አሜከላ እያበቀልን አስመረርነው እንጂ እርሱስ ብርቱ አትክልተኛ ነበር ፤ ስለዚህ መግደላዊት ማርያም ሆይ አትክልተኛ ቢመስልሽም አልተሳሳትሽም፡፡ https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings      ‹‹ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ›› የሚለው ጥያቄም ቢሆን ከእውነታው አንጻር እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ጌታን በእርግጥ ከመቃብር ማን ወሰደው? ማንስ አስነሣው? ራሱ አይደለምን፡፡ ማርያም ‹አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርከው ንገረኝ› አለችው፡፡ ማርያም ሆይ ጥያቄሽ ተገቢ ነው ፤ ብቻ አጥብቀሽ ጠይቂው ፤ የወሰደው እርሱ ራሱ ነው፡፡ ሥጋውን ከመቃብር ሕያው አድርጎ ነስነሥቶ የወሰደው ከፊትሽ ቆሟል፡፡ ማስረጃ ከፈለግሽ ‹‹ነፍሴን ደግሞ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ፤ ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ›› ብሎ ሲናገር ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ሰምቶ ማስረጃ መዝግቦ ይዞበታል፡፡ አጥብቀሽ ያዢው! እንዳትለቂው! በፈቃዱ እንደሞተ ነፍሱንም ሊያኖራት ሥልጣን ያለው ከመቃብርም በሥልጣኑ የተነሣው እርሱ ነው፡፡ ማንም ወሰደው ሲሉ ብትሰሚ አትመኚ ፤ ኢየሱስን ከሙታን መካከል ወስዶ ሕያው ያደረገው ይኸው ከፊትሽ
إظهار الكل...
16👍 4
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.