cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ስለ ቀልባችን

«ስለ ቀልባችን…» •የዚህ ቻናል ዓላማ፦የልብ ድርቀት ለመቋቋምም ሆነ ለማከም ሰበብ ይሆን ዘንድ አላህ ያገራልንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከ ቁርኣን እና ከሀድስ መድሐኒቱን ለመጠቆም ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
7 644
المشتركون
-324 ساعات
+2397 أيام
+52430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

•ጊዜው ወደ ሀራም ለመድረስ በጣም ቀላል ከሆነ አላህን መፍራቱ በጣም ትልቅ ምንዳን ያስገኛል። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
إظهار الكل...
👍 102😢 13👌 3
ያ ረብ! •መረጋጋትንና እርካታን ፍለጋ ብዙ መንገድ ተጓዝን ነገር ግን አንተ ዘንድ ብቻ እንጂ አላገኘናቸውምና እባክህን ወደ አንተ ጥሩ አመላለስን መልሰን። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
إظهار الكل...
👍 114😢 17
• ቀልብ .... 🎙ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጁ = t.me/Muhammedsirage
إظهار الكل...
ቀልብ.mp32.34 MB
👍 25
AUDIO-2020-12-29-19-05-27.m4a6.62 KB
👌 60👍 37🕊 7
•አላህን ስታምፀው ሁሉም ነገር አንተን ሲወቅስህ ታገኘዋለህ‥ መልእክት ሁሉ ላንተ የተላኩ ይመስልሃል፣ ሁሉም የቁርአን አንቀፆች አንተ ላይ የሚነበቡ ይመስልሃል፣ የሆነ ነገር ሲከሰት ስታይ ትፈራለህ።ይህ ሁሉ ስሜት  አላህ ከእርሱ ሸሽተህ ወዴትም እንዳትሄድ ብሎ ነው። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
إظهار الكل...
👍 103😢 27🕊 5👌 3
በጥበቡ አንድን በር ይዘጋና፤በእዝነቱ ሺህ በርን ይከፍትልሃል። የኔ ጌታ…
إظهار الكل...
👍 191🕊 8👌 5
ኸልዋ! ~ ኸልዋ ውስጣችንን ለማዳመጥና ለራሳችን ጊዜ ለመስጠት ከምንጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ነው። ራሳችንን ለማደስ፣ ድክመታችንን ለማረምና የበለጠ ለመጠንከር እንጠቀምበታለን። አንዳንድ ጊዜ በዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ ብቻ እንጂ ሊመለሱ የማይመለሱ ጥያቄዎች ይኖሩናል። ተገልለን ከራሳችን ጋር ስናወራ፣ ራሳችንን ስንገመግም፣ ከራሳችን ጋር ብቻ ለብቻ ስንሆን፣ ውስጣችንን ስናዳምጥ ጥያቄዎቹ ይመለሱልናል። ...የዱንያ ሕይወት ትሠለቻለች። የሰው ልጅ በአንድ ነገርና ስሜት ላይ አይረጋም። ስሜታችን እንደ አየር ፀባይ ሁሉ ተለዋዋጭ ነው። ብቸኝነት ሲበዛ ከሰው መቀላቀል... ከሰው መቀላቀል ሲበዛ ብቸኝነትን መምረጥ፣ በጥሩ መንፈስ ለመቆየት አንዱ የኑሮ ስልት ነው። ስለዚህ አንዳንዴ ኸልዋ ግድ ነው። ኸልዋ የተመስጦ ዓለም ነው። ወደ ሰማዩ ዓለም ከፍ ለማለት፣ ወደፊት ለመንደርደር እና ለመስፈንጠር ተጨማሪ ኃይል እና ጉልበት ነው። ኸልዋ ለዚክር፣ ለዒባዳ እና ተገልሎ ወደ አላህ (ሱ.ወ.) ለማልቀስ ብቻ አይደለም አስፈላጊነቱ። በዱንያ ሩጫዎች መሃል ቆሞ ብሎ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅና ራስን ለመገምገም፤ ከግምገማ በኋላም ጥሩ ውጤት ይዞ ለመውጣት ኸልዋ አስፈላጊ ነው። ከአላህ ጋር ተገልለው ለብቻ ሲሆኑ፤ ኸልዋ መደበቅ ሳይሆን ጎልቶ መታየት ነው፤ መጥፋት ሳይሆን መኖር ነው፤ መራቅ ሳይሆን ወደ አላህ መቅረብ ነው። ጌታዬ ሆይ! እየኝ እዚህ ነኝ ማለት ነው። ለሐኪም እንደሚደረገውና ሁሉ ነገር በግልጽ እንደሚነገረው፤ አልትራሳውንድ ፊት በሽታን ለመፈተሽ ራቁት እንደሚቀረበው ሁሉ፣ አላህ ፊት በመቅረብ ሁሉን ገላልጦ ማሳያ ቦታ ነው -ኸልዋ። በኸልዋ ጎጆ ውስጥ  አንድም ነገር ሳይቀር ለአላህ ይነገራል። ዱዓ በችግር ጊዜ ብቻ የምንናገርበት መድረክ፣ ጥቅምን ብቻ የምናሳድድበት ነፃ መስመር አይደለም። ከልብ የሆነ ዱዓ ሲደረግ በይድረስ ይድረስ መልኩ አይደረግም፤ ያለህንና የያዝከውን አራግፈህ ቶሎ አትሮጥም። ባይሆን የፍቅር አምላክ ለሆነው ጌታ ጉዳይህን ታቀርባለህ።  ታንሾካሹካለህ። ዱዓ በአዛኝ እና በሚታዘንለት፣ በሀብታምና ድሃ፣ በፈጣሪና ፍጡር፣ ሁሉን ባለው እና ምንም በሌለው፣ ሁሉን ማድረግ በሚችል ኃያል እና ምንም ማድረግ በማይችል ደካማ መካከል የሚደረግ ሚስጢር ነው። በዚያ ቦታ ላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ ምንም የምትደብቀው ጉዳይ፤ አንድም የምታፍርበት ነገር አይኖርም። ኸልዋ ያቆርነው እንባ ግድቡን የሚደረምስበት ጓዳ ነው። ያደከመንን፣ ያሳሰበንን፣ መሸከም ያቃተንን ኮተት ሁሉ የምናራግፈበት ሜዳ ነው። በትኩረት ዱዓ ለማድረግ፣ በተመስጦ አላህን ለማውሳትም ሆነ ቁርኣን ለመቅራት፣ በልዩ ሁኔታ ከአላህ ጋር ለመሆን አንዳንድ ኸልዋ ያስፈልጋልና እንጠቀምበት። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
إظهار الكل...
👍 88👌 15🕊 4
ታመናል በጠና! ውጫችን ተውቦ በሱና አሸብርቆ የሚያስደምም ሆኖ ዟሂራችን ደምቆ ቀልብ ካልረባማ ከተቆራመደ የድብቅን ወንጀል ከተለማመደ ከባድ አደጋ ነው ታመናል በጠና ፈውሱን እንፈልገው ከቁርአን ከሱና ጀግና መስለን ውለን በቀን በጠራራ ሌቱን ከገፋንው ከኢብሊሱ ጋራ ምኑን ተከተልንው የነብዩን ስራ?! ልባችን ደካክሞ ባጋንነቶች ጭፍራ! ይብቃን አረ ይብቃ እንዲህ መዳከሩ በድብቅ ወንጀሎች ሌት ቀን መነከሩ መንገዱን እንጀምር በዲን በመስመሩ!! ✏️ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጁ―
إظهار الكل...
👍 134😢 18👌 4🕊 4
ሲትር ታውቃላችሁ?ሽፈና ማለት ነው። የገመና መሸፈን። አዎን…በድብቅ ከምንሠራቸው ወንጀሎች አንፃር የአላህ ሲትር ባይኖርልን ኖሮ ሁላችንም እርቃናችንን በቀረን ነበር። ስንቶቻችን በተዋረድን!ቀላል ፀጋ እንዳይመስላችሁ ! የአላህ ሲትር ከላያችን ላይ ቢገፈፍ ስንት ፀጋዎቻችን በረገፉ ነበር። በሰው ዘንድ ያለን ክብር፣ መወደሱም፣ መደነቁም በአንድ ጊዜ እርግፍ ይል ነበር። አሁንም ሰትረን ጌታዬ። =t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
إظهار الكل...
👍 138😢 28
02:06
Video unavailableShow in Telegram
የቀልብ መሞት!
በወንድም አብዱረዛቅ ባጂ
إظهار الكل...
12.26 MB
👍 84😢 6👌 2
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.