cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ልዩ መረጃ

#ልዩ መረጃ #በዚህ ቻናል ለኢትዮጵያ ፍቅር ሰላም አንድነት ስለ ፍትህ የምናወራበት ድምፅ ላጡ ድምፅ የምንሆንበት ነው #መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ #ጥቆማ ለመስጠት 👇👇👇👇 @Liyumereja999bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
15 822
المشتركون
+5224 ساعات
+1477 أيام
+5 56730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የቴሌግራም ቻናል ጥቆማ‼️👇 መረጃ ለማድረስ እንዲሁም ለመከታተል ቴሌግራም ተመራጭ እየሆነ ነው‼️ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያልተሰሙ እና አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው join በማድረግ ተከታተሉ። ብዙ አዳዲስ መረጃዎችን ታገኛላችሁ እንዲሁም በቻናሉ ማስታወቂያ ብታሰሩ እጅግ አዋጪ ነው። ቻናሉን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ👇👇👇👇👇 https://t.me/fannomedia27 https://t.me/fannomedia27 https://t.me/fannomedia27
إظهار الكل...
ሊባኖስ ፔጀርስን፣ ዎኪ-ቶኪዎችን በሁሉም በረራዎች ላይ ጥቅም ላይ እንዳይዉሉ አገደች‼️ የሊባኖስ የሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ተሳፋሪዎች በማንኛውም አውሮፕላን ላይ ፔጀር እና ዎኪ ቶኪዎችን ይዘዉ እንዳይሳፈሩ የሚያግድ አዲስ መመሪያ ማውጣቱን የመንግስት የዜና ወኪል ኤን ኤን ዘግቧል።እገዳው በቤሩት ራፊክ ሃሪሪ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚያልፉ ጭነት ፣የሚፈተሹ እና በእጅ ሻንጣዎች ላይ የሚተገበር ሲሆን የአየር ማረፊያው ጥበቃ እነዚህን መሳሪያዎችን ይዞ የተገኘ ማንኛውንም መንገደኛ ይወርሳል። አዲሱ ህግ ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን የማሻሻያ ማስታወቂያ እስኪወጣድረስ ተግባራዊ ይሆናል።ፔጀር የሬዲዮ ዌቭ የሚጠቀም የመገናኛ ዘዴ ነው። ሰዎች መረጃ ሲልኩ የሚተላለፈውም የሬዲዮ ፍሪክዌንሲ በመጠቀም ነው። መልዕክት የተላከለት ሰው መልዕክቱ እንደደረሰው በንዝረት መልዕክት መስጠት የሚችል ሲሆን አጭር የጽሑፍ ወይም የድምፅ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ይችላል።እ.አ.አ 1980ዎቹ እንዲሁም 90ዎቹ በስፋት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ የግንኙነት መሳሪያ አሁን ላይ በሞባይል ስልክ ቢተካም አሁንም ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ጥቅም ላይ ይውላል። በሌላ መረጃ ቱርክ እስራኤል በጋዛ ያለውን ጦርነት ወደ ሊባኖስ ለማስፋት እየፈለገች ነው ስትል ከሳለች።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን በመንግስት የሚተዳደረው ቲአርቲ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበዉ በሰጡት መግለጫ "በአካባቢው ያለው ዉጥረት መባባስ አሳሳቢ ነው" ብለዋል። እስራኤል ጥቃቷን በደረጃ ወደ ሊባኖስ ስትወስድ እናያለን ሲሉ አክለዋል።እስራኤል በፍንዳታው ዙሪያ የተናገረችው መረጃ ባይኖርም ቱርክ ሀገሪቱን ተጠያቂ አድርጋለች። በእስራኤል የተከናወኑ ጸብ ቀስቃሽ ተግባራት በአጸፋ ምላሹም ኢራን፣ ሂዝቦላህ እና ለእነሱ ቅርብ የሆኑ አካላት ዝምታን አይመርጡም ሲሉ ፊዳን ተናግረዋል። ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በደቡብ ጎንደር ዞን ከሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ለቀው ወጡ‼️ በደቡብ ጎንደር ዞን በሚገኙ ከአምስት ወረዳዎች ከ2016 ዓ.ም ማብቂያ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ዘግባለች።   የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እስቴ መካነ ኢየሱስ፣ አንዳቤት፣ ሙጃ፣ ስማዳ እና ታች ጋይንት ከሚባሉ ወረዳዎች ከነሐሴ ዕኩሌታ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ባሉት ጊዜያት ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን ዋዜማ ተገንዝባለች።  የመንግስት ኀይሎች ለምን ከአካባቢው እንደወጡ በይፋ አልተናገሩም። በወረዳዎቹ የነበሩ የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሙሉ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር ወደ ዞኑ መቀመጫ ደብረታቦር ገብተዋል። ይህን ተከትሎም በወረዳዎች ኹሉም ዓይነት የመንግሥት አገልግሎቶች የተቋረጡ ሲሆን፣ በፖሊስ እና በሚሊሻ የሚሰጡ አገልግሎቶችም በተመሳሳይ ቆመዋል።  በአንጻሩ በእነዚህ ወረዳዎች ባንኮች እና የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ነው ተብሏል። ትምህርት ቤቶች እስካሁን ምዝገባ አላከናወኑም።  የአማራ ክልል መንግስት የኮምኒኬሽን ቢሮ ስለጉዳዩ ላቀረብንለት ጥያቄ ጉዳዩን መመለስ የሚችለው የኮማንድ ፖስቱ ነው ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከወረዳዎቹ ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ በቦታው የተተኩት የፋኖ ታጣቂዎች የራሳቸውን የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት ጥረት እያደረጉ ነው። በአንጻሩ የዞኑ ዋና መቀመጫ ደብረታቦር እንዲሁም ንፋስ መውጫ፣ ፎገራ እና ደራ ወረዳዎች ዋና ከተሞቻቸው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ስር ይገኛሉ። ሆኖም በዞኑ ዋና ከተማ ደብረታቦር ዙሪያ ታጣቂዎች በብዛት እንደሚገኙ ሰምተናል።  በሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችም ሰሞኑን በኹለቱ ኃይሎም መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ ቆቷል።  ሰሞኑን በመንግስት ወታደሮች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆኑት በጎንደር እና በደባርቅ ከተሞች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ ሲካሄድ ሰንብቷል። ይህን ተከትሎም በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ተገንዝበናል። በክልሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ግጭት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞትና ለአካል ጉድት መዳረጋቸውን ብሎም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ።   Via ዋዜማ ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
إظهار الكل...
👍 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
ተፈታለች‼️ ደራሲ እና አርቲስት አዜብ ወርቁ መታሰሯ ከሰዓታት በፊት ተዘግቦ ነበር ዛሬ በቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው አዜብ ወርቁ ለግማሽ ቀን ያህል በእስር ከቆየች በኋላ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ተለቃለች። አርቲስቷ ሰሞኑን "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ ብዙዎች ተጋርተውት እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ አይዘነጋም። ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
إظهار الكل...
አስደሳች ዜና ለአንባቢያን በሙሉ‼️ በዚህ መፅሀፍ በተወደደበት ሰኣት  ማንኛውንም መፅሀፍ በPDF መልክ ምታገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን እና የሚፈልጉትን መፅሀፍ ይዘዙን ወዲያውኑ እንልክልወታለ። ለማዘዝ የሚከተለውን link ይጠቀሙ👇👇👇 https://t.me/bookshelf566
إظهار الكل...
👍 5
በሶማሌ ክልል ዋርዴር መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መደላቸው ተነገረ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዋርዴር ከተማ በአንድ መስጂድ ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የአገር ሽማግሌ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ሶማሊ ተናገሩ። ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ.ም. በምሥራቃዊ የክልሉ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ዶሎ ዞን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ፤ በአካባቢው ባሉ ጎሳዎች መካከል ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረ ግጭት ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ተነግሯል። አቂል ሞሐመድ ሞሐሙድ የተባሉት የአካባቢው የአገር ሽማግሌ ጥቃቱ መፈጸሙን እና ወጣቶቹ መገደላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የተገደሉት ወጣቶች የሃይማኖት ተማሪዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌው “በስድስቱ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ ዘግናኝ ነው” በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል። ወጣቶቹ የተገደሉት ኩጂር በተባለው መስጂድ ውስጥ ለሶላት እየተዘጋጁ ሳለ መሆኑን የገለጹት የአገር ሽማግሌው፤ “ታጣቂዎቹ በአነስ ባለ መኪና ወደ መስጂዱ መጥተው በልጆቹ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል” ብለዋል። በጥቃቱ መስጂድ ውስጥ የተገደሉት ስድስቱ ወጣቶች ወንዶች የቀብር ሥነ ሥርዓት ረቡዕ ዕለት እዚያው ዋርዴር ከተማ ውስጥ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ግድያው በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ድንጋጤና የፈጠረ ሲሆን፣ ከዚህ በፊት አጋጥሞ የነበረ የጎሳ ግጭትን መሠረት ያደረገ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከወራት በፊት ወንድማማች በሆኑት ጎሳዎች መካከል ግጭት አጋጥሞ እንደነበር ነዋሪዎች አስታውሰዋል። ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ዶሎ ዞን ዋርዴር ወረዳ በሁለት ንዑስ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ሕይወት ማለፉን አንድ የክልሉ ባለሥልጣን እና የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በተጨማሪም በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በወቅቱ ባወጣው መግለጫ፤ “በሁለት ወንድማማች ንዑስ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሰው ሕይወት ጠፍቷል” ብሎ ነበር። በወቅቱ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲቃድር ረሺድ በተከሰተው ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ያረጋገጡ ሲሆን፣ በክልሉ የሚሠራው የሰብዓዊ መብት ድርጅት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመድ መሐመድ ደግሞ ሟቾች አራት መሆናቸውን ገልጸው ነበር። ይህ በዚህ ሳምንት በመስጂድ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ከወራት በፊት አጋጥሞ ከነበረው ግጭት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተገምቷል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው ተሰማርተው የደኅንነት ጥበቃ እና ስለግድያ ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ክስተቱን በተመለከተ የዶሎ ዞን ኃላፊዎችም ሆነ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት እስካሁን ያሉት ነገር የለም። @ቢቢሲ
إظهار الكل...
👍 7 2
ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ለመጠበቅ በቀጣዩ ወር የጦር መርከቦቿን ልትልክ ነው‼️ ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ተገልጿል ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ከውጭ ከሚሰነዘር ስጋት ለመከላከል በመጪው ወር የጦር መርከቦቿን በአካባቢው ልታሰማራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡  በተያዘው የፈረንጆቹ አመት መጀመርያ የመከላከያ ስምምነትን የተፈራረሙት ሞቃዲሾ እና አንካራ በሁለትዮሽ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡  ቱርክ በቀጣዩ ወር በሶማሊያ የባህር ክልል ታሰማረዋለች የተባለው የባህር ሀይልም የዚህ የመከላከያ ስምምነት አንድ አካል ነው፡፡ ወደ ቀጠናው የሚመጡት ሁለት አይነት መርከቦች ሲሆኑ አንድኛው አንካራ በአካባቢው ለምታደርገው የነዳጅ ማውጣት እንቅስቃሴ የሚያግዝ ሲሆን ሌሎቹ ድግሞ የሶማሊያን የባህር ክልል እና የነዳጅ አውጭ ቡድኑን የሚጠብቁ ናቸው ተብሏል፡፡ ቱርክ በሶማሊያ የሚሳኤል እና የጠፈር ሮኬት መሞከርያ ጣቢያ ልትገነባ ነው የቱርክ የኢነርጂ ሚንስትር አልፓረሰላን ቤራክታር ባሳለፍነው ሳምንት ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን እንደተናገሩት ተርኪሽ ፔትሮሊየም የተባለው ኩባንያ እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ኪሎሜተር ስኩየር በሚሸፍኑ ሶስት አካባቢዎች ላይ የነዳጅ ፍለጋ እንዲያደርግ ከሶማሊያ ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡   ሀገራቱ በገቡት ስምምነት መሰረትም እንደሚገኘው የነዳጅ መጠን ለመከፋፈል እና ላስፈለጋቸው አካል መሸጥ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡  ይህን ተከትሎም ሁለት መካከለኛ የውግያ መርከቦች እና ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ አጋዥ መርከቦች አካባቢውን ለመቃኘት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ሚድልኢስት አይ ዘግቧል፡፡ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እንደሚሰማሩ የተነገረላቸው እነዚህ መርከቦች ከባህር ላይ ሽፍቶች እንዲሁም ከምድር ሊሰነዘር የሚችል የትኛውንም ጥቃት የመመከት እና የቅኝት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችል አቅም ያላቸው ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ ከሶማሊያ ጋር ትብብሯን እያጠናከረች የምትገኘው ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗም ተዘግቧል። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በወደብ ጉዳይ የተፈራረመችውን የመግባብያ ስምምነት ተከትሎ ሞቃዲሾ እና አንካራ የመከላከያ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ስምምነት ፈጽመዋል፡፡    አንካራ በሶማሊላንዱ ወደብ ምክንያት ቅራኔ ውስጥ የሚገኙትን አዲስአበባ እና ሞቃዲሾ ለማሸማገል ሁለት ያልተሳኩ ጥረቶችን ማድረጓ የሚታወስ ነው። ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
إظهار الكل...
👍 5😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
ለታጋቾች ማስለቀቂያ ብር ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች እራሳቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰማ ‼️ 👉5 አምስት ያህል ግለሰቦች ደግሞ ከእገታው ቦታ ማምለጣቸው ተነግሯል፡፡ ከሳምንት በፊት በአርሲ ዞን ሲርካ ወረዳ 38 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን  መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከ250ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎም አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘቡን ለመክፈል ወደ ተባሉበት ቦታ ማቅናታቸውን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች ገንዘብ አቀባዮቹ በቦታው ሲደርሱ ግን እራሳቸው በታጣቂዎቹ መታገታቸውን ነው የገለጹት ፡፡ ‹‹ካሉበት ቦታ ሆነው ስልክ ደውለው እኛም ታግተናል›› አሉን የሚሉት አንድ ምንጭ የታገቱትን አስፈትተው ይመጣሉ ብለን ተስፋ ስናደርግ እነሱም መያዛቸው ሌላ ጭንቀት ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡ ታጋቾችን ለማስለቅ የሚያስችል ገንዘብ አሁን ላይ እንደሌላቸው የሚገልጹት እነዚህ የታጋች ቤተሰቦች የቀደሙትንም ለማስፈታት በገበያ ቦታ፣ በእድርና በመሰል ማህበራዊ አደረጃጀቶች በኩል ጥረት ተደርጎ ገንዘቡ እንደተሰበሰበ ገልጸዋል፡፡ መንቀሳቀስና መስራት ውድ እየሆነ መጥቷል፤ መንግስትም የህግ የበላይነት የሚባለውን መሰረታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በማለትም አካባቢው ላይ የሚታይ ስጋት አሁንም እንዳለ ነው ያስታወቁት፡፡ በሌላ በኩል ታግተው ከነበሩ 38 ሰዎች ውስጥ 5 ያህል ታጋቾች ማምለጣቸውንም እነዚህ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ምንጮች አሁን ላይ ያመለጡት ታጋቾች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ የሸኔ ታጣቂ ቡድኖቹ በአርሲ ዞን ሲርካ ወረዳ ከጎቤሳ ከተማ ወደ ተለያዩ ከተሞች በመጓዝ ላይ የነበሩ አጠቃላይ 8 የህዝብ ማመላለሻዎችን ጋለማ በሚባል ጫካ ውስጥ በማስቆም 38 ሰዎችን በመምረጥ ማገታቸው የሚታወስ ነው። አዲስ ማለዳ ============================== ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇 Telegram :https://t.me/+VzJa-EeOEzZlODBk YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
إظهار الكل...
👍 4 1🔥 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.