cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

✝️የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፎቶግራፍ 📸✝️

🙏እግዚአብሔር ነግሠ ስብሐቲሁ ለብሰ መዝ፦፺፪፥፩✝️ ''እግዚአብሔር ነገሰ ምስጋናን ሁሉ ለበሰ'' ✝️ይሄ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ✝️ መዝሙሮች ✝️ መንፈሳዊ ትምህርቶችና ✝️ መንፈሳዊ ፎቶግራፍ የሚለቀቅበት ቻናል ነው #Share #share #share እያደረጋችሁ🙏

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
290
المشتركون
+124 ساعات
-47 أيام
+530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🕊 †  🌼  መስከረም [ ፬ ] 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት 🌼  † [ †  🕊  እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።  🕊 †  ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †  🕊 ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን  🕊  † † ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ አውሴ ይባላል:: ዘመኑ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ፪፻፲፭ [215] ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና ሊቀ ነቢያትሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ ፹ [80] ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ ፵ [40] ዓመቱ ነበር:: ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ [፵] 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ኢያሱ ማለት " መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት :- ፩. ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል:: ፪. ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ [ጥላ] እንዲሆን ነው:: ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል [አገልግሎታል] : እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ ደብረ ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው [፹] 80 እየሆነ ነበር:: † እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን [አስተዳዳሪ] እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ: ¤ ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ: ¤ ሕዝቡን አሻግሮ: ¤ የኢያሪኮን ቅጥር [፯] 7 ጊዜ ዙሮ: ¤ በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ: ¤ የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ: ¤ ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ:: የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ፲፪ [12] ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም [በኤሎም ሸለቆ] አቆመ:: ሰባት አሕጉራተ ምስካይ [የመማጸኛ ከተሞችን] ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ፵ [40] ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ :- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: [ኢያ.፳፬] (24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ:: ይህችውም የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ ፫ [3] ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ፫ [3] ወገን [በነፍስ: በሥጋ: በልቡና] ድንግል ናት:: አንድም በ፫ [3] ወገን [ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት] ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው አባሕርያቆስ "ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" [የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ] ሲል ያመሰገናት:: ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ፹ [80] ዓመት: በተወለደ በ፻፳ [120] ዓመቱ [ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ፻፲ [110] ዓመቱ ይላል] በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ፴ [30] ቀናት አለቀሱለት:: †  🕊  ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ  🕊  † † አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው:: ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ፲፭ [15] ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው:: ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ፸ [70] ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል:: ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል:: † እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው :- ¤ ወንጌላዊ ¤ ሐዋርያ ¤ ሰማዕት ዘእንበለ ደም ¤ አቡቀለምሲስ [ምሥጢራትን ያየ] ¤ ታኦሎጐስ [ነባቤ መለኮት] ¤ ወልደ ነጐድጉዋድ ¤ ደቀ መለኮት ወምሥጢር ¤ ፍቁረ እግዚእ ¤ ርዕሰ ደናግል [የደናግል አለቃ] ¤ ቁጹረ ገጽ ¤ ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ [ከጌታ ጎን የሚቀመጥ] ¤ ንስር ሠራሪ ¤ ልዑለ ስብከት ¤ ምድራዊው መልዐክ ¤ ዓምደ ብርሃን ¤ ሐዋርያ ትንቢት ¤ ቀርነ ቤተ ክርስቲያን ¤ ኮከበ ከዋክብት † በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ: ከአባቱ ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች:: †   🕊   አባ ሙሴ ዻዻስ   🕊  † እሥራኤላዊ ሲሆኑ ከአቡነ ሰላማ ቀጥለው የመጡ የሃገራችን ዻዻስ ናቸው:: ፍጹም ገዳማዊና ትጉህ: ባለ ረዥም ዕድሜ ጻድቅም ናቸው:: ገዳማቸው ወሎ ውስጥ ቢገኝም አስታዋሽ ያጣ ይመስላል:: መናንያኑ ለዕለት እንኩዋ የሚቀምሱት አጥተው ሲቸገሩ መመልከቱ እጅግ ያማል:: † በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቸሩ ጌታ ስም አጠራራቸው ካማረና ከከበረ ወዳጆቹ በረከትን ያሳትፈን:: 🕊 [  † መስከረም [ ፬ ] 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  🌼  ] ፩. ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ [ነቢይና መስፍን] ፪. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ [ልደቱ] ፫. ቅዱሳን ዘብዴዎስና ማርያም ባውፍልያ ፬. አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት ፭. አባ ሙሴ ዻዻስ [  † ወርኀዊ በዓላት  🌼   ] ፩. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ ፪. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት ፫. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት] † " አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" † [ኢያሱ.፳፬፥፲፬] (24:14) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
“መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይለናል።”   መዝ 90፥15
መልካም አዲስ  ዓመት
፪፼፲፯|2017 ዓ.ም Orthodoxphotographs
إظهار الكل...
👏 4
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌻2017🌻መልካም🌻አዲስ አመት🌻             🌻🌻🌻      መልካም🌻አዲስዓ መት   መልካም🌻     አ🌻ዲ🌻ስ መልካም 🌻        ዓ🌻መ🌻ት ለወዳጄ 🌻          ዓ🌻መ🌻ት 🌻🌻🌻🌻        አ🌻ዲ🌻ስ                          ዓ🌻መ🌻ት                        አ🌻ዲ🌻ስ                      አ🌻ዲ🌻ስ                    ዓ🌻መ🌻ት                  አ🌻ዲ🌻ስ             ዓ🌻መ🌻ት         አ🌻ዲ🌻ስ       ዓ🌻መ🌻ት    አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት               🌻🌻🌻🌻 🌻መ🌻ል 🌻ካ🌻ም🌻🌻🌻🌻 🌻አ🌻ዲ🌻ስ🌻ዓ🌻መ🌻ት 🌻             🌻   🌻   🌻       🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት        🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻              🌻  🌻  🌻                                      🌻🌻አዲስ            🌻🌻🌻አመት         🌻🌻መ🌻ልካም    🌻🌻አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት   🌻መልካም  🌻 አዲስዓመት   🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻    አዲስዓመት🌻ለወዳጄ🌻🌻   🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌺 ይ🌻ህ🌻🌻አ🌻መ🌻ት🌻🌼 የ🌻ሰ🌻ላ🌻ም🌻🌻አመት🌻🌷 የ🌻ፍ🌻ቅ🌻ር 🌻🌻አመት🌻🌷                                የ🌻ሞገስ 🌻                                        የ🌻ክብር  🌻                                     የ🌻ሹመት🌻                            የ🌻ታላቅነት🌻                                     🌻ዓመት 🌼               🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻🌷🌹🥀               🌻ይ🥀ሁ🌹ን🌷ላ🌼ች🌹ሁ 🌾                  🌻🥀 🌼    🥀🌹🌺   🌷                                  🌻የበረከት 🌻                        🌻የሹመት 🌻                       🌻የምርቃት 🌻                      🌻የመግዛት 🌻                     🌻የከፍታ 🌷🌻                     🌻ዓመት 🌷🌻                     🌻 ይሁን 🌻🌻                    🌻🌻🌻🌻🌻                    🌻🌻🌼🌼🌼 🇪🇹ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት 🙏 🕊🌻🌻 🌻🌻🌻  ያሰብነው የሚሳካበት          🌻🌻 🌻🌻🌻                                         🌻🌻 🌻የካሳ🌻የሰላም🌻የጤና🌻የበረከት🌻🌻 🌻🌹⁣🌾ዓመት 💐🌷ይሁንልን።🌻🕊🌻🌻                    🌼🌼🌼🌼
إظهار الكل...
2
1
🕊  [  † እንኩዋን ለታላላቁ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት : ቅድስት ክርስቶስ ሠምራና ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። †  ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † [ †  🕊 ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ  🕊 † ] † ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይን ናቸው:: ጻድቁን መንካት የቤተ ክርስቲያንን ዐይኗን መጠንቆል ነው:: ተክለ ሃይማኖት እንደ ሊቃውንት ሊቅ: እንደ ሐዋርያት ሰባኬ ወንጌል: እንደ ሰማዕታት ብዙ ግፍ የተቀበሉ: እንደ ጻድቃን ትሩፋት የበዛላቸው: እንደ ደናግል ንጽሕናን ያዘወተሩ: እንደ ባሕታውያን ግኁስ: እንደ መላዕክትም ባለ ክንፍ አባት ነበሩ:: ለዚሕ ነው ተክለ ሃይማኖትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዐይኔ የምትላቸው:: 🕊 ቅዱስ ተክለ-ሃይማኖት  ሐዋርያዊ  🕊 [   ልደት   ] መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ:  ጸጋ-ዘአብ  ካህኑና  እግዚእ-ኃረያ  ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ : በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል:: በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው  ቅዱስ ሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት : እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ [ከአረማዊ ጋብቻ] አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል:: አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት ፳፬, በ፲፪፻፮ (፲፩፻፺፮) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ ፳፬, በ፲፪፻፯ (፲፩፻፺፯) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል:: [   ዕድገት  ] የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን [ብሉያት: ሐዲሳትን] ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ  አባ ጌርሎስ  ተቀብለዋል:: [   መጠራት    ] አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ:: የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ ፦ "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት [ተክለ ሥላሴ] ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ:: [    አገልግሎት    ] ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ [ጽላልሽ] አካባቢ ብቻ በ፲ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ  ኢትዮዽያ  ፪ መልክ ነበራት:: ፩.ዮዲት [ጉዲት] በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል:: ፪.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር:: ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት  ሐዲስ ሐዋርያ  አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን [ጠንቁዋዮችን] አጥፍተዋል:: [   ገዳማዊ ሕይወት    ] ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ፫ ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል:: እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ፲፪ ዓመታት: በአቡነ  ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ፯ ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ፯ ዓመታት: በአጠቃላይ ለ፳፮ ዓመታት አገልግለዋል:: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ  ዞረሬ  ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ፳፪ ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም ፮ ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ፯ ዓመታት ጸልየዋል:: [  ስድስት ክንፍ    ] ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ  እሥራኤል  የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት  አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:- ¤ በቤተ መቅደስ ብስራቱን ¤ በቤተ ልሔም ልደቱን ¤ በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን ¤ በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን ¤ በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር:: የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው  ቀራንዮ  ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ:: በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ  እመቤታችን ድንግል ማርያም  ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደሰማይ አሳረገቻቸው:: በዚያም :- ¤ የብርሃን ዐይን ተቀብለው ¤ ፮ ክንፍ አብቅለው ¤ የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው ¤ ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው ¤ ከ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው ¤ ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው ¤ "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል:: [   ተአምራት    ] የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው:: † ሙት አንስተዋል ፥ ድውያንን ፈውሰዋል ፥ አጋንንትን አሳደዋል ፥ እሳትን ጨብጠዋል ፥ በክንፍ በረዋል ፥ ደመናን ዙፋን አድርገዋል:: ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና:: [   ዕረፍት    ] ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ፺፱ ዓመት: ከ፰ ወር: ከ፩ ቀናቸው ነሐሴ ፳፬, በ፲፫፻፮ (፲፪፻፺፮) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: ፲ ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል:: ይህች ዕለት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ናት፡፡ [ † 🕊  ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  🕊 † ] እጅግ የከበረችና የተመሰገነች እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እናመሰግናታለን:: እርሷ በሁሉ ጐዳና ፍጹምነትን ያሳየች ኢትዮዽያዊት እናት ናት:: ገና ከልጅነት የነበራት የትሕትናና የመታዘዝ ሕይወት እጅግ ልዩ ነበር:: እናታችን ቅድስናን ያገኘችው ገና በትዳር ውስጥ እያለች ነው:: ከተባረከ ትዳሯ ፲፪ [ 12 ] ልጆችን አፍርታ: ምጽዋትን የዕለት ተግባሯ አድርጋ ኑራለች:: በዚህ ደግነቷም ሙት እስከ ማንሳት ደርሳለች:: አብያተ ክርስቲያናትን አንጻ አንድ ልጇን [ዳግማዊ ቂርቆስን] አዝላ ምናኔ ወጥታልች::
إظهار الكل...
👍 1
በደብረ ሊባኖስ ውስጥ የቆየችው ቅድስት እናት ተጋድሎዋን የፈጸመችው ግን ጣና ሐይቅ ውስጥ ነው:: በተለይ ለ፳፪ [22] ዓመታት ሐይቁ ውስጥ አካሏ አልቆ: አሣ በሰውነቷ ውስጥ እስከሚያልፍ ድረስ ተጋድላለች:: በቀኝና በግራ ፲፪ [12] ጦሮችን ተክላም ጸልያለች:: ብዙ ኃጥአንን አማልዳ: ፲፪ [12] ክንፎችን አብቅላ: ከፍ ከፍ ብላለች:: ከርሕራሔዋ ብዛት የተነሳ ሰይጣንን እንኩዋ ለማስታረቅ ሞክራለች:: ጌታም ከሲዖል ነፍሳትን እንድታወጣ ፈቅዶላታል:: ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ያረፈችው በዚህ ዕለት ሲሆን አጽሟ ዛሬ በራሷ ገዳም [ጣና ዳር] ይገኛል:: [ † 🕊  ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ  🕊 † ] ቅዱስ ቶማስ "መርዓስ" በምትባል ሃገር የፈለቀ የንጋት ኮከብ: ጻድቅ: ገዳማዊ: ዻዻስ: ሐዋርያ: ሰማዕትና ሊቅ ነው:: የዚህን ቅዱስ ተጋድሎ እንደ እኔ ያለው ሰው አይቻለውም:: የእርሱ ሕይወት ክርስትና ምን እንደ ሆነ ያሳያል:: - " ቅዱስ ቶማስ " ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ - ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ - መርዓስ በምትባል ሃገር ዽዽስና ተሹሞ በእረኝነት ያገለገለ - በሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስትና የመለሰ - በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው:: ጨካኞቹ ቅዱሱን ለ፳፪ [22] ዓመታት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለ ነበር ፪ [2] እግሮቹ: ፪ [2] እጆቹ: ፪ [2] ጀሮዎቹ: ፪ [2] አፍንጫዎቹ: ፪ [2] ዐይኖቹ: ሁሉ አልነበሩም:: ነገር ግን እንዲህም ሆኖ አልሞተም ነበር:: በመጨረሻም በዘመነ መናፍቃን አርዮስን ካወገዙት ፫፻፲፰ [318]ቱ ሊቃውንት እንዳንዱ ተቆጥሯል:: ቅዱስ ቶማስ ዽዽስና በተሾመ በ፵ [40] ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የጻድቃንን: የሰማዕታትን: የሐዋርያትንና ሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል:: † የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች † ፩. ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ፪. ፍስሐ ፅዮን ፫. ሐዲስ ሐዋርያ ፬. መምሕረ ትሩፋት ፭. ካህነ ሠማይ ፮. ምድራዊ መልዐክ ፯. እለ ስድስቱ ክነፊሁ [ባለ ስድስት ክንፍ] ፰. ጻድቅ ገዳማዊ ፱. ትሩፈ ምግባር ፲. ሰማዕት ፲፩. የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ ፲፪. ፀሐይ ዘበፀጋ ፲፫. የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ ፲፬. ብእሴ እግዚአብሔር [የእግዚአብሔር ሰው] ፲፭. መናኒ ፲፮. ኤዺስ ቆዾስ [እጨጌ] † እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:: † አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ ምልጃ ክብራቸውን ያድለን:: በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን:: 🕊 [  † ነሐሴ ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [ መምሕረ ትሩፋት ] ፪. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ [ ጻድቅት ] ፫. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ ፬. አበው አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ [  †  ወርኀዊ በዓላት   ] ፩. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን ፪. ቅዱስ አጋቢጦስ [ ጻድቅ ኤዺስቆዾስ ] ፫. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ ፬. "24ቱ" ካኅናተ ሰማይ [ ሱራፌል ] ፭. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም † " ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል::" † [ማቴ.፲፥፵] (10:40) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
👍 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.