cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Sozo Visa and Medical Travel

ለጤናዎ ነፃ ምክር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ https://t.me/sozovisa ን ይቀላቀሉ። ወደ ውጭ አገር ለሕክምና፣ ለትምህርት፣ ለስራ ወይም ለጉብኝት መሔድ ይፈልጋሉ ? ይጠይቁን ። ስልክ፦0934999995 Facebook- https://www.facebook.com/Sozomedtravel/

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
233
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
እነሆ፥ለሕዝቡ ሁሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለኹና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ሉቃ. 2፥10-11
إظهار الكل...
==የአካል ክፍል ንቅለ-ተከላ ሕክምና (organ transplantation)== 1. የአካል ክፍል ንቅለ ተከላ ሕክምና ምንድን ነው? 👉የአካል ክፍል ንቅለ ተከላ (organ transplantation) ሥራውን ያቆመ የአካል ክፍል (failed organ) በጤነኛ የሚተካበት የቀዶ ጥገና ሂደት ነው። 2. የንቅለ ተከላ ሕክምናው መቼ ተጀመረ? 🌐የተሳካ ንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው እ.አ.አ በ1954 በአሜሪካ ነው። ይህም በተመሳሳይ መንትዮች ሰጭ-ተቀባይነት የተሰራ የኩላሊት ንቅለተከላ ነው። 👉የጉበት፣ የቆሽት፣ የልብ፣ የቀጭን አንጀት፣ የሳንባ ስኬታማ ንቅለ ተከላ ሕክምናዎች ከ1960ዎቹ ጀምሮ በውጭው ዓለም በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ። 🇪🇹በኢትዮጵያ አገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ንቅለተከላ የተጀመረው በ2015 እ.አ.አ በአገራችን ብቸኛ በሆነው የቅ/ጳውሎስ ሆስፒታል ብሄራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ነው። በማዕከሉ ከ300 በላይ የኩላሊት ንቅለተከላ የተሰራ ሲሆን የሕክምናው ውጤት ከአደጉት አገሮች የሚስተካከል መሆኑን ማስረጃዎች ያሳያሉ (በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎቱን ለማስቀጠል፣ ለማስፋትና ተደራሽ ለማድረግ ቢቸገርም) ። 3. ንቅለ ተከላ የሚያስፈልገው ሰው ‘’የሰው አካል’’ ከዬት ያገኛል? o በሕይወት ካለ (live donor) ፈቃደኛ ዘመድ ወይም የትዳር አጋር፣ 👉ኩላሊት፣ ጉበት፣ ሳንባ፣ ቆሽት፣ ቀጭን አንጀት በሕይወት ካለ ፈቃደኛ ዘመድ ሊወሰዱ ይችላሉ። o በባንክ ከተቀመጠ የሰው አካል (deceased donor) 👉 ደም በባንክ እንደሚቀመጥ ሁሉ የሰው አካልም በባንክ ይቀመጣል። ኩላሊት፣ ጉበት ፣ ልብ ፣ ሳንባ ፣ ቆሽት፣ ቀጭን አንጀት ለዚሁ ተብሎ በተሰራ ባንክ ይቀመጣሉ። o በዚህ ዘርፍ በአገራችን ያለን የዓይን ባንክ ብቻ ነው። 4. የንቅለተከላ ሕክምና የተሰራለት ሰው በሽታ የመከላከል አቅሙ ደካማ የሚሆነው ለምንድነው?? 🔫ማንኛውም ሰው ሰውነቱ በሽታን የሚከላከልለት/ የሚዋጋለት በሽታ ተከላካይ ሥርዓት (immune system) አለው። 🔫የዚህ ሥርዓት ዋና ተግባሩ እንደ ባክቴርያ፣ ቫይረስ፣ ፈንገስ ያሉ በሽታ አምጭ ተህዋስያን/ ጀርሞችን በተለያየ መንገድ ወደ ሰውነታችን ሲገቡ ጀርሞቹን ለይቶ በመዋጋትና ከሰውነታችን በማስወገድ በሽታን መከላከል ነው። 🔫የሌላ ሰው የአካል ክፍል በንቅለ ተከላ የሚተከልለት ታካሚ (ተቀባይ) ፣ የበሽታ ተከላካይ ሥርዓቱ አዲስ የተተከለለትን የሌላ ሰው አካል ክፍል እንደ እንግዳ አካል (እንደጀርም) ስለሚገነዘበው፣ ሥርዓቱ በተተከለው አካል ላይ ጥቃት ይጀምራል። ይህ ጥቃት የተተከለውን አካል ለይቶ ከጥቅም ውጭ ያደርገዋል። ይህም rejection ይባላል። 👉ይህንም ለመከላከል የተቀባዩን በሽታ ተከላካይ ሥርዓት በመድኃኒት እንዲዳከም ይደረጋል። 👉ነገር ግን ሰጩና ተቀባዩ ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ መንትዮች (identical twins) ከሆኑ የበሽታ ተከላካይን ማዳከም አያስፈልግም። 5. ይህ የተተከለ አካል በተቀባዩ በሽታ ተከላካይ (recipient's immune system) ጉዳት ሊደርስበት የሚችል መቼ ነው? 👉ሰጭና ተቀባይ ደማቸው ካልተመሳሰለ (Mismatch) 👉የተቀባዩ ዲ.ኤስ.ኤ (DSA) የሚባል ፕሮቲን በደሙ ውስጥ ካለ፣ 👉የተቀባዩ በሽታ ተከላካይ በመድኃኒት ካልተዳከመ፣ 📢ጉዳቱ (rejection) በንቅለተከላ ሰዓት፣ ከንቅለ ተከላ በኋላ ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት ወይም ዓመታትንም ዘግይቶ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት ይችላል ። 📢የሚተከለው አካል ጉዳት (rejection) እንዳይከሰት፦ 👉ሰጭና ተቀባይ ደማቸው መስማማቱን አስቀድሞ በምርመራ ማረጋገጥና፣ 👉 የተቀባዩን በሽታ የመከላከል አቅም ከንቅለተከላ ዋዜማ እለት ጀምሮ በመድኃኒት ማዳከም ነው። 6. በሽታ ተከላካይ ሥርዓትን የሚያዳክሙ መድኃኒቶች ለምን ያህል ጊዜ ይወሰዳሉ? 📢ከንቅለ ተከላ መጀመሪያው አካባቢ በመጠንም በዓይነትም ብዙ መድኃኒቶች ይወሰዳሉ። የሚወሰዱ መድኃኒቶቾ ከ3-6 ወር ባለው ጊዜ በመጠንም በዓይነትም ይቀነሳሉ። 📢የተወሰኑ መድኃኒቶች ግን እድሜ ልክ ሳይቋረጡ እንዲወሰዱ ሕክምናው ያስገድዳል። 7. በሽታ ተከላካይ ሥርዓት ሲዳከም ለበሽታ አያጋልጥም? 📢 ያጋልጣል፤በተለይ የአዳገኛ እንፌክሽን ተጋላጭነትን ይጨምራል። 📢ተቀባዩ በሽታ የመከላከል አቅሙ በመድኃኒት እንዲዳከም ሆነ ማለት በተለያየ መንገድ (በትንፋሽ፣ በምግብና ውሃ፣ በደም ስር፣ በሽንት ቱቦና በመራቢያ ብልት፣ በቆዳ ስንጥቅ/ቁስል) ወደተቀባዩ ሰውነት የሚገቡ ተህዋስያን (ባክቴርያ፣ ቫይረስ፣ ፈንገስ፣ ...) ያለምንም ተከላካይ በፍጥነት እንዲራቡና በመላ ሰውነቱ በደም ስር እንዲሰራጩ ይመቻቸዋል። ይህ ክስተት ሲፈጠር ኢንፌክሽን በተቀባዩ ላይ ተከሰተ እንላለን። 8. ኢንፌክሽኑን እንዴት መከላከልና ማከም ይቻላል? 👉ኢንፌክሽኑ ከተከሰተ በኋላ ከማከም ይልቅ ኢንፌክሽን እንዳይከሰት መከላከሉ ቀላል ነው። 📢ኢንፌክሽኑን እንዳይከሰት ለመከላከል፡- 1. በባለሙያ የሚነገሩ ሕይወት አድን የጥንቃቄ መልዕክቶችን መተግበር፣ 📢ይህም በሽታ አምጭ ጀርሞች በትንፋሽ፣ በምግብና መጠጥ፣ በቆዳ ክፍተት/ቁስለት፣ በሽንት ቱቦና መራቢያ ብልት ወደሰውነታችን እንዳይገቡ የሚወሰዱ ዝርዝር የጥንቃቄ መልዕክቶችን ያካትታል። 2. ኢንፌክሽንን የሚከላከሉ መድኃኒቶችን ሐኪም በሚያዝዘው መሰረት በትክክል መውሰድ። 📢የተለዩ ምልክቶች (ሳል፣ የስውነት ሙቀት መጨመር፣ ተቅማጥ፣ ሽንት ማቃጠል/ ማጣደፍ፣ የህመም ስሜት፣ ...) በተቀባዩ ላይ ከታዩ፣ ቶሎ ወደ ሐኪም ቤት በመሔድ በዘርፉ ባለሙያ መታየት ያስፈልጋል። 9. ከንቅለ ተከላ በኋላ ታካሚው በአማካይ ስንት ዓመት በሕይወት ሊኖር ይችላል? 📢ንቅለተከላ በተሰራላቸው ታካሚዎች ላይ የተሰሩ ጥናቶች ኩላሊት ተቀባይ በአማካይ ከ 15-20 ዓመታት እንደሚኖር ያመለክታሉ። 📢የጉበት፣ የልብ፣ የሳንባ፣ የቆሽት እንዲሁም የቀጭን አንጀት ንቅለተከላ የተሰራላቸው ሰዎች፣ ከንቅለተከላ በኋላ ዓመታትን በመልካም አንጻራዊ ጤንነት እንደሚኖሩ ይታወቃል። 10. ኩላሊቱን የሚሰጥ ሰው በመስጠቱ ምክንያት የመሞት እድሉ ምን ያህል ነው? 📢በጣም ዝቅተኛ (0.05%) ነው። ማጠቃለያ- 📢 በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያሰራችሁ፣ ለማሰራት ዝግጅት ላይ ያላችሁ ታካሚዎች ወይም ቤተሰቦች ስለሕክምናውና በተለይ ከሕክምናው በኋላ ስለሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎች፣ ስለሚወሰዱ መድኃኒቶችና ስለሕክምናው ክትትል አስፈላጊነት ጥሩ ግንዛቤ መያዝ ያስፈልጋችኋል። ተጨማሪ መልዕክት👇👇 📢ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ የፋይናንስ ተቋማት (ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን የምትገነቡ ባንኮች)፣ የህግ ባለሙያዎች፣ ዲያስፖራው እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ ጤና ተቋማትን መገንባትበማሟላት የሰው ሕይወትን መታደግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው። ☝️ቢያንስ አንድ ሰፊ የንቅለተከላ ተቋም ለምን አልኖረንም? ዶ/ር ዮም፣ የቀዶ ጥገና ሐኪም Follow us on: Facebook:👇 https://www.facebook.com/Sozomedtravel/ Telegram👇👇 https://t.me/sozovisa ለጥያቄ 👉 https://t.me/sozo_v ላይ ይላኩ።
إظهار الكل...
Log in to Facebook

Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.

👍 16👏 3 2
የጨጓራ ቁስለት በሽታ (Peptic Ulcer Disease) 1. የጨጓራ ቁስለት ምንድ ነው? 📢 የጨጓራ  ወይም  የላይኛው ቀጭን አንጀት (Stomach Or Duodenum) ግድግዳ በተለያየ ምክንያት ከውስጥ ወደ ውጭ መቦ'ርቦር ወይም መ'ላጥ ማለት ነው። 2. መነሻ ምክንያቱ ምንድ ነው? 📢 ጨጓራ እንዲቦረቦር / እንዲላጥ በሚያደርጉ አጋላጭ ምክንያቶችና ይህን በሚከላከሉ  ምክንያቶች መካከል በሚኖር መስተጋብር አለመመጣጠን ሲኖር ጨጓራ ወይም የመጀመሪያው ቀጨን አንጀት ይቆስላል፣ ይቦረቦራል። 📢 ቁስለቱ  እንዲፈጠር የሚያደርጉ ዋና ዋና አጋላጭ ምክንያቶቹ፦     ሀ. የጨጓራ አሲድና ፔፕሲን መብዛት፣    ለ. አንዳንድ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች (NSAIDs)፣    መ. የጨጓራ ባክቴርያ (H. Pylori)   ሠ. በሌላ በሽታ በጽኑ ህመም ላይ መሆን (Critical illness)   ረ. ሲጋራ ማጨስ   ሰ. በአደጋ የተጎዱ (የጭንቅላት አደጋ፣ የእሳት ቃጠሎ አደጋ) መሆን።   ሸ. (በእድሜ መግፋት)   ቀ. ለረዥም ጊዜ የቆዬ ከፍተኛ ጭንቀት (Stress)። 📢 ተከላካይ (አዎንታዊ) ምክንያቶች ጨጓራና አንጀታችን ከላይ በተጠቀሱት አሉታዊ ምክንያቶች  እንዳይጎዳ የሚከላከሉልን ናቸው፤ እነሱም፦     👉. የጨጓራ ሙከስ (mucus) - ጨጓራን አሲድና የፔፕሲን ኢንዛይም እንዳይጎዱት ጨጓራን ከውስጥ በኩል የሚሸፍን ወፍራም ዝልግልግ ፈሳሽ ነው።    👉. ባይካርቦኔት    👉. በቂ የጨጓራ ደም ዝውውር ና ሌሎችም።     3. ምልክቶቹ 👉. የሆድ ህመም ፣ ከእንብርት በላይ ማቃጠል።     ይህ ዋነኛው ምልክት ሲሆን ለጨጓራና ለቀጭን አንጀት ቁስለት ይለያያል። 📢 ጨጓራ ከቆሰለ፣ ህመሙ በምግብ ይባባሳል። ታማሚውም ህመሙን ስለሚፈራ በቂ ምግብ አለመውሰዱን ተከትሎ ኪሎው ይቀንሳል። 📢 ላይኛው ቀጭን አንጀት ከቆሰለ፣ ህመሙ ምግብ ያስበላል። ይህም ክብደት እንዲጨምር ያደርጋል።  በአብዛኛው ህመሙ የሚሰማ ምግበ ከተበላ ከ2-3ሰዓት በኋላ ነው።  በህመሙ ከእንቅልፍ የመንቃት ሁኔታ ይኖራል።     👉. የማስገሳትና ቶሎ የመጥገብ     👉. ትውከት ና ማቅለሽለሽ     👉. እንደከሰል የጠቆረ ሰገራ ወይም የቡና አተላ የሚመስል ትውከት (የጨጓራ ቁስል ሲደማ የሚከሰት)።    👉. የደም ማነስ ምልክት ( ድካም፣ ብዥታ፣ ራስ ህመም፣ ማዞር፣) 4.      ምርመራዎች    - በካሜራ የታገዘ ምርመራ (Oesophagogastrodoudenoscopy)   - ከጨጓራ ቁስል የሚወሰድ ናሙና ምርመራ ( ቁስለቱ ካንሰር አለመሆኑን ለማረጋገጥ)     👉👉የጨጓራ ቁስለት 5% ካንሰር የመሆን ዕድል አለው።   - የደም ናሙና ምርመራ   - የሰገራ ምርመራ   - ከትንፋሽ በሚወሰድ ምርመራ   - ሲ ቲ ና ሌሎችም እንደአስፈላጊነታቸው። 5. ሕክምና 📢 በመድኃኒት የሚደረግ ሕክምና፦ መድኃኒቶቹ መወሰድ ያለባቸው አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ በባለሙያ ሲታዘዙ ነው።     -👉.የጨጓራ አሲድን የሚቀንሱ መድኃኒቶች (Proton pump inhibitors- PPI's በክኒን ወይም በመድፌ ሊሰጡ ይችላሉ።           ለወራት፣ አንዳንዴ ደግሞ እድሜ ልክ እንዲወሰዱ በሐኪሙ ሊታዘዙ ይችላሉ።     - 👉. የጨጓራ ባክቴሪያን የሚያጠፉ መድኃኒቶች ፦ 3 ወይም 4 ዓይነት መድኃኒቶች በአንድ ላይ ሊታዘዙ ይችላሉ።     - 👉. የሚጠጡ (ቁስሉን አሲድ እንዳይጎዳው የሚሸፍኑ) መድኃኒቶች። 📢 በቀዶ ጥገና የሚደረግ ሕክምና፦ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው ቁስለቱ ሲወሳሰብ ነው። 6. ተወሳሰበ የምንለው መቼ ነው?   ሀ. ቁስሉ የጨጓራ ወይም የላይኛው ቀጭን አንጀት መበሳትን / መቀደድን ( Perforation) ሲያስከትል። ለ.  ቁስለቱ ሲደማ (Bleeding Ulcer) ሐ . ቁስለቱ የጨጓራ ወይም የላይኛው ቀጭን አንጀትን ሲዘጋ (Gastric Outlet Obstruction). መ. የመድኃኒት ሕክምናው አልሰራ ሲል (Intractability). 7. ከተወሳሰበ እንዴት ይታወቃል? 📢 ጨጓራ ተበሳ/ ተቀደደ (perforated) የምንለው፥ የጨጓራ ግድግዳ ሙሉ በሙሉ በቁስለቱ ተቦርቡሮ በሚፈጠረው ቀዳዳ የጨጓራ አሲድ፣ ጋዝና የበላነው ምግብ ከጨጓራ ውጭ በመፍሰስ ሙሉ የሆድ ዕቃ መበከልን ሲያስከትል ነው።   በዚህ ጊዜ ከፍተኛና ድንገተኛ ጠቅላላ ሆድ ሕመም ይኖራል።   ለመንቀሳቀስ፣ ለመተንፈስ፣ ለመሳል መቸገር።   የሰውነት ሙቀት፣ የልብ ምት፣ የደም ግፊት መዛባት ይኖራል። ደም ናሙና ለምርመራ ይወሰዳል። የደረት ራጅ (ከተቻለ የቁም፣ ካልተቻለ በግራ ጎን የተኝቶ ራጅ) የጨጓራ መቀደድን ያሳያል። 📢 ቁስለቱ ከደማ የቡና አተላ የሚመስል (አንዳንዴ ቀይ ደም) ማስታወክ፣  ሰገራ  መጥቆር ይታያል። በዚህም ደም ካነሰ ድካም፣ ማዞር፣ የዕይታ ብዥታ ይኖራል። 📢 የጨጓራ/ላይኛው ቀጭን አንጀት ከጠበበ ወይም ከተዘጋ፣ የሚበላ ምግብ ወዲያውኑ በትውከት ይወጣል። ክብደት ይቀንሳል። በኢንዶስኮፒ ወይም በባርዬም ራጅ ይረጋገጣል። 8. ከተወሳሰበ  እንዴት ይታከማል። 📢 ጨጓራ ወይም ላይኛው ቀጭን አንጀት ከተበሳ/ከተቀደደ፣ በአስቸኳይ ቀዶ ጥገና በሙሉ ማደንዘዣ ይሰራል። በደም ስር ውሃ ምግብ (በተለምዶ ግሉኮስ)፣ የሕመም ማስታገሻ፣ የባክቴሪያ መድኃኒት ይወስዳል። እንደአስፈላጊነቱ ሌሎችም መድኃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ። በቀዶ ጥገናው በአሲድና በምግብ ፍሰት የተበከለው ሙሉ የሆድ ዕቃ ይፀዳል። የተቀደደው ና ያፈሰሰው ክፍል በቀዶ ጥገናው ተስተካክሎ ይሰራል። አንዳንዴ ድጋሜ እንዳይከሰት አሲድ እንዲጨምር የሚያደርገውን የጨጓራ ነርቭ ቀዶ ጥገና ሊሰራ ይችላል። ከቀዶ ጥገና በኋላ  አሲሲድ የሚቀንሱ መድኃኒቶች ለዕድሜ ልክ ሊታዘዙ ይችላሉ። 📢 ቁስለት ሲደማ በአብዛኛው በመድኃኒት መድማቱ ሊቆም ይችላል። መድማቱ ካልቆመስ?ኢንዶስኮፒ የሚፈስበትን ቦታ በካሜራ በማየት 'ሚፈሰውን ደም ስር ማሰር ወይም ፍሰቱን የሚያቆም መድኃኒት ቦታው ላይ በመርጨት እንዲቆም ይደረጋል። በዚህም መድማቱ ካልቆመስ? 👉በቀዶ ጥገና የሚፈሰውን ደም ማቆም። 👉ደም ማነስ ስለሚኖር ደም መስጠት ሊያስፈልግ ይችላል። 📢 የጨጓራ ወይም ላይኛው ቀጭን አንጀት ከጠበበ ወይም ከተዘጋ፣ ዋናው ሕክምና በቀዶ ጥገና ማስተካከል ነው። አንዳንዴ የጠበበውን ክፍል በኢንዶስኮፒ በመታገዝ ያለቀዶ ጥገና የጠበበውን ለማስፋት ሊሞከር ይችላል። 📢 ታካሚው በጣም የከሳ (ክብደቱ የቀነሰ) ከሆነ ፣ ክብደቱ ከዋናው ቀዶጥገና በፊት መስተካከል ስላለበት ጤነኛው ቀጭን አንጀት ላይ በሆድ በኩል በመለስተኛ ቀዶ ጥገና በሚተከል የምግብ ቱቦ ለተወሰነ ጊዜ ፈሳሽ ምግብ እንዲመገብ ና ክብደቱ እንዲስተካከል ይደረጋል። ክብደቱ ሲስተካከል ዋናው ቀዶ ጥገና ይሰራል። 📢 በመድኃኒት የማይድን ቁስለት ከሆነ፤ ቫገስ በሚባለው አሲድ እንዲመረት የሚያደርግ የጨጓራ ነርቭ ላይ ቀዶ ጥገና ሊሰራ ይችላል። በመድኃኒት የማይድን የጨጓራ ቁስለት ካንሰርም ሊሆን ይችላል። 9. ማጠቃለያ ፦ 📢 የጨጓራ ቁስለት የመድኃኒት ሕክምናው ና ሌሎች ምክሮች በአግባቡና ሐኪም በሚያዝዘው መሰረት ካልተተገበሩ የጨጓራ መቀደድ፣ መድማት ወይም መዘጋት ሊያስከትል እንደሚችል፣ ይህም በድንገት ህይወትን ሊቀጥፍ እንደሚችል ልብ ይበሉ። ዶ/ር ዮም፣ የቀዶ ጥገና ሐኪም ለጥያቄ፦ 👉በ https://t.me/sozo_v ይላኩ። Join 👇 https://t.me/sozovisa
إظهار الكل...
👍 10🙏 6🥰 2
የድብርት/ድባቴ ህመም(Depressive disorders) 🔹🔸🔹🔸 ▻ በእለት ተእለት ኑሯችን ሃዘን፣ ደስታ፣ ፍርሃት፣ ንዴት፣ መደነቅ ፣መጠየፍ እና የመሳሰሉ ስሜቶችን እናስተናግዳለት :: እነዚህ ስሜቶች መኖራቸው ህይወታችን ጣዕም እንዲኖራት አድርጓል:: ከነዚህ ስሜቶች አንዱ ሚዛን የደፋና ሌሎች ስሜቶችን እንዳናስተናግድ ያረገን ጊዜ ጭንቅ ይሆናል:: ▻ በድብርት ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች በየቀኑ በሚባል ደረጃ ለተከታታይ ሳምንታት በድብርት/ሆድ የመባስ/ተስፋ መቁረጥ፣ ደስታን ማጣት፣ ትኩረት ለማድረግ መቸገር፣ ድካም፣ ረብ የለሽ እንደሆኑ መሰማት፣ ራስን መውቀስ፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ የምግብ ፍላጎት እና ክብደት መዛባት፣ አለፍ ሲልም ራስን ለማጥፋት በማሰብ(2/3ኛዎቹ ራስን ስለማጥፋት ሲያስቡ ከ10-15% ሊፈጽሙት ይችላሉ) ይናጣሉ:: ▻ ከበድ ሲልም የመጠራጠር: የመፍራት: ለሌላ ማይሰማ እና የማይታይ ነገር ተሰማኝ/ታየኝ የማለት ምልክቶች ሊከሰቱ ይችላሉ:: psychosis ይባላል:: ▻ የድብርት ህመም በስራቸውን እና በሌላ የህይወት መስካቸን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ድብርትን እንደ ህመም እንድንወስደው የሚያደርግ ቅድመ ሁኔታ ነው::     ▻በነገራችን ላይ እስከ 70 % ገደማ የባይፖላር ህመም (በድብርትና በ ሜኒያ    ስሜት መዋዠቅ) ጅማሬው በድብርት ህመም ነው:: 🔶 ስርጭቱ ▻ 11.1% - 14.6% ገደማ ስርጭት እንዳለው ይጠቆማል::: 🔶 ምክንያቶቹስነ ህይወታዊ ምክንያቶች - 40 % ያህል አጋላጭ ምክንያት ▻ Genetics/ዘረመል- በቤተሰብ ተመሳሳይ ህመም ያለበት ሰው ካለ ተጋላጭነትን ይጨምራል ▻ የጭንቅላትን ስራ የሚያውኩ ህመሞች፣ አደጋዎች፣ መድሃኒቶች፣ እጾች፣ የውስጥ ደዌ ህመሞች፣የሆርሞን መዛባቶች፤ ▻ ሴቶች ከወንዶች በእጥፍ የተጋለጡ ናቸው   ምክንያቶቹ :- ሴቶች ማህበራዊ ጫናዎች መብዛት : የሆርሞን መቀያየሮች(ለምሳሌ በእርግዝና እና ድህረ ወሊድ ወቅት ለድብርት ተጋላጭነታቸው ይጨምራል) ➡ ማህበራዊና ስነልቡናዊ ችግሮች - 60 % አጋላጭ ምክንያቶች 🔘ስነ-ልቡናዊ ▻የልቦና ውቅራችን በጊዜ ሂደት የሚገነባ ነው:: ከልጅነታችን ጀምሮ ያሉት ክስተቶች ተደምረው አሁናዊ እኛነታችንን ይሰራሉ:: ▻ ከወላጆች ጋር ጥሩ መስተጋብር ያልነበራቸው ልጆች(insecure attachment)፣ ትኩረት የተነፈጋቸው(Neglect) ፣ በተለይም ከ 11 አመታቸው በፊት ወላጆቻቸውን በፍቺ/ሞት ያጡ፣ አካላዊ/ስነልቦናዊ/ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ለድብርት የመጋለለጥ እድላቸው ከፍ ይላል:: ▫️የልቦናችን እድገት ጤናማ መሆን አለመሆን ነገሮችን የምናይበትን መንገድ፣ አስተሳሰብና ድርጊታችንን፣ የችግር አፈታት ችሎታችንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ይወስናል:: 🔘 ማህበራዊ ጫናዎች ▪️በተለይም ለረጅም ጊዜ ሳይፈቱ የዘለቁ እንደሆነ ለድብርት የማጋለጣቸው እድል ይጨምራል:: 🟧 ህክምናው ▫️የመድሃኒት ህክምና ▻ ጸረ-ድብርት መድሃኒቶች-  ▻▻የጎንዮሽ ጉዳታቸውም እምብዛም ነው:: የመላመድ ባህርይ የላቸውም:: መድሃኒቶቹ የሚሰጡበት የጊዜ ርዝመት እንደየሰው እና የህመሙ ደረጃ ይለያያል:: ▫️ ለድብርቱ መንስኤ የሆኑ ተጓዳኝ የሆኑ ደዌዎች ካሉ ማከም ▫️አጽ ተጠቃሚም ከሆኑ ለመቀነስና ማቆም መሞከር ▻▻ከእጽ ጋር ተያይዞ የተከሰተ የድብርት ህመም እጹ ሲቆም በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ ይሄዳል:: 🔷 የስነ ልቦና ህክምና- ▻▻በተለምዶ የምክር አገልግሎት ቢባሉም: አላማቸው ምክር መስጠት ብቻ አይደለም:: ☑️ እንደምሳሌ Cognitive and Behavioral Therapy በመጠኑ እንይ 1️⃣ ለሚገጥሙን ሁነቶች ቅጽበታዊ አረዳድ ይኖረናል:: Automatic thought እንላቸዋለን:: ሚዛናዊ ሊሆኑም ይሆኑም ይችላሉ::  የድብርት ህምም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሚዛናዊ ግንዛቤያቸውን ያጣሉ፡፡ 2️⃣ አስተሳሰብና አረዳዳችን የተለያየ ስሜት(feeling) ይፈጥርብናል 3️⃣ ከዠእነዚህ ስሜቶቻችን በሰውነት ስርአታችን ላይ መንጸባረቅ ይጀምራሉ::( በኛ ሃገር: የድብርት ስሜታቸውን በአካላዊ የህመም ምልክቶች መግለጽ የተለመደ ነው-- Mind-body connection ) 4️⃣ ከነዚህ የስሜት መለዋወጦች ለመውጣት የተለያዩ መፍትሄ የምንላቸውን ነገሮች እንሞክራለን::  እነዚህ ድርጊቶች በጥቅምና ጉዳታቸው በአጭርና ረጅም ጊዜ መለካት ይኖርባቸዋል::    ▻▻ ይህን ኡደት ተያያዥና ተመጋጋቢ ነው:: CBT አረዳዳችንን እና ድርጊቶቻችንን በጊዜ ሂደት ሚዛናዊ ማድረግና ማቃናት ላይ አተኩሮ ይሰራል:: 🔷Electroconvulsive therapy (የኤሌክትሪክ ንዝረት ህከምና)- ▻ ራስን የማጥፋት ተጋላጭነት ላላቸው፤ catatonia(ምግብ እምቢ ላሉ፣ አልንቀሳቀስ አና አላወራ ላሉ..) ታማሚዎች አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጣል:: የድብርት ህመም መታከም የሚችል የአዕምሮ ህመም ነው:: አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው https://t.me/DrEstif
إظهار الكل...
👍 5
"ልጆቻችን ቴሌቪዥን ስለመመልከት (Screen time) ማወቅ አለብን?" በዶ/ር አብዲ ከበደ ፤ የሕፃናት ሐኪም አማርኛ | Afan Oromo | Af Somali ➡ የልጆች ስክሪን ጊዜ ወይም የቲቪ መመልከቻ ገደቦች በዚህ ዘመን ልጆች የስክሪን ጊዜያቸውን ወይም ቲቪ ፣ ሞባይል እና ታብሌቶችን በመመልከት ላይ ናቸው እና ከ2 አመት በታች ያሉት እንኳን አሁን ከሚመከረው የጊዜ መጠን አልፈዋል። ➡ ምን ማወቅ እንዳለበት: ዕድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የስክሪን ጊዜን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳሉ ፣ ከ 2 እስከ 5 ዓመት እድሜ ያላቸው ህጻናት ግን በቀን ከ 1 ሰዓት አይበልጥም።   ➡ እነዚህ መመሪያዎች በዓለም ዙሪያ የወጡ ቢሆንም ኢትዮጵያን ጨምሮ መመሪያዎቹን በማክበር ረገድ ትልቅ ክፍተት ስላለ ለሕዝብ ለማሳወቅ ትክክለኛ ምክሮች ያስፈልጋል። 1. ከሁለት አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የስክሪን ጊዜን ሙሉ በሙሉ ያስወግዱ 2. በትናንሽ ልጆች ከፍተኛ ደረጃ የስክሪን አጠቃቀም ከእድገታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ጋር ሊዛመድ ይችላል 3. ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በጣም የዲጂታል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ናቸው። 4. የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ (AAP) እና WHO ዕድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት (ከቪዲዮ ቻት ውጭ) የስክሪን ጊዜ እንዳይወስዱ እና ዕድሜያቸው ከ 2 እስከ 5 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት በቀን 1 ሰዓት እንዲቆይ መክረዋል። TV Daawachuu Yookiin Screen Time Daa'imaaf Eeyamamu Maal Beekuu Nurraa Eegama?                                                                                                       Screen Time/ Yeroo TV ilaaluu  Ijoolleef hayyamamuu qabu  Yeroo Ammaan tana Daa'imman Hedduun, kannen umurii ganna lamaa gadii dabalatee ; TV,Moobayilafaa sa'a/yeroo eeyamamuu Ol Daawachaa Jiraachun beekamadha.  Maal Beekuu nurraa eegama  1.Daa'imman Umuriin Isaani Ganna 2 gadi ta'an TV/ Moobayilaa goonkuma akkan hinlaale  2.Yeroo Hedduuf TV/ Moobayilaa fayyadamuun Ijoollee ,keessattu Ganna 2 kan tayan irratti Rakkoo Guddina sammuu akka geesissu qorannowwan garaagaraa ni Nibeeksisu 3.Yeroo ammaan tana daa'iman Ganna 5 gadi tayan Hedduun Yeroo isaanii TV/ Mobile fayyadamuuf dabarsan akka dabalaa jiru ni beekama                                   4.Akka dhaabatni fayyaa addunyaa fifi American Academy of Pediatrics Gorsaniti ,daa'ima ganna 2 gadi ta’an goonkuma dhorkuu( video chat ala) fifii umuriin isaani 2- 5 tayaniif immoo guyyaatti Sa'a 1 ( daqiiqaa 60 ) qofa akka daawatan Gorsa! Dr. Abdi Kebede {Ispeeshalistii Yaala Daa’imanii} Maxan kaogaana Karnaa dwakhtiga ay caruurta daawanayaan shaashada dhalasa Tiifiga  Dr.Cabdi Kabade {Dhakhtarka carruurta} Wakhtiga xadidan ee caruurtu daawadaan shaadhadaha. •Wakhtiyadan dambe dhamaan caruurta yaryar waxay daawadaan tiifiiga, tabletka iyaga oo daawanaya in kabadan wakhtigii loogu-talagalay  waxa larabo in la'ogaado  Hagaha dhalaanka iyo caruurta ayaa qeexaya, dhamaan  caruurta yaryar ee laba (2) sano kayar in ayna daawan shaashadaha dhalooyinka, halka caruurta ay da'doodu udhaxayso 2 ilaa 3 sano, maalintii hal saac wax kabadan aan loo ogolayn.laogolayn  1)aruurta ay da'doodu kayar tahay laba (2) sano, gabi ahaan-ba Ka ilaali shaashadaha (marka laga reebo maqalka iyo muuqaalka) 2)Wakhtiga badan ee ay caruurtu daawadaan shaashadaha waxay Ku keentaa dhibaa-  3)kuwa ugu badan ee  daawada shaashadaha waa caruurta ay da'doodu tahay shanta (5) sano iyo wixii kayar 4)Macaluumaadka dhalaanka ama caruurta ee maraykanka The....... AAP) iyo wasaarada caafifimaad-ka ayaa soo jeedisay in gabi ahaan-ba caruurta ay da'doodu laba (2) sano kayar tahay laga fogeeyo shaashadaha ( waxaan ka'ahay Maqalka iyo muuqaalka), dhanka kale caruurta ay da'doodu udhaxayso 2 ilaa 5 sano hal saac loogu xadiido wakhtiga ay shaashadaha daawanayaan
إظهار الكل...
👍 4
አጣዳፊ የሃሞት ከረጢት ብግነት/ቁስለት (Acute Cholecystitis) 👉 የሐሞት ከረጢት ብግነት በሐሞት ከረጢት  ወይም በሐሞት ፈሳሽ መተላለፊያ ቦይ ውስጥ ጠጠር በመኖሩ ምክንያት ወይም ጠጠር ባይኖርም በጽኑዕ ህሙማን ላይ ሊከሰት የሚችል የሐሞት ከረጢት ግድግዳ መቆጣት (መቁሰል) ነው።   . መንስኤው፡- 👉   የሃሞት ከረጢት ብግነት ከ90% በላይ የሚከሰተዉ የሃሞት ጠጠር ካለባቸው ሰዎች ላይ ነው ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ~30% የሐሞት ከረጢት ብግነት የሐሞት ኢንፌክሽን ይኖረዋል፡፡ ይህ ቁስለት ና ኢንፌክሽን በሰዓቱ ካልታከመ፣ እየተወሳሰበ ይሄድና እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፤ ሕክምናውና የሕክምና ወጩም ከባድ ይሆናል። 👉 ጥቂት ሰዎች ላይ ደግሞ ሐሞት ከከረጢቱ ወደ አንጀት የሚወስደው የሃሞት መፋሰሻ ቦይ በእጢ ሲዘጋ የሃሞት ከረጢት ብግነት ሊከሰት ይችላል፡፡ 👉 ሌላው  ጠጠር ሳየኖር የሚከሰተው ብግነት በአብዛኛው በሌላ በሽታ በጽኑ ታመው የተኙ ሰዎች ላይ የሚታየው ነው፡፡ . በይበልጥ ተጋላጮች እነማን ናቸው? 👉 በዕድሜ 40ዎቹ አካባቢ የሆኑ፣ ወፍራም ና ብዙ የወለዱ ሴቶች የሐሞት ጠጠር በብዛት የሚኖርባቸው በመሆኑ ለሐሞት ከረጢት መቆጣትም (ብግነት) የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። •  ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው? 😴 የማያቋርጥ የሆድ ህመም (ላይኛውና የቀኝ ፊል የሆድ ክፍል) 😴 ትኩሳት (የሰውነት ሙቀት መጨመር) 😴  ትውከትና ማቅለሽለሽ 😴 ቅባታማ ምግብ አለመስማማት/ ማስጠላት 👉  የሽንት መቅላትና የሰገራ መገርጣት፣ የዓይን ቢጫ መሆን፡፡(የሃሞት ቧንቧ በጠጠሩ ሲዘጋ ) 👉  ሆድ አካባቢ የእንቅስቃሴ መገደብ (እንቅስቃሴ ና ሳብ አድርጎ መተንፈስ ህመም ስሜቱን ያባብሰዋል)፡፡ 👉 ላይኛው ሆድ ክፍል ሲነካ ከፍተኛ ህመም (tenderness) ይኖራል፡፡ •  መፍትሄውስ? 👉  ቶሎ ወደ ሃኪም ቤት (hospital) መሄድ። 👉  ቅባት ያለው ምግብ አለመጠቀም። 👉  ሐኪሙ የቃልና የአካላዊ ምርመራ ከጨረሰ በኋላ እንደአስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ምርመራዎችን (የደም፣ የአልትራሳውንድ፣ ራጂ፣ሽንት…) እንዲሰሩ ያዝዛል፡: 👉  ታካሚው/ዋ የድንገተኛ ተኝቶ ህክምና ይጀምራል፡፡ 👉 በደም ስር የሚሰጡ መድሃኒቶች (የምግብ፣ የባክቴሪያ፣ ህመም ማስታገሻ፣ ትኩሳትና ትውከት የሚያቆም) ይጀምራል፡፡ 👉 በአብዛኛው  ህመሙ ከ72 ሰዓታት (3ቀን) በላይ የቆዬ ከሆነ በመድሃኒተ ማከሙ ይቀጥላል፡፡ 👉 ህመሙ፣ ትኩሳቱና ትውከቱ ሲስተካከል ወደቤቱ ይላክና በቀጠሮ ከ1 ወር ተኩል (6 ሳምንት) በኋላ የቀዶ ጥገና ህክምና ይሰራል፡፡ 👉 በመድሃኒት ካልተመለሰ ወይም ህክምና ላይ እያለ ህመሙ ከተባባሰ በድንገተኛ ቀዶ ጥገና እንዲታከም ይደረጋል፡፡ 👉 ህመሙ 72 ሰዓት ያልሞላው ከሆነና ታማሚው ቀዶጥገና መቋቋም የሚችል ከሆነ፣  በደም ስር የሚሰጡ መድሃኒቶችን እንደጀመረ  ቀዶ ጥገናው ሊሰራ ይችላል፡፡ 👉 በቀዶ ሕክምናው ብዙውን ጊዜ የቆሰለው የሐሞት ከረጢት እንዲወጣ ይደረጋል። . ቶሎ ባይታከም ምን ችግሮችን ያስከትላል? 1.  የሃሞት ከረጢት መምገል፣ መበስበስ፣ ወይም መፈንዳት:: (Abscess, gangrene, rupture) 2. የሃሞት ቦይ ና የጉበት  መመርቀዝ (Cholangiohepatitis)። 3. ሙሉ የሆድ እቃ መመርቀዝ (Generalized Peritonitis) 4.  በመላ ሰውነት የኢንፌክሽን መሰራጨት (Sepsis) 5.  ራስን መሳት (Coma)፣ 6. የደም ግፊት መውረድ (Septic Shock) 👉 እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ከባድ ችግሮች ከተከሰቱ፡- 1.  ህክምናው ውስብስብ ይሆናል፡፡ 2.  ሆስፒታል ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ውድ መድሃኒቶችን እየወሰደ እንዲቆይ ያስገድዳል፡፡ የመታከሚያ ወጭን ይጨምራል፡፡ 3.  ከድንገተኛ ቀዶ ጥገናው በኋላ ከሰመመን ያለመንቃት ችግር ሊኖር ይችላል፡፡ 4.  በህይወት የመቆየት እድልን በእጀጉ ይቀንሳል፡፡ የማጠቃለያ መልዕክት፦ 📢  በቀኝ የላይኛው ሆድ የማያቋርጥ ድንገተኛ ህመም፣ የሰውነት ሙቀት መጨመር (ትኩሳት) ፣ ትውከትና ማቅለሽለሽ ካለ፤ ቅባታማ ምግብ ካስጠላ፣ ሰገራ ከነጣ፣ ሽንት ከቀላ፣ ዓይን ቢጫ ከሆነ ችግሩ ከሐሞት ከረጢት እና / ወይም ከሐሞት ቱቦ ስለሚሆ በሽታው ከመወሳሰቡ በፊት ቶሎ በሐኪም ታይቶ መታከም ያስፈልጋል። ዶ/ር ዮም፣ የጠቅላላ ቀዶ ጥገና ሐኪም t.me/sozovisa https://www.facebook.com/Sozomedtravel
إظهار الكل...
Sozo Visa and Medical Travel

ለጤናዎ ነፃ ምክር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ

https://t.me/sozovisa

ን ይቀላቀሉ። ወደ ውጭ አገር ለሕክምና፣ ለትምህርት፣ ለስራ ወይም ለጉብኝት መሔድ ይፈልጋሉ ? ይጠይቁን ። ስልክ፦0934999995 Facebook-

https://www.facebook.com/Sozomedtravel/

👍 10
የሐሞት ከረጢት ቁስለት ☝️👇
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1
ሶዞ ቪዛና የሕክምና ጉዞ አማካሪ፡ SOZO Visa and Medical Travel Consultancy .......................................................... ሶዞ ቪዛና የህክምና ጉዞ አማካሪ ልምድ ባላቸው ሀኪሞችና የዘርፉ ባለሙያወች ህብረት የተቋቋመና በአገራችን ኢትዮጵያ በዘርፉ ህጋዊ እውቅና የተሰጠው የጉዞ አማካሪ ድርጅት ሲሆን በአገራችን መታከም ያልቻሉና ውጭ አገር ለሕክምና ለሚሄዱ ሁሉ፡- 1. ከጉዞ በፊት ከክፍያ ነጻ የህክምና ማማከርና በፍላጎትወት የሚስማማወትን ሆስፒታል እናማርጥወታለን። 2. በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ  በሆኑና እጅግ በዘመኑ አጋር  ሆስፒታሎቻችንና ተመራጭ ሐኪሞቻችን በተመጣጣኝ ወጭ የተሳካ ሕክምና እንዲያደርጉ እናግዞታለን። 3.  ለህክምና በሚሄዱበት ሀገር ቪዛና ቲኬት በማመቻቸት ለአላስፈላጊ እንግልትና ወጭ ሳይዳረጉ በሰላም እንዲመለሱ እንሰራለን። 4. ከአጋር ሆስፒታሎቻችን ጋር በመተባበር በሚሄዱበት ሀገር የትራንስፓርት፣ የቋንቋና የሆቴል መቆያወትን እናመቻችሎታለን። 5. ህክምናወትን ጨርሰው ከተመለሱ በኋላ ከአከመወት ሃኪም ጋር በTelemedicine ክትትል እንዲያደርጉ እናመቻችሎታን። 6. አገር ውስጥ የማይገኙ #መድኃኒቶች በሐኪም ከታዘዘሎት፣  የታዘዙትን መድኃኒቶች #ከውጭ #አገር እናስመጣሎታለን።  አጋር ሆስፒታሎቻችን፡- 1.#በህንድ (#Apollo Hospitals, #Max Superspeciality Hospitals) 2. #ታይላንድ (##Bangkok Hospital) 3. #ቱርክ (#Medical Park Hospitals Group, #Medicana Hospitals, #Acibadem Hospitals Group) አገር ይገኛሉ። በአገር ውስጥ ለሚታከሙ፣ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎች (የግልም ሆነ የመንግስት) መረጃና አድራሻ ካጡ፣ ሃሎ ይበሉን! እናግዞታለን! የመረጃና ማማከር አገልግሎቶቻችን #ከክፍያ #ነጻ ናቸው! ይምጡና ይጎብኙን በአገልግሎታችን ተደስተው ይመለሳሉ! #አድራሻ፡-   አዲስ አበባ ፣ #መገናኛ ፣ #መተባባር ህንፃ ቢሮ ቁጥር #405 Mobile/ WhatsApp: +251 934 99 99 95  E-mail: [email protected] Telegram: https://t.me/sozomedtravel @sozovisa Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=61553443854591
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.