cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Abdurehman Seid

For any thoughts and comments @ibnuseid_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
325
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የዕርዳታ ጥሪ ይህ የምትመለከቱት ወንድማችን ሁሴን አደም በደረሰበት የደም ካንሰር ምክኒያት ከሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመምጣት ለ 2 ዓመት ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ውጪ ሃገር መሄድ እንዳለበት በመግለፅ በጠቅላላ 4.000.000 (አራት ሚሊዮን ብር) የህክምና ወጪ እንደሚያስፈልግ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መረጃ ሰጥቷል።ይህን ለማድረግ ቤተሰቡ አቅማቸው ስላልቻለ በተለያየ የበጎ አድራጎት ማህበር ላይ እና ሶሻል ሚዲያ ላይ በማሰባሰብ ይገኛሉ።እኛም ወንድማችንን ለማዳን የቻልነውን ያህል ከስር በተቀመጠው አካውንት በመላክ ሰበብ እንሁን! ማሳሰቢያ፦ በዚ ሁለት ወር ገንዘቡ ተሰብስቦ መታከም ካልቻለ በህይወት መቆየት እንደማይችል ተነግሮታል ለአሏህ ስንል በገንዘብም መርዳት የምንችል በተቀመጠው አካውንት እንርዳ! በገንዘብ የማንችል ሼር በማድረግ እና በማስተባበር የአጅሩ ተካፋይ እንሁን! CBE_1000637031717 Mohammed Adem Ararse & Husen Adem Ararse. Abyssinia_138487172 Yasin Adem Ararse የቤተሰቡ ስልክ ቁጥር ሙሃመድ አደም 0921945259 ያሲን አደም 0918368315 @Ibnuseid
إظهار الكل...
📜ኢማሙ_አሕመድ_ኢብኑ_ሐርብ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «አሏህን ለሀምሳ አመታት ያክል ተገዝቼዋለሁ። ሶስት ነገራቶችን እርግፍ አድርጌ በመተዌ ምክንያት እንጅ የዒባዳን ጥፍጥና ማግኘት አልቻልኩም ነበር:- ❶ የሰዎችን ውዴታ መፈልግን ስተው ሐቅን መናገር ቻልኩ፣ ❷ አመፀኞችን መጎዳኘት ስተው ደጋጎችን መጎዳኘት ቻልኩ፣ ❸ የዲንያን ጥፍጥናዋን ስተው የአኼራ ጥፍጥናን ማገኘት ቻልኩ።» @Ibnuseid
إظهار الكل...
👍 5
📜ራፊዒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «የወንድ ልጅ ሙሉነት በሁለት ነገሮች ነው። ፊቱ ላይ ባለው ፂምና ቤቱ ውስጥ ባለችው ሚስቱ።» @Ibnuseid
إظهار الكل...
😢 2
📜ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «እውነተኛ ልቦች እና መልካም ዱዐዎች የማይሸነፋ ሰራዊቶች ናቸው።» @Ibnuseid
إظهار الكل...
👍 2
📜የሕያ_ኢብኑ_ሙዓዝ_አርራዚ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ይቺን ዓለም መተው ከባድ ነው። ጀነትን መተው ደግሞ ከሷ የበለጠ ከባድ ነው። የጀነት መህሯ (ጥሎሽ) ደግሞ ይህችን አለም መተው ነው።» @Ibnuseid
إظهار الكل...
👍 6
📜ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ልብ ንጉስ ሲሆን የሰውነት አካላት ደግሞ ወታደሮቹ ናቸው። ንጉሱ መልካም ከሆነ ወታደሮቹም መልካም ይሆናሉ። ንጉሱ ከተበላሸም ወታደሮቹም ይበላሻሉ።» @Ibnuseid
إظهار الكل...
👍 7
📜ወህብ_ኢብኑ_ሙነበህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - «ዱንያና አኺራህ ልክ 2 ሚስቶች እንዳሉት ወንድ ናቸው። አንዷን ሲያስደስት፤ ሌላኛዋ ትቆጣለች።» @Ibnuseid
إظهار الكل...
👍 4
"ሁለታችንም የጀነት ነን!" ------------ ዒምራን ቢን ሃሰን ሚስቱ በጣም ቆንጆ ናት።እሱ ግን መልከ ጥፉ ነበር።አንድ ቀን ዒምራን ለሚስቱ "ሁለታችንም የጀነት ነን አላት"። ሚስቱም እንዴት ባክህ? አለችው።ምን መሰለሽ ባለቤቴ እኔ አሏህ አንቺን የመሰለች ውብ ሚስት ስለሰጠኝ አመሰገንኩት፤አንቺ ደሞ እኔን ያህል መልከ ጥፉ ባል ጋር እየኖርሽ ትዕግስት አደረግሽ።ታዲያ አመስጋኝ እና ታጋሽ ሁለቱም የጀነት አይደሉምን? አላት። @Ibnuseid
إظهار الكل...
4👍 2👏 2
ሼር እያደረጋችሁ! @Ibnuseid
إظهار الكل...
በሰርጉ_ወቅት_የሞተው_ወጣት_ታሪክ.mp32.16 MB
"ግዙፉ ዝሆን" ------------ `አንድ መንገደኛ አንድ ግዙፍ ዝሆን ታስሮ በማየቱ ተደምሟል።መንገደኛውን ያስደነቀው የዝሆኑ ታስሮ መቆም አይደለም።ዝሆኑ የታሰረበት ገመድ እጅግ ሲበዛ ቧልት(ቀልድ) ሊመስል በሚችል መልኩ ቀጭን እና እዚህ ግባ የማይባል መሆኑ ነው።ገመዱ ዝሆንን ቀርቶ አንዲት የበግ ግልገል እንኳ ሊያስር የማይችል አይነት ነው።ዝሆንን የሚያክል ትልቅ ፍጥረት በዛች ትንሽ እና ቀጭን ገመድ መታሰሩ ያልተዋጠለት መንገደኛ እንዴት ይህ ሊሆን ቻለ? ትንሿ ገመድ ትልቁን ዝሆን ያቆመችበት ሚስጥር ምንድን ነው? እያለ ደጋግሞ አሰበ! ነገሩ ቢከነክነው ወደ ዝሆኑ ቀረብ ብሎ ገመዷን በእጆቹ ዳሰሰና ጥንካሬዋ እስከምን ድረስ እንደሆነ ሊያረጋግጥ ሞከረ።ገመዷ በሩቅ ካስገረመችው የበለጠ ቀርቦ ሲያስተውላት አግራሞቱን ጨመረችበት።ወደታች ገመዷን ቃኝቶ ወደላይ ዝሆኑን ሲመለከት የእውነታው ተቃርኖ ፈገግ አሰኘው።በሁኔታው በእጅጉ ተገረመ።አንዲት ፍየል እንኳ ማሰርና ማቆም የማትችል ገመድ ይህን ግዙፍ ዝሆን አስራ አቆመችው? ብሎ ግራ ተጋባ።በኋላም ድንገት ወደተመለከተው የዝሆኑ ባለቤት ተጠግቶ፦ ይቅርታ የኔ ወንድም! የዚህን ገመድ ሚስጥር ማወቅ እሻለሁ።እውን ይህን የሰማይ ስባሪ የሚያክል ዝሆን ወደዛና ወደዚህ እንዳይል አስራ ያቆመችው ይህች ገመድ ናት? ሲል ጠየቀ።አንድ ሰው የሁለት እጆቹን መዳፎች አገጣጥሞ የአባይ ወንዝን አቆመ ብንባል አይደንቀን ይሆን? ነገሩ እንደዛ ነው። የዝሆኑ ባለቤት በመንገደኛው ጥያቄ አልተገረመም።ምክኒያቱም ይህን ጥያቄ ብዙዎቹ ሲጠይቁትና ሲመልስ ነበር።እንዴት መሰለህ የኔ ወንድም የዚህን ዝሆን የመቆም እጣ ፈንታ የወሰነችው ይህች ገመድ አይደለችም አለው።ዝሆኑን ከልጅነት ጀምሮ ያሳደኩት እኔ ነኝ።ይህች ገመድ በልጅነቱም የሚታሰርባት ገመድ ናት።አድጓል ብዬ ገመዷን አልቀየርኳትም።በእርግጥም ዝሆኑን ያቆመችው ይህች ገመድ አይደለችም።ዝሆኑን ያቆመው የራሱ እምነት ነው።እንቅስቃሴውን የገታው የራሱ አስተሳሰብ ነው።አለው ባለ ዝሆኑ።"አልገባኝም አለ መንገደኛው። "እንደነገርኩህ ይህች ገመድ ይህንን ዝሆን ያኔ ህፃን እያለ አስርባት የነበረች ገመድ ናት።ገመዷ በውፍረትም በቁመትም አልተለወጠችም።እናም በልጅነቱ የታሰረባት ገመድ በመሆኗ "አሁንም እንደ ልጅነቴ ታቆመኛለች"ብሎ ራሱን አሳምኗል።ገመዷ ልታቆመውም ላታቆመውም እንደምትችል ተታግሎ ሳይሞክር ታቆመኛለች ብሎ አምኗል።በዚህም አስተሳሰቡ ምክኒያት ከታሰረበት ቦታ ነቅነቅ ሳይል ተገትሮ ይውላል። "አየህ የምንሸነፈው አቅም ያጣን ዕለት ሳይሆን ሁኔታዎችን ለመለወጥ ጥረት ማድረጋቸውን ያቆምን ዕለት ነው።ከጉልበት ማነስ ይልቅ የእምነት መኮሰስ፣ከአቅም እጥረት ይልቅ የአስተሳሰብ ጉድለት ወዳቂዎች ያደርገናል። ሲል መለሰለት። @Ibnuseid
إظهار الكل...
👍 4
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.