cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Show more
Advertising posts
14 385
Subscribers
+424 hours
+127 days
-1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ዓለመቱ አሽ–ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ ኢብነኑ ባዲስ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ «በዚህ  ዘመን ሸይኽ ኢቢኑ አብዱልወሃብ ከሌሎች ሰዎች ቀድመው ወደ ቁርኣን ፣ ሱና እና  ወደ ቀደሙት ሰለፉ አስ–ሷሊሒን  መመሪያ በመጣራት ፣ቢድዓዎችን እና ጥመትን በመዋጋት ላይ ይታወቃሉ ። ስለሆነም ወደዚህ ጥሪ ያደረጉ ሁሉ "ወሃቢያህ” ይባል ጀመር።» መጀለቱ «አሽ–ሺሃብ» ቅፅ 10/ ገፅ 261)
Show all...
👍 29
Photo unavailableShow in Telegram
በዚህ አንቀጽ አላህ ተዓላ እርሱን የሚዘክሩ አማኞችን እርሱን ሲዘክሩ በፍርሃት፣ በስጋት እና በርጋታ ገልጿቸዋል። ይህም ከእምነታቸው ጥንካሬ እና ጌታቸውን በማክበራቸው እርሱ ፊት እንዳሉ... ያህል ሲለሚሰማቸው… የመነጨ ነው። እንጂ…… እንደ አህያ ጩኸት የሚያናፉ፣ የሚጮሁ፣ አላዋቂዎች ተራው ሕዝብና ሙብተዲዎች እንደሚያደርጉት አይደለም። በዚህ ( ጭፈራ፣ፉጨት፣ጩሀት…)   ውስጥ ለተሰማራ፤ ይህን ድርጊቱን "ወጅድ" "ኹሹዕ" ነው ብሎ የሚሞግትን ፡- አላህን በማወቅ፣ በመፍራት እና በማወደስ የመልእክተኛውንም ሆነ የባልደረቦቻቸውን ደረጃ ላይ አልደረስክም ይባላል። ” 📚ተፍሲሩ አልቁርጡቢ (7/328) ሱረቱ አል አንፋል አያ (2) ማብራሪያ ይመልከቱ
Show all...
14👍 12
መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!} ~~~~~~~ በሺርክ የተወረረውን፣ በኹራፋት ያበደውን፣ በመውሊድ የታጀበውን የሱፍዮች እስልምና “ነባሩ እስልምና” እያሉ የሚያሞካሹ ጩኸቶችን አልፎ አልፎ እንሰማለን። ይህንን የማይቀበለውን “ወሃቢ” በማለት በሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ የተጠነሰሰ መጤ ኢስላም እንደሆነ ሊነግሩን ነው የሚውተረተሩት። ይህ “ነባሩ” የሚሉት “ኢስላም” ግን ፍፁም እንግዳ የሆኑ መጤ አስተሳሰቦችን አጭቆ የያዘ እምነት ነው። የዚህ ፎርጅድ “ኢስላም” አብይ መገለጫ የሆነውን መውሊድን እንደ አብነት ብንወስድ ደጋፊዎቹ ሳይቀሩ ከነባሩ ኢስላም ውስጥ የማይታወቅ መጤ እንደሆነ መስክረዋል። ለምሳሌ፡- 1. አቡ ሻማ፡- “በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ነገሮች ያማረ ከሆነው የላቀው አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ በያመቱ ከነብዩ ﷺ የልደት ቀን ጋር በሚገጥመው ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎች፣ በጎ ነገሮች፣ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነው።” [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 95] 2. ኢብኑ ሐጀር፡- “የመውሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐ ነው። ከሶስቱም ክፍለ-ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም።” [አልሓዊ ሊልፈታዊ፡ 1/188] 3. ሰኻዊ፡- “የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” [ሱቡሉል ሁዳ ወርረሻድ፡ 1/439] 4. ተዝመንቲ፡- “የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” [አሲረቱ አሻኒያህ፡ 1/441] 5. አልሓፊዙል ዒራቂ፡- “ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናውቀውም።” [ተሽኒፉል ኣዛን፡ 136] 6. ሲዩጢ፡- “የመጀመሪያው ይህን ስራ የፈጠረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዞፈር ነው።” [አልሓዊ፡ 1/189] (መጤ እንደሆነ መናገራቸውን ለመውሰድ ያክል እንጂ ንግግራቸውን ያጣቀስኩት መውሊድ የተጀመረው በሺዐዎች እንደሆነ በማስረጃ አሳልፌያለሁ።) 7. ዘርቃኒ፡- “መውሊድን መፈፀም ቢድዐ ነው።” [ሸርሑል መዋሂብ፡ 1/264] ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ እንደሆነ ግን ባንድ ድምፅ እየመሰከሩ ነው። (وَشَهِدَ شَاهِدࣱ مِّنۡ أَهۡلِهَاۤ) የድሮዎቹ መውሊድ አክባሪዎች ከነ ክፍተታቸው የሆነ ያክል ኢንሷፍ ነበራቸው፣ ሚዛናዊነት። ቢያንስ እንዲህ እቅጩን ይናገራሉ። የዛሬዎቹ ግን አይናቸውን በጨው አጥበው እነ አቡበክርንና እነ ዑመርን ሳይቀር መውሊድ አክባሪዎች ሲያደርጓቸው ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጣቸውም። አንዳንዶቹማ ከዚህም አልፈው ነብዩን ﷺ ሳይቀር መውሊድ አክባሪ ለማድረግ የማያመነቱ ሃፍረተ ቢሶች ናቸው። ነብዩ ﷺ “በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] ስለዚህ አንባቢ አንድ ቁም-ነገር ሊጨብጥ ይገባል። እሱም መውሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ (ስምምነት) መጤ ፈሊጥ ነው፣ ቀደምቶች ሙስሊሞች ዘንድ የማይታወቅ በሺዐዎች የተጠነሰሰ ቢድዐ!! በየመንደሩ ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚበጠብጡ አካላት ይሄ አስደንጋጭ መብረቅ ነው!! “ነባሩ እስልምና” እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት ይድረሳቸው። ነባሩ ኢስላም ማለት የነብዩ ﷺ፣ የሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑ ታቢዒን ኢስላም ነው። የአራቱ አኢማዎች፣ የነ ቡኻሪ፣ የነ ሙስሊም፣… ኢስላም እንጂ የሱፍዮች ኢስላም አይደለም። ይሄ ኢስላም ነባር ካልሆነ የማን ኢስላም ነው ነባር የሚሆነው?! እንዳየነው መውሊድ በደጋፊዎቹም በነቃፊዎቹም ኢጅማዕ ቢድዐ ነው፣ መጤ ፈሊጥ። መጤ ደግሞ በየትኛውም አረዳድ “ነባር” ሊሰኝ አይችልም። ስለሆነም መውሊድና ነባሩ እስልምና ፈፅሞ አይተዋወቁም። ስለዚህ መውሊድን የሚቃወመው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ወዝጋባ ሱፍዮች እንደሚሉት የሃያና የሰላሳ አመት እድሜ ያለው ወይም በ “ወሃብዮች” የተጀመረ አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ስሩ ከነብዩ ﷺ ዘንድ የሚዘልቅ ከሱፍዮቹ የተንሻፈፈ አረዳድ የቀደመ ጥንታዊ ነው ማለት ነው። ከ “መውሊድ፤ ታሪክ፣ ግድፈት፣ እርምት” መፅሐፍ ተነካክቶ የተወሰደ
Show all...
👍 20
Photo unavailableShow in Telegram
ኢማሙ አሰኻዊ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ "የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንዳቸውም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” 📖(ሱቡሉልሁዳ ወርረሻድ፡ 1/439) 🔁 https://t.me/sultan_54
Show all...
👍 7
قال ابن القيم رحمه الله:  (لما كثر المُدّعون للمحبة، طولِبوا بإقامة البيّنة على صحة الدعوى، فتأخر الخَلق كلُهم وثبت أتباع الحبيب في أفعاله وأقواله وأخلاقه)  📚 مدارج السالكين(3/8)
Show all...
👍 9
02:27
Video unavailableShow in Telegram
لا مجاملة في الدين…
Show all...
25.97 MB
👍 10
አል ፋክሃኒይ መውሊድ ስለማክበር ሲጠየቁ፦ “ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም ሆነ በሱና ውስጥ  መነሻ  አላውቅልትም። የመውሊድ ስራ በሃይማኖት አርአያ ከሆኑ እና የቀደምት የዲን አባቶች ትውፊት አጥብቀው ከያዙ ከሆኑ የሀገሪቷ ምሁራን የተላለፈ አይደለም። ይልቁንም ከንቱ የሆኑ ሰዎች ትኩረት ያደረጉበት ሥራ ፈት ሰዎች ያመጡት አዲስ ፈጠራ እና የነፍስ ስጋዊ ፍላጎት ነው።” 📚(አልፋክሃኒ /አልመውሪድ ፊ ዐመሊ አልመውሊድ) ገፅ(20)
Show all...
👍 10👌 7
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.