cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ

"አላህ እንዳንተ አይነት መፍጠሩን ቀጥሏል ብዬ አላስብም ነበር፡፡" ኢብኑ ደቂቀል ዒድ "ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!" ኢብኑል ሐሪሪ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏሂ] የተጻፈ መጽሐፍ፡፡

Show more
Advertising posts
664
Subscribers
-124 hours
+77 days
+2030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🍀የንጋት ቅምሻ🍀 📖 ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐብይ! ሶሐባው ሰዕድ ኢብን አቢል ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡፡በአንድ ወቅት ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ከነቢዩ (ዐለይሂሰላም) ቤት ሊገባ ፍቃድ ጠየቀ፡፡ ከነቢዩ (ዐለይሂሰላም) ዘንድ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያወሩ ሴቶች ነበሩ፡፡ የዑመርን ድምፅ ሲሰሙ ሒጃባቸውን አስተካክለው ሊለብሱ ተሯሯጡ፡፡ ረሱል (ዐለይሂሰላም) እየሳቁ ለዑመር እንዲገባ ፈቀዱለት፡፡ ዑመርም “አላህ ጥርስህን ያስቀው የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አላቸው፡፡ ነብዩም (ዐለይሂሰላም) “እነዚህ እኔ ጋር የነበሩ ሴቶች ገረሙኝ፡፡ ድምፅህን ሲሰሙኮ ወደ ሒጃባቸው ተሯሯጡ” አሉት፡፡ ዑመርም “አንተ ነህ ልትከበርና ልትፈራ የሚገባህ ያረሱለላህ” ካለ በኋላ “እናንተ የነፍሶቻችሁ ጠላቶች እኔን ትፈራላችሁ የአላህ መልእክተኛን አትፈሩምና?!” ሲላቸው “አዎ ከረሱል (ዐለይሂሰላም) ይልቅ አንተ ደረቅና አስፈሪ ነህ” አሉት፡፡ ከዚያም ረሱል (ዐለይሂሰላም) እንዲህ አሉ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ ሸይጧን በአንድ መንገድ ላይ በጭራሽ አያገኝህም መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ ቢሄድ እንጂ” ቆይማ እዚች ጋ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ሺዐዎች የዑመር ስም ሲነሳ በጥላቻ እብደታቸው እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ድረስ ይሄ ነገር በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እ.ኢ.አ በ2005 ኢራቅ ውስጥ 15 ሰዎች ስማቸው ዑመር ስለሆነ ብቻ በሺዐዎች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ በርካታ ዑመሮች በሌላ ሳይሆን በስማቸው ብቻ ከስራ ተባረዋል፡፡ ዑመርን ምን ያህል ቢጠሉት ነው በስም ብቻ እንዲህ የሚደረገው? ሌላ ነገር፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ዐለይሂሰላም) መስጂድ ካሉት በሮች ውስጥ አንዱ “የዑመር በር” ነው፡፡ ታዲያ ሺዐዎች ምን አሉ “ለዑመር ካለን ጥላቻ የተነሳ ወደ መስጂዱ ስንገባ በዑመር በር በኩል አንገባም” አሉ፡፡ አንዱ ዐሊም ምን አላቸው “ረዲየላሁ ዐንከ ያ ዑመር! ሸይጧን በህይወትህ ሳለህ ብቻ አይለም ሞተህም ይሸሸሃል!!!” አላሁአክበር!!! ©Ibnu Munewor 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Show all...
ማነህ?

መኖርህ ምንድነው ጥቅሙ? በመሞትህ የምታጣ ነገር አለን?

~ደስ የሚለው ነገር…ጠዋት ላይ የምትወጣው ፀሐይ ብቻ አይደለችም፡፡ለመኖር ተስፋ እንዲኖረን የሚገፋፉ መልካም ሰዎች፣ማማረር እንደማይገባንና በሕይወት ለመቆየት ብዙ ምክንያት እንዳለን የሚመመክሩ ደጋግ ባሮችም አብረዋት ይወጣሉ፡፡ አላህን የሚያስታውሱን ዉብ ፊቶችም ይወጣሉ፡፡ ነግቶ እስክናያቸው የምንጓጓላቸው፣ የምንወዳቸው፣ የምንናፍቃቸው ሰዎችም ይወጣሉ፡፡ አላህ ያቆይልን። እናንተን በማየቴ ደስ ብሎኛል በሉ፡፡ ተደሰቱ!።ሰዎችም ከአንደበታችሁ በሚወጣው ቃል ይደሠቱ፡፡ =t.me/AbuSufiyan_Albenan
Show all...
👍 2
የመውሊድ ማምታቻ ሹብሀዎች ....? ሙብተዲዕ ማለት አይጥ ማለት  ነዉ! 🎙በኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ t.me/Darutewhide
Show all...
መውሊድ.mp33.96 MB
እውነታው ይኸው ነው * በሰሞኑ በኦሮምያ ክልል ባሌ አካባቢ በአንድ የመንግስት ታጣቂ ፖሊስ የተደበደበችው እህት እውነታው ከቦታው በማጣራት እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ። ይህን ክስተት ያጣሩልን ወንድም ነዋሪነታቸው በሳዑድ አረቢያ የሆነ አሁን ላይ ለቤተሰብ ጥየቃ የመጡ ሸይኽ ሮቤ ይባላሉ። 1- የተደበደበችው እህት ሙስሊም እንጅ የሌላ ሀይማኖት ተከታይ አይደለችም። [ሙስሊሟን እህት በውሸት ማክ — ፈር ተገቢ ነውን?] 2- የደበደባት ፖሊስም ወደዚህ ጣቢያ ከተመደበ ገና ወራቶችን ያስቆጠረ ሙስሊም ነው። 3- ይህች ተበዳይ በዋስ ያስወጣት ሙስሊም የሀገር ሽማግሌ ነው። 4- አሁን ከቪድዮው ፖሊሱ ቀርቦ የሰጠው ምላሽ ይህች እህት ተጠርጣሪ ሆና በማየቱ በስሜት እና ተገቢ ባልሆነ መንገድ አፀያፊ ተግባር ፈፅሜያለሁ ፤ ለዚህም የርሷ እና የኔ ጉዳይ በሀገር ሽማግሌ ተይዞ የኔም የርሷም ጎሳ ቀርበው በተነጋገሩት መሰረት ክብሯን እና በደሏን የሚመልስ ነገር ባይሆንም ለመካስ ተስማምተናል ይለናል። ይህ ጉዳይ እንዳይደገም: ሀቅ እንዳይደበቅ ጊዜውን ሰጥቶ አቀራርቦ ከዚህ ደረጃ ያደረሳቸውን ሸይኽ ሮቤ አላህ ጀዛህን ይክፈልህ። እውነታው ይህ ነው ። ኢንጅነር አብዱ ሙሃመድ = ማሳሰቢያ ~ ሰሞኑን የሌላ እምነት ተከታይ የሆነች የታወቀች ሌባ ናት፣ ሌላ ጊዜ ወንድ ነው የሚሉ ቅንብሮችን አዘጋጅተው የለቀቁት ሆን ተብሎ የታሰበበት ተንኮል ነው። አላማው በተበዳይ እህታችን ሂሳብ ወንጀለኛን መደበቅ፣ አጀንዳ ማስቀየር ነው። ስንት ህዝብ በእህታችን ላይ እንደፈረደ አስቡት። ውጤቱ ግን ከዚህም የከፋ ነው። ከዚህ በኋላ እህቶቻችን ላይ የሚደርስ በደል በቂ ግፊት እንዳይገጥመው የሰውን ስነ ልቦና የሚያቀዘቅዝ፣ ለኒቃብ ጠል ሃይሎች ግብአት የሚሆን ትወና ነው ሰሞኑን የተሰራው። ከመጀመሪያም ጀምሮ አንዴ ሙስሊም ያልሆነች አመለኛ ናት፣ አንዴ ወንድ ሆኖ ተገኘ ሲባል በጣም ነው ያመመኝ። ይበልጥ ያመመኝ የሰውን ሃሳብ በማሳሳት ላይ የተሰማሩት ታዋቂ አክቲቪስቶች መሆናቸው ነው። ነገሩን በቅንነት በየዋህነት ተመልክታችሁ በነዚህ አካላት የተሸወዳችሁ ወገኖች ትምህርት ውሰዱ። ያለፈውን መመለስ ባንችል እንኳ ይህኛውን በደንብ "ሼር" በማድረግ ትንሽም ብናካካስ ደስ ይለኛል። በምትችሉት መጠን ሁሉ ሼር አድርጉት። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ክፍል-7 [2.2.1] #መውሊድን_ማን_ጀመረው? ሐሰን ታጁ መውሊድን የጀመሩት "ፈጢሚዮች ናቸው" የሚለውን ሀሳብ እንደማያምንበትና እንደማይቀበለው ገልጿል። በርግጥ አለመቀበል መብቱ ነው። ይሁን እንጂ "ፋጢሚዮች ናቸው የጀመሩት" የሚሉ ሰዎች እንዲህ የሚሉት "ምናልባትም ከፍትሃዊው ንጉስ ከመሊክ ሙዞፈር ጋር መያያዙ የትችታቸውን ግለት ስለሚቀንሰው ወይም ተአማኒነቱን ክፉኛ ስለሚጎዳው ይመስለኛል " ማለቱ አንድም በሀሳብ የማይጋሩትን ሰዎች በመሰለው ከመወረፍ የማይመለስ መሆኑን ሁለትም ነገሮችን የሚለካበት ሚዛን የተዛነፈ መሆኑን ነው የሚያሳየው። እንጂ ሙግቱን ተቀብለን "ሙዞፈር ፍትሃዊ ነበር"ብንል እንኳ በምን ስሌት ነው የንጉሳን ስራ መለኪያ ሆኖ የሚቀርበው? አይደለም ባለስልጣናት ታላላቅ ዓሊሞች ሳይቀር ባላሰቡት መልኩ ቢድዐህ ላይ ሲወድቁ ያጋጥማል። ለዚህ በርካታ ተግባራዊ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል። የአህሉስሱንናህ አካሄድ ግን ከታላላቆች ስለመጣ ብቻ ሳያጣሩ መቀበል ሳይሆን የትኛውንም ከመረጃ ጋር የሚጋጭ ነገር እርምት በመስጠት ነው የሚታወቀው። ስለመውሊድ አጀማመር የተሰጡ ሀሳቦች ባሉኝ መረጃዎች መሰረት ሶስት አይነት ናቸው። 1️⃣. አንደኛው በንጉስ አልሙዞፈር፣ አቡ ሰዒድ ኩኩቡሪ (630 ዓ.ሂ) ኢርቢል ላይ ነው የተጀመረው የሚል ነው። 2️⃣. ሌላኛው ሀሳብ ደግሞ መውሊድ በሸይኽ ዑመር ኢብኑ ሙሐመድ አልመላ (571 ዓ.ሂ) መውሱል (ዒራቅ) ውስጥ ነው የተጀመረው የሚል ሲሆን ይህንን ሀሳብ አቡ ሻመህ (665 ዓ.ሂ) የጠቀሱት ሲሆን ሙዞፈር ከሱ እንደወሰደ ይናገራሉ። [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 24] ይህንን እውነታ ሲብጥ ኢብኑል ጀውዚም ገልፀውታል። [ሚርኣቱዝዘማን፡ 8/310] ኢብኑ ከሢር ከሸይኽ ዑመር መውሊድ ላይ ንጉሳን፣ አሚሮች፣ ዑለማዎችና ሚኒስትሮች እንደሚካፈሉ መጥቀሳቸው ይሄኛው መውሊድ አፈፃፀሙ "ህዝባዊ" የሚባል አይነት እንደሆነ ያመላክታል። [አልቢዳያህ ወንኒሃያህ፡ 12/263] ስለዚህ "በመንግስት ደረጃ ስላልተፈፀመ ብቻ ህዝባዊ አይባልም" ካልተባለ በስተቀር ሙዞፈር ነው የጀመረው የሚለውን ትርክት ይሄኛው ሀሳብ ፉርሽ ያደርገዋል። 3️⃣. ሶስተኛው ሐሳብ መውሊድን ግብፅ ላይ የጀመሩት "ፋጢሚያህ" ሺዐዎች ናቸው የሚል ነው። እነዚህ ሺዐዎች ግብፅ ላይ የነገሱት ከ 357 ዓ.ሂ ነው። ይሄኛው ሀሳብ የቀደመ እንደመሆኑ ያለፉትን ሁለቱንም ሀሳቦች ይደመስሳል ማለት ነው። ስለዚህ በአጀማመሩ የጊዜ ቅደም ተከተል ስንመለከት "ፋጢሚዮች" ግብፅ ላይ እንደጀመሩት ግልፅ መረጃ አለ። ቀጥሎ ደግሞ ሸይኽ ዑመር አልመላ መውሱል ላይ እንደጀመረውና ድግስም ላይ ንጉሳን ይካፈሉ እንደነበር አቡ ሻማህ ገልፀዋል። ቀጥሎ ከሳቸው #በመኮረጅ ንጉስ ሙዞፈር ኢርቢል ላይ ጀምሮታል። ስለዚህ በመረጃ ለሚየያምን ሰው የመውሊድ ጠንሳሾች ሺዐዎች ናቸው። የባጢኒያ ሺዐዎችን ሴራና ክፋት በማንሳት የሚሰነዘረውን ትችት ለመሸሽ ሲባል "ሙዞፈር ነው የጀመረው" ብሎ ችክ የሚል ካለ በዚህ ድርጊቱ እራሱን እንጂ ማንንም አይሸውድም። ሙዞፈር ከሺዐህ ክልል ውጭ ባሉ የሙስሊም ግዛቶች ውስጥ መውሊድን በማክበር #ከመሪዎች የመጀመሪያው #ንጉስ ነው ማለት ግን ይቻላል። ሐሰን ታጁ "ፋጢሚዮች ናቸው የጀመሩት" የሚለውን ሀሳብ እንዳለ ቢያምንም በዚያኛው ወገን ያለውን መረጃ እንዳቀረበው የዚህኛውንም አላቀረበውም። የማነፃፀር ስራም አልሰራም። ከዑለማእ ያንፀባረቁትንም አልጠቀሰም። "ምን ያክል ክብደት አለው?" የሚለውንም አልፈተሸም። ይልቁንም "ድርጊታቸውን በደጉ እንተርጉምላቸው ካልን ለዘመናት ተረስቶ የኖረውን የአህሉል በይት ክብር ለመመለስ አንድ እርምጃ ወደፊት እንደተራመዱ ይቆጠራል" ይላል። አለፍ ብሎም "የለም ክፉዎች ስለሆኑ የህዝብ ሙስሊሙን ዐቂዳ ለመበከል የሸረቡት ሴራ ነው የሚል ክፉ ጥርጣሬ መኖሩን ሳንዘነጋ" ይላል። [መውሊድ፡ 55] እዚች ጋ አንዴ እንቁምማ፦ 1️⃣. "የአህሉል በይት ክብር በሱንናው አለም ተረስቶ ሺዐዎች መለሱት" ማለት ግልፅ ጥፋት ነው። በአንዳንድ ፖለቲከኞች ስለተገፉ "ክብራቸው በሺዐዎች እስከሚመለስ ድረስ ተረስቶ ቆይቷል" ማለት የተንሻፈፈ ፍርድ ነው። 2️⃣. የአህሉል በይት ክብር የሚመለሰው በመውሊድ ነው የሚል ካለ ያለጥርጥር ስማቸውን ለርካሽ ቢድዐው ማሻሻጫ እየነገደበት ነው። በውስጡም "ሰለፎች የአህሉል በይትን ክብር ዘንግተው ኖረዋል" የሚል ክስ አለበት። 3️⃣. ደግሞስ ዲንን ለማጥፋት ሲታትሩ፣ ዑለማዎችን ሲጨፈጭፉ የነበሩ የ"ፋጢሚዮችን" ድርጊት በጥርጣሬ መመልከት እንዴትስ "ክፉ ጥርጣሬ ይባላል?!!" ለዑበይዲዮች መልካም ጥርጣሬ እየሰጠህ "ወሃቢዮች" ለምትላቸው ግን ክፉ ጥርጣሬ ሐሰን?! ፍርደ-ገምድልነትህ ለከት አላጣም?! 📚 መውሊድ ታሪክ፤ ግድፈት፤ እርምት ለሐሰን ታጁ መውሊድ መጽሐፍ የተሰጠ ምላሽ ገጽ 60-62📚 📔 ዝግጅት ሙሐመድ አሕመድ ሙነወር ✍️ ابو رسلان 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Show all...
00:53
Video unavailableShow in Telegram
ቁርዓን በምን በምን ይተረጎማል 🎙 ዓብዱሶመድ ሙሐመድ ኑር 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Show all...
13.79 MB
ክፍል-6 [2.2] #ታሪካዊ_ብዥታ፣ #የመውሊድ #ታሪካዊ_አመጣጥ [2.2.1] "ይቺ ጠጋ ጠጋ እቃ ለማንሳት ነው" ሐሰን ታጁ መውሊድን "የነፍስ-ወከፍ" እና "ኦፊሴል" ሲል ለሁለት ከፍሎታል። የነፍስ-ወከፍ ማለት እሱ ዘንድ የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም ሲሆን የኦፊሴል የሚለው ደግሞ በ7ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ ላይ ንጉስ ሙዞፈር የጀመረው ነው። ሊለን የፈለገው በተለያዩ ምክንያቶች ዘገየ እንጂ የዛሬው መውሊድ ከነብዩ ﷺ አስተምህሮት መሰረት አለው ነው። እንዲያውም በድፍረት መውሊድን ከነብዩ ﷺ አስተምህሮት መሰረት አለው ነው። እንዲያውም በድፍረት መውሊድን በነፍሰ-ወከፍ ደረጃ የጀመሩት እራሳቸው ነብዩ ﷺ እንደሆኑ ይናገራል። ይሄ በጣም አደገኛ የሆነ ድፍረት ነው። በነብዩ ﷺ ላይ መዋሸት በሌላ ከመዋሸት የከፋ ነው። "በኔ ላይ መዋሸት በማንም ላይ እንደመዋሸት አይደለም። ሆን ብሎ በኔ ላይ የዋሸ መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ" ሲሉ አደጋው ከፍ ያለ እንደሆነ እራሳቸው መልእክተኛው ﷺ ተናግረዋል። [ቡኻሪ፡ 1291፣ ሙስሊም፡ 5] ስለዚህ ይሄ "የነፍስ-ወከፍ" እና "ኦፊሴል መውሊድ" ብሎ መከፋፈል ድፍረት የተሞላበት መሰረተ-ቢስ ክፍፍል ነው። እራሱ ሐሰን ታጁ ከሚያጣቅሳቸው ዑለማዎች አንዱ የሆኑትን የሰኻዊን ንግግር ብደግ እንዲህ ይላሉ፦ "የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች #ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።" [ሱቡሉልሁዳ ወርረሻድ፡ 1/439] እኚህ ሸይኽ የመውሊድ ደጋፊዎች ከሚያጣቅሷቸው ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ናቸው።ሆኖም ግን ሐሰን ታጁ ኢብኑል ዐለዊን በማጣቀስ ምን እንዳለ ተመልከቱ። "መውሊድ በግለሰብ ደረጃ መከበር የጀመረው በነብዩ ﷺ ዘመን በራሳቸው በመልእክተኛው ﷺ ነው። ይህም በመሆኑ በፋጢሚዮች ዘመን እንደተጀመረ የሚናገሩ ሰዎች አንድም መሃይምን፣ አለያም እውነቱን የሚያድበሰብሱ ናቸው።" መሀይሙ ወይም አድበስባሹ ማን እንደሆነ በመረጃ የምናየው ይሆናል። እስከዚያው ግን እንዲህ እንበል። ይሄ ቢድዐህ በግለሰብም ደረጃ ይሁን በመንግስት ደረጃ በነብዩ ﷺ ዘመን አልነበረም። በሶሐቦችም፣ በታቢዒዮችም፣ በአትባዑትታቢዒንም፣... ዘመን አልነበረም። "አይ ነበር" የሚል ሰው የማይገናኙትን የሰኞንና የዓሹራን ፆም ከሚያጣቅስ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ አመት ጠብቀው ልደታቸውን ያከብሩ እንደነበር የሚያሳይ መረጃ ሊያቀርብ ይገባል። ይህን ደግሞ ማንም ቢሆን {ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባ ድረስ} ሊያደርግ አይቻለውም። ለዚህ ግልፅ መረጃ ቢቀርብማ ይሄ ሁሉ ንትርክ ቀድሞም ባልተከሰተ፣ ቢከሰትም መቋጫ ባገኘ ነበር። ነብዩ ﷺ እና ምርጥ ሶሐቦቻቸው መውሊዳቸውን ያከብሩ ነበር የሚል ሰው ከሚከተሉት ጥያቄዎች አንዷን ሊመልስ አይቻለውም። 1️⃣. የመጀመሪያው መውሊድ በየት ቦታ ተከበረ? 2️⃣. የመጀመሪያው መውሊድ በስንተኛው ዓመተ-ሂጅራ ተከበረ? 3️⃣. በየ አመቱስ በየትኛው ወር በስንተኛው ቀን ነበር የሚከበረው? 4️⃣. ነብዩ ﷺ በህይወታቸው ስንት መውሊዶችን አክብረዋል? 5️⃣. መውሊድ ላይ የሚባሉ መንዙማዎች፣ ነሺዳዎችና ግጥሞች ምን ምነ ነበሩ? 6️⃣. መውሊድ ላይ ይቀርቡ የነበሩ ምግቦች፣ የታረዱ እርዶች ምን ምን ነበሩ? 7️⃣. በእያንዳንዱ ኸሊፋ ዘመንስ ስንት መውሊድ ተከበረ? 8️⃣. ከነዚያ ከመቶ ሺህ በላይ ከሚበልጡ የነብዩ ﷺ ሶሐቦች ውስጥ አመት ጠብቆ ልደታቸውን ያከብር የነበረ ሁለት ሳይሆን አንድ ሶሐባ ጥቀስ። እነዚህን ጥያቄዎች አንድም የመውሊድ አቀንቃኝ ሊመልሳቸው አይችልም። በግለሰብ ደረጃ የለ በመንግስት ደረጃ የለ!! አንድም መረጃ ሊቀርብ አይችልም። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ "ግለሰባዊ አከባበር" "ህዝባዊና ኦፊሴላዊ አከባበር" እያሉ መፈላሰፍ ርካሽ የሆነ የክርክር ስልት ነው። ከነብዩ ﷺ ህልፈት አንስቶ ሶስት መቶ አመት ቢቆጠር መውሊድን በግለሰብ ደረጃ እንኳን ያከበረ አንድም ሰለፍ አይገኘም። 📚 መውሊድ ታሪክ፤ ግድፈት፤ እርምት ለሐሰን ታጁ መውሊድ መጽሐፍ የተሰጠ ምላሽ ገጽ 58-59📚 📔 ዝግጅት ሙሐመድ አሕመድ ሙነወር ✍️ ابو رسلان 👉 @Twehid12 👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.