cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ስብዕናችን #Humanity

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Show more
Advertising posts
29 264
Subscribers
-1124 hours
-897 days
-36630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌗ንብ እና እርግብ ተገናኝተው እየተጫወቱ ነው። እርግብም በማፅናናት መንፈስ ሆና <<እኔ የምልሽ ወይዘሪት ንብ እንዲህ ታትረሽ እየሰራሽና ማር እያመረትሽ የሰው ልጅ ግን ያንችን ማር እየሰረቀ እየበላና እየሸጠ ሲኖር ባንቺ ልፋት ሲከብር አያሳዝንሽም>> ? እርግብ ጠየቀቻት። ንብ እንዲ ስትል መለሰች "በፍፁም አይሰማኝም፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ማሬን እንጂ ማር የማዘጋጀት ጥበቤን ሊሰርቀኝ አይችልም፡፡" 💡ሰዎች ብልጠታቸውን ተጠቅመው ገንዘባችንን፣ ያለንን ንብረት ሊወስዱብን ይችላሉ፤ ነገር ግን ያን ሁሉ እንድናፈራ ያስቻለንን እውቀትና ጥበብ መስረቅ አይችሉም፡፡ ስለዚህ በተወሰደብህ ነገር ላይ አትብሰልሰል። ባለህ እውቀት ላይ ትኩረትህን አድርግ። ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በተናደ ጊዜ ይህንን ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያህም ቢሆን ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ። የአሰራሩ ጥበብ እና ልምድ ያለው አንተ ጋር ነውና። 📍ከውድቀትህ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍራ፡፡ እንደገና ስትጀምር እኮ የምትጀምረው ከዜሮ ሳይሆን ከስህተትህ ትምህርትና ልምድ ካገኛችሁበት ደረጃ በመነሳት ነው። ከትናንትናው ዛሬ አድርገሀል ፣ ተለውጠሀል፣ በስለሀል ፣ ጥበብ አግኝተሀል ፣ በርትተሀል፣ ነገሩ ገብቶሀል ማለት ነው ፡፡ 🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።            ውብ አሁን❤️                    @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Show all...
👍 43 34
Photo unavailableShow in Telegram
👍 4
የአለማችን ትልቁ የክሪፕቶ platform ባይናንድ  የራሱን moonbix የተሰኘ የቴሌግራም ቡት ይዞ መጥቷል። የቴሌግራም የዚህ አመት ለውጥ አስገራሚ ነው። https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_339245018&startapp=ref_339245018&utm_medium=web_share_copy
Show all...
Moonbix

Moonbix is a Binance crypto-themed game on Telegram Mini App game. Explore the galaxy, collect items, and boost your score!

Photo unavailableShow in Telegram
💡የሆነ መንደር ውስጥ አንድ ጅል ይኖራል። የመጨረሻ ጅል ከመሆኑ የተነሳ አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አይችልም። እና የመንደሩ ነዋሪዎች ይመጡና "አንተ ጅል ና እስቲ ከዚህ ምረጥና ውስድ" ብለው አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም ሲያስቀምጡለት አስሯን ያነሳል። "ይሄ (አምሳውን) ይሻልሃል" ሲሉት "እምቢ ብሎ ያለቅሳል። 🔆 "አይ ይሄ ጅል … ኑ ጉድ እዩ፤ ኑ ጉድ እዩ" ይሉና አስር ሳንቲም እና አምሳ ሳንቲም ድጋሚ ያስቀምጡለታል። አሁንም አስሯን ያነሳል። ኧረ ይሄ ይሻልሃል ሲሉት "እምቢ፣ እምቢ" ብሎ ያለቅሳል። በኋላ በዚህ ጅል ዘመዶቹ እያፈሩ ሄዱ። አንዱ ዘመዱ መጣና "አንተ ጅል … ሁሌ ባንተ እንዳፈርን እንቅር? ኧረ ተው ግድ የለህም፣ ተው ግድ የለህም። አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አቅቶህ አምሳ ሳንቲም ሲሰጡህ በአስር ሳንቲም ታለቅሳለህ? ኧንደው ምናለ አምሳውን ብታነሳ?" ብሎ ሲመክረው። "ጅልስ አንተነህ ነህ! አምሳውን ያነሳው ቀን አያስመርጡኝም። 🔆ማነው ጅል? እነሱ ወይስ ጅል ብለው የሚያስቡት ብልጥ? አያችሁ እሱ ብልጥ ጅል ነው፤ እስከ ኖረ ድረስ አስር፣ አስር ሳንቲሟን እየመረጠ የተጃጃለ መስሎ ያጃጅላቸዋል፤ ምክንያቱም አምሳዋ አንዴ ነች፤ አስሯ እስካለ ትቀጥላለች። 💡እንደነሱ ከሆነ አምሳ ሳንቲሟን የብልጠቱ፣ አስር ሳንቲሟን ደግሞ የጅልነቱ መገለጫ አድርገዋታል። ለሱ ግን አስር ሳንቲሟ የብልጠቱ መሰወሪያ፣ መደበቂያ ነች። አምሳዋን የመረጠ ቀን ጅልነቱ ያበቃል፤ ማንም አያስመርጠውማ። ምክንያቱም አውቋል፤ ነቅቷል ይሉታላ። ✍ዓለማየሁ ገላጋይ ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን😁 @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Show all...
60👍 35
Photo unavailableShow in Telegram
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ 🌼አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ ከትላንት ስህተቶች የምንማርበት፣ አዲስ አላማ ቀርፀን የምናሳካበት፣ ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን !  🌻ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፤ ❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን እንመኛለን። መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን 💛 ስብዕናችን 💛 @EthioHumanity @EthioHumanity
Show all...
42👍 17
🌍ምክር ለወዳጅ 📍ወዳጄ ሆይ ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነትህ እንደ ወንዝ ይሁን! ሳትመርጥ፣ ለለመነህ ሁሉ እጅህን ዘርጋ። ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት ይኑርህ። መርዳት ዕድል ነውና ተጠቀምበት ፡፡... ሌላው የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ በዝምታ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ሌሎችን ከፍ እንደማድረግ ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ፤ እንዲህ ደግ ሰራው እያሉ መጮህ የደግነትን ክብር ይነካል፤ እንደ ወንዝ በዝምታ፤ ለሌሎች መልካም መሆን ነው እውነተኛው ደግነት ነው። ወደኛ የመጣች ደግነት ወደሌሎቹ ካልሔደች ደስታ አይኖረንም  የተቀበልነውን ደግነት እኛም ለሌሎች እናሳይ፡፡ ጥሩ ሥራን ለሕሊና ምግብነቱ እንጂ ለሰማይ ሽልማቱ ብቻ አትሥራው ። የመልካም ነገር ዋጋ ከፋይ ፈጣሪ መኖሩንም እመን ። 📍ወዳጄ ሆይ ! ባለሀብት ብዙ ያለው ሳይሆን ካለው ብዙ የሚሰጥ ነው።ከሚደልሉ አንደበቶች የሚመፀውቱ እጆች እጅግ ይልቃሉ ። ልግስና ማለት የኪሳችንን ቦርሳ መክፈት መቻላችን ብቻ ሳይሆን ልባችን መክፈት መቻላችን ነው። አንተም ለመልካም ስራ እጅህን ለግስ "ልግስና የነፍስ ምግብ ነውና'' ደስታ ለሚሰጥ አብዝቶ ይመለስለታል። ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈስህንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል። ታላቅ የሆነ ጥበብ እና ማስተዋልንም ይዞልህ ይመጣል ። ደስተኛ የመሆን ቀላሉ መንገድም መልካም ነገር ማድረግ ነው። ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሰሩት ስራ ሁሌም ውብ ነውና። 📍ወዳጄ ሆይ ! አቅመ ደካማን ሰው ጥሪቱን ብትገፈው የምታጌጠው በተቀደደው ልብሱ ነው ፣ ድሀን ዘርፈው ባለጠጎች የሆኑም ሲያፍሩ የሚኖሩ ናቸው ። አንተም የግፍን እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ!! ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል። ፈጣሪ መስረቅን በትእዛዙ ቢከለክልህም ፣ የዘረፍከውን እንዳትበላ ግን በፍርዱ ያግድሃል።ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣.........የቆምን መስሎን የዘነጋን ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል። 📍ወዳጄ ሆይ ! ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ።መልካም ዘር ዘርተህ መልካም ምርት እፈስ፣ፍቅር የዘራ ፍቅር ያገኝል። ጥላቻ የዘራም ጥላቻ ያመርታል። ቅሬታ የተከለ ቅሬታ ይለቅማል። መልካም ዘር የዘራ መልካም ፍሬ ያጭዳል።አለም የአስተሳሰብህ ግልባጭ ናት፣ መስታወትህም ናት። 📍ወዳጄ ሆይ ! ከሚንጫጫ ብዙ ፣ ዝም ያለውን አንድ ሰው ፍራ ። ከሚጮኸው ውሻ ፣ የማትጮኸው ግመል ብዙ በረሃ ታቋርጣለች ። ያነበበ ቢተኛ እንኳ ነቅቶ የተኛ ነው ። ሳታነብ ሰው ሁሉ ከሚወድህ አንብበህ ብቸኛ ብትሆን ይሻላል ። ዓለም በጫጫታና በመዋከብ ውስጥ ብቻ ትልቁ ደስታ ያለ ይመስላታል፣ ዝም ያለች ጥበብ ግን አጥብቆ ለሚሻት እጅጉን ቅርብ ናት። ብልህና ትጉ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ላይ ላሉበት ክፍተቶች በዙሪያው ከሚያስተውላቸው የቀን በቀን ክስተቶች እርማርትን ነቅሶ ይወስዳል፣ በሌሎች ላይ የሚመለከተውን ደካማና እኩይ አካሄድንም በራሱ ላይ እንዳይታይ በመጠንቀቅ እራሱን ወደተሻለ አቋም ያሸጋግራል! 📍ወዳጄ ሆይ ! ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!  መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሁሌም ከሰዎች ውስጥ መልካም ገጻቸውን ፈልገህ አንጥረህ ተመልከት፣ ጥሩነታቸውን በማድነቅ ገንባ፣ ከአፍህ መልካም ቃል ይውጣ፤ መልካም ዘር ዝራ።ሰው የሚዘራውን ያጭዳልና መልካም ዘር ዝራ። ልብ በል! ክፋት፣ ጥላቻ፣ ቂም፣ ቅሬታ አይጠቅሙህም። ይልቅስ ይጎዱሃል፣ በሽታ ያመጡብሃል፣ ወደታች ይስቡሃል። 🔑እናም ወዳጄ ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።ሰዎች የዘሩትን ሲያጭዱ ስታይ አንተም ዛሬ እየዘራህ ነገ ደግሞ የምታጭድ መሆኑን አስብ። አለም ሁሉ ሲዋዥቅ፣ ሳትዋዥቅ የምትኖር እውነት ብቻ ናት ።        መጪው ዘመን ሰላማዊ እንዲሆን                 ፈጣሪ ይዘዝልን❤️ ውብ አዲስ ዘመን😊 @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Show all...
43👍 37
Photo unavailableShow in Telegram
6👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
💎በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ አንድ ቀን ስለ ዉልደትና ሞት ፍልስፍና ሲወራ በዋለበት የአንድ ወዳጃችን ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከድር ሰተቴ የተወራውን ሁሉ ሲታዘብ ቆይና እንዲህ ብሎን ጥሎን ወጥቶ ሄደ ። "ቢተኮስ ቢፎከር እኛ ምን አስፈራን ሰተት ብለን ገብተን... ሰተት ብለን ወጣን" ሰተት ብለን በዉልደት በር እንደገባን ፣ በሞት በር ደግሞ ሰተት ብለን ዉልቅ እንላለን ። ብልጭ ብላ ድርግም እንደምትል ብርሃን ነን።... መነሻዋም ሆነ መድረሻዋ በግልጽ የማይታወቅ ብርሃን ። 📍ይህን ጥያቄ መመለስ ሳይሆን፣ ሰዉ የመሆን ቁም ነገሩ በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ። በመጠላለፍ  ብልጣ ብልጥነት ሳይሆን በመደጋገፍ ሰዋዊነት። የክፋት ጠቢባን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ያበጁልንን ቦይ ትተን የነብሳችንን እንከተል። ፈጣሪ የሰው ልጅን በእድሜው ብራና ላይ የየራሱን መልካም ታሪክ ይከትብ ዘንድ በስጋና ነፍስ ፈጥሮታል፣ የልባችሁን ሀቅ በመከተል ለሚደርስባችሁ የትኛውም ግፍ ፈጣሪ ከእናንተ ጎን ለመቆሙ አትጠራጠሩ።           📓መንገደኛዉ ባለቅኔ           ከድር ሰተቴ ውብ ምሽት❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Show all...
52👍 22
t.me/empirebot/game?startapp=hero339245018 🔥Play with me, grow your startup. 💸 +5k coins as your first gift 💵 +25k coins if you have Telegram Premium
Show all...
X Empire

Build your own empire!

🌗በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ በስተመጨረሻም ቀናቶቹ ሁሉ ትርጉም አልባ ሆኑበት፡፡ 📍የ”አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ይመስለኛል፡፡ እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው፡፡ ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አያምንም ነበር። ሃይማኖቶች እግር ይከዳቸዋል፡፡ …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም፡፡ በዚህች ሰከንድ በሰውነታችን ውስጥ ህዋሳት እየሞቱ እራሳቸውን ባያድሱ ህልው መሆን አንችልም፡፡ ሞት እንደብዙዎቻችን እምነት፣ የህይወት ማብቂያ አይደለም፡፡ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ  መሸጋገርያ ድልድይ  እንጂ ፣ የብዙዎቹ ሐይማኖቶች  መሠረቱ ይሄ ነው ። እኛ ግን ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም፣ ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ። ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡ 💡ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ።  በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል።የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነው። ሞትና ሕይወትም ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡ 🔑ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ህይወት በትክክለኛው መንገድ ከተኖረ ሞት አይፈራም። ህይወትን ከኖራችሁ ሞትን በፀጋ ትቀበላላችሁ ምክንያቱም እንደ እረፍት፣ እንደ እንቅልፍ ትመለከቱታላችሁ። ከህይወት ጫፍ መድረስ ከቻላችሁ ሞት ውብ እረፍት ፣ ብረከት ይሆናል። በተቃራኒው ካልኖራችሁ ግን በርግጠኝነት ሞት ጊዜያችሁን ፣ የህይወት እድሎቻችሁን ይነጥቃችኋል። ካልኖራችሁ ነገ የሚባል ነገር የለም ፍርሃት ይነግሳል። ፍርሃቱ የሚመጣው በሞት ሳቢያ ሳይሆን በደንብ ህይወትን ባለመኖር ነው።"                ውብ አሁን❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Show all...
67👍 34👎 3
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.