cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tikvah-University

Show more
Advertising posts
263 916
Subscribers
+76224 hours
+3 9257 days
+22 27830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ጥቆማ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #በሜዲካል_ራዲዮሎጅ_ቴክኖሎጅ ፖስት ቤሲክ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የሚከታተሉ 20 ተማሪዎችን በ2017 ዓ.ም ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከመስከረም 10-20/2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ አመልካቾች ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ በመንግሥት እና/ወይም በግል የህክምና ተቋማት ያገለገሉ እንዲሁም በራሳቸው ስፖንሰርነት ወይም ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርነት ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ኦንላይን ለመመዝገብ 👇 http://www.dmu.edu.et/Online-Application-form/ @tikvahuniversity
Show all...
👍 76😢 6👎 2 2
Photo unavailableShow in Telegram
የናይጄርያ መንግሥት በሐሰተኛ የትምህርት ሰነድ ላይ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ጀምሯል። የሀገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ ፌደሬሽን የሀሰት ሰርተፊኬት የያዘ የትኛውንም ግለሰብ ከሥራ እንዲያባርር ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ቀጣሪ ተቋማት ከሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሊጠበቁና የብቃት ማረጋገጫዎች ትክክለኛነትን ሊያረጋግጡ እንደሚገባም ገልፀዋል። ለሀገሪቱ የአካዳሚ ትምህርት መረጃዎች የሚሰጡ የመንግሥት ድርጅቶች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ የአሜሪካ ድምፅ ዘገባ ያሳያል። የናይጀሪያ ትምህርት ሚኒስትር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ፕሬዝዳንት ቲኑቡ የሀገሪቱ የሲቪል ሰርቪስ ፌደሬሽን ኃላፊ የሀሰት ሰርተፊኬት የያዘ ማንኛውንም ገልሰብ እንዲያባርሩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። የናይጄርያ መንግሥት ከባለፈው ጥር ጀምሮ በ107 የግል ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ይህም የሀሰት ዲግሪዎችን መስፋፋት ለመከላከል ተጨማሪ ጥረት ነው ተብሏል። #VOA @tikvahuniversity
Show all...
👍 65👏 15 4
Photo unavailableShow in Telegram
#STEMpower በስድስት የስቴም ፓወር ስልጠና ማዕከላት ትምህርታቸውን ተከታትለው በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን STEMpower ገልጿል። ቓላሚኖ ስቴም ማዕከል፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል፣ ወላይታ ሊቃ አዳሪ ትምህርት ቤት እና ኦልማ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ካሳለፉ የስቴም ማዕከላት መካከል ይጠቀሳሉ። STEMpower በኢትዮጵያ 61 የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ የስልጠና ማዕከላት አሉት። @tikvahuniversity
Show all...
👍 23 20🙏 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ትምህርት ዘመን ጥሪ የተደረገላቸው ነባር ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል። ዩኒቨርሲቲው ነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 09 እና 10/2017 እንደሚከናወን መግለፁ ይታወሳል። @tikvahuniversity
Show all...
👍 26 6
Photo unavailableShow in Telegram
🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት! 🌼🌼🌼 እስከ መስከረም 10/2017 ዓ.ም ለሚመዘገቡ ሰልጣኞች ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ የ15% ቅናሽ አድርገናል! በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው  ስልጠናዎች ባሉን ውስን ቦታዎች አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ! ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች ይማሩ! 🌼 Graphics Design 🌼 Video Editing 🌼 Digital Marketing 🌼 Adobe Photoshop 🌼 English Language 🌼 Website Design 🌼 Programming 🌼 Interior Design 🌼 Database 🌼 Basic Computer 🌼 Accounting Softwares 🌼 SPSS & STAΤΑ 🌼 MS-Project 🌼 Foreign & Local Languages አድራሻ፦ ቁ.1: መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ቁ.2: ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) (ትንሹ ኬኬር) ቁ.3: ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️    0991929303 / 0991929304 /          0991926707 Telegram: https://t.me/topinstitutes
Show all...
👍 15
Photo unavailableShow in Telegram
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ! የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡ የውድድሩ መመሪያ 1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡ 2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡ Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg ለ Instagram @TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1 ለ TikTok @TecnoEt https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ። በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
Show all...
👍 22 2
#DebreBerhanUniversity በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከ2ኛ-6ኛ ዓመት ያሉ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምሯል፡፡ ካምፓሱ ለ2017 ትምህርት ዘመን በመደበኛው ፕሮግራም ከ 1,200 በላይ ነባር እና አዲስ ገቢ የህክምናና የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ይጠበቃል፡፡ @tikvahuniversity
Show all...
👍 68 7😢 6🥰 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የቻይናው First Highway Engineering Company (CFHEC) ለ102 ወጣት ኢትዮጵያውያን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። የግዙፉ CCCC ኩባንያ እህት ተቋም የሆነው CFHEC፤ ስልጠናውን ለአንድ ወር የሚሰጥ ሲሆን፤ ሰልጣኞቹ ከCCCC የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ሳይቶች የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል። ግንባታ፣ ሰርቬዪንግ፣ የግንባታ ቁሳቁስ ፍተሻ እና የቻይንኛ ቋንቋ በስልጠናው የተካተቱ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል። Seagull Talent Nurturing Project በሚል የሚሰጠው ስልጠና፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት፣ በሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ እና በ CFHEC በጋራ የተዘጋጀ ነው። #Xinhua @tikvahuniversity
Show all...
👍 30 4👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#SPHMMC ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን Hematology and Oncology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አስጀምሯል። ይህ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ሠልጣኞች ዘመናዊና ጥራት ያለው የካንሰር ህክምና፣ ትምህርት እና ምርምር እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል። ፕሮግራሙ የሁለት ዓመት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን፤ ኮሌጁ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ የሚሆኑ ሦስት ፌሎውስ በዚህ ወር እንደሚቀበል ይጠበቃል። @tikvahuniversity
Show all...
👍 31👎 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
ገቢዎን እና ወጪዎን እንዴት ማስተዳደር እንደሚችሉ ይማሩ! 📊💡 "የግል በጀት አወጣጥ መሠረታዊ ነገሮች" በሚል ላዘጋጀነው የኦንላይን ስልጠና ይመዝገቡ! 🗓 መስከረም 10/2017 ዓ.ም ⏰ ከቀኑ 8:00-11:00 ሰዓት 💻 https://forms.gle/t2KczdEpPrNstvjz5 በመጠቀም ይመዝገቡ! ይህ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ!
Show all...
👍 15 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.