cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከመጽሐፍት መንደር💠

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨 🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥 ለማንኛውም አስተያየት @manbabemuluyadergal_bot

Show more
Advertising posts
3 880
Subscribers
+724 hours
+157 days
+3630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ተሰብሬ አውቃለሁ ሁኔታዬ አይመስልም አይደል ?? ጀርባዬን ሰጥቼ ቆሜ ተገፍቼ አውቃለሁ አወዳደቄን ያከፋው የገፋኝ ሰው ላይ የነበረኝ እምነት ነው !! እምነቴ ሲናድ ድባቴ መላአካላቴ ውስጥ ተሰራጭቶ ነበር ። ጠዋትም ማታም ስተኛ እና ስነሳ የሚሸኘኝ ድባቴ ነበር ። ቀን ተጠራቅሞ ድባቴ ሞተ !! የጠላኝ አይነት ተግባር ሳይ ድባቴዬ ከሞተበት አፈር ልሶ ይነሳል ። ማን ነበር የሰበረኝ ??? እኛ ማለት ያላወራነው ገመናችን ነን !! ገመናችን ፍርሃታችን ውስጥ ፣ ብዙ የማናብራራው ሃሳብ ውስጥ፣ አልያ ከምናወራው በተቃራኒ የቆመ ሃቅ ውስጥ ጥቅልል ብለን የተደበቅን ይመስለኛል ስለ እምነት የሚተነትነው የተካደ ወይ የካደ ይመስለኛል ፣ ስለሃብት የሚተነትነው ገንዘብ ገዢ እንደሆነ በሆነ መንገድ ጀርባውን የገረፈው እውነት ያለው ይመስለኛል ? ዋጋ ያላስከፈለን ነገር ቢኖረንም በየደቂቃው አናስታውሰውም!! ሃይለኛ ነኝ ፣ ሃይለኛ ነኝ ፣ ሃይለኛ ነኝ የሚለው ሰነፍ ነው ደካማ ነው ብለው እንዳያጠቁት የሚፈራ የመስለኛል .... :- እኛ ያላወራነው ወይ ብዙ ግዜ የምናወራው ተቃራኒ ነን እላለሁ ...! ሰው አዘውትሮ ከሚተነትነው ጉዳይ ጋር ያስተሳሰረው የህይወት ድር አይጠፋውም ሳይፈልገው ምላሱ አይኑ ጆሮው ቀልቡን ይስብበታል ። ማን ነበር ግን የሰበረኝ ?? የተሰበርንበት ቦታ ፣ ታሪክ ፣ ሁኔታ ፣ አይነት ይለያያል እንጂ ማን አለ ያልተሰበረ?! ©Adhanom Mitiku
Show all...
👍 3🥰 1😢 1
* ነጭ ሽንኩርት በእግር ላይ ቢታሽ ወዲያው በደም ስር ውስጥ አልፎ በሣምባ በኩል በሚወጣ አየር በትንፋሽ ጠረን ውስጥ ይታወቃል፡፡ ❖ የቤት መስታወት ማንኛውም እቃ __ ተወርውሮበት _ ሲሰበር የሚራገፈው ወደ ውጭ ሳይሆን እቃው ወደ ተወረወረበት አቅጣጫ ነው፡፡ * የወይን ዘለላ ማይክሮዌቭ ምድጃ ላይ ከተቀመጠ ፍንዳታን ይፈጥራል፡፡ ❖ በፖለቲካ ወይም ርዕዮተ ዓለም ልዩነት ሰበብ ታላቋ ጀርመን በ1961 በግዙፍ ግንብ የበርሊን ግንብ ለሁለት ተከፈለች፡፡ የበርሊን ግንብ ሁለቱን ምስራቅ ጀርመንና ምዕራብ ጀርመንን ለ28 ዓመታት ከለየ በኋላ የፈረሰው ኦክቶበር 3/1989 ነው፡፡ ❖ ኮንዶም ከቤት ወደ ቤት የሚሸጥበት አገር ቢኖር ጃፓን ነው፡፡ ❖ ኔቫዳ በተባለች የአሜሪካ ግዛት ደግሞ በኮንዶም መጠቀም ክልክል ל-! ❖ በማዕከላዊ አውስትራሊያ ውስጥ የሚገኙት ዋሊብሪ ጎሳዎች ወንዶቹ ሲገናኙ ሰላምታ ሚለዋወጡት እጅ በመጨባበጥ ሳይሆን (የወሲብ እቃቸውን) በመጨባበጥ ነው፡፡ * RHTHYM አናባቢ የሌለው ረጅሙ የእንግሊዘኛ ፊደል ነው፡፡ * Praeyertransssubstaintiationalistically ረጅሙ የእንጊልዘኛ ፊደል ነው
Show all...
👍 3
❝እያፈቀርኳት ከታመምኩት ህመም በላይ እንዳፈቀርኳት ሳልነግራት የምቆያት እያንዳንዷ ደቂቃ ልቤን እንዴት እንደምታቆስል ብታውቅ ኖሮ ምናልባት ታፈቅረኝ ነበር❞ እያለ የእናቱ ጉልበቶቼ ላይ ሄዶ እርፍ አለ........ ይሄን ሲናገር ያቺ እንዲህ የተዜማለትና ያፈቀራት  ሰሎሜ ጓዷ ውስጥ ሆና እየሰማችው እንደሆነ አላወቀም ነበር... 📓ሰሎሜ
Show all...
👍 2🥰 2
ከፀበልተኞች ስልክ መስረቅ ስራዬ ነው፡፡ዛሬም እድል ቀንቶኝ ተጠምቄም ሰርቄም ተሸፋፍኜ ልወጣ ስል ግን የሆነ ደንቃራ ሰውዬ አስቆመኝ።እያለከለከ ነው።በፅኑ የታመመች የምትመስል ትንሽዬ ልጅ እግሩ ስር ተቀምጣ አንጋጣ ታየኛለች።እሱም በልምምጥ እያየኝ... እባክህ እስከፀበሉ እናድርሳት ልጄ ታማኝ ነው አግዘኝ አለኝ ... ቸኩያለሁ።ፀበል ቤት ሲጠመቁ ጠብቄ የሰረቅኳቸው ጠበልተኞች ሲጨርሱ ስልካቸውን መጠየቃቸው ስለማይቀር እየተርበተበትኩ አግዤው ቶሎ ለማምለጥ ስል ብቻ ወድያው እሺ አልኩት።ሰውየው ግን በዚህ አላቆመም... ይቅርታ እንግዴ እዚህ ከመጣን አይቀር ልብሷን ላውልቅና ፀበሉስር አድርገናት ትሄዳለህ የህፃን ነገር.....(መለፍለፉን ቀጠለ እኔ ደሞ ላብ ያጠምቀኝ ጀመር እ..እሺ እሺ ግን ምን ሆና ነው??(መደንገጤን ላለማስነቃት በድንገት ያወጣሁት ቃል ነበር። ታሪኩ ብዙ ነው ወንድሜ።የታመመችው እሷ ሳትሆን እኔ ነኝ።ታውቃለህ አንዳንዴ እግዜር ሲቀጣህ ህመማቸውን ልታይ አደለም ልታስብ በማትፈልጋቸው ሰወች ለኔ ባደረገው እስክትል ድረስ ይመጣብሀል።ግን አይሆንም። ባንተ በደል ደሞ ልጅህ ስትታመም ስታይ ከሷ በላይ አንተ ትታመማለህ.... ይሄን ያህል ግን ምን ብታደርግ ነው...(እየተቁነጠነጥኩ ጠየኩት አይ የኔማ ልክ የለውም።እዚህ ፀበል ቦታ ስመጣ ረጅም ጊዜ ሆኖኛል ግን ሚገርምህ እኔ ምመጣው ለመዳን ሳይሆን ለመታመም ነበር።ይህ ማለት ከተማ የለመድኩትን ስርቆት እዚህ በቀላሉ ሰው እቃውን አስቀምጦ ሲጠመቅ ኪስ መበርበር መስረቅ ጀመርኩ።ነገሩ ደሞ ቀላል ስለሆነ ለአመታት ተጠማቂ መስዬ ስሰርቅ ኖርኩኝ።ብዙ አተረፍኩ።በኋላ ግን ሁሉን ትቼ ሳገባ ግፌ ዞሮ ሊከፈለኝ እቺ ልጄ ሽባ ሆና ተወለደች።እኔም ለወራት በአፍንጫዬ ደም እየፈሰሰ ታማሚ ሆንኩ።እናም በብሬ ልታከም ብሞክርም ህመሜ መድሀኒት የታጣለት ከመሆኑም በላይ በነብስ የመጣ መሆኑ ተነገረኝ። እንግዲህ ከምሞት ብዬ ባለማመን ለስርቆት የመጣሁበትን ፀበል በነብሴ ሲመጣ በእምነት ለመጠመቅ መጣሁ።ልጄንም አመጣኋት። ከዛ ወዲህ ይኸው አለው....(የህፃኗን ልብስ አውልቆ እንደጨረሰ ፈገግ እያለ... ቡጡዬ በቃ ሂጂና ተጠመቂ እሺ አሁን ጨርሻለሁ (ሲላት ሽባ የተባለችው ህፃን ቀልጠፍ ብላ ተነስታ እየሮጠች ፀበል ቤት ስትገባ እኔ ደሞ በተራዬ እግር እጄ ሽባ ሆኖ ደርቄ ቀረሁ... ምን???እየቀለድክብኝ ነበር??ቆይ ምን ፈልገህ ነው?? ማነህ አንተ?ያልታመመች ልጅ...(እየጮኸኩበት ለመሄድ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ ተረጋጋ ወንድም።ምንም አልዋሸሁክም!! ሁሉም እውነት ነው። ያልነገርኩህ ሽባዋ ልጄ በመድሀኒአለም ፀበል የዛሬ ወር መዳኗንና እኔም ደሜ መቆሙን ነው።አንዳንዴ ጤና ሆነህ የደፈርከው አምላክህን አሳምሞ ዝም ሲልህ ከመፍረድህ ከመፍራትህም በፊት ቶሎ መመለስን ከኔ ተማር።ስናጠፋ እያየ ዝም የሚለን በምንሰራው የማይቀፅፈን በሀጥያታችን የማያጠፋን ታግሶን እንጂ ከብደነው አደለም!! እሱ ልጆቹን መቅጣትም ማዋረድም አይፈልግም፡፡ እኛ ግን ሀጥያታችን እየበዛ ከኛ አልፎ ቅጣታችን በልጆቻችን በምንወዳቸው ድረስ ይመጣል።እየውልህ ያኔ አይሁድኮ ክርስቶስን ሲሰድቡት ሲገርፉት ሲሰቅሉት በዛ ልክ ዝም ያላቸው ሊያጠፋቸው አቅቶት እንዳይመስልህ የትእግስቱና የፍቅሩን ጥግ እየገደሉትም ሲያሳያቸው እንጂ።እኛም እንዲሁ ነን ክርስቶስን እንደ አይሁድ ሀጥያት በተባለው ሁሉ እየበደልነው እየሰቀልነው ነው ካልተመለስን ቁጣውን ችለን አንቋቋመውም እኔን ያየ ይማር.... እንግዲህ ይኸው ነው በል ደና ዋል.....(ብሎኝ ሲያቀረቅር በቆምኩበት ልቤ ሲመታ ተሰማኝ እጄን ሳላዘው ከኪሴ ሁለቱንም ስልክ አውጥቶ ለወጣቱ ሲሰጠው ራሴን አልተቆጣጠርኩትም ነበር። እባክህ ይቅር በለኝ እኔም ለወራት እዚህ እየመጣሁ... ተው አትንገረኝ...አውቃለሁኮ። እኔም ለወራት ተከታትዬሀለው። አታቀኝም እንጂ ከዳንኩ ወዲህ የዚህ ግቢ ዘብ ነኝ።ስለቴ ነበር።ሁሌ ስትሰርቅ እያየሁክ ዝም ያልኩት በራስህ እስክትተው ነበር አንተ ግን አላቆምክም ለዚህ ዛሬ ስትመጣ ልጄን ይዤ በር ላይ የጠበቅኩህም ሆነ ብዬ ነው።ሌባ ብዬ በሠዋርድህ ጠፍተህ ትቀራለህ እግዜርም በስውር ቀጥቶ በአደባባይ የሚምር አምላክ ስለሆነ በዘዴ ታሪኬን ነገርኩህ አንተም ልብህ ተመለሰ።ከዚህ በኋላ ፀበሉን ለመዳኛ እንጂ ለመሞቻ አትጠቀመው ያ ወንበዴ ትዝ አይልህም?? በመጨረሻ ሰአት መስቀሉ ላይ አምላኩን ለምኖ ለነብሱ ምህረት አግኝቷል አንተም የወንበዴውን ፀሎት አሁኑኑ ሂድና ፀልየው።ልቤን መልስልኝ ማረኝ አስበኝ በለው ሂድ አምላክህ እየጠበቀህ ነው...እቺን ደሞ ምሳ ከቸገረህ እንኳ..(ከኪሱ ብር አውጥቶ እየሰጠኝ ለደቂቃ አቀርቅሬ አለቀስኩኝ ፈራሁኝ አፈርኩኝ ብቻ ግን ለመደበቅ ይሁን ለመፀለይ ሳይገባኝ ፀበል ቤቱን አልፌ ከቤ/ክኑ ጀርባ ዳግም ለይቅርታ ወደቅኩና ማረኝ አልኩት።መሀሪው ይማርን ይመልሰን!! ✍️
ቻቻ
Show all...
20👍 3
እንደማሰብ አለና ‹‹ስልካቸውን ተቀባሏቸውና አስገቧችው››ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
ይቀጥላል ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇 https://t.me/manbabemulusewyaderegal https://t.me/manbabemulusewyaderegal https://t.me/manbabemulusewyaderegal ♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
Show all...
👍 12
‹‹ምን ማለት ፈልጎ ነው…?ይሄ ሁሉ ሰራዊት እዚህ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል…..?ችግር ውስጥ ገባን ማለት ነው?››ትእግስት ነች ጥያቄዎቾን ደራርባ እዝራን የጠየቀችው፡፡ ‹‹አላውቅም…ቆይ እስኪ በፀጥታ ላስብበት…የሆኑ የሆኑ ነገሮች እየተገጣጠሙልኝ  ነው››አለትና አይኖቹን እንደመጨፈን ብሎ በጥልቀት ማሰብ ጀመረ፡፡ እዝራ አእምሮውን ጥልቅ ደረስ ዘልቆ  በረበረ…ስለወንድሙ አካሄድና አንዳንድ ፈላጎቶች አሰበ ..እና እሱን ለመቋቋምና ለሌሎች ሰዎች  ሳይጎዱ እሱ ባጠፋው ጥፋት ልክ ቅጣቱን ማግኘት እንዲቸል ለማድረግ እንዲያስችለው ነገሮችን  በንቃት ማድረግ እንዳለበት ወሰነ ፡፡በንቃት  ላይ ያለ ሠው  ደግሞ አሁን ላይ መገኘት፤እያንዳንዶን ደቂቃና ሰዓት በጥልቀት መኖር፤ነገሮችን ባሉበት ተፈጥሯዊ ይዘት የመቀበል ችሎታ  እና የሌላውን ህመም በጥልቀት መረዳት ብቃት ሊኖረው የግድ ይላል፡፡እና እዝራ ሀሳብን እልባት ሳያበጅለት  አጋቹ መጣና ጥሎት በሄደበት ቦታ ከእነሱ  ፊት ለፊ ቁጭ አለ፡፡ ‹‹እሺ..እዚህ ምን እግር ጣላችሁ?አሁን ልሰማችሁ ዝግጁ ነኝ››አላቸው፡፡ እዝራ ከዚህ ትርምስም  እሱንም ሆነ ሌሎችን የሚወዳቸውን ሰዎች በጥበብ ይዞ መውጣት እንደለበት ወስኗል ፡፡አዎ አሁን በንዴት ሳይሆን በስሌታ ማሰብ እንዳለበት እራሱን አሳመነ  …..መጀመሪያ የጠረጠራቸው ነገሮች በትክክል የተፈጸሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንዳበት ተሰማው… አእምሮውን ለመጠቀም ወሰነ‹‹ከወንድሜ ጋር ወደ እዚህ ቦታ አብረን ለመምጣት ተቃጥረን ነበር፡፡ከዛ ግን ጠፋብኝ…ማለቴ ስልኩ ሁሉ አይሰራም…ሌሎች ቦታዎች  ከፈለኩት በኃላ ምን አልባት በስራ ውጥረት ተዘናግቶ እኔን እረስቶኝ ወደእዚህ መጥቶ ይሆናል ብዬ በመጠራጠሬ ነው የመጣሁት››ሲል ቦታው ላይ የተገኙበትን ምክንያት አብራራለት፡፡ ‹‹በዚህ ምሽት  አራት ሰዓት ካለፈ በኃላ?፡፡››ሰውዬው የተናገረውን አንዳላመነው በሚያሳብቅ የድምፃ ቅላፄ ጠየቀው፡፡ ‹‹አይገርምም…በጊዜ ከእሷ ጋር ተገናኘተን ትንሽ እየቀማመስን እየተዝናናን ነበር….ከዛ ወደቤት ለመሄድ ላዳ ውስጥ እንደገባን ወንድሜ ጥዋት ወደእዚህ ቦታ እንሄዳለን ብሎኝ እንደነበረ ትዝ አለኝና ላዳው ወደእዚህ እንዲያመጣን ነገርኩት..ይሄው ነው….አሁን ወንድሜ የት ነው? ላናግረው እንደምፈለግ ንገረው፡፡››ማስመሰሉን  ቀጠለበት፡፡ ‹‹ወንድምህ እዚህ እንዳለ በምን አወቅክ?›› ‹‹ ነገርኩህ እኮ!ሌላ ቦታ እንደሌላ  አረጋግጬለሁ…እዚህ ካልሆነ ሌላ የት ይሆናል?ብዬ ነዋ›› ‹‹እንግዲያው እርምህን አውጣ …ወንድምህ  እዚህ የለም….እኛም ቀኑን ሙሉ ስንጠብቀው ነው የዋልነው››መለሰለት ‹‹ልጁስ ?››እዝራ እንደዋዛ ቀጣዩን ጥያቄ ሰነዘረ፡፡ ‹‹የቱ ልጅ?››ኮስተር ብሎ ‹‹መንግስቱ ነዋ…የያዛችሁት ልጅ›› ‹‹አለ …ከጀርባ ባለው ክፍል  ነው›› እዝራ በእርካታ ተነፈሰ….ትእግስት በእዝራ ብልጠት ተደመመች‹‹እና ኮሪደሩ ላይ ያሉት ጓደኞችህ ምንድነው የሚጠብቁት?››ስትል ለአጋቹ ሌላ ጥያቄ አቀረበችለት፡፡ ‹‹ልጁቷን ነዋ…ስለሷ አልነገራችሁም እንዴ..?እርግጥ እሷን እኛ አይደለንም ያገትናት  ..ቀደም ብላ እዚህ ነበረች››› ‹‹አሮራ ነች?››እዝራ ትንፋሽ በሚያሳጣ ድንጋጤ  ውስጥ ሆኖ ጠየቀ፡፡ ‹‹አዎ ..ዘፋኟ….የገዛ ልጁን ለምን እንዳገታ አልገባኝም….?ምን አልባት ወንድ ላይ እየጠንጠለጠለች አስቸግራው ሊሆን ይችላል…..››የራሱን ግምት በማስቀምጥ ማንነቷን አረጋገጠላቸው፡፡ ሁለቱም ልክ እንደተነጋገረ ሰው ከመቀመጫቸው በርግገው በመነሳት ወደኮሪደሩ ተንደረደሩ…ጠባቂዎቹ መንገዳቸው ላይ እጃቸውን ሰትረው በመደርደር ግድግዳ ሆነው አገዷቸው…ሲያወራቸው የነበረው ሰው ከኃላቸው መጣና‹‹ሰዎች እሷን ለማነጋር የግድ የግርማ ፍቃድ ያስፈልጋል››አላቸው፡፡ ‹‹ግርማ እኮ አሁን እዚህ የለም …መፍቀድ የምትችለው አንተ ነህ›› ‹‹አይ አቶ ግርማ እዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን አቋም በግልፅ ነው የነገረኝ …ልጅቷ ያለእሱ ፍቃድ ማንም ሊያናግራት አይችልም…ከቻላችሁ በስልክ አግኙትና ….ያናግሯት  ብሎ ይንገረኝ፡፡›› ትእግስት ስሜቷን መቆጣጠር አቅታት‹‹እንደውም እስከአሁን የነገርንህን ሁሉ እርሳው…ከግርማ ጋር የተነጋርከውን ብር ለማግኘትና ችግር ሳይፈጣር ከዚህ ጣጣ ውስጥ ለመውጣት ከፈለክ ከእኛ ጋር መስማማት የግድ ይልሀል››አለችው ፍጥጥ ብላ፡፡ ሰውዬው ኩስትርትር አለ‹‹አልገባኝም ..ከእናንተ ጋር ምን ይሁንልኝ ብዬ ነው የምስማማው…የቀጠረን ግርማ ነው…ብራችንንም የሚከፍለን እሱ ነው፡፡እስከአሁን እንደውም ለምን እንዳልመጣና እንደዚህ አይነት እርስኪ ያለው ስራ ካሰራን በኃላ እንዴት እንደዚህ  እንዝላል እንደሆነ ገርሟኛል ፡፡በዛ ላይ እናንተ እኮ በእኔ ቁጥጥር ስር ነው ያላችሁት... አልገባችሁም እንዴ? አሁን እኮ በቃ ታጋቼ ሆናችኋል፡፡›› ‹‹እንደዛ እንኳን አይመስለንም …ይሄንን ምንነግርህ ግርማ መምጣት ስለማይችል ነው››አለው እዝራ፡፡ ‹‹መምጣት እንደማይችል!! በምን አወቅክ…?አሁን ከጥዋት ጀምሮ ፈልጌ አጣሁት ስትል አልነበረ እንዴ?›› ‹‹ዋሽቼህ ነው፡፡›› ሰውዬው ትዕግስቱ ተሞጠጠበትና ሽጉጡን ከሻጠበት መልሶ አውጥቶ ደቀነባቸው‹‹መቀባጠሩን አቁማችሁ ትክክለኛ እየሆነ ያለውን ነገር ንገሩኝ…ካለበለዛ ግንባራችሁን አፈራርሰዋለሁ፡፡›› ትእግስት‹‹ቆይ›› አለችና ስልኳን በማውጣት ደወለች‹‹ሄሎ ክንዴ›› ‹‹ሄሎ ትእግስት መንጌ ተገኘ እንዴ?›› ‹‹አይ እስከአሁን እያፈላለኩት ነው…ግን አሁን የደወልኩት እስከጥዋት ተመልሶ ማይማጣ  ከሆነ ጥዋት ሁለት ሰዓት ድረስ ብሩን ይዤ ለመምጣት እንደተዘጋጀው ልነግርህ ነው፡፡›› ‹‹ጥሩ ያስማማናል›› ‹‹ከዛ ግርማን ታስረክበኛለህ ›› ‹‹ምን ጥያቄ አለው..ዝግጁ ስትሆኚ ደውይልኝ …የእኛ ልጆች ያገኙሽና በጥንቃቄ ..ማለቴ ፖሊስና ሌላም ሰው እንደማይከተልሽ እርግጠኛ ከሆኑ በኃላ ወዳለንበት ያመጡሻል፡፡›› ‹‹እሺ አመሰግናለሁ… ቸው››ስልኩ ተዘጋ፡፡ ሽጉጥ የደቀነባቸው የመንግስቱ አጋች‹‹እና አጋቹን ያሳገታችሁት እናንተ ናችሁ ማለት ነው?››ሲል በገረሜታ ጠየቀ፡፡ ‹‹አይ ያሳገተው መንግስቱ ነበር..እኛ አይደለንም››ትእግስት መለሰች ከት ብሎ ሳቀ…‹‹የሚገርም የፊልም እስክሪፕት ይወጣዋል..ታጋቹን አላመንኩትም እንጂ ሊነግረኝ ሞክሮ ነበር..ይገርማል….!!ቆይ አንተም በወንድምህ መታገት እጅህ አለበት?››ወደ እዝራ ዞሮ ጠየቀው፡፡ ‹‹የለሁበትም…መታገቱ ግን ይገባዋል ባይ ነኝ..አሁን አስገባንና አሮራን እንያት… ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ዋናው ምክንያት የእሷ ከእይታችን መሰወር ነው…እሷ ጤና መሆኗን እንይና ከዛ ቁጭ ብለን ሁላችሁም ብራችሁን አግኝታችሁ ማንም ሰው ሳይጎዳ ከዚህ ትርምስምስ የምንወጣበትን እና ወደየህይወታችን  የምንመለስበትን  ሁለታ  ላይ እንነጋገራለን፡፡›› አጋቹ የእዝራን ንግግር ከሰማ በኃላ ወደትእግስት ዞሮ‹‹አንቺ መንግስቱ ምንሽ ነው?››ሲል ጠየቃት፡፡ ‹‹ጓደኛዬ›› ‹‹ ግርማስ? የት ነው ምታውቂው..?›› ‹‹የእሱ ሰራተኛ ነኝ..ማለቴ የአሮራ ረዳት ሆኜ ነው የምሰራው፡፡›› አጋቹ በድጋሜ መገረም ሳቅ   ሳቀ…..‹‹እርስ በርሳችሁ ነዋ እየተጠፋፋችሁ ያላችሁት፡፡›› እዝራ‹‹እንደዛ መሰለኝ..ስለዚህ ምንልህን  ስማትና አሁን ወደ አሮራ አስገባንና እንያት ….ከዛ ቁጭ ብለን እናንተም ገንዘባችሁን ሳታጡ..ሌላ ወንጀል ውስጥም ሳይገባ ሁኔታዎችን እናስተካክላለን…በዛ ቃል እንገባልሀለን፡፡›› አለው፡፡
Show all...
አሮራ ምዕራፍ-24 ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ (ግማሽ ልቤን እና ግማሽ ነፍሴን ያመኛል) ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ነው። ትዕግስት ስልኳ ሲጠራ እዝራ ደረት ላይ ተኝታ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ነበር። ተንጠራራና ስልኩን አንስቶ ሰጣት።አየችው ።የምታውቀው ቁጥር አይደለም።ግራ በመጋባት ውስጥ ሆና አነሳችው። "ሄሎ"ነጎድጓዳማ  እና የሚገፋተር ድምፅ  ነው። "ትዕግስት ነሽ?" "አዎ ነኝ...ማን ልበል? አላወቅኩህም።" "አታውቂኝም ክንዴ እባላለሁ...መንግስቱ  ነበር ከቀናት በፊት  ስልክሽን የሠጠኝ....የእኔ ስልክ ካልሰራልህ በእሷ በኩል ታገኘኛለህ ብሎኝ ነበር" "እሺ ምን ልታዘዝ?" "ሰባት ሰዓት አካባቢ ደውዬለት ወደአንተ እየመጣሁ ነው ብሎኝ ነበር ።ከዛ ስልኩ ይጠራል አይነሳም አሁን ደግሞ ጭራሽ አይሰራም.....ምን ነካህ እቃውን ይዘን እየጠበቅንህ ነው በይልኝ።" "ምን? የምን ዕቃ?" ስልኩ ተቋርጧል። መኝታዋን ለቃ ወረደችና እርቃኗን ወለል ላይ ቆመች። "ምንድነው ችግር አለ?"እዝራ ነው ግራ በመጋባቷ ግራ ተጋብቶ የጠየቃት። "እኔ እንጃ ...በደንብ አልገባኝም"መንግስቱ ጋር ደወለች። አይጠራም። ገስትሀውስ ደወለች..በአይን ካዩት   ሶስት ቀን እንደሆናቸው ነገሯት። "ወይኔ ጉዴ?!!!ልጅ ምን ሆነ? ክንዴ ነኝ ብሎ የደወለላትን ልጅ ጋር ደወለችለት። "ወንድሜ ይመስለኛል በጠቀስከው ሰዓት እኛ ጋር ነበረ ..ስትደውልለት ወደአንተ ነበር የመጣው" "ታዲያ ወደእኔ እየመጣ ከሆነ የሰላሳ ደቂቃ መንገድ አምስት ሰአት ሙሉ ምን ይሰራል?" "እኔም አልገባኝም" "እና ምን ላድርግ? እቃውን ልልቀቀው?" "ምንድነበረ ስምምነታችሁ?" "መጥቶ ሊያናግረውና ሰውዬውን ተረክቦ ብራችንን ሊከፍለን ነበራ።" "አሁን የዕቃው ምንነት ገባት።" "በቃ ሁኔታውን አጣርቼ መልሼ ደውልልሀለሁ" "ቶሎ በይ ካልሆነ ዕቃውን ወደቦታው እንመልሰዋለን።" "አይ...እሱ ካልመጣ, እኔ መጣለሁ..ስንት ብር ነበር የተስማማችሁት።" "መቶ ሺ ብር ተስማምተናል።ሰላሳ ከፍሎናል።" "በቃ እስከጥዋት አቆዩት ፤እስከዛ መንጌ እንኳን ባይገኝ እኔ ጥዋት ቦታው ድረስ ብሩን ይዤ እመጣና እቃውን  ትሰጡኛላችሁ" "እንደዛ ከሆነ አሪፍ ነው...በቃ ቸው የደረሺበትን ደውለሽ አሳውቂኝ" "እሺ...ዕቃውን ፎቶ አንስተህ በዚህ ቁጥር ትልክልኛለህ?" "ይቻላል"ስልኩ ሲዘጋ እዝራ ልብሷን ከመታጠቢያ ቤት አምጥቶ  እንድትለብስ እያቀበላት ነበር። "ያንተስ አልደረቀም?" "ለበስኩት እኮ...ከጃኬቱ በስተቀር ሌላው ምንም አይልም" "በቃ ስንወጣ ጃኬት እንገዛለን ...እኔም ፓንቴ ስላልደረቀ ባዶ ቂጤን መሆኔ ነው።" "አስወልቆ ሚያይሽ የለ ምን ችግር አለው?።ለመሆኑ ምን እየተከሰተ  ነው?" "እኔ እንጃ ።እየሆነ ያለው እኔንም ግራ እያጋባኝ ነው።መንግስቱ እምጥ ይግባ ስምጥ የሚያውቅ ሰው የለም...ወንድምህ ግርማ ደግሞ..." ንግግሯን ሳትጨርስ  ስልኳ ድምፅ አሰማ... ከፈተችው።እና ቀጥታ ለእዝራ አቀበለችው።የወንድሙ የግርማ ፎቶ ነው።እጅና እግሩ ከወንበር ጋር ታስሮ ሲቁለጨለጭ ይታያል።" "ማነው ያሳገተው?"ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ጠየቃት። "ማን ይሆናል ?መንግስቱ ነዋ ።የሚገርመው አሳግቶት የት እንደጠፋ ነው?"ለማንኛውም ተነስ እንውጣና እየሄድን ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገር።" "እሺ"አለና በሀሳቧ ተስማምቶ ተከተላት። መንግስቱ ይገኝበታል ብለው የሚጠረጥሩት ቦታ ሁሉ እስከምሽቱ አራት ሰዓት እየተዞዞሩ ፈለጉ...ያቃቸዋል ብለው የሚገምቱት   ሰዎች ጋር ሁሉ እየደወሉ ጠየቁ።አንዳቸውም መንግስቱን እንዳላዩት አረጋገጡላቸው።እሷ ጋም መንግስቱን ፍለጋ የደወሉ ሰዎች ነበሩ። ከካናዳ የተመለሠው አጎቱና ሚስቱ ውቢት በየተራ ደውለውላት መንግስቱ የት እንዳለ የምታውቅ ከሆነ ጠይቀዋት ነበር። እንደማታውቅና ካገኘችው እየፈለጉት እንደሆነ  መልዕክቱን እንደምትነግረው ነግራቸው ነበር...። "አሁን ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ የምንችል አይመስለኝም...ባይሆን ይንጋና ጥዋት ማድረግ የምንችለውን ነገር እናያለን?" "ትክክል ነሽ"በቃ ወደቤት እንሂዳ አላት እዝራ።ትእግስት ስለእዛ ቤት ስታስብ የሚታያት በደም የተጨማለቀ አንሶላ...ሽጉጥና የአሮራ በጥይት የተበሳሳ ሰውነት ነው። "አይ እዛ ቤትማ አልሄድም... " "በቃ  ቤርጎ እንያዛ..." "እሺ ..ጥሩ ሀሳብ ነው" "ቆይ እዚህ ሰፈር ያለውን የግርማን ቤት ታውቀዋለህ?" "አዎ አንዴ አይቼው ነበር...ምነው?" "ዘበኛው ካስገባን እዛ እንደር" "ዘበኛው እኮ እታች ቤት የሚሰራ ነበር...በደንብ ነው የማውቀው" ‹‹እና እንሂድ " "አዎ እንሂድ"ለላደው ቦታውን ነገሩት።ወደእዛው መንዳት ጀመረ። እዝራ ሲከነክነው የነበረውን  ጥያቄ ጠየቃት"እቤቱን እንዴት አወቅሽው?" "እንዴ የአሮራን የመጨረሻ ክሊኘ የተቀረፀው እኮ እዚህ ቤት ነው ...ሶስት ቀን አድረናል" "እ...እንደዛ ነው?"አለ ፈገግ ብሎ። "አዎ...አይዞህ ከወንድምህ ጋር ምንም የተፈፀመ ነገር የለም....ማለቴ ሙከራው ነበረ ..ግን ሙከራ ብቻ ነው።" "ይሁን" ደረሱና ለላዳው ተገቢውን ክፍያው ከፍለው አሰናበቱት እና  ወደ ጊቢው ተጠጉ። ጭልምልም ብሏል። ከዚህ  በፊት በውጭ መብራት ድምቅምቅ ያለ ነበር።የውጩን መጥሪያ ደጋግመው ተጫኑ። ከደቂቃዎች በኃላ"ማን ነው?"የሚል ድምፅ ከውስጥ ተሰማ። "ጋረደው እኔ እዝራ ነኝ  ክፈት...ግርማ ልኮኝ ነው?" የውጩ የብረት በር ወለል ብሎ ተከፈተ...ከፍቹ በበራፉ እራሱን ከልሏል..ትዕግስትና እዝራ ተከታትለው ገብ።በራፍ በፍጥነት ተዘጋ ። ፊት ለፊታቸው ጠብደል ወጠምሻ የሆነ ሰው ሽጉጥ ደቅኖባችዋል። የጠበቁት ጋረደው በቦታው የለም።ደነገጡ። "ምንድነው...እኔ እዝራ ነኝ የግርማ ወንድ?" "ሠማሁህ እኮ...አሁን ቀጥሉ ..ወደቤት ግብ"ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ። እጅ ለእጅ ተያይዘው  እንዳላቸው ወደቤት ተንቀሳቀሱ። ግቢ ውስጥ አራት የሚሆኑ ክላሽ ጭምር የታጠቁ ሰዎች ፈንጠርጠር ብለው በጥንቃቄ ቆመዋል።ሳሎን ሲገብ ወደ ውስጥ (ወደ መኝታ ቤቶች) የሚወስደው  ኮሪደር ላይ ሌሎች ሁለት መሳሪያ  የታጠቁ ሰዎች ይታያሉ።ይዟቸው የመጣው ሰው የደቀነባቸውን  ሽጉጥ  ወደጎኑ መልሶ ሻጠና ወደ ሳፋው በአገጩ እየጠቆመ ተቀመጡና  ለምን እንደመጣችሁ አስረድኝ?"አላቸው።እንዳላቸው ተቀመጡና በፍራቻ መቁለጭለጭ ጀመሩ። ከበራፍ ተቀብሎ ወደውስጥ በማስገባት ሶፋ ላይ እንዲቀመጡ ያዘዛቸው የአጋቾቹ መሪ የሚመስለው  ሰው ፊት ለፊታቸው ተቀምጦ በዝምታ እየተመከታቸው ነው፡፡አስተያቱ ደግሞ በሁለቱም ውሰጥ ሽብር ነዛባቸው፡፡ ከተቀመጠበት ድንገት ተነሳና…‹‹እስክመለስ ድረስ ለምን እዚህ እንደመጣችሁ እሰባችሁበት ጠብቁኝ››አለና ተነስቶ ወደውስጥ ገባ፡፡
Show all...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ሻማው ቀልጧል ወርቁ አልቆ የሰም ክምር ተቆልሏል የሀገር አፈር በደም ልውስ ጭቃ ሆኖ ደረቅ ሲል በሰው እምባ ደግሞ ርሶ ከምሬት ጋር ተለውሶ በጭድ ፈንታ፤ዋይታ ይሉት ማጠንከሪያ ታክሎበት ከጣሪያ ስር ተመረገ ቤት ሊለማ የእግዜሩ ቤት ክቡሩ ሰው ፈራረሰ። ✍Shewit
Show all...
እሷም ልትፅፍልኝ እያሰበች..... እኔም ልፅፍላት እያሰብኩ.... እልፍ ጊዜያቶች አለፉ....ሁለታችንም የልባችንን ሳንባባል በጣም በሚያስፈሩ ዝምታዎች ውስጥ ጠለቀን...... እየናፈቀችኝ.....እሳት እየሆነችብኝ....ልቤ ትር ትር እያለላት......ግን ማውራት አልቻልኩም....ምክንያቱም እነዚህ ውበቶች በምናቤ ፊትለፊቴ ሲመጡ ብዙ ነበልባሎች በሰውነቴ ላይ እንደፈሰሱ ይሰማኛል።ከዛ በጣም እፈራለው.....ቃላት እስካጣልሽ ድረስ በጣም እፈራለው... እንጂማ........ሊያወራሽ የሚናፍቀው ልቤ መቼ ትርታውን አቁሞ ያውቃል....እ ሲኞሪታ.......አንቺን እኮ ነው የምልሽ....አዎ  አንቺን ነው...ከምር
Show all...
🥰 6
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.